YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሰበር ዜና

#የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለን አሟሟት እና የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ምርምራን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ #መግለጫ #ተሰረዘ

#መግለጫ የተሰረዘው የፌደራል ጠቅላይ ዋና አቃቤ ህግ አቶ #ብርሃኑ ጸጋዬ አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ ባልደረባ ለዲ ደብሊው እንደተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሄዳቸው መግለጫው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።” መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ቢነገርም ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልተነገረለትም።

#በዛሬው መግለጫ የኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እና ከሰኔ አስራ ስድስቱ ቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።

#ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ሲዘዋወር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. ይሰጣል ተብሎ የነበረው መግለጫ ወደ ዛሬ ጳጉሜ 1 መተላለፉ ይታወሳል።

ምንጭ ፦ DW
@YeneTube @Mycase27
እነ እስክንድር ነጋ ዛሬ ጋዜጣዊ #መግለጫ እንዳይሰጡ በፖሊስ መከልከላቸው #ህጋዊ መሰረትም ሆነ ሞራላዊ አግባብነት የለዉም ።

ማንኛውም ግለሰብ ህገመንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ በሰላማዊ መንገድ መሰብሰብና መቃወም ሊፈቀድለት ይገባል። ህግ ከጣሰ በአግባቡ ሊጠየቅ ይገባል እንጂ መብቱን እንዳይጠቀም መከልከል የለበትም። ብዙዎች የሞቱት፤ አካላቸው የጎደለው፣ ነፃነታቸው ያለአግባብ ተገፎ ለአመታት እስርቤት የማቀቁት ይህ መብት እንዲከበር ብለው መሆኑ ለአፍታም ቢሆን መረሳት የለበትም።

ሽግግሩ ወደተሻለ መንገድ እንዲሄድ ካስፈለገ የተለያዩ ሃሳቦችን ማስተናገድ የሚችል ሆኖ መቀጠል ይገባዋል። ከእስክንድር አቋም ጋር የማንስማማ ሰዎች ብንኖርም በእውቀትና በእውነት ላይ ተመስርተን መወያየትና አለፍ ሲልም መከራከር እንጂ እራሳችንን ብቸኛ የእውቀትና የእውነት ባለቤት አድርገን ከእኛ አስተሳሰብ ጋር ስላልተስማማ ብቻ እገዳ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤ የሀገሪቱን ህግም ይጥሳል። የዛሬውን ድርጊት የፈፀሙ የመንግስት አካላት ተግባራቸው ሀገሪቱን ለጊዜው የሚያረጋጋ ሊመስላቸው ቢችልም የታየውን የዲሞክራሲ ተስፋና የለውጥ ሂደት ሊያደናቅፍ እንደሚችል ሊያስተውሉ ይገባል። እንዲህ አይነት እርምጃዎች የመንግስትና የለውጡን ቅቡልነት የሚያሳጡ እንደሆኑ መንግስትን ጨምሮ ሁላችንም ልብ ልንል ይገባል።

©Jawar Mohammed
@Yenetube @FikerAssefa
ኦዲፒ‼️

በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የተሰጠ #መግለጫ

የህዝቦች ወንድማማችነትና የአብሮነት መልካም እሴቶች በአፍራሽ ሃይሎች ተልዕኮ #አይደናቀፉም!
በአገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የፖለቲካ ምህዳሩ #ሰፍቶ ማንኛዉም አካል በነጻነት የመደራጀት፣ የፈለገዉን የፖለቲካ አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ እንዲያራምድ፣ የሀገራችን ህዝቦች ለዘመናት የታገሉለትና ዉድ መስዋዕትነት የከፈሉበት እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ረገድ #ተስፋ_ሰጪ ተጨባጭ ዉጤቶችም በመመዝገብ ላይ ናቸዉ፡፡

ሆኖም አንዳንድ የፖለቲካ ሃይሎች ዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመዉ በሰለጠነና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ #አጀንዳቸዉን_ከማራመድ ይልቅ የብሄር ጽንፈኛ አስተሳሰብን አንግበዉ በመነሳት፣ ህጋዊና ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴን ከህገ ወጥና #የግጭት መንገድ ጋር እያጣቀሱ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታይቷል፡፡

እነዚህ ጽንፈኛ የፖለቲካ ሃይሎች የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ለዘመናት በአብሮነት እና #በፍቅር የኖረን ህዝብ ሊያቃቅሩ ብሎም ሊያጋጩ የሚችሉ አጀንዳዎቸን በመቅረጽ ህዝብን ከህዝብ ጋር በማጋጨትና ንፁሃን ዜጎችን በእሳት በመማገድ ሀገራችን ከማትወጣበት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመክተት የለዉጥ እንቅስቃሴዉን ማደናቀፍ ዋነኛ አላማቸዉ አድርገዉ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሰሞኑንም በአማራ ክልል #የኦሮሞ_ብሄረሰብ አስተዳደርና በክልሉ በሰሜን #ሸዋ_ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በነዚህ ሃይሎች ቀስቃሽነት ግጭቶች መከሰታቸዉና በሰዉ ህይወት፣በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

ኦዲፒ በግጭቱ ለጠፋዉ የሰዉ ህይወት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ዉድመት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ በግጭቱ ዉድ ህይወታቸዉን ያጡ ወገኖች ፈጣሪ ነብሳቸዉን በገነት እንዲያኖር እየተመኘ ለተጎጂ ቤተሰቦችም #መፅናናትን ይመኛል፡፡ የጥፋት ድርጊቱንም አጥብቆ #ያወግዛል፡፡

በህዝብ ደም የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞች የተፈፀመዉ ጥፋት በየትኛዉም መልኩ ተቀባይነት የሌለዉና ማንኛዉንም ህዝብ የማይወክል መሆኑን አዲፒ ይገነዘባል፡፡ የግጭቱን ጠንሳሾች እና ተሳታፊዎች ለህግ ለማቅረብ በህግ አስከባሪ አካላት የሚደረገዉን የህግ የበላይነት የማስከበር እንቅስቃሴ እንዲሳካ ፓርቲያችን ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደርጋል።

ፓርያችን ኦዲፒ የተፈጠረዉን ችግር ለማረጋጋት እና ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና ከአማራ ክልላዊ መንግስት ጋር በመቀናጀት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በእኩይ የጥፋት ድርጊት የሰከሩ ሀይሎች ሰሞኑን የለኮሱት የጥፋት እሳት የህዝብ ለህዝብ ግጭት በማስመሰልና ችግሩ በኦሮሚያ ክልል እንዲስፋፋ በማድረግ ለዘመናት በወንድማማችነትና በመተሳሰብ በሰላም አብረዉ እየኖሩ ያሉ የኦሮሞና የአማራ ወንድማማች ህዝቦችን በግጭት እሳት በመማገድ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡

በሰላም አብሮ የሚኖሩትን ወንድማማች ህዝቦች ለማጋጨት የሚደረግ ማንኛዉም ሙከራና ድርጊት ህዝቦች ለዘመናት ባካበቱት የአብሮነት ዕሴት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሴራዉን ለማክሸፍ ኦዲፒ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንክሮ ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚም የኦሮሞ ህዝብ በተለመደዉ የአቃፊነት ባህሉ ወንድም ከሆነዉ የአማራ ህዝብ እና ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያለዉን አብሮነት በማጠናከር፣ በክልሉ በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ የጥፋት ሀይሎቸን ሴራ ለማጋለጥ እና ለማክሸፍ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ኦሮሚያ የሁሉም ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቤት እንደሆነች ኦዲፒ በጽኑ ያምናል፡፡ በክልላችን የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች አሁን የደረሰንበት የለዉጥ ምዕራፍ ላይ እንድንደርስ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አንድ ሆነዉ ከመሪዉ ፓርቲ ኦዲፒ ጎን ተሰልፈዉ ታግለዋል፡፡ ዉድ መስዋዕትነትም ከፍለዋል፡፡ ፓርቲያችን ኦዲፒ ለዚህም ታላቅ አክብሮት እንዳለዉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

በክልላችን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሰላም፣ በእኩልነት፣ በወንድማማችነት እና በነጻነት እንዲኖሩ ችግሮች ሲከሰቱም ከአሁን ቀደም እየፈታናቸዉ በመጣንበት መንገድ እየተወያየን መፍትሄ እየሰጠን ለመሄድ ዝግጁ መሆናችንና ለጽንፈኛ እና ለከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎች የሚከፈት በር እንደማይኖር፤ ለዚህም ፓርቲያችን መላዉን የክልሉን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ከማንኛዉም ጊዜ በበለጠ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

ፓርቲያችን ኦዲፒ የህዝቦች ወንድማማችነት፣ የኢትዮጵያን አንድነት እና የለዉጡን እንቅስቃሴ ለመገዳደር የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ እና የከሰሩ የፖለቲካ ሃይሎችን ከመላዉ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከለዉጥ ኃይሎች ጋር በመተባበር በጽናት የሚታገላቸዉ መሆኑን ደግመን እናረጋግጣለን!

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
ሚያዚያ 01፣ 2011
@YeneTube @FikerAssefa
የ12ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ 11 ሰዓት ላይ ይለቀቃል!!

የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ከፍል ውጤትን አስመለክቶ ከአንድ ሰዓት በኋላ #መግለጫ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃነን ጠርቷል።

መግለጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ተፈታኞች ከ11 ዐሰት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ ገብተው ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።


ምንጭ:- ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@Yenetube @FikerAssefa
👍1