#በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች #የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይፈጸምበት ነበር የተባለውን ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራው #ማእከላዊ ማረሚያ ቤት #በዛሬው እለት ተዘጋ ፡፡
የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ እየወሰደ ከሚገኘው የለውጥ እርምጃዎች መካከል ባለፉት አመታት በክልሉ ህዝብ ላይ ሲፈጸሙ የነበሩትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ዋነኛው ነው፡፡
📌የክልሉ መንግስት ካቢኔ ከትላንት ወዲያ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሚታጎሩበትና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸምበት የነበረ ነው በሚል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ማእከላዊ ማረሚያ ቤት እንዲዘጋ ወስኗል፡፡
በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፤ ታዋቂ ግለሰቦች ፤ ሙሁራን እንዲሁም ለረጅም አመታት በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመዟዟር በክልሉ የሚፈጸሙትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችን ሲቃወሙና ሲታገሉ የቆዩት አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ #አብዱላሂ ሁሴንና አክቪስቲስት #አብዱረሺድ አሊ ሸአ በተገኙበት ማረሚያ ቤቱ በዛሬው እለት በይፋ #ተዘግቷል፡፡
በዛሬው እለት የተዘጋው የጅግጅጋ ከተማ ማእከላዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ህጉን መሰረት በማድረግ እንደሚለቀቁም ከክሉ መንግስት ለኢቢሲ የተላከው መግለጫ ያለክታል፡፡
📌የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርም በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የማሰቃያ ማዕከሉን መንግስት ለመዝጋት መወሰኑ መልካም እርምጃ ሲል በትዊተር ገፁ አወድሶታል፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27

YeneTube
በአዲስ አበባ አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ባለ ወንዝ መውደቁ ተሰማ። አደጋው 12:30 ግድም እንደደረሰ ሰምተናል። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ ከየትኛው አቅጣጫ እንደመጣም ለጊዜው አልታወቀም ተብሏል።እስካሁንም ምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈ አልታወቀም ተብሏል።ይህንኑ አደጋ በተመለከተም 12 አምቡላንስ መመደቡን ሰምተናል። የሰው ህይወትም ለማትረፍ ክሬን እና…
#አንድ_ወንድ እና #አንድ_ሴት አርፈዋል፤ በርካታ ተሳፋሪዎች ጉዳት ላይ ናቸው።
የአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልገሎት ላይ የነበረ ፤ #ከፈረንሣይ_ለጋሲዮን_የተነሳችው 55 ቁጥር ተሳፋሪዎችን እንደያዘ እስጢፋኖስ ድልድይ ሥር ወድቋል፡፡
የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ ሠራተኞች - በክሬይን በመታገዝ የተገለበጠውን አውቶብስ ለማንሳት እየጣሩ ነው፡፡ ከተገለበጠው አውቶብስ ስር ሰዎች ይኖራሉ ተብሎ ተጠርጥሯል፡፡
ፖሊስ ‹‹ሾፌሩ ከአደጋው ተርፏል፤ የአደጋ መንስኤን በማጣራት ላይ ነኝ ››- ብሏል፡፡
ከመስቀል አደባባይ ወደ 4 ኪሎ የሚወስደው መንገድ ለጊዜው #ተዘግቷል።
Via :- ጌጡ ተመስገን
@YeneTube @FikerAssefa