#ሰበር ዜና
#የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለን አሟሟት እና የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ምርምራን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ #መግለጫ #ተሰረዘ።
#መግለጫ የተሰረዘው የፌደራል ጠቅላይ ዋና አቃቤ ህግ አቶ #ብርሃኑ ጸጋዬ አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ ባልደረባ ለዲ ደብሊው እንደተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሄዳቸው መግለጫው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።” መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ቢነገርም ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልተነገረለትም።
#በዛሬው መግለጫ የኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እና ከሰኔ አስራ ስድስቱ ቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።
#ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ሲዘዋወር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. ይሰጣል ተብሎ የነበረው መግለጫ ወደ ዛሬ ጳጉሜ 1 መተላለፉ ይታወሳል።
ምንጭ ፦ DW
@YeneTube @Mycase27