Breaking!
የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር በአለም የመጀመሪያ የተባለውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማረጋገጫ ሰጠ!
ክትባቱ የተሰራው ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው ጋማሌያ ኢንስቲትዩት ውስጥ ነው ተብሏል። ይህም የሆነው ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሰው ላይ ተሞክሮ ነው ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል። ቭላድሚር ፑቲን ክትባቱ ሁሉን አስፈላጊ ደረጃዎች ተፈትኖ እንዳለፈ ጠቅሰው፣ ሴት ልጃቸው ሳይቀር ይህን ክትባት እንደወሰደችውና ውጤታማ እንደሆነ ተናግረዋል።
ምንጭ: ዘ ሰን
@YeneTube @FikerAssefa1

ከሀጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ብጥብጥ ውስጥ ተሳትፎ አድርገዋል ተብለው በተጠረጠሩ ከ1 ሺህ 200 በላይ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል - የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለፈው ወር ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተከሰተው ብጥብጥ ላይ ተሳትፎ በማድረግ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የተጠረጠሩ የመንግሥት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ላይ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው ብጥብጥ ውስጥ ተሳትፈዋል እንዲሁም በሕግ የተቀመጠውን ኃላፊነት አልተወጡም በሚል የተጠረጠሩ በቀበሌ፣ በወረዳ እና በዞን ደረጃ ያሉ ከ1 ሺህ 200 በላይ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ቢሮው ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ ከ500 በላይ የሚሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት እና ብጥብጡ ውስጥ በመሳተፍ ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል።የሕግ የበላይነትን የማስከበር ጉዳይ በባለሥልጣናት እና በሠራተኞች የጋራ ጥረት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚደረግ መሆኑን በቅርቡ የተካሄደው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ኮንፈረንስ አቅጣጫ አስቀምጧል።
#ETV

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ እጥረት ለመቀነስ በከተማ ግብርና በአጭር ግዜ ሊደርሱ የሚችሉ አትክልት ሰብሎችን ለማምረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 421 ሄክታር መሬት እንደ ት/ቤቶች፣ ተቋማት እና የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለይቶ የመሬት ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
ከሰሞኑ በወላይታ ዞን የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው መገለጫ ሰጥተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ በመግለጫቸዉ መንግስት ከክልል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ህግና ስርዓት በሚፈቅደው አግባብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆንም በወላይታ አንዳንድ አመራሮች ግን ይህንን ህጋዊ አካሄድ በሚጣረስ መልኩ የሄዱበት ያለው መንገድ በአካባቢው ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት ሆነዋል ብለዋል፡፡አመራሮቹ ሀገር የማፍረስ አላማ ካላቸው አካላት ጋር ተቀናጀተው ተልዕኮ በመቀበል እየሰሩ ነበር ብለዋልም፡፡መንግስት በአካባቢው የተፈጠረውን ሁኔታ በህግ አግባብ ብቻ የሚፈታው እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሰላምና ደህንነቱን ሊጠበቅ ይገባል ብለዋል በሰጡት መግለጫ፡፡

ለ12ኛ ክፍል አይነ ስውራን ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና በታሰበለት ደረጃ እየሄደ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሁሉም አይነሰውራን ተማሪዎች በኦንላይን እንዲፈተኑ ለማድረግ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን አስታወቋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ ዓሊ ተማሪዎቹ ፈተናውን በኦንላይን ለመፈተን የሚያስችላቸውን መሰረታዊ እውቀት እየያዙ መሆኑን ተናግረዋል።ገና ስልጠናው ሳይጀመር ለፈተና ብቁ ሊሆኑ አይችሉም ብሎ መገመት ለተማሪዎቹ ዝቅ ያለ ግምት መስጠት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በተቻለ መጠን ለፈተና ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።እንደ አስፈላጊነቱ አጋዥ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችም ለመመደብ እቅድ መያዙን አብራርተዋል።
ተማሪዎቹ እንደየ አካባቢያቸው ሁኔታ ከዚህ ቀደም የኮምፒውተር እውቀት ያላቸውና የሌላቸው በመሆናቸው ተመሳሳይ አቀባበል የላቸውም ያሉት የተስማሚ ቴክኖሎጂ ለአይነስውራን በኢትዮጵያ ዳይሬክተርና አሰልጣኝ ታምሩ እውነቱ (ዶ/ር) ይህንን ታሳቢ በማድረግ ተማሪዎችን በመለየት ለፈተና ዝግጁ ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።ተማሪዎቹ በበኩላቸው አብዛኞቻችን ከዚህ ቀደም የኮምፒውተር እውቀት ስለሌለን የስልጠናው ጊዜ ቢራዘም የሚል ጥያቄ አንስተዋል።ከመላ ሃገሪቱ የተውጣጡ 250 ዓይነስውራን ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተስማሚ ቴክኖሎጂ ስልጠና እየወሰዱ ነው።ስልጠናው ለፈተና ዝግጁ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለሚኖራቸው የስራ ጊዜ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል።
(EPA)

YeneTube
Breaking! የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር በአለም የመጀመሪያ የተባለውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማረጋገጫ ሰጠ! ክትባቱ የተሰራው ሞስኮ ውስጥ በሚገኘው ጋማሌያ ኢንስቲትዩት ውስጥ ነው ተብሏል። ይህም የሆነው ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሰው ላይ ተሞክሮ ነው ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናግረዋል። ቭላድሚር ፑቲን ክትባቱ ሁሉን አስፈላጊ ደረጃዎች ተፈትኖ እንዳለፈ ጠቅሰው፣ ሴት ልጃቸው ሳይቀር…
ሩሲያ አገኘሁት ላለችውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት 'ስፓትኒክ' የሚል ስያሜ ሰጥተዋለች። ስፓትኒክ(Sputnik) በ1957 በሩሲያ የተሰራውና በአለም የመጀመርያው ሳተላይት ስያሜ ነበር።
ከክትባቱ ጋር በተያያዘ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶዝ በ20 ሀገራት እንደታዘዘ ተገልጿል።
ምንጭ: ዘ ጋርዲያን
@YeneTube @FikerAssefa1
ከክትባቱ ጋር በተያያዘ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶዝ በ20 ሀገራት እንደታዘዘ ተገልጿል።
ምንጭ: ዘ ጋርዲያን
@YeneTube @FikerAssefa1
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1662 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 90 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
በወላይታ 21 ሰዎች መገደላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ተናገሩ!
(በዶይቸ ቨለ)
በወላይታ ዞን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 21 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ105 በላይ መቁሰላቸውን እንዳረጋገጡ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ታደሰ ለዶይቼ ቬለ ገልጹ።የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ "አምስት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ አስራ አምስት ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል።በወላይታ ዞን በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 21 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ105 በላይ መቁሰላቸውን እንዳረጋገጡ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ታደሰ ለዶይቼ ቬለ ገልጹ።የጸጥታ አስከባሪዎች በዞኑ ሰዎች በጅምላ ማሰር መጀመራቸውን የገለጹት አቶ አንዱዓለም በሶዶ እና በአካባቢው ወታደሮች በብዛት መሰማራታቸውን አክለዋል።እንደ አቶ አንዱዓለም ከሆነ "መንገዶች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች" ተዘግተዋል።
የዐይን እማኞች እንደሚሉት የዞኑ ባለሥልጣናትን ጨምሮ የወላይታ ክልል እንዲመሠረት ግፊት በማድረግ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ማሕበረሰቦች ተወካዮች ባለፈው እሁድ መታሰራቸው ከተሰማ በኋላ በተለይ ሶዶ እና ቦዲቲ ከተሞች የበረታ ተቃውሞ ተቀስቅሶባቸዋል።ከአዲስ አበባ 295 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የቦዲቲ ከተማ የጸጥታ ኃይሎች በትንሹ ስምንት ሰዎች ተኩሰው መግደላቸውን በከተማዋ የሚገኝ የጤና ማዕከል ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ተመስገን ሕሊና ለሬውተርስ ተናግረዋል።ሟቾቹ “ጭንቅላታቸው፣ ሆዳቸው እና ደረታቸው ላይ በጥይት ተመተዋል" ያሉት ተመስገን “የመጀመሪያ ሕክምና የሰጠኋቸው እኔ ነኝ። ከዚያ ሞቱ" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ አቶ ተመስገን ከሆነ ከሟቾች መካከል የ14 አመት አዳጊ ይገኝበታል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇👇👇
https://telegra.ph/-08-11-593

በአርቲስት ሀጫሉ ግድያ የተጠረጠረው ከበደ ገመቹ ፍርድ ቤት ቀረበ!
በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረውና ሸሽቶ በሃምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም አዳአ ድሬ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለው ከበደ ገመቹ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።በዛሬው የችሎት ውሎም መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ በተጠርጣሪው ላይ የሰራውን ምርመራ ስራ ገልጿል።በዚህ ጊዜም ከተጠርጣሪው እጅ ላይ ከተገኘው ስልክ የድምጽ እና የመልዕክት ልውውጥ ከኢትዮ ቴሌኮም በማስመጣት በርካታ ማስረጃ ማሰባሰቡን ለችሎቱ አብራርቷል።በእጁ ላይ የተገኘው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ለብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ለምርመራ መላኩን ያብራራው መርማሪ ፖሊስ፥ በዛሬው ችሎት መገለጽ የሌለባቸው ከበስተጀርባ ያሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ገልጿል።
በዚህ መልኩ እየተከናወኑ ላሉ ስራዎች ተጨማሪ ምርመራዎች 14 ቀን እንዲሰጠውም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ተጠርጣሪው በአስተርጓሚ አስተያየት ካለው እንዲያቀርብ የተጠየቀ ቢሆንም፥ ምንም አይነት አስተያየት እንደሌለው ምላሽ ሰጥቷል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለተጨማሪ መርመራ ለፖሊስ 14 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በተያያዘ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ቃለ መጠየቅ በማድረግ ፕሮግራሙን ቆርጦ በማቅረብ፤ እንዲሁም ሰኔ 22 እና 23 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ.ኤም.ኤን) አመጽና ብጥብጥ እንዲነሳ በመቀስቀስ የተጠረጠረው ጋዜጠኛ ጉዩ ዋርዮም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተጠርጣሪው ጋዜጠኛ ከላይ በተጠቀሰው ሚዲያ አመጽ እንዲነሳ ቅስቀሳ ማድረጉን የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ ማሰባሰቡን እና ተጨማሪ የምስክር ቃል መቀበሉን ተናግሯል።በእጁ ላይ የተገኘ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ በፎረንሲክ እያስመረመረ መሆኑንም መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሰልጣን እና ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃ ለማሰባሰብና ቀሪ ምርመራ ለመስራት ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም የምርመራ መዝገቡን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነሃሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
#FBC

የሲሚንቶ ኢንቨስትመንት ሊፈቀድ ነው!
የሲሚንቶ እጥረትን ለማሻሻል እና እያደገ የመጣውን የሲሚንቶ ፍላጎት ከግንዛቤ በማስገባት የአዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካ ኢንቨስትመንቶችን የሚከለክለውን ህግ መንግስት ሊያነሳ መሆኑ ታወቀ።ረቂቅ የማሻሻያ ደንብ ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ለንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት እና በቅርቡም በሚወጣው አዲስ የኢንቨስትመንት ደንብ ላይ እንዲካተት እየተሰራ መሆኑንም በኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብዓት የኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲዩሽን የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ጥናት እና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት ስመኝ ደጉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።
Via Addis Maleda

"በወላይታ ዞን የጸጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል ከመጠቀም ሊቆጠቡ ይገባል!" ሲል -ኢሰመኮ አሳሰበ!
በወላይታ ዞን አንዳንድ ከተሞች ነሐሴ 4 /2012 በተደረጉት ተቃውሞዎች የፀጥታ ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት እርምጃ ተመጣጣኝነት አጠያያቂ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የተለያዩ ምንጮች እንደጠቆሙት የተቃውሞ ሰልፉ የተቀሰቀሰው ሰኞ ዕለት በፌዴሬሽኑ ውስጥ አዲስ የክልል መንግሥት መመስረትን በተናጠል ለማወጅ በፈለጉ በርካታ ከፍተኛ የዞኑ ባለስልጣናት እስርን ተከትሎ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ግን ታሳሪዎቹ በአካባቢው አለመረጋጋት ለመፍጠር ሲያሴሩ ተይዘዋል መባንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ የመረጃ ምንጮች እንዳአስረዱት የባለስልጣናቱን እስር ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፈኞች በዞኑ ዙሪያ በሚገኙ በርካታ ከተሞች ወደ ጎዳናዎች የወጡ ሲሆን በዞኑ ዋና ከተማ በሶዶ አንድ ሰው እንዲሁም በቦዲቲ አምስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል ፡፡በሰኞው እስር ወቅት በጠቅላላው 178 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 28ቱ የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሆናቸው እና በወላይታ ሶዶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ውስጥ በቁጥጥር ስር የሚገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቃል አቀባይ፣ አቶ አሮን ማሾ እንደገለጹት “የፀጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፎችን በሚቆጣጠሩበት ወቅት የሞት አደጋን የሚያስከትል የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጠቡ ይገባል፤ እንደነዚህ ያሉ እርምጃዎች ቀድሞውኑን የነበረ ውጥረትን ያባብሱ እንደሆን እንጂ መፍትሔ አይሆኑም” ብለዋል፡፡
አቶ አሮን አያይዘውም በግጭቱ ወቅት የተከሰተው የ6 ሰልፈኞች አሟሟትን እና የጸጥታ ኃይሎች የኃይል አጠቃቀምን አስመልክቶ ፈጣን ምርመራ የሚያስፈልግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡እንዲሁም የታሳሪዎችን መብቶች ማክበርና በአፋጣኝ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ለስረ-ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ከመፈለግ አንጻርም የፌዴራልና የክልሉ መንግስታት በክልሉ ውስጥ ለተነሱት የክልልነት ጥያቄዎች ወቅታዊና ሰላማዊ መፍትሔ በስራ ላይ እንዲውል ከፍተኛ ጥረትና ትኩረት ሊያደርጉ ይገባልም ብለዋል፡፡
[አዲስ ማለዳ]

በትግራይ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ ነገ ይጀመራል ተባለ።
የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ስራ አመራር አባልና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሐላፊ ተባባሪ ፕሮፌሰር መረሳ ፀሃየ ዛሬ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ በክልሉ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶችና 11 የግል ተወዳዳሪዎች ይፎካከራሉ ብለዋል። ለነዚህም የሚዲያ ሽፋን የአየር ሰዓት ድልድል ተካሂዷል። የቢሮ ስራ ሲያደራጅና የምርጫ አስፈፃሚዎች ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ
የላብራቶሪ ምርመራ :- 11881
በበሽታው የተያዙ :- 584
ከበሽታው ያገገሙ :- 285
በጽኑ የታመሙ :- 190
ህይወታቸው ያለፈ:- 20
@Yenetube @Fikerassefa
የላብራቶሪ ምርመራ :- 11881
በበሽታው የተያዙ :- 584
ከበሽታው ያገገሙ :- 285
በጽኑ የታመሙ :- 190
ህይወታቸው ያለፈ:- 20
@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የላብራቶሪ ምርመራ :- 11881 በበሽታው የተያዙ :- 584 ከበሽታው ያገገሙ :- 285 በጽኑ የታመሙ :- 190 ህይወታቸው ያለፈ:- 20 @Yenetube @Fikerassefa
ባለፋት 24 ሰዓታት #የ20_ሰዎች_ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 440 አድርሶታል።
በትናንትናው ዕለት 285 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ይህም ባጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 10,696 አድርሶታል፡፡
#በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 24,175 ደርሷል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በትናንትናው ዕለት 285 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን ይህም ባጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 10,696 አድርሶታል፡፡
#በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 24,175 ደርሷል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
በዋስ ከተለቀቁ በኋላ ይግባኝ ተጠይቆባቸው እስር ቤት ያሉት የሕወሃት አባላት ዛሬ እንደገና ፍርድ ቤት እንደቀረቡ የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የሀገር ሚስጢርን ለአሸባሪዎች አሳልፈው ስለመስጠጣቸው ማስረጃ እንዳሰባሰበ ፖሊስ ለችሎቱ በማስረዳት፣ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ ችሎቱም በፖሊስ ጥያቄ ላይ ነሐሴ 11 ውሳኔ እሰጣለሁ ብሏል፡፡ እስር ላይ ያሉት ተጠርጣሪዎች፣ አዲስ አበባ የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ተወልደ ገብረ ጻዲቅ፣ የደኅንነቱ መስሪያ ቤት ባልደረባ አጽብሃ አለማየሁ፣ የሕግ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ተስፋለም ይኸድጎ እና የማዕከሉ 2 ሹፌሮች ናቸው፡፡
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
ችሎቱ በአቶ እስክንድር ነጋ ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ቀለብ ስዩም ላይ ዐቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክር እንዲያሰማ ፈቀደ!
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በአቶ እስክንድር ነጋ ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ቀለብ ስዩም ላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር እንዲያሰማ ብይን ሰጥቷል፡፡እነ አቶ እስክንድር ነጋ የአርቲስት ሀጫሉን ሞት ተከትሎ ግጭት እንዲቀሰቀስ ማድረጋቸውና በውጤቱም የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙ ብሎም ሌሎች ወንጀሎችን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ ለችሎቱ አቤቱታ አቅርቧል፡፡በወንጀሎቹ ላይ የሚያስረዱ 7 ምስክሮችን ስም ዝርዝርንም ዐቃቤ ህግ አካቷል፡፡በምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ 699/2003 መሰረት አራት ምስክሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ማንነታቸው ሳይታወቅ እንዲመሰክሩና ቀሪዎቹ ደግሞ በዝግ ችሎት የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጥ ነው ዐቃቤ ሕግ ያመለከተው፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተገቢውን መቃወሚያ ለማቅረብ የዐቃቤ ሕግ አቤቱታ ግልባጭ ቅጅ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ስለምስክሮች ሁኔታም አቤቱታ ለማቅረብ ጊዜ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ዐቃቤ ሕግም በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጥቷል፡፡የግራቀኙን ክርክር የሰማው ችሎቱ የቀዳሚ ችሎት ዓላማ ማስረጃ ማቆየትና ምስክሮችንም በመስቀለኛ ጥያቄ በሚፈተኑበት ስርዓት ስለሚመራ እንዲሁም ይህ ችሎት ውሳኔ የሚሰጥ ባለመሆኑ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚፈጠር ጫና የለም ብሏል፡፡በዚህ የቀዳሚ ምርመራ ችሎት የአቤቱታ ቅጂ ለጠበቆች ይሰጥ የሚል ህግ ባለመሆኑ ይህንን ክርክር አልተቀበልኩም ብሏል፡፡በመሆኑም የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማትና ከምስክሮች ጋር በተያያዘ ከጠበቆች የሚነሳውን መቃወሚያ ለመስማት ችሎቱ ለነገ ነሐሴ 6፣2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

አቶ ጃዋር መሐመድ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በልደታ አዳራሽ የአቶ ጃዋር መሃመድን ጉዳይ ተመልክቷል።አቶ ጃዋር መሃመድ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መረሰት ነው በዛሬው እለት ከአንድ ጠበቃ ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት።መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሃመድ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ መዝገብ ማጠናቀቁን ገልጾ፤ አቃቤ ህግ በከፈተው ቅድመ መርመራ መዝገብ እንዲቀርቡልኝ ሲል በጽሁፍ አቤቱታ አቅርቧል።
የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቃ በበኩላቸው “መርማሪ ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፤ የተጠርጣሪውን ዋስትና የሚያስከለክል ደረጃ ማስረጃ ስላላቀረበ ዋስትና ይፈቀድላቸው” ሲል ጠይቋል።ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ቢቀርብ የሰው ህይወት ባለፈበት ወንጀል የተጠረጠሩ መሆኑን ተከትሎ እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ መሆኑን ካለው ድንጋጌ መረዳት ይቻላል ብሏል።በዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፥ መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው!
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳይች ላይ በባህርዳር ከተማ እያካሄደው ያለው መድረክ እንደቀጠለ መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ።መድረኩን በተመለከተ እንደተጠናቀቀ አጠቃላይ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።ሆኖም ግን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ከመድረኩ ባህሪና ነባራዊ ሁኔታ ባፈነገጠ መንገድ የተዛቡ መረጃዎች እየተዘዋወሩ መሆኑንም አስገዝንቧል።ለአብነት ያህል “በመድረኩ አመራሩ ለሁለት ተከፍሏል” የሚሉና አመራሮቹን በስም በመጥራት እገሌ ይህንን ብለዋል በሚል የተለቀቁ የሀሰት መረጃዎች ይገኙበታል ብሏል ጽህፈት ቤቱ።በመሆኑም መረጃወቹ ከእውነት የራቁ መሆኑን ያስታወቀው ጽህፈት ቤተ፥ በመድረኩ የሚደረሱ ድምዳሜወችንና የፓርቲውን አቋም የግምገማ መድረኩ እንደተጠናቀቀ እንደሚያደርስም አስታውቋል።
#APP
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጀት (ኢባትሎአድ) በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ!
በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 104% ማሳካት ችሏል፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 104% ማሳካት ችሏል፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ባሕር ዳር ገቡ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ባሕር ዳር ገብተዋል።ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በባሕር ዳር በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#AMMA