የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የ 400 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ በአጭር ግዜ እንዲፈፀም መመሪያ ሰጠ!
ባሳለፍናው ሳምንት ለ 400 ሺ ሜትሪክ ቶን ግዢ ለወጣው ጨረታ የቀረበው ዋጋ ከፍተኛ ነው በሚል በመንግስት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የጨረታው ሂደት መሰረዙን ተከትሎ ተቆጣጣሪው አካል፣ የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድጋሚ የሚወጣው ጨረታ በአጭር ግዜ እንዲጠናቀቅ መመሪያ ሰጠ፡፡የግዢ አገልግሎቱ ግዥውን ተሎ ለመፈፀም በማሰብ በልዩ ጨረታ ለማከናወን ኤጀንሲውን ቢጠይቅም፤ ኤጅንሲው ከልዩ ጨረታ ይልቅ የግዢ ሂደቱ በአጭር ግዜ የሚፈፀምበት መንገድ የተሻለ ነው በሚል ግዢው በ 25 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡ይህም ከተለመደው የ 35 ቀናት የጨረታ ሂደት በመጠኑ ያነሰ ነው፡፡በግዢ አገልግሎቱ የቀረበው የልዩ ጨረታ ሂደት የተመረጡ ተጫራቾችን በማሳተፍ በአጭር ቀናት ውስጥ የግዢ ሂደቱን ለማጠናቀቅ ያስችል ነበር፡፡ ሆኖም ኤጀንሲው ሃሳቡን ባለመቀበሉ ጨረታው ክፍት ሆኖ መሳተፍ የፈለገ አቅራቢ መሳተፍ ይችላል፡፡
የ400 ሺ ሜትሪክ ቶን የስንዴ ግዥው በንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት ገበያን ለማረጋጋት በማሰብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት በቀረው በጀት አመት ውስጥ ለገዛ የነበረ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች ግዥው እስካሁን ሊፈፀም አልቻለም፡፡በሌላ በኩል ባሳለፍነው ሳምንት ጂምኮርፕ ኮሞዲቲስ ትሬዲንግ የተባለ የብሪታንያ ድርጅት በሌላ የጨረታ ሂደት ባሸነፈበት የ 200 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ለማከናወን ተስማምቷል፡፡ጨረታ ሰነዱ በሚፈቅደው መሰረት የግዢ አገልግሎቱ ከ 200 ሺ ሜትሪክ ቶኑ በተጨማሪ 20 በመቶ (40ሺ ሜትሪክ ቶን) እንዲያቀርብ ከለንደኑ ድርጅት ጋር ተስማምቷል፡፡የግዢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፅዋዬ ሙሉነህ ለካፒታል እዳስረዱት የ400 ሺ ሜትሪክ ቶን ግዢው መዘግየት በፍላጎት ሊፈጥር የሚችለውን ክፍተት እንዲሞላ በማሰብ ጂምኮርፕ በጨረታ ከወጣው በተጨማሪ 40 ሺ ሜትሪክ ቶን እንዲያቀርብ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ጠቅላላ ግዢውም 48.8 ሚሊየን ዶላር ግድም ነው፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa

በአፍሪካ ፈጣን የኢንተርኔት አቅራቢው በኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት ፍላጎት አሳየ!
የማደጋስካሩ አክሲያን ግሩፕ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ኢንደስትሪ ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳየ፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ጥቀዊት አመታት ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ ይታወቃል፡፡በአምስት አፍሪካ አገራት በቴሌኮም ኢንደስትሪ የተሰማራው አክሲያን ለካፒታል ጋዜጣ እንዳለው በኢትዮጵያ ገበያ የመሰማራት እድል ካገኘ በሌሎች አገራት ያስመዘገበውን ውጤት በአገሪቱም እውን ያደርጋል፡፡ከሳምንታት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን የዲጂታል ትራንስፎርሜንሽን ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ፍላጎት እንዳለውም የማደጋስካሩ ድርጅት ተናግሯል፡፡መንግስት በቴሌኮም ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ሁለት ድርጅቶች ፍቃድ ለመስጠት የፍላጎት መጠይቅ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡በፍላጎት መጠይቁ የተለያዩ ድርጅቶች መሳተፋቸው የታወቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሳፋሪ ኮም ይገኝበታል፡፡

12 ድርጅቶች በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት አሳዩ!
ባሳለፍነው ሰኞ እኩለ ቀን በተዘጋው የፍላጎት መጠይቅ 12 ድርጅቶች ፍላጎታቸውን መግለፃቸውን የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ለካፒታል ጋዜጣ በላከው መግለጫ አስታወቀ፡፡ከ12ቱ ድርጅቶች ዘጠኙ የቴሌኮም ድርጅቶች ሁለቱ በሌላ ዘርፍ ያሉ እና አንድ ድርጅት ያልተሟላ ሰነድ ያስገቡ እደሆኑ ታውቋል፡፡የቴሌኮም ድርጅቶቹ Vodafone, Vodacom, and Safaricom (በጋራ) Etisalat, Axian, MTN, Orange, Saudi Telecom Company, Telkom SA, Liquid Telecom እና Snail Mobile ሲሆኑ፡፡ ሁለቱ የቴሌኮም አንቀሳቃሽ ያልሆኑት ድርጅቶች ደግሞ Kandu Global Telecommunications እና Electromecha International Projects የተባሉ ናቸው፡፡ከሁለት አመት በፊት የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ የመንግስት ግዙፍ ድርጅቶችን በከፊል ወይም በሙሉ ለመሸጥ እንዲሁም በመንግስት ሙሉ ድርሻ ተይዘው የነበሩ ዘርፎችን ለተጨማሪ አንቀሳቃሾች በከፊል እንዲከፈቱ በወሰነው መሰረት የቴሌኮም ዘርፉ ቀዳሚ ሆኗል፡፡ለአንድ ወር የቆየው የፍላጎት መጠይቅ ሁለት ተጨማሪ የቴሌኮም አንቀሳቃሾችን በአገሪቱ ለማስገባት ያለመ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም ጀመረች!
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ እንዳደረገው ድርጅቱ የታጁራ ወደብን በይፋ መጠቀም ጀምሪያለው ብሏል፡፡የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት ወደቡ ከተገነባ ባኋላ ላለፉት 3 አመት አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል ሆኖም ባሳለፍነው ሳምንት የመጀመሪያዋ መርከብ የኢትዮጵያን ጭነት ይዛ በወደቡ መህልቋን መጧሏን እና የያዘችውንም የድንጋይ ከሰል ጭነት በጥሩ ሁኔታ እያራገፈች ነው ብለዋል፡፡
ወደቡ በዋናነት በአፋር ክልል ለሚመረተው የፖታሽ ማእድን መውጫነት የተገነባ ቢሆንም የፖታሽ ምርቱ እስካሁን መመረት እንዳልጀመረ ይታወሳል፡፡ሆኖም ወደቡ ለጥቅል ጭነት/ general cargo እንቅስቃሴ ማገልገል ቢችልም በጅቡቲ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ከ 3 አመት በፊት የተገነባው ወደብ ወደስራ መግባት ሳይችል ቆይቶ ነበር፡፡ሆኖም ባለፈው ህዳር 120 ኪ.ሜ የሚረዝመው እና ታጁራን ከ ኢትዮጵያ ድንበር በበልሆ በኩል የሚያገናኘው የመንገድ ግንዳታ መጠናቀቁ ወደቡን ወደስራ እንዲገባ ማድረግ አስችሏል፡፡
አቶ ሮባ ስለወደቡ እንቅስቃሴ ሲያስረዱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እቃ ማራገፍ የተቻለ መሆኑን ገልፀው እስከ 4 ሺ ሜትሪክ ቶን የድንጋይ ከሰል በአንድ ቀን እስከማራገፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ ይህም ከፍተኛ መጠን ነው ሲሉ አክለዋል፡፡በቀን ከ 50 እስከ 100 ተሽከርካሪዎች ምርቱን ይዘው ወደ አገር መግባት መቻሉን ማወቅ የተቻለ ሲሆን፡፡ በተለይ ከታጁራ እስከ በልሆ የተሰራው መንገድ አዲስ በመሆኑ ተሸከርካሪዎች በፍጥነት መመላላስ እንዲያስችላቸው አድርጓል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለካፒታል ገልፀዋል፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1

ኢትዮጵያዊ ፕሮግራሞችን በአገራዊ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ለማቅረብ ያቀደው ግዙፉ የፈረንሳይ ሚዲያ ተቋም ካናል ፕሉስ ግሩፕ በቀጣዩ መጋቢት ወደ ስርጭት እንደሚገባ አስታወቀ፡፡
ለክፍያ ስርጭቱ ኢትዮጵያዊ አጋር የሆኑት የብሩህ ኢንተርቴመንት ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ አብርሃም እንደተናገሩት ስርጭት ሲጀመር 50 በሚሆኑ ቻናሎች ይጀመራል ብለዋል፡፡ከነዚህም መካከል አብዛኞቹ በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፉ ኢትዮጵያዊ ቻናሎች ናቸው ብለው፡፡ ቻናሎችን ለማስገባት ካሉ የሚዲያ ተቋማት፣ ከፊልም አዘጋጆች፣ ባለሞያዎች እና ሃሳብ ካላቸው ጋር በመነጋገር ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡የልጆች ቻናሎች፣ ፊልም፣ ዶክመንተሪ እና ሌሎች ቻናሎች እንደሚኖሩት የሚጠበቀው አዲስ የክፍያ ስርጭት፡፡ ስርጭቱን ተደራሽ ለማድረግ ዲኮደር እና ወርሃዊ ክፍያ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ማጋ ይቀርባል ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ፡፡
የሃይ ዴፍኔሽን ጥራት የሚኖራቸውን ስርጭቶች የጥራት ደረጃ ከመጠበቅ አንፃር ካናል ፕሉስ ግሩፕ በሌሎች አፍሪካ አገራት እንዳደረገው የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያደርጋል ያሉት የብሩህ ኢንተርቴመንት ባለቤት ይህም ከስርጭት ባለፈ ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው ሲሉ ይገልፃሉ፡፡አሁን ላይ በኢትዮጵያ ዲኤስ ቲቪ እና ሰታር ታይምስ የተባሉ የአሜሪካ እና ቻይና የክፍያ ቴሌቭዥን ስርጭቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሆኖም ኢትዮጵያዊ የሆነ ቻናል የላቸውም፡፡
እ.ኤ.አ ከ1997 አንስቶ ካናል ፕሉስ ግሩፕ ሲስኮም ኃ/ተ/ግ/ኩ ከተባለ የአገር ውስጥ ድርጅት ጋር በመሆን ካናል ፕሉስ ሆራይዘንስ ስርጭትን በክፍያ ለፈረንሳይና ተናጋሪዎች ያቀርብ ነበር፡፡ ሆኖም ካናል ፕሉስ ግሩፕ ትኩረቱን ወደ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካ አገራት ትኩረቱን ለማድረግ በመወሰኑ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ቆይቷል ሲሉ የሲስኮም ባለቤት ወ/ት ትእግስት ይልማ ያስታውሳሉ፡፡

በአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኖች በጅቡቲ እና ድሬዳዋ ለማረፍ ተገደዱ!
ትላንት ሐምሌ 28 እና ዛሬ የሚታየው ጭጋጋማ አየር ወደ ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ለማረፍ ይመጡ የነበሩ የተወሰኑ አውሮፕላኖች ላይ እንቅፋት በመፍጠሩ አቅጣጫቸውን በመቀየር ወደ ጅቡቲ እና ድሬዳዋ ለማረፍ መገደዳቸው ተሰማ፡፡ምንጮች እንዳሉት ከጅቡቲ ጋር የአየር ማረፊያዋን በአማራጭ አየር ማረፊያነት ለመጠቀም ባለው ስምምነት መሰረት አንዳንድ ገቢ በረራዎች በመዳረሻቸው ቦሌ ማረፍ ባለመቻላቸው ወደ ጎረቤቲቱ አገር እንዲሁም ድሬዳዋ እንዳረፉ ጠቅሰዋል፡፡የነበረው ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታ የተወሰኑ አውሮፕላኖች አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ማስገደዱን ያስታወቁት ምንጮች አብዘኞቹ የትላንት በረራዎች ማምሻውን እና ዛሬ ማለዳ ካረፉባቸው ቦታ ወደ መዳረሻቸው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡ትላንት አየር መንገዱ የአየር ፀባዩ እክል ለተፈጠረ የበረራ መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቆ ሌሎች አማራጭ ማረፊያዎች እንደሚጠቀም አስታውቆ ነበር፡፡

ከ700 ሺ በላይ የፓስፖረት ደብተር በክምችት እንደያዘ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ!
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል በቂ ፓስፖት መግባቱን ገልፀው በፓስፖርት ማግኘት ሂደት ውስጥ የሚኖረውን የተንዛዛ ስራ ለመቅረፍ በተለያየ መልኩ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡የፓስፖረት እድሳት በተቋሙ መምጣት ሳያስፈልግ በአማራጭነት ኦንላይን ሂደቱን ማከናወን የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ተደራሽነትን ማስፋት ሌላው አካሄድ ነው፡፡ ሆሳእና፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ቅርንጫፍ የመክፈት ሂደቱ እየተጠናቀቀ ነው ያሉት አቶ ሙጂብ በአዲስ አበባም 2 ቅርንጫፍ ከመክፈት የቢሮ ኪራይ ጨረታ አውጥተናል ብለዋል፡፡እጥረት ሲፈጠር ብልሹ አሰራር ይታያል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በህገወጥ ተዋናዮች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ጠቅሰዋል፡፡የፓስፖርት እጥረት ባለፉት ሁለት አመታት ግድም በመታየቱ የፓስፖርት መስጫ ግዜ ወደ 75 ቀን ግድም ሆኖ ነበር፡፡ ሆኖም እጥረቱ በመቀረፉ የመስጫ ግዜ ወደ 30 ቀን ወርዷል ብለዋል፡፡ይህም የተለመደ አሰራር ነው ለምሳሌ በፓስፖርት ምርት ታዋቂ የሆነችው ጀርመን ፓስፖረት ለመስጠት ከ4 እስከ 6 ሳምንት ያስፈልጋል፣ በማለት አብራርተዋል።አጣዳፊ ጉዳይ ኖሮት ማስረጃ የሚያቀርብ ባለጉዳይ በተጨማሪ ክፍያ በቀናት ፓስፖርቱን ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ እጥረት ለመቀነስ በከተማ ግብርና በአጭር ግዜ ሊደርሱ የሚችሉ አትክልት ሰብሎችን ለማምረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 421 ሄክታር መሬት እንደ ት/ቤቶች፣ ተቋማት እና የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለይቶ የመሬት ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጀት (ኢባትሎአድ) በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ!
በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 104% ማሳካት ችሏል፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
በአጠቃላይ ድርጅቱ ከሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 25.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ከታክስ በፊት 25.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 104% ማሳካት ችሏል፡፡
#Capital
@YeneTube @FikerAssefa1
ኬንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ 373 አውሮፕላን የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ያቀረበውን ጥያቄ እንደማትቀበል አስታወቀች!
የኬንያ ኔሽን ጋዜጣ እዳስነበበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ 737 ከናይሮቢ የጭነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ጥያቄ የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እንዳልተቀበለው አስታውቋል፡፡የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ኃላፊ ጂልበርት ኪቤን ጠቅሶ ኔሽን እንደዘገበው የቦይንግ 777 የጭነት አገልግሎት እንደሚቀጥል ዘግቦ ኃላፊው ለመለስተኛው አውሮፕላን ፈቃድ የተከለከለበትን ምክንያት ይፋ ማድረግ አያስፈልግ ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡
ከኮሮና ተህዋስ መዛመት ጋር ተያይዞ የኬንያ አየር መንገድ የአለም አቀፍ በረራዎቹን በመግታቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኬንያ የግብርና ምርቶችን በአዲስ አበባ በኩል ወደ አለም አቀፏ የገበያ ማእከል ሌዥ ፣ ቤልጄም በማድረስ ለኬንያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አጋርነቱን ማሳየቱ ይታወሳል፡፡
ምናልባት የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የቦይንግ 737 በረራ ፈቃዱን የነፈገው የኬንያ አየር መንገድን ከውድድር ለመጠበቅ ሳይሆን አንደማይቀር ይታመናል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በአህጉሪቱ ግንባር ቀደም እንደሆነ ይታወሳል፡፡

የህዳሴ ግድብ በወቅቱ መጠናቀቅ ለምስራቅ አፍሪካ የተፋሰሱ አገራት የኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ አስታዋጾ እንደሚያደርግ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ጥናት አሳየ!
የግድቡ ሙሌት እ.ኤ.አ በ2024 ቢጠናቀቅ እና ወደስራ ቢገባ የተፋሰሱ አገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ) አመታዊ ጠቅላላ የስራ ውጤት (real GDP) በ2024 የ 8.07 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ እንደሚኖረው ጥናቱ አመላክቷል፡፡በግድቡ ወደ ስራ መግባት ኢትዮጵያ የ6.79 ቢሊየን ዶላር፣ ሱዳን የ1.11 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ግብፅ የ0.17 ቢሊየን ዶላር አገራዊ ጠቅላላ የስራ ውጤት (real GDP) ያገኙበታል ብሏል ጥናቱ፡፡