YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ድጋሚ እንዳልታሰር ስጋት አለኝ አሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ(ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪዋ ወይዘሮ ሂሩት ክፍሌ በአዲስ አበባ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ወጣቶችን አስተባብረው ተንቀሳቅሰዋል በሚል ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አይዘነጋም፡፡ወይዘሮ ሂሩት በዋናነት ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጋር በመሆን በቅድስተ ማሪያም አካባቢ አንድ መቶ ያህል ወጣቶች በማስተባበር ሁከት ለማስነሳት ሞክረዋል የሚል ነው፡፡ይሁንና ለአራት ያህል ጊዜ ችሎት የቀረቡት ወይዘሮ ሂሩት ፍርድ ቤት በስድስት ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ በይኗል፡፡ከሁለት ዓመት በፊት የተፈጠረው የአመራር ለውጥ ከመምጣቱ በፊት ለአራት ጊዜ ያህል ታስረዋል፡፡ከሁለት ዓመት ወዲህ ሲታሰሩ ግን የአሁኑ የመጀመሪያው ነው፡፡ምንም እንኳን ሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከእስር ቢለቀቁም አሁንም ግን ስጋት እንዳላቸው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡አሐዱ የሚያሰጋቸውን ሁኔታ ምን ይሆን ሲል ላነሳላቸው ጥያቄም ከቀረበባቸው ክስ እና አጠቃላይ ሂደቱን መነሻ በማድረግ ይህ መሰል ስጋት እንዳደረባቸው ምላሽ ሰጥተዋል በቅድሰተ ማሪያም አካባቢ ከወይዘሮ ሂሩት ጋር በመሆን ሁከትና ብጥብት ሊፈጥሩ ነበር የተባሉት አቶ እስከንድር ነጋ አሁንም በቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ 94.3)
@YeneTube @FikerAssefa1
ከ600 በላይ ዜጎች የኢትዮጵያን ዜግነት ጠይቀው ማስተናገድ እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡

ኤጀንሲው የኤርትራ፣ የሶሪያ፣ የኢራን እና የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ በርካቶች የኢትዮጵያን ዜግነት ጠይቀውኛል ብሏል፡፡የዜግነት ጠያቂው ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም ኤጀንሲው በአዲስ የተቋቋመ መሆኑ እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አገልግሎት ማቋረጡን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ገልጸዋል፡፡ተቋሙ እንደ አዲስ የተቋቋመ እና ስራውንም የሚሰራው በኮሚቴ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ፣ ከፖሊስና ከኤጀንሲው ተውጣጥቶ የተዋቀረ ኮሚቴ ቢኖርም ወደ ስራ ሳይገቡ የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ መከሰት አገልግሎቱን አዘግይቶታል ብለዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)
@YeneTube @FikerAssefa1
በዎላይታ ዞን ከትናንት ጀምሮ ስለተፈጠረው አለመረጋጋት የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት "ከትናንት ጀምሮ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት አካላት እየተነሳ ያለውን የክልል እንሁን ጥያቄ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዳይፈታ ለማድረግ ሲጥሩ የነበሩ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው" ብለዋል፡፡

እስካሁን ባለው ሁኔታ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

"አመራሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በአካባቢው መንገድ የመዝጋትና ግርግር የመፍጠር አዝማሚያ ታይቷል፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል" ብለዋል፡፡አሁን ላይም አካባቢው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እንዲመለስ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa1
እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛው ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ!

በእነ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ችሎቱ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በልደታ አዳራሽ መስማት ተጀምሮ ነበር።ይሁን እንጅ እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ላይ ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን ተመልክቶ ዳኛው መዝገቡ እንዲመረመርና በመዝገቡ ላይ ትዕዛዝ እስከሚሰጥበት ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲቆዩ እና መጥሪያ ሲደርሳቸው የሚመጡ ይሆናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል፡፡ከዚህ በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 5 ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ ማቅረቡ ይታወሳል።ፍርድ ቤቱም አምስቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን መስጠቱ የሚታወስ ነው።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1387 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 64 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡የአንድ ሰው ህይወትም በቫይረሱ ምክንያት አልፏል።

@YeneTube @FikerAssefa1
'የትግራይ ክልል ምርጫ ኮምሽን' ኮምሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማሪያም የትግራይ ክልል ምርጫ ከመስከረም 5-10 ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ ለSBS አማርኛ ተናግረዋል፤ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ኮሚሽነሩ አክለው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሁሉን ያቀፈ እና አሳታፊ የሆነ ሰፊ የኦሮሞ ምክክር መድረክ (broad based Oromo national dialogue) እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ።

ፓርቲው በሂልተን ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ ውይይቱን የማካሄጃ "ጊዜው አሁን ነው" ብሏል።ውይይቱ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኦሮሞ ልሂቃን፣ አክቲቪስቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አራማጅ ድርጅቶች (civic organizations) እና ቄሮና ቀሬን ያሳተፈ እንዲሆን ጠይቋል። ውይይቱ ላይ የኦነግ ነባርና መስራች አባላት፣ የቀድሞ የኦነግ አባላት እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ከድርጅቱ የራቁ፣ ከድርጅቱ ጋር ትስስር ያላቸውና ግዴታቸውን የተወጡ እና በመወጣት ላይ ያሉ አባላትን ያቀፈ መሆን እንዳለበት ጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪ ግንባሩ 600 የሚሆኑ አባላቱ በመንግስት እንደታሰሩበት አስታውቋል።በርካታ አባላት ስላሉን መቶ በመቶ ሰላማዊ ትግሉን ተቀብለው ይንቀሳቀሳሉ የሚል ሙሉ እምነት የለንም ብሏል።በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ብንወስንም የድርጅታችን አመራሮች እና አባላትን ማሰር እና ማጠልሸት እየተሰራ ነው፣
በኦነግ እና በሕወሓት መካከል አለ እየተባለ የሚወራውም ፍፁም ሀሰት እና የሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት የጦርነት ግንኙነት ነው የነበረው ሲል ኦነግ አስታውቋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር & አዲስ ማለዳ)
@YeneTube @FikerAssefa
መከላከያ ሚኒስቴር በከባድ ወታደራዊ የጦር መሳሪያ ማሽከርከር ሙያ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች አስመረቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለ6 ወራት ያህል በአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በከባድ ወታደራዊ የጦር መሳሪያ ማሽከርከር ሙያ ያሰለጠናቸውን ሙያተኞች ማስመረቁን ገልጿል።ተመራቂዎቹን የምድር ሃይል ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በክብር እንግድነት ተገኝተው አስመርቀዋል።ተመራቂዎች በማሰልጠኛ ት/ቤቱ በነበራቸው ቆይታ የቀሰሙትን የአስተሳሰብ ፣ የቴክኒክና የአካል ብቃት በመጠቀም የሰራዊቱን የማድረግ አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸው ምክትል አዛዡ ተናግረዋል፡፡

የአዋሽ አርባ የውጊያ ቴክኒክ ት/ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ ከበደ በበኩላቸው ፣ ምንም እንኳን ጦርነት ቀዳሚ ምርጫችን ባይሆንም ስልጠናውን ከወቅታዊ አገራዊ ሁኔታችንና ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በማያያዝ እውነተኛ ልምምድ እንዲሰሩ አድርገናል ብለዋል ፡፡የት/ቤቱ ምክትል አዛዥና የስልጠና ሃላፊ ኮሎኔል ብርሃኑ አሰፋ በሰጡት አስተያየት ፣ ስልጠናው ለስድስት ወራት ያክል በቀንና በሌሊት የተሰጠ ሲሆን ፣ ከተያዘው እቅድ ከ90 በመቶ በላይ ማሳካታቸውን ገልፀዋል፡፡በስልጠናው ከ99 ከመቶ በላይ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ከሆኑ ተመራቂዎች መካከል ወ/ር የምክር መሰለ እና ወ/ር ኩሳ ባይሳ በሰጡት አስተያየት ፣ በሚመደቡበት ክፍል ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣትና የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበር መዘጋጀታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር በድረገጹ አስታውቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa1
በኮንታ ልዩ ወረዳ ሰሞኑን በተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ናዳ ተከስቶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

በልዩ ወረዳዉ ሰሞኑን ተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት በጨካ ቦቻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮማ መንደር በቀን 3/12/2012 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ የሶስት ሰዎች ህይወት በናዳ ማለፉን የሟች ቤተሰቦችና የአከባቢዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ወረዳዉ አደጋ ስጋትና አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፊን ጎበዜ በልዩ ወረዳዉ ከሚገኙ ቀበሌያት 23ቱ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ያለባቸዉ መሆኑን ተናግረዉ ከእነዚህም አንዱ በሆነዉ ጨካ ቦቻ ቀበሌ ሰሞኑን ተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ናዳ ተከስቶ ዕድሜያቸዉ የ8፣ 10 እና 12 ዓመት የሆኑ ልጆች ህይወታቸዉ ማለፉን አብራርተዋል፡፡

በአስከሬን ፍለጋ የሁለቱ ተገኝቶ የተቀበረ ሲሆን የአንዱ አስከሬን ፍለጋ መቀጠሉን የተናገሩት ኃላፊዉ በሌሎችም በተተነበዩ ቀበሌያት መሰል አደጋ እየተከሰተ በመሆኑ ህብረተሰቡ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡የልዩ ወረዳዉ ከፍተኛ አመራር አካላትና የፀጥታ አካላት በቦታዉ ተገኝተዉ አስከሬን የማፋለግና የሟቾች ቤተሰቦችን ያጽናኑ ሲሆን የልዩ ወረዳዉ ም/አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ተፈራ ልዩ ወረዳዉ ካለዉ መሬት አቀማመጥ መነሻ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጥሮ አደጋ እየተከሰተ መሆኑን ገልፀዉ፣ በተመሳሳይ አደጋ በልዩ ወረዳዉ ጥቅምት 2/2012 ዓ.ም የ22 ሰዎች ህልፈት በኋላ የተፈናቀሉትን ወገኖች መልሶ ማቋቋም ስራ ሳይጠናቀቅ ከወዲሁ መሰል አደጋ እየተከሰተ ስለሆነ የክልሉ መንግስት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለቅድመ-ጥንቃቄ ስራ የድርሻቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

(የልዩ ወ/ኮሙ/ጉ/ጽ/ቤት)
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 773 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 11,039 የላብራቶሪ ምርመራ 773 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 205 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 23,591 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 420 ደርሷል፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 10,411 ደርሰዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
ዛሬ ምሽት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የህዳሴው ግድብ ድርድር ወደሚቀትለው ሳምንት ተራዘመ።

የውሃ፣ የመስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ድርድሩ ወደሚቀጥለው ሳምንት የተራዘመው በሱዳን ጥያቄ መሰረት ነው።ሃገራቱ ድርድሩን በመቀጠል የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ቢሮ ስብሰባ በተካሄደ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመካከለኛ እና የመጨረሻ ሪፓርት ለህብረቱ ሊቀ መንበር ሪፓርት እንዲያቀርቡ ይጠበቅ ነበር፡፡ይሁንና ግብጽ እና ሱዳን ባቀረቡት ማራዘሚያ ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ድርድር ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጽ/ቤት እ.ኤ.አ በጁላይ 24 ቀን 2020 ባወጣው መግለጫ እንዲሁም የሦስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስቴሮች በሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በጋራ ሰነድ ላይ ለመስራት በደረሱት መግባባት መሰረት ኢትዮጵያ የበኩሏን የግድብ ሙሌት ደምብ ማቅረቧ አይዘነጋም፡፡የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የግድቡ አደራዳሪ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማምፖሳ ሶስቱ አገራት በአፍሪካዊ ስሜት ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ ማሳሰቡ ይታወሳል።ድርድሩ በመጪው ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2012 እንሚቀጥል ይጠበቃል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
በደቡብ ክልል የዎላይታ ዞን የተለያዩ ከተሞች ዛሬ በወጣቶችና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተካሄደ ግጭት ቢያንስ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የየከተሞቹ ነዋሪዎች ገለጹ።ነዋሪዎቹ እንዳሉት ግጭቱ ሊከሰት የቻለው 26 የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው።አመራሮቹና ባለሙያዎቹ ሊያዙ የቻሉት ኢመደበኛና ህገ ወጥ ቡድኖች ያሏቸውን በማደራጀት የጥፋት ተግባር ለመፈጸም በመንቀሳቀሳቸው ነው ሲሉ የሚናገሩት የደቡብ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው በግጭቱም የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ለዶቼ ቨለ አረጋግጠዋል ።

@YeneTube @FikerAssefa1
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 500 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።ርዕሰ-መስተዳድሩ፣ በአፋር ክልል የአዋሽ ወንዝ ያስከተለው ጎርፍ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የዛሬው የኦነግ መግለጫ የኔ እውቅና የለውም አሉ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ዛሬ ከሰዐት በሂልተን ሆቴል ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ በተገኙበት መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።ሆኖም የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ይህ መግለጫ እኔ ሳላውቀው የተደረገ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።አቶ ዳውድ እንዳሉት ምክትሌም ትናንት ስለ መግለጫው እንደማያውቅ ከነገረኝ በኋላ ነው የተገኘው፣ የስብሰባው አላማ ምን እንደሆነም የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከሰሞኑ እሳቸው ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በነበረበት ወቅት በተደረገውና ምክትላቸው አቶ አራርሶ የመሩት ስብሰባ ብዙ የተምታቱ ነገሮች የነበሩበት ነበር ብለው፣ ይህንንም የግንባሩ የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እንደሚያጣራው አክለው ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የሊባኖስ መንግሥት ሥልጣን ለቀቀ!

ባለፈው ማክሰኞ በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የሊባኖስ መንግሥት በገዛ ፈቃዱ ሥልጣን ለቋል።ከ200 በላይ ሰዎች ለሞት የተዳረጉበት በሊባኖስ ቤይሩት በሚገኝ ወደብ ላይ የደረሰው ፍንዳታን ተከትሎ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ተፋፍመው ነበር።ሰኞ አመሻሽ ላይ ነው ገዢው የሊባኖስ መንግሥት ሥልጣን መልቀቁን በቴሌቪዥን መስኮት ያሳወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ናቸው።በርካታ ሊባኖሳዊያን ለፍንዳታው የገዢው ፓርቲ አመራሮችን ይወቅሳሉ፤ በሙስና ተጠምደው ረስተውናልም ይላሉ።ቤይሩትን ያናወጠው ፍንዳታ የተከሰተው 2750 ቶን የሚመዝን አሞኒዬም ናይትሬት የተባለ ንጥረ ነገር ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ ለበርካታ ዓመታት በመከማቸቱ ነው።ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በደረሰው ፍንዳታ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 መድረሱንና 110 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንደማይታወቅ የቤይሩት ከተማ ከንቲባ ማርዋን አቡድ አል-ማርሳድ ለተሰኘው የዜና ምንጭ ተናግረዋል።

በርካታ የውጭ አገር ዜጎችና የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የገቡበት ካልታወቁ ሰዎች መካከል ናቸው ብለዋል ከንቲባው።በፍንዳታው ሳቢያ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል፤ የቀሩትም በርና መስኮቶቻቸውም ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።ፍንዳታውን ተከትሎ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ሰልፈኞች የቤይሩትን መንገዶች አጨናንቀዋል፤ ፖሊስም ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጭስ ለመበተን ሞክሯል።ሊባኖሳዊያን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሲያሰሙ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ለዓመታት የዘለቁ ናቸው።አገሪቱ በምጣኔ ሃብት ድቀት መመታቷ ሳያንስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ኑሮ መቀዛቀዙ ለሊባኖሳዊያን ፈተና ሆኗል።ነገር ግን የዕለተ ማክሰኞው ፍንዳታ ብዙዎች ጣታቸውን መንግሥት ላይ እንዲቀስሩና ለተቃውሞ ወደ አደባባይ እንዲወጡ አድርጓቸዋል።አሁን ያለው የሊባኖስ መንግሥት ባለፈው ዓመት በአገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሥልጣን የለቀቀውን መንግሥት ተከትሎ ወንበር የጨበጠ ነበር።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ከዛሬ ጀምሮ ባለው አንድ ሳምንት ከሰሞኑ እየጣለ ያለው ዝናብ ከምስራቃዊና በከፊል ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ውጪ በአብዛኛው አካባቢ እንደሚቀጥል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ትንበያና ምርምር ማዕከል (ICPAC) አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በጎርፍ አደጋ 114 ሺህ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ!

አዲስ አበባ፡- በሀገሪቱ ከመደበኛ በላይ በጣለው ዝናብ በተለያዩ ክልሎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በ114 ሺህ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና ከእነዚህም ውስጥ 44 ሺህ 875 ሰዎች መፈናቀላቸውን የብሔራዊ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን አስታወቀ።ለተጎጂዎች ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ መላኩን ገለጸ፡፡የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ከመደበኛ በላይ በጣለው ዝናብ ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጎርፍ አደጋ እየተከሰተ ይገኛል።በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም በጋምቤላ ክልሎች በአጠቃላይ 114 ሺህ ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 44 ሺህ 875ቱ ለመፈናቀል ተዳርገዋል፡፡

በአፋር ክልል በአሳይታ 21 ሺህ 200 ሰዎች በአደጋው መጎዳታቸውን አቶ ደበበ ጠቅሰው፣ ከእነዚህ መካከል ስምንት ሺህ 480 ሰዎች መፈናቀላቸውንም አስታውቀዋል።በዱብቲ በ7 ሺህ 770 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ከእነዚህ መካከልም 3 ሺህ 108 ተፈናቅለዋል።በሚሌ አንድ ሺህ 250 ሰዎች መጎዳታቸውን፣ ከእነዚህ መካከልም አምስት መቶው መፈናቀላቸውን አብራርተዋል።በአፋንቦ ሁለት ሺህ ሰዎች ተጎድተዋል፤ ከእነዚህ 800 ተፈናቅለዋል ሲሉ አብራርተዋል።በሌሎች የአፋር አካባቢዎች ጉዳት እና መፈናቀል መድረሱን ጠቀሰው፣ በአፋር ክልል በአጠቃላይ 49 ሺህ 65 ሰዎች መጎዳታቸውንና ከእነዚህ መካከልም 19 ሺህ 626 ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ደበበ ገለጻ፤ በአማራ ክልል አምስት ሺህ 520 ሰዎች ተጎድተዋል ፤የተፈናቀለ ሰው የለም፣ በኦሮሚያ 15 ሺህ ሰዎች ተጎድተዋል ፤የተፈናቀሉት አምስት ሺህ 33 ናቸው።በጋምቤላ 12 ሺህ 500 ሰዎች ሲጎዱ አራት ሺህ 900 ሰዎች ተፈናቅለዋል ፤በደቡብ ብሄር ቤረሰቦችና ህዝቦች 32 ሺህ ሰዎች ሲጎዱ 15 ሺህ 316 ሰዎች ተፈናቅለዋል።ኮሚሽኑ ለተጎጂዎች ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ መላኩን የጠቀሱት አቶ ደበበ፣ ከተላኩት ምግቦች ውስጥ ለሕፃናት የሚሆን አልሚ ምግብ 35 በመቶ እንደሚይዝ አመልክተዋል።በቀጣይ የዝናቡ ሁኔታ ከመደበኛ በላይ የሚቀጥል በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃ እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።ጎርፍ በሚበዛባቸው ቦታዎች የውሃ ማቆር ሥራ በማከናወን በቀጣይ በጋ ወራት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል።ኮሚሽኑም በቀጣይ ሊከሰቱ ለሚችሉ አደጋዎች ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

(ኢ.ፕ.ድ)
@YeneTube @FikerAssefa1
መሪ የልማት እቅዶችን ከገዥው ፓርቲ ነጥሎ መመልከት ይገባል-የምጣኔ ሀብት ተንታኝ

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በኩል ይፋ እየሆኑ ያሉትን የ10 አመት መሪ የልማት እቅዶችን ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና የስልጣን ቆይታ እና የፖለቲካ አጀንዳ ነጥሎ ማየት እንደሚገባ የምጣኔ-ሐብት ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡እቅዶቹ ሊመዘኑ የሚባቸው ለሀገሪቱ በሚኖራቸው ምጣኔ-ሐብታዊ ፋይዳ እንጂ ስልጣን ላይ ካለው ፓርቲ አንፃር አለመሆኑን የሚገልፁት አቶ ዋሲሁን የተቀመጡት መሪ የልማት እቅዶችም የፓርቲ ናቸው ብሎ ማመን ተገቢ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

አቶ ዋሲሁን አያይዘውም በእቅዶቹ ላይ የተቀመጡት መዳረሻ ግቦች በዝርዝር ሊታዩ ይገባል ብለዋል፡፡በተለይም የፋይናንስ ምንጭ ይሆናሉ ተብለው የተቀመጡ መንገዶች ምን ያህል አዋጪ ናቸው የሚለው አሁንም ሊጤን ይገባዋል ብለዋል ባለሙያው፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)
@YeneTube @FikerAssefa1
በደቡብ ክልል የዎላይታ ዞን የተለያዩ ከተሞች በወጣቶችና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተካሄደው ግጭት ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን ሮይተርስና ኒዮርክ ታይምስ ዘግበዋል። የጤና ተቋም ባለሙያዎችን ጠቅሰው እነዚህ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በቦዲቲ ከተማ 6 ሰዎች ከፀጥታ ሃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሞተዋል፣ በተመሳሳይ በሶዶ ከተማ ደግሞ 4 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። በቦዲቲ ከሞቱት መሃል የ14 አመት ታዳጊ እንደሚገኝበትና ተጨማሪ 34 ሰዎች መጎዳታቸውን የተጠቀሰ ሲሆን የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይን በስልክ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አለመሳካቱ ተገልጿል።

Photo: Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ መንግስት የያሲን ጁማን የዋስ መብት በማክበር ከእስር እንዲለቀው ጥያቄ ቀረበ!

ቢቢሲ (BBC) ትላንት ረፋድ ላይ ይዞ በወጣው መረጃ መሰረት ፎሪን ኮሮስፖንዳንትስ አሶሲዬሽን ኦፍ ኢስት አፍሪካ (Foreign Correspondents Association of East Africa) የተሰኘው የጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማክበር ኬንያዊውን ጋዜጠኛ ከእስር እንዲለቀው በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልእክት ጠይቋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአገሪቱ በተፈጠረው ረብሻ ላይ በማነሳሳት እና በቀጥታ ተሳታፊነት ተጠርጥሮ በማረምያ ቤት የሚገኘው ያሲን ጁማ ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ የዋስ መብቱ ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፍርድቤት ቢወስንም ጋዜጠኛው አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኝ ያስታወሰው የማህበሩ መልእክት አክሎም የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማክበር እንደሚጠበቅበት አስረግጦ ገልጿል። ያሲን ጁማ በኢትዮጵያ የፅጥታ አካላት በጃዋር መሀመድ መኖርያ ቤት ውስጥ በሰኔ 26 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥጥር መዋሉ ይታወሳል።

ፎሪን ኮሮስፖንዳንትስ አሶሲዬሽን ኦፍ ኢስት አፍሪካ (Foreign Correspondents Association of East Africa) በኬንያ የተመዘገበ ድርጅት ሲሆን በስሩ ከ500 በላይ ምስራቅ አፍሪካ ላይ በማተኮር የሚሰሩ ጋዜጠኞችን ያቀፈ ማህበር እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa1