ቢቢሲ በአገሪቱ ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የጤና ባለሙያዎች ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዳሰሳ ቅኝት አድርጓል።
በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ-19 ያላቸው ተጋላጭነት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝቧል። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እየተስፋፋ መሆኑን ያነጋገርናቸው ክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
የጤና ቢሮ ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከጥንቃቄ ጉድለት፣ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር እና በሌሎች ስፍራዎች በሚኖር የቫይረሱ ተጋላጭነት ምክንያት መያዛቸውን ተናግረዋል።
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa

በሲዳማ ክልል በሚገኘው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ከ100 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ ለቢቢሲ ገለፁ።
ክልሉ ባለፉት 12 ቀናት በኢንዱስትሪ መንደሩ ባደረገው ምርመራ የኢንዱስትሪ መንደሩ ሠራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛችን ያረጋገጠ ሲሆን፤ ቫይረሱ በተለይ በሁለት ማዕከላት (ሼዶች) ውስጥ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ዶ/ር ማቴ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ
https://telegra.ph/hawassa-08-12-2

በትግራይ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡ ቅስቀሳው በመገናኛ ብዙሐን የሚካሄድ ሲሆን ፣ በቀን በአጠቃላይ 10 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የክልሉ ሚድያዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ፕሮግራሞች ያሰራጫሉ፡፡
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa1
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ዲቡ አርሶ አደር ቀበሌ የአዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ 526 አባወራዎችን ለችግር አጋልጧል፡፡የጎርፍ አደጋው ለጊዜው ግምቱ የማይታወቅ ንብረትን አውድሟል፡፡ጎርፉ በቀበሌው ከለሊቱ 6 ሰዓት የተከሰተ በመሆኑ ተጎጂ አባወራዎች ከነቤተሰባቸው መውጫ መንገድ አጥተዋል፡፡የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዲሪርሳ ዋቁማ ተጎጂ አካላትን የማውጣት ስራ እየተከናወ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግን ያለው ጀልባ ትንሽ በመሆኑ ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ተገልጧል፡፡ለዜጎቹ መጠለያ እና ምግብ እንዲሁም የከብቶች መኖ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የዞኑ አስተዳደር ገልጿል።
#OBN
@YeneTube @FikerAssefa1
#OBN
@YeneTube @FikerAssefa1
እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዳኛ ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እነ አቶ ጃዋር ባቀረቡት አቤቱታ ላይ መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡በዚህም አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ይህን ተከትሎም ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ የሚታይ ይሆናል ተብሏል፡፡በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ 14 ሰዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ በኮቪድ19 ተጠርጥሮ ችሎት አልቀረበም፡፡እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ከትናንት በስቲያ ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
#FBC

የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸው ተነሱ።
የኦሮሚያ ክልልን በመወከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የነበሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከአባልነታቸው መነሳታቸው ተጠቁሟል። ሰሞኑን ደግሞ ከኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው መታገዳቸው ይታወሳል።ከአቶ ለማ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ የነበሩት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰንና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኦሮሚያ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሚልኬሳ ሚደጋ (ዶ/ር) ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸው መነሳታቸውን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ አመልክቷል።
ጨፌ ኦሮሚያ ክልሉን በመወከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ለማ፣ ወ/ሮ ጠይባና ሚልኬሳ (ዶ/ር) ከአባልነታቸው እንዲነሱ የወሰነው ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ እንደሆነም ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።ጨፌ ኦሮሚያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ተጓድለዋል በሚል ምክንያት ሦስቱ አመራሮች በሌሎች እንዲተኩ ማድረጉን መረጃዎቹ አመልክተዋል
በመሆኑም ጨፌው በሦስቱ አመራሮች ምትክ አዲስ አባላትን መርጦ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስታወቀ ሲሆን፣ አቶ ለማን ተክተው የተመረጡትም በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና በጨፌ ኦሮሚያ የክልሉ መንግሥት ተጠሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ናቸው።በሌሎቹ ሁለት አባላት ምትክ ደግሞ የክልሉ ፓርቲ አደረጃጀት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻና አቶ አብዱል ሐኪም መመረጣቸው ታውቋል። የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ለማ ሰሞኑን በተካሄደ የፓርቲ ስብሰባ ከኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው መታገዳቸውም ይፋ ሆኗል።
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ በአዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብስባ ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. አጠናቆ ባወጣው መግለጫ፣ አቶ ለማን ጨምሮ ሦስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ላልተወሰነ ጊዜ መታገዳቸውን አስታውቋል።የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን ስብሰባና ውሳኔዎቹን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ስብሰባው በፓርቲው ክልላዊ መዋቅር ላይ የተስተዋሉ ድክመቶች ላይ በስፋት ተወያይቶ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የተመለከቱ ውሳኔዎችን እንዳሳለፈ ገልጸዋል።
በፓርቲው የክልል መዋቅር ከፍተኛ አመራሮች ላይ ባደረገው ግምገማም በማዕከላዊ አባልነት ሲያገለግሉ የነበሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ፣ ወ/ሮ ጠይባና ሚልኬሳ (ዶ/ር) ላልተወሰነ ጊዜ ከማዕከላዊ አባልነታቸው እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቀዋል።አቶ ለማ መገርሳ ከማዕከላዊ አባልነታቸው እንዲታገዱ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባዎች ላይ በተደጋጋሚ አለመገኘታቸው መሆኑን አመልክተዋል።በተጨማሪም የመከላከያ ሚኒስትር ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተጣሉባቸው መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ላይም በተደጋጋሚ አለመገኘታቸውን አቶ ፍቃዱ በምክንያትነት አንስተዋል።
[Ethio FM]

ኬንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ 373 አውሮፕላን የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ያቀረበውን ጥያቄ እንደማትቀበል አስታወቀች!
የኬንያ ኔሽን ጋዜጣ እዳስነበበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ 737 ከናይሮቢ የጭነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ፈቃድ ጥያቄ የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እንዳልተቀበለው አስታውቋል፡፡የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ኃላፊ ጂልበርት ኪቤን ጠቅሶ ኔሽን እንደዘገበው የቦይንግ 777 የጭነት አገልግሎት እንደሚቀጥል ዘግቦ ኃላፊው ለመለስተኛው አውሮፕላን ፈቃድ የተከለከለበትን ምክንያት ይፋ ማድረግ አያስፈልግ ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡
ከኮሮና ተህዋስ መዛመት ጋር ተያይዞ የኬንያ አየር መንገድ የአለም አቀፍ በረራዎቹን በመግታቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኬንያ የግብርና ምርቶችን በአዲስ አበባ በኩል ወደ አለም አቀፏ የገበያ ማእከል ሌዥ ፣ ቤልጄም በማድረስ ለኬንያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አጋርነቱን ማሳየቱ ይታወሳል፡፡
ምናልባት የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የቦይንግ 737 በረራ ፈቃዱን የነፈገው የኬንያ አየር መንገድን ከውድድር ለመጠበቅ ሳይሆን አንደማይቀር ይታመናል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት በአህጉሪቱ ግንባር ቀደም እንደሆነ ይታወሳል፡፡
#Capital

የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ ውሃ መለቀቅ ተጀመረ!
የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ በክረምቱ ዝናብ እየሞላ በመምጣቱ ውሃ መለቀቅ ተጀምሯል፡፡ከግድቡ በየደረጃው የሚለቀቀው ዉሃ በታችኛው ተፋስስ ላይ ቅፅበታዊ ጎርፍ እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ነው፡፡ወደ ግድቡ የሚገባውን ውሃ ሁሉ እንደመጣ ላለመልቀቅና የተመጠነ የውሃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ ሊያጋጥም የሚችለውን ጉዳት ለማስቀረት ከአደጋ መከላከልና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጋር በመሆን በተፋሰሱ የታችኛው ክፍል የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩና መልዕክቶች ሲተላለፉ ቆይተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ግድቡ በተከታታይ በቀን በአማካይ 40 ሳ.ሜ. ከፍታ ያለው ውሃ እየያዘ በመሆኑ በመካከለኛ ከፍታ ላይ የሚገኙ የግድቡን ውሃ ማስተንፈሻዎች በመክፈት ትላንት ከእኩለ ቀን ጀምሮ ለስድስት ሰዓታት በሰከንድ ወደ 2ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መልቀቅ ተጀምሯል፡፡ ዛሬም በተመሳሳይ ውሃ የመልቀቅ ሂደቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደግድቡ የሚገባውን ውሃ ታሳቢ ያደረገ ተጨማሪ ውሃ ሊለቀቅ ስለሚችል አሁንም በኦሞ ጊቤ የታችኛው ተፋሰስ የሚገኙ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዲችሉ የአካባቢው አመራሮች ተገቢውን መልዕክት እንድታስተላልፉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጥሪውን ያቀርባል፡፡
Via EEP

የጎረቤቷን የኤቲኤም ካርድ በመስረቅ ከ580 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጋ ለግል ጥቅሟ ያዋለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች::
በየካ ክፍለ ከተማ የጎረቤቷን የኤቲኤም ካርድ በመስረቅ ከ580 ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጋ ለግል ጥቅሟ ያዋለች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ገለፀ፡፡የግል ተበዳይ ወ/ሮ ሰናይ ቦጋለ እና ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለችው ግለሰብ የቅርብ ግንኙነት እና ጉርብትና አላቸው፡፡በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መርማሪ ረዳት ሳጅን እስጢፋኖስ ገ/ታቲዎስ እንደገለፁት ተጠርጣሪዋ ከግል ተበዳይ ጋር ያላትን ቅርበት ተጠቅማ ወደ ወ/ሮ ሰናይ ቦጋለ መኝታ ክፍል በመግባት ቁም ሳጥን ውስጥ ተቀምጦ የነበረ የዘመን ባንክ ኤቲኤም ካርድ ከነ ሚስጥር ቁጥሩ ሰርቃ በመውሰድ እና በተለያዩ ጊዜያት ከ5መቶ 80 ሺ ብር በላይ ከባንኩ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሟ አውላች፡፡
የግል ተበዳይ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ መሆናቸውን የገለፁት ተወካያቸው አቶ ወርቁ ለገሰ ወይዘሮ ሰናይ ቦጋለ የኤቲኤም ካርዱን ከባንኩ ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ተጠቅመውበት እንደማያውቁ እና ባላወቁት ሁኔታ ገንዘቡ ከባንክ ወጪ መደረጉን ባወቁ ጊዜ ለፖሊስ ማመልከታቸውን ተናግረዋል።ፖሊስ ከባንኩ ባገኘው መረጃ መሰረት በተጠርጣሪዋ ላይ ክትትል በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ክልል ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዳዋላት እና በአሁኑ ወቅትም ምርመራ እየተጣራባት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
#AMN

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያናና በጊዳ አያና በሚገኙ ጥቂት ወረዳዎች ኮቪድ-19 በስፋት እየተዛመተ በመምጣቱ ለጥቂት ቀናት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ማድረጋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ገልፀዋል።በነቀምቴ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ለኮሮናቫይረስ ተጋልጠው ህክምና ላይ ከነበሩ አንድ መቶ ሃምሣ ዘጠኝ ሰዎች መካከል ሃምሣ ሰባቱ ማገገማቸውን ሆስፒታሉ አስታውቋል።
#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
የህዳሴ ግድብ በወቅቱ መጠናቀቅ ለምስራቅ አፍሪካ የተፋሰሱ አገራት የኢኮኖሚ እድገት አዎንታዊ አስታዋጾ እንደሚያደርግ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ጥናት አሳየ!
የግድቡ ሙሌት እ.ኤ.አ በ2024 ቢጠናቀቅ እና ወደስራ ቢገባ የተፋሰሱ አገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ) አመታዊ ጠቅላላ የስራ ውጤት (real GDP) በ2024 የ 8.07 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ እንደሚኖረው ጥናቱ አመላክቷል፡፡በግድቡ ወደ ስራ መግባት ኢትዮጵያ የ6.79 ቢሊየን ዶላር፣ ሱዳን የ1.11 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ግብፅ የ0.17 ቢሊየን ዶላር አገራዊ ጠቅላላ የስራ ውጤት (real GDP) ያገኙበታል ብሏል ጥናቱ፡፡

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የሚቆጣጠር ሶፍት ዌር ይፋ ሆነ!
ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የሚቆጣጠር እና የሚያረጋግጥ እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግሥት የሚያገኙትን አገልግሎት የሚያፋጥን ሶፍትዌር በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጎልብቶ ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ መሰጠቱ ተገለጸ።ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለኤጀንሲው በዕርዳታ መልክ የሰጠው ሶፍትዌር፣ በዋናነት ተግባሩ ሥራን ከማቅለል ባለፈ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች በቀላሉ የሚቆጣጠር እንደሆነ ታውቋል።አዲሱን ሶፍትዌር አልምቶ ለማስረከብ አንድ ዓመት እንደፈጀበት ሚኒስቴሩ ያስታወቀ ሲሆን፤ አተገባበሩም ቀላል እና ለአጠቃቀም ውስብስብ እንዳይሆን ተደርጎ መዘጋጀቱንም ተቋሙ ለአዲስ ማለዳ አሰታውቋል።

በወላይታ በተከሰተው አለመረጋጋት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሰ
በወላይታ ዞን እሁድ እለት የዞኑ ከተፍተኛ አስተዳዳሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ አለመረጋጋት እስከ ትናንት ነሐሴ 05/2012 ድረስ 16 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።
ከተለያዩ ሆስፒታሎች መረጃዎችን ማጠናቀራቸውን የሚናገሩት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል (ኦቶና ሆስፒታል) መምህርና የአጥንት ክፍል ሐኪም የሆኑት መብራቱ ጪሻ (ዶ/ር ) ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ዶ/ር መብራቱ መረጃዎቹን ከሚያስተምሩበትና ከሚሰሩበት ኦቶና ሆስፒታል፣ በወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል፣ ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ቦዲቲ ጤና ጣብያ ማጠናቀራቸውን በመግለጽ፤ ወደ ጤና ተቋማቱ በመግባት የሕክምና አገልግሎት ያገኙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር 16 መድረሱን አረጋግጠዋል።
በነበረው አለመረጋጋት ጉዳት ደርሶባቸው የመጡት 49 ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰው በጥይት ተመትተው ዶ/ር መብራቱ ጪሻ አስታውቀዋል።
ከእሁድ ማታ ጀምሮ በጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል ከመጡት መካከል 16 ሰዎች ሲሞቱ 30 ሰዎች ሕክምና አግኝተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ሦስቱ ደግሞ በክርስቲያን ሆስፒታል በጽኑ ሕክምና ክፍል መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
ከእሁድ ማታ ጀምሮ በነበረው አለመረጋጋት ግጭቱ በበረታባት በቦዲቲ ከተማ የሞቱት ሰባት መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር መብራቱ፤ ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል በአጠቃላይ 21 ሰዎች ተጎድተው የመጡ ሲሆን ሆስፒታሉ እንደደረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሁለት መሆናቸውን ተናግረዋል።
Via:- Addis Maleda

የጃክ ማ ፋውንዴሽን በአለም ምግብ ኘሮግራም ለተገነባው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆሰፒታል አገልግሎት ለማስጀመሪያነት እንዲውሉ ሰማንያ ስምንት ሺህ ዶላር የሚያወጡ የህክምና አልባሳትና ቁሳቁሶች፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያዎች እና ቬንትሌተሮችን ለግሰዋል።
via:- lia tadess
@yenetube @Fikerassefa
via:- lia tadess
@yenetube @Fikerassefa
በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ላለፉት 30 ዓመታት በሬንጀርነት ያገለገሉት አቶ አድማሱ አካሞ የ2020 አፍሪካ ሬንጀር አዋርድ አሸናፊ ሆኑ፡፡
አቶ አድማሱ ፓርኩ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በሰመረ ግንኙነት አንዲዘልቅ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡
ከ5 በላይ በአካባቢው የሚነገሩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሲሆን ይህም ለላቀ መግባበት እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡
via:- Mystical Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮጰያ ሰባዊ መብት ኮምሽን በወላይታ ዞን የቀጠለው ሁከት እና የፀጥታ ኃይሎች በሰልፈኞች ላይ የሚጠቀሙት ከመጠን ያለፈ ኃይል በእጅጉ እንዳሳሰበው ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ በዞኑ ሁከቱ ከተቀሰቀሰበት ነሐሴ 4 ጀምሮ፣ ረቡዕ ዕለት ለሞት የተዳረገ 1 ተጨማሪ ሰውን ጨምሮ፣ የሟቾች ሰዎች ቁጥር ወደ 17 ማሻቀቡን ጠቅሷል፡፡ ከሟቾቹ ውስጥ ሕጻናት እንደሚገኙበትም የኮሚሽኑ መግለጫ አመልክቷል፡፡
ሶዶ ውስጥ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ሰዎች ሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ እንደሚገኝ የጠቀሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የፀጥታ ኃይሎች በተቻላቸው መጠን ኃይል ከመጠቀም እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡
የፀጥታ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚገልፁ ሰልፈኞች ላይ ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ኃይል ከመጠቀም መቆጠብ አለባቸው፤እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች እንዲሁም ውጥረት የመላበትን ሁኔታ ከማባባስ ውጪ ፋይዳ አይኖረውም ብሏል ኮሚሽኑ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤን ጨምሮ ባለፈው እሑድ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ የዞኑ ባለሥልጣናትና የማኅበረሰብ መሪዎች ትናንት ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰምቷል።
የባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞም ትናንት በቦዲቲ ከተማ መቀጠሉ ተሰምቷል፡፡
Via:- Sheger FM
@Yenetube @FikerAssefa

አቶ እስክንድር ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት የማይታይ ከሆነ ችሎት መቅረብ እንደማይፈልጉ ገለጹ::
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ጉዳያቸው በግልጽ ችሎት የማይታይ ከሆነ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይፈልጉና ጠበቃቸውንም ማሰናበታቸውን ለፍርድ ቤት ገለጹ።
አቶ እስክንድር ነጋ ለፍርድ ቤት ይህን ያሉት እራሳቸውና አብረዋቸው የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው መሰራት ለምስክሮች ደኅንነት ሲባል ከመጋረጃ ጀርባ በዝግ ችሎት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ውሳኔ መሰጠቱን ተከትሎ ነው።
via BBC
@YeneTube @Fikerassefa

አፊኒ መፅሔት በሲዳማ ክልል ባሉ ሁሉም ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባ በስፋት በመሸጥ ላይ ነው:: መፅሔቱን ለመግዛት የሚትፈልጉ ከስር የተቀመጡ አድራሻዎችን ተጠቀሙ:: ዋጋውም 25 ብር ብቻ ነው::
መልካም ንባብ!
ሐዋሳ:- አሮጌ መናኸሪያ: ሲዳማ ቡና ህንፃ
*ዜና ሞባይል...ምድር ላይ...0926923274
*ቆንጆ ቡና...2ኛ ፎቅ
ይርጋለም: ዳሌ, ወንሾ እና ሎካ አባያ
*0916798424
*0949206762
አላታ ወንዶ እና ጩኮ:
*0916529229
*0903083425
ባንሳ; ቦና; ጭሬ; ሆሮሬሳ እና አከባቢው:
*0982373336
ሻባዲኖ እና ዳራ ቃዋዶ:
*0924326779
ሀርባጎና እና አከባቢው:
* 0916980609
መልካም ንባብ!
ሐዋሳ:- አሮጌ መናኸሪያ: ሲዳማ ቡና ህንፃ
*ዜና ሞባይል...ምድር ላይ...0926923274
*ቆንጆ ቡና...2ኛ ፎቅ
ይርጋለም: ዳሌ, ወንሾ እና ሎካ አባያ
*0916798424
*0949206762
አላታ ወንዶ እና ጩኮ:
*0916529229
*0903083425
ባንሳ; ቦና; ጭሬ; ሆሮሬሳ እና አከባቢው:
*0982373336
ሻባዲኖ እና ዳራ ቃዋዶ:
*0924326779
ሀርባጎና እና አከባቢው:
* 0916980609