YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከነሃሴ መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ለማድረግ ወላጆችን እያስገደዱ መሆኑ እና ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።ይህንን በተመለከተም የትምህርት ሚኒስቴር የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ መጨረሻ በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንማይቻል እና ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።የምዝገባው የግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተፈለገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የ ቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።ወላጆች ከተሳሳተ መረጃ እራሳቸውን በመጠበቅ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልእና መንግስት ትምህርት እንዲጀመር ሲያሳውቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አውቀው ልጆቻቸውን በእጃቸው ላይ የሚገኙትን የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዲያነቡና እንዲያጠኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ:የትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa1
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የ1382 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ 81 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 506 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa1
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነሐሴ 1-3/2012 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በክልሉ ምክር ቤት የጉባዔ አዳራሽ ያካሄዳል፡፡

#SNNPR_Council
@YeneTube @FikerAssefa1
ራማፎሳ ለኮቪድ-19 የተመደበ በጀትን የሚመዘብሩ ግለሰቦችን አስጠነቀቁ!

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለኮሮናቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር የተመደበን የሕዝብ ሃብት በሚበዘብዙና “ጅቦች” ሲሉ የጠሯቸው ግለሰቦች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ።ይህ የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ ትኩረቱን ያደረገው የመንግሥት ኃብትን በሚመዘብሩ ባለስልጣናት፣ በኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና፣ የእርዳታ ምግብን በድብቅ የሚያከማቹ የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላይ ነው።“በየእለቱ የዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ካለው ቀውስ ለማትረፍ መጣር የጥንብ አንሳ ባህሪ ነው። ልክ የተጎዳውን ሰለባውን እንደሚከብ ጅብ መሆን ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ራማፎሳ።“ግለሰቦች እና ድርጅቶች ያለምንም ርህራሄ በዘረፋ መሰማራታቸውን አስተውለናል” ሲሉም አክለዋል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት፣ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት ኣፈ ጉባኤ፣ ለተፃፈው ደብዳቤ የተሰጠ መልስ።

ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮምኒኬሽን ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በ1 ቀን የ26 ሰዎች ህይወት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አለፈ!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ6907 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 583 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በማህበራዊ ሚድያ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ26 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡330 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19,289፣ ያገገሙት 7931፣ የሟቾች ቁጥር 336 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 145 ነው።

@YeneTube @FikerAssefa1
በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,497 ደርሷል፡፡

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረጉ 3,836 የላብራቶሪ ምርመራዎች 386 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ ከተደረጉ 265,747 የላቦራቶሪ ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,497 መድረሱን የጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ ሃያ ሶስት (21 ከሬሳ ምርመራ፣2 ከጤና ተቋም) ሰዎች ህይወት በኮሮና ምክንያት አልፏል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ሦስት ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን አንድ የክልሉ ሠላም ግንባታና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ፣ የቤንሻንጉል ሠላም ግንባታና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ለቢቢሲ እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ሦስት የጉባ አካባቢ ነዋሪዎችን እንደወሰዱና እስካሁን የት እንዳሉ አለመታወቁን ገልጸዋል።እገታው የተፈጸመው ቅዳሜ ዕለት መሆኑን የሚናገሩት አቶ አብዱለዚዝ "ታጋቾቹ የጉሙዝ ብሔረሰብ አባላት" ናቸው በማለት የደረሱበት ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው ለአካባቢው ባለስልጣናት ማመልከታቸውን ተናግረዋል።ታጋቾቹ የጉባ ወረዳ ነዋሪዎች ሲሆኑ ታጣቂዎቹ ያገቷቸውን ሰዎች ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ ከማለት በተጨማሪ የቤተሰብ አባሎቻቸው ከአካባቢው መስተዳደሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመጥቀስ መታገታቸውን ቤተሰቦቻቸው እንደተናገሩ ኃላፊው ጠቅሰዋል።

የታገቱትን ሰዎች በተመለከተ "ስላሉበት ሁኔታ የታወቀ ነገር የለም። ስላሉበት ሁኔታ እርግጠኞች አይደለምን። ነገር ግን ተይዘው በተወሰዱበት አቅጣጫ የመከላከያ ሠራዊት ተሰማርቶ ታጣቂዎቹን ለመያዝና ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላም መከላከያ እና ልዩ ኃይል ታጣቂዎቹ ተደብቀውባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ላይ አሰሳ በማድረግ ጥቂት የማይባሉት እንደተገደሉ የተናገሩት አቶ አብዱላዚዝ "[ታጣቂዎቹ] ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ውስጥ ስለገቡ የቻሉትን ያህል ጥፋት መፈጸም ነው ፍላጎታቸው። ነገር ግን መውጫ የላቸውም ሠራዊቱ ተሰማርቶ እያሰሰ ነው" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከብሮድካስት ባለሥልጣን ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው ዋዜማ ዘግቧል፡፡መንግሥታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ማስጠንቀቂያ የደረሰው፣ በቅርቡ ያስተላለፋቸው ፕሮግራሞች የስነ ምግባር ጉድለት የታየባቸው፣ የሕግ ጥሰት ያለባቸው እና የብሮድካስት አዋጁን የጣሱ ሆነው በመገኘታቸው ነው፡፡ ጣቢያውን ለማስጠንቀቂያ የዳረጉት፣ በተለይ የድምጻዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በሠራቸው ፕሮግራሞች እና ባቀረባቸው ቃለ ምልልሶች ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ የሚወስዱ አውራ ጎዳናዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከወትሮ ቀንሶ መታየቱን አሽከርካሪዎች እና ነዋሪዎች ተናገሩ።

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ ትናንት ዲለላ ከተማ አቅራቢያ ለ30 ደቂቃ ከተፈጠረ የተሽከርካሪዎች መስተጓጎል በስተቀር በክልሉ በየትኛውም አካባቢ የጸጥታ ችግር አልተከሰተም ብለዋል።በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ የገለጹት እንዳሉት ከአዲስ አበባ ጅማ ከሻሸመኔ አዲስ አበባ እና ከሻሸመኔ ባሌ የሚወስዱ መንገዶች ከትናንት ጀምሮ ተዘግተዋል አልያም የተሽከርካሪዎች ፍሰት ከወትሮው እጅጉን አንሶ ተስተውሏል። ከአዲስ አበባ ጂማ መስመር በተለይም ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ በምትገኘው የዲለላ ከተማ አካባቢ ትናንት መንገድ መዘጋቱን ተከትሎ የመንግስት ጦር በስፍራው እስኪደርስ ድረስ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ እንደነበር ከአዲስ አበባ ጅማ የህዝብ ማመላለሻ ላይ የሚሰሩ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አሽከርካሪ ለDW ተናግረዋል።

Read more 👇👇👇
https://telegra.ph/-08-03-770
በድሬዳዋ 21 የጤና ባለሙያዎች በሥራቸው ላይ ሳሉ በኮሮና መያዛቸውን አስተዳደሩ አስታወቀ!

በድሬዳዋ 21 የጤና ባለሙያዎች በሥራቸው ላይ ሳሉ በኮሮና መያዛቸውን የከተማ አስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስታወቀ። በድሬዳዋ በኮሮና ከተያዙ መካከል 23 ታራሚዎች እና 24 የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል። የዘጠኝ አመት አዳጊን ጨምሮ ለስደት ወደ ጅቡቲ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በተሕዋሲው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ይዘሮ ለምለም በዛብህ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በህብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ባለው መዘናጋት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱንና ድሬደዋ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ከፍተኛ ስጋት ያለባት ከተማ ሆናለች።በአስተዳደሩ አቅም በፈቀደ መልኩ እየተካሄደ ባለው የኮቪድ ምርመራ ቫይረሱ እየተገኘባቸው ካሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን ኃላፊዋ አስረድተዋል። 

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
ባለፈው በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ከዕቅድ በላይ ደም መሰብሰቡን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ አስሩም የደም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም መለስተኛ ደም ባንክ አቋቁመው አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች ተወካዮች በተገኙበት የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ አካሂዷል፡፡ባለፈው በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 58 ሺህ 440 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 59 ሺህ 271 ዩኒት ደም መሰብሰቡን ጤና ቢሮው ገልጿል። አፈጻጸሙ 101 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑንም የቢሮው የደም ባንክ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፉ ገልጸዋል፡፡

#AMMA
@YeneTube @FikerAssefa1
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ የሚደረገው ድርድር እንደገና መቀጠሉ ተገለጸ!

የኢፌዴሪ ውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ውኃ ሀብት ሚኒስቴሮች መካከል በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ የሚያደርጉትን ድርድር በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት መቀጠሉን አስታወቋል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
ቦይንግ 737 ማክስ በድጋሚ ለመብረር ተቃርቧል ተባለ!

የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ)ም እንዲሁ አውሮፕላኑ ዳግም ወደ በረራ ከመግባቱ በፊት ማሟላት ያለበትን ዝርዝር ነገሮች ማቅረቡ ተሰምቷል።737 ማክስ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ከበረራ ከታገደ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል።አውሮፕላኑ ሙሉ ሙሉ ከበረራ የታገደው በጎርጎሳውያኑ መጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ነበር።ቦይንግ 737 ማክስ እንዲያሟላ የተጠየቀውን ዝርዝር ነገሮች አሟልቶ በጎርጎሳውያኑ አዲስ አመት ዳግም ወደ በረራ ለመመለስ አቅዷል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት 305 ተሽከርካሪዎችን ገዝቶ ለመንግስት ተቋማት ማስረከቡን የመንግስት የግዥና የንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።

በኤጀንሲው የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ደፊል እንዳሉት በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት 305 ተሽከርካሪዎችን ገዝቶ ችግሩ ላለባቸው የፌደራል እና የክልል ተቋማት በጨረታ ገዝቶ ማስረከቡን ተናግረዋል።የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ያለባቸውን የተሽከርካሪ ችግር ለማቃለል እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሥር ለሚገኘው ሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል በአስቸኳይ ለአገልግሎት መቅረብ ያለባቸው ተሽከርካሪዎችን በመለየት በውስን ጨረታ ግዥ እንዲፈጸም መደረጉም ተገልጿል፡፡በውስን ጨረታ የግዥ ዘዴ ከዱባይ ሀገር በ6 ምድብ የተሽከርካሪ ዓይነቶች 305 ተሽከርካሪዎችን ከ366 ሚሊዮን በላይ ብር ግዥ መፈጸሙን አቶ መልካሙ ገልጸዋል፡፡የተሽከርካሪ ግዥ የተፈጸመላቸው የፌዴራል ተቋማት አምቡላንስ ፣ፒካፕ ፣ሚኒባስ ፣ከ28 ሰው በላይ የሚጭን ኮስትር መኪና እንደሚገኝበትም ተነግሯል፡፡ለብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግዥ ለመፈጸም ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ውል መፈረሙንም ከዳይሬክተሩ መስማት ተችሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2012 በጀት ዓመት ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ፡፡
ተቋሙ በ2012 በጀት ዓመት 56 ነጥብ 92 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ66 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ሰብስቧል፡፡ ይህም የዕቅዱን 116 ነጥብ 5 በመቶ በማከናወን ከዕቅድ በላይ ገቢ መገኘቱ ተገልጿል፡፡በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ 37 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር ከጅቡቲ እና ቀሪው 29 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከሱዳን የተገኘ ነው ተብሏል፡፡በዚህ ዓመት ከሁለቱ ሀገራት የተገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ከ2011 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

#EPA
@YeneTube @FikerAssefa1