YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ሐሙስ ወይም ዐርብ በሕዳሴው ግድብ ላይ ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ አሕራም ድረገጽ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የጸጥታው ምክር ቤት ምንጮች ግን ዘገባውን አላረጋገጡም፡፡ አሜሪካ ጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲወያይ ትፈልጋለች፡፡ ተለዋጭ መቀመጫ ያላት ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ፣ ጉዳዩ ጊዜ እንዲሰጠው ፍላጎት አላት፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎዛ፣ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ እና ግብጽ መሪዎችን እያነጋገሩ ነው ተብሏል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የትግራይ ክልል ምክር ቤት “ኮቪድ 19ኝን እየተከላከለ 6ኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የወሰነ በመሆኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ ውሳኔውን ተቀብሎ ምርጫውን እንዲያስፈፅም፣ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ እና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቀን” ሲል ጥያቄ አቅርቧል፡፡በመላ አገሪቱ በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የሚደረጉ ምርጫዎችን የማስፈፀም ስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 102 (1) ላይ ተደንግጓል ፡፡ህገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ የቦርዱን ስልጣን እና ሀላፊነት የወሰነው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በአንቀጽ 7.1 ይህ የቦርዱ ስልጣን በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ምርጫዎች እና ህዝበ ውሳኔዎችን በሙሉ እንደሚሸፍን በተብራራ ሁኔታ ገልጾታል።

በተጨማሪም የቦርዱን የስራ ሃላፊነቶች በተለያየ ሁኔታ በዝርዝር በሚገዙት ህጎች ማለትም በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እንደተደነገገው በማንኛውም የምርጫ ዑደት የሚፈጸሙ ዋና ዋና ክንዋኔዎች ማለትም የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ ለምርጫ የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣የምርጫ አስፈፃሚዎችን መልምሎ ማሰማራት፣ ጣቢያዎችን ማቋቋም፣ ምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም በመጨረሻም የውድድሩን ውጤት አረጋግጦ ለህዝብ ይፋ ማድረግ እና የመሳሰሉት ከማንኛውም የመንግስት ተቋም በተለየ ለቦርዱ የተሰጠ እና ከማንም አካል ጋር የማይጋራው ህጋዊ ስልጣኑ ነው፡፡ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ እያለ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባገራችንም በመከሰቱ ምርጫውን ለማስፈፀም ሲያካሂዳቸው የነበሩት ስራዎች እንደተስተጓጎሉ ይታወቃል፡፡

ወረርሽኙ በኢትዮጵያ መከሰቱ እንደተረጋገጠ ሁናቴውን መገምገም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቦርዱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ 6ኛውን አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ቀደም ሲል ቦርዱ ባወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ የማይቻል በመሆኑን ወስኖ ይህንኑ ውሳኔ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም የቀረበለትን የቦርዱን ውሳኔ ተቀብሎ የህገመንግስት ትርጉም እንዲሰጥበት መወሰኑ ይታወሳል፡፡የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ምርጫውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የህዝብ ጤና ስጋት ሆኖ ባለበት ሁኔታ ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የፌደራልና ክልል ምክርቤቶች የስልጣን ዘመን እንዲቀጥል እንዲሁም አጠቃላይ ምርጫው ስልጣን ያላቸው አካላት ወረርሽኙ የህዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡበት ጀምሮ ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ አመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡

ስለሆነም፤

1. 6ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሄድም፡፡

2. በተጨማሪም ከላይ እንደተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም ስልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን፣ አፈጻጸምንም ሆነ ተያያዥ ሁኔታን የሚወስነውም ቦርዱ ብቻ ነው፡፡በመሆኑም የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ውስጥ 6ተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ህጋዊ መሠረት የለውም። በመሆኑም ቦርዱ ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን፣ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብ አለመኖሩን ያሳውቃል፡፡

-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
የደወሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ተዘጋ!

"ጥንቃቄ የጎደለው" የተባለውና ከጅቡቲ ለሚመለሱ ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀው የደወሌ ለይቶ ማቆያ ተዘጋ።በመጠለያው አንድ ክፍል ከነበሩ 425 ሰዎች 97 በኮሮና መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ዶክተር ጽጌረዳ በኮሮና የተያዙ እና ያልተያዙ መጸዳጃ እና ውኃ በሌለው በዚሁ መጠለያ ይቆዩ ነበር ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው ኃይል ተቋረጠ!

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደርና አካባቢው በተፈፀመ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ስርቆት በኢንደስትሪ መንደሩና በአካባቢው ኃይል ተቋርጧል።132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በዘራፊዎች ተፈቶና ተቆርጦ በመውደቁ በሌላ ምሰሶ ላይ ተጨማሪ ጉዳት በማድረስ ነው ኃይል የተቋረጠው።በዚህም የኢንደስትሪ መንደሩን ጨምሮ በሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ በቦሌ አራብሳ፣ በአየር መንገድ ማህበር፣ በጎሮ፣ በአይሲቲ ፓርክ፣ በገርጂ ወረገኑና በገርጂ ካሳንቺስ አካባቢዎች ኃይል ተቋርጣል።

ችግሩ እንደተከሰተ የተቋማችን የትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽን የጥገና ባለሙያዎች ችግሩን ለመቅረፍ እንቅስቃሴ ቢጀምሩም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምሰሶውን መልሶ በማቆም መስመሩን ማገናኘት አልተቻለም።

የተሰረቁትን የምሰሶ አካላት በሌላ ተክቶ መልሶ ለማቆም መለዋወጫና በርካታ ቀናት የሚፈልግ ቢሆንም ሌላ ተለዋጭ የእንጨት ምሰሶ በመትከል መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ተጀምሯል።በመሆኑም በኢንደስትሪ መንደሩም ሆነ ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል መልሰን እስከምናገናኝ ድረስ ህብረሰተቡ በትዕግስት እንዲጠብቀንና ሌሎች የኃይል አማራጮችን እንዲጠቀም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያሳስባል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቦሌ ለሚ መስመር ጋር የተገናኘው የቃሊቲ አካባቢ መስመር ተጠግኖ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

#EEPCO
@YeneTube @FikerAssefa
ሸገር ዳቦ : 2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን

2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ማምረቻ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ይመረቃል
ዛሬ - ኢንጂነር ታከለ ኡማና ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ልዩ ልዩ ባለስልጣናት በተገኙበት ይመረቃል።
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ቀን ይሁንሎት
#ግድቡየኔነው
#itsmydam
በኢትዮጵያ የ'114 ዓመት' የእድሜ ባለጸጋ ከኮሮናቫይረስ አገገሙ!

በኮሮናቫይረስ ተይዘው በአዲስ አበባ በሚገኘው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የ114 የእድሜ ባለጸጋ ከበሽታው አገግመው መውጣታቸውን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ያሬድ አግደው በፌስቡክ ገጻቸው አስታወቁ፡፡አዛውንቱ ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል እንደሚገኙም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡አዛውንቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ ለዚህ ስኬት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የጤና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
“የአፍሪካ ሎጀስቲክስ” ባወጣው ሪፖርት መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚያጓጉዛቸው መንገደኞች ብዛት፣ በሚበርባቸው መዳረሻዎች ብዛት ፣ ባለው የአሮፕላን ቁጥር ብዛት እንዲሁም በሚያገኘው ገቢ ከአፍሪካ የአንደኛነት ስፍራ አግኝቷል። በአለም አቀፍ ደረጃም በሚበርባቸው መዳረሻዎች ብዛት 4ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ በቅቷል።

Via Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በ2013 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት ላይ ተወያይቷል።

በውይይቱም የበጀት ዝግጅቱን አስመልክቶ በገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ማብራሪያ ተሰጥቷል።ዶክተር እዮብ በዘህ ወቅት እንደገለጹት የ2013 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅ የ2012 ዓ.ም የበጀት አፈጻጸም ግምገማ ከመካሄዱም ባለፈ የኮረና ወረርሽኝ ተጽዕኖ ታሳቢ ተደርጎ በቅርብ ጊዜያት በአገራችን በኢኮኖሚው ዘርፍ የተገኙ ድሎችን ለማስጠበቅ ታስቦ የታቀደ በጀት ስለመሆኑ አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ ለካፒታል እና ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ግቦች ማጠናከሪያ በጥቅሉ 476 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልጸው÷ ከዚህ ውስጥ 350 ቢሊየን ብሩ ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮችና ከዕርዳታ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የተናገሩት።አያይዘውም ለ2013 በጀት ዓመት የቀረበው በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር መጠነኛ ጭማሪ እንዳለው ጠቁመው÷ በጀቱ በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ለምለም ሐድጉ÷ በቀጣይ በረቂቅ በጀቱ ላይ ተጨማሪ ውይይት መኖሩን መጠቆማቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለሲሚንቶ ግብዓት የሚያገለግለውን የድንጋይ ከሰል 60 በመቶ በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉ ተገለፀ!

ለሲሚንቶ ግብዓት የሚያገለግለው የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተደረገው ጥረት 60 በመቶ የሚሆነውን በአገር ውስጥ ምርት መተካቱ መቻሉ ተገለፀ።የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ ስመኝ ደጉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሲሚንቶን ለማምረት አስፈላጊ ከሆነው አጠቃላይ ግብዓት 60 በመቶውን በአገር ውስጥ መተካት መቻሉ ዘርፉን ውጤታማ ማድረጉን አመልክተዋል።ቀሪው 40 በመቶ ለሲሚንቶ ምርት ግብዓት የሚሆነው አሁንም ከውጭ እንደሚገባ አመልክተው ፣ሁሉም የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ከሚጠቀሙት መጠን እና ከላብራቶሪ ውጤታቸው በመነሳት በቀጣይ በዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች ለመቅረፍና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የድንጋይ ከሰል በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ማለትም በአማራ፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መኖሩ በጥናት መረጋገጡን አመልክተው ፣ ይሁንና የተፈጥሮ ሀብት መጠኑ፣ ዘላቂነቱና ጥራቱ ምን ያህል ነው የሚለውን ለመመለስ ምርምር እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል ። ይህም በምርምር ኮሚቴው እየተጠና መሆኑን አመልክተዋል።በሲሚንቶ ገበያ የንግድ ሰንሰለት ውስጥ ደላሎች የሚፈጥሩትን ጤናማ ያልሆነ የንግድ ቅብብሎሽ ጤናማ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አመልክተው ፣ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ ምርቱን እንዲትረፈረፍ በማድረግ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል ብለዋል።በተለይም የሀገር ውስጥ ግብዓቶች ላይ በመስራት ከውጭ የሚገባውን ምርት በመቀነስ የውጭ ምንዛሪን ማዳንና ዘርፉን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ምንጭ፡- ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ማኪ ሳል ራሳቸውን ለሁለት ሳምንት አግለዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ይህንን ያደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር መገናኘታቸው ከታወቀ በኃላ ነው።ፕሬዝዳንቱ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ ቢሆኑም ለማንኛውም በሚል ነው ለሁለት ሳምንት ያህል ራሳቸውን አግለው ለማቆየት የወሰኑት ብሏል ጽ/ቤታቸው፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ!

በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ። በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ካርቱም ገቡ።

ፕሬዘዳንቱ ወደ ሱዳን ካርቱም ያቀኑት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ጋር በሁለቱ አገራት እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር እንደሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ አስታውቋል።ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት በሱዳኑ አቻቸው ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን ግብዣ እንደሆነም ተገልጿል። ፕሬዘዳንቱ ወደ ካርቱም ያቀኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ኦስማን ሳሌህ እና አማካሪያቸውን የማነ ገብረአብን አስከትለው ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤና ጋዜጣዊ መግለጫ አራት ኪሎ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ግቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Photo: Samuel Getachew(on Twitter)
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር የምስረታ ጉባኤና ጋዜጣዊ መግለጫ አራት ኪሎ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ግቢ በመካሄድ ላይ ይገኛል። Photo: Samuel Getachew(on Twitter) @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ!

በኢትዮጵያዊያን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተነሳሽነት የተጀመረው እና በርካታ አባላትን የያዘው ማህበር ህጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ተመሰረተ።በአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የመገናኛ በዙሀን ድርጅቶች ባልደረቦች አባልነት የተቋቋመው ማህበሩ ዛሬ ሰኔ 18/2012 ምስረታውን በሚመለከት መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው በመገናኛ ብዙሃን ሙያና ሙያተኞች ላይ የተለያዩ አካላት በተለያየ መልኩ የሚደረገውን ተፅዕኖ እና ጫና ለማስቀረት ፣ ለባለሙያው መብት እና ጥቅም የሚቆም፣ ሙያዊ ብቃቱን የሚያሳድግለት እና የኔ የሚለው የሙያ ማህበራት ጥቂት በመሆናቸው እንዲሁም በአመርቂ ሁኔታ ለሙያተኛው ጥቅም እየሰሩ ባለመሆኑ ይህ የመገናኛ ባለሙያዎች ማህበር በመገናኛ ብዙሃን እና በሙያተኞች መካከል ትብብር እና አብሮ የመስራትን መንፈስን ለመፍጠር ታቅዶ መመስረቱ ተገልጿል።

ማህበሩ ከሲቪክ ማህበራት ማደራጃ ኤጀንሲ ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ የተመሰረተ ሲሆን ከዚህ ቀደም በተከናወነው የመስራቾች ጉባኤ ላይ የማህበሩን መመስረት አስፈላጊነት፣ ስያሜውን እንዲሁም አላማዎቹ ላይ በመወያየት የማህበሩን አደረጃጀት በማፅደቅና ዘጠኝ የስራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ እና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ በማርቀቅ ወደስራ መግባቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በመግለጫው ላይ አስታውቋል።በዚህም መሰረት ማህበሩ መስራች፣ መደበኛ እንዲሁም የክብር አባላትን በማህበሩ ዌብሳይት እና የአባላት ምልመላ ክፍል አማካኝነት የሚመዘግብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በቁርጠኝነት ለመስራት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተገልፆል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ3500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት ከ3 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ የተጠቁ ሲሆን 15 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይም በክረምት ወቅት፣የህብረተሰቡን ጤና በእጅጉ ከሚፈትኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የእብድ ዉሻ በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡በአማራ ክልል ከ 3 ሽህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የተፈቀደው ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ!

ከሁለት ዓመት በፊት በተላለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተጨማሪ ውሳኔ በጡረታ ለተሰናበቱ ከፍተኛ የአገርና የመንግሥት አመራሮች ሲሰጥ የነበረ ልዩ ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ተወሰነ።የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም.  ባካሄደው ስብሰባ በጡረታ ለተሰናበቱ  የአገርና የመንግሥት አመራሮች ከአዋጅ  ውጪ በልዩ ውሳኔ የተፈቀደላቸው ልዩ  ጥቅማ ጥቅም ቀሪ እንዲሆን ወስኗል።

እነዚህም በጡረታ የተሰናበቱ የአገርና የመንግሥት አመራሮች በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት በተሰጣቸው ቤት መኖር እንዲቀጥሉ፣ አንድ አውቶሞቢልና አንድ  የመስክ ተሽከርካሪ እንዲሰጣቸው  እንዲሁም በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት  ያገኙ የነበረው የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንዲቀጥሉ የሚፈቅዱ ናቸው።

ከሳምንት በፊት የተላለፈው አዲሱ  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ከላይ  የተገለጹት ሦስት ተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች እንዲሻሩና በአዋጁ መሠረት ብቻ  እንዲስተናገዱ የሚል ነው:: በዚህ ውሳኔ መሠረት ቤት የተሰጣቸው በጡረታ የተሰናበቱ አመራሮች እንዲኖሩበት የተሰጣቸውን ቤትና የመስክ ተሽከርካሪ እንዲመልሱ የተባለ ሲሆን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርም ይህንን  ውሳኔ እንዲፈጽም ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም.ትእዛዝ ደርሶታል።

#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት እና ኢዲዩ ከኢትዮጵያ የፌዴራሊስ ኃይሎች ጥምረት አባልነት ታገዱ!

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓት እና ኢዲዩን ከጥምረቱ አባልነት አገደ፡፡ጥምረቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ በነበረው ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባወጣው የአቋም መግለጫ እንዳመለከተው፤ ጥምረቱ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰቦች አካትቶ በማቀፍ የተሻለ ህብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ለመገንባት እና ለብሔር ብሔረሰቦች ተጠቃሚነት ሲል በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እየሰራ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ህወሓትና ኢዲዩ የጥምረቱን ጉዞ ለማደናቀፍ ብሎም ጥምረቱን ተጠቅመው አገር ለማተራመስ እየሰሩ ይገኛል ይላል መግለጫው፡፡ይህ ደግሞ በጥምረቱ ዓላማ፣ አሰራርና ደንብ መሰረት ተቀባይነት ያለው ባለመሆኑ ሁለቱ ድርጅቶች ከጥምረቱ እንዲታገዱ ሆኗል ተብሏል፡፡በተለይ ህወሓት ጥምረቱ የራሱ ጥገኛ አድርጎ ሊጠቀምበት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የተናገሩት የጥምረቱ ሰብሳቢ አቶ ደረጀ በቀለ፤ ህወሓትና ኢዲዩ የጥምረቱ ማዕከል መቀሌ እንዲሆን በመሻት በአዲስ አበባ ያካሄደው ሶስተኛ እና አራተኛ የጥምረቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው መርምሮ ያፀደቃቸው ረቂቅ አዋጆች፦

👉የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ፤

👉የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤

👉የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኳታር መንግሥት የማዕድን ሥራዎች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀደቃቸው ስምምነቶች፦

👉በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለበረሃ አንበጣ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገው የብድር ስምምነት፤

👉ኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንዲያግዝ ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የዕድገትና ተወዳዳሪነት የልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት፤

👉በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት፤ በሁለቱ አገሮች መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት፤

👉በኢትዮጵያ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት እና በሁለቱ አገራት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት የሚያስችለው ስምምነት ናቸው።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
አነስተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጫናን የሚያቃልል ጥናት አስጠንቶ ለመንግሥት ሊያቀርብ መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ችግሩን ይፈታል የተባለ ጥናት ኮሚሽኑ ከኮንስትራክሽንና ቤቶች ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥናት ማስጠናቱንና ጥናቱም በቅርቡ ለመንግሥት እንደሚቀርብ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ገልጸዋል።”ጥናቱ በዋነኛነት ለረጅም ዓመታት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሲሰሩ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ደሞዝ የሚኖሩ ሰዎች አሁን ላይ ከተፈጠረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መናርና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚበሉበትን እስከማጣት የሚደርሱ መሆናቸውን ጥናቶቻችን አሳይተውናል” በማለት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ/ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa