YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከአማራ ክልል ባልተገባ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል በተካለሉ አካባቢዎች ምርጫ እንዳይኬሄድ የእግድ ጥያቄ ሊያቀርብ መሆኑን አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው የኮሮና ቫይረስ ስጋት መሆኑ ካቆመ ከዘጠኝ ወር በኋላ ይከናወናል ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚቀበለውና በህግ መንገድ እንደተካሄደ እንደሚያምን ገልጿል። የንቅናቄው ምክትል ሊቀ መንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት "የአማራ ህዝብ ግዛቶች በነበሩትና በትግራይ ክልል አስተዳደር በማን አለብኝነት ያለአገባብ በተወሰዱት አካባቢዎች ማለትም በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በራያ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ምርጫ እንደምንወዳደር በማኒፌስቷችን አስቀምጠናል" ብለዋል።ትግራይ ክልል ምርጫ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ በነዚህ ግዛቶች አሁን ሊደረግ የታቀደው ምርጫ እንዲታገድልን ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ማኪ ሳል ራሳቸውን ለሁለት ሳምንት አግለዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ይህንን ያደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር መገናኘታቸው ከታወቀ በኃላ ነው።ፕሬዝዳንቱ ምርመራ አድርገው ከቫይረሱ ነጻ ቢሆኑም ለማንኛውም በሚል ነው ለሁለት ሳምንት ያህል ራሳቸውን አግለው ለማቆየት የወሰኑት ብሏል ጽ/ቤታቸው፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ከ3500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው በመገባደድ ላይ ባለው ዓመት ከ3 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ የተጠቁ ሲሆን 15 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለይም በክረምት ወቅት፣የህብረተሰቡን ጤና በእጅጉ ከሚፈትኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የእብድ ዉሻ በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡በአማራ ክልል ከ 3 ሽህ 500 በላይ ሰዎች በእብድ ዉሻ በሽታ መጠቃታቸውን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

#Ethio_FM
@YeneTube @FikerAssefa