«የግድቡን ጉዳይ ወደ ፀጥታው ም/ቤት መውሰድ ፋይዳ የለዉም » ክራይስስ ግሩፕ
በግጭቶች ላይ የሚሰራው ዓለምአቀፍ ተቋም ክራይስስ ግሩፕ ግብጽ የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ ወደ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት መውሰዷ ችግሩን ለመፍታት መፍትሔ አይሆንም አለ። ተቋሙ እንዳለው በግድቡ የውኃ ሙሌት እና ልቀትም ሆነ በወንዙ ዘላቂ አጠቃቀም ላይ መፍትሔው በውይይት በሚደረስ ስምምነት ብቻ ነው ሲል አስታውቋል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

Forwarded from YeneTube
EmpowerMed የተሰኘ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ዘርፍ በእጅጉ የመደገፍ ብሎም የመዋቅር ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረሠናይ ድርጅት ነው። መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው ይህ ግብረሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፉን በመክፈት እየሰራ ይገኛል። በቅርቡ በተቀሰቀሰው COVID-19 ወረርሽኝን ምክንያት ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን ለመርዳት ፕሮግራም በመቅረፅ ማገዝ ይፈልጋል። በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል ያላችሁ የህክምና ተማሪዎች ማለትም Medical, Nursing, Midwifery ወዘተ እና የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች በሙሉ ከድርጅታችን ጋር ህብረት መፍጠር የምትፈልጉ በሙሉ በተገለፀው ዌብሣይት እና የ ፌስቡክ ገፃችን ላይ በመግባት መመዝገብ እና ህብረት መፍጠር ትችላላችሁ ።
የድርጅቱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ facebook.com/empowermed.ngo ነው።
የድርጅቱ ዌ ብ ሳ ይ ት
http://EmpowerMed.ngo
ነው።

ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች 33 ዓመቱ ሲሆን በቤልግሬድ አንድ የቴኒስ ውድድር አሰናድቶ ነበር ሰሞኑን፡፡ በዚህ ውድድር ወቅት ታድያ ቢያንስ አራት የሚሆኑ ዕውቅ የቴኒስ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው ታውቋል፡፡ ጆኮቪችም ለተፈጠረውን ነገር ከልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ እያለ ነው።
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ
ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ በተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።
ጥቃቱን በማቀነባበርና በመምራት አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተ ሲሆን ሁለት ሰዎች ደግሞ አለመያዛቸውን በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ጸጋ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
አምስቱ ግለሰቦች ላይ የቀረበው ክስ የሽብር ድርጊት የሚል ሲሆን የፀረ ሽብር አዋጁ 652/2001 አንቀጽ 3 ስር መከሰሳቸውን አብራርተዋል።
የሰኔ 16 ተከሳሾች መዝገብ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ተከሳሾች የመጨረሻ ይቅረብል ያሉት ሰነድ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ፍቃዱ፣ እርሱ ላይ ብያኔ ለመስጠትና የፍርድ ውሳኔውን ለማዘጋጀት እን ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮች መኖራቸውን ለመወሰን ቀጠሮ ተሰጥቶ እንደነበር ገልጸዋል።
ከኮሮናወረርሽኝ ወዲህ ችሎቶች ሥራ በማቋረጣቸው የተከሳሾች ጉዳይ አለመንቀሳቀሱን አቶ ፈቃዱ ጸጋ አመልክተዋል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩት አምስቱም ተከሳሾች ይከላከሉ ተብሏል ያሉት አቶ ፍቃዱ፣ እነርሱም መከላከያ ምስክር የሚሉትን አሰምተዋል ሲሉ ገአስታወስኣል።
"ነገር ግን በምስክርነት የጠቀሷቸው አንዳንድ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎችን የመከላከያ ምስክሮቻችን ናቸው በሚል ስለጠየቁ፣ በወቅቱ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቀርበው ስለተናገሩ ብቻ፣ ፍርድ ቤቱ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አለው ወይስ የለውም ተገቢ ነው፣ አይደለም የሚለውን ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቶ በነበረበት ወቅት ነው ወረርሽኙ ተከስቶ ችሎቱ የተቋረጠው።"
ነገር ግን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አቃቤ ሕግ ማስረጃ የማሰማት ሂደት ማለቁን ጨምረው ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስላልዋሉት ሁለት ሰዎች ሲናገሩም አንደኛው የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ የነበሩትና ሌላኛዋ ይህንን ጉዳይ አቀናብራለች የተባለች ሴት በክሱ ላይ ተጠቅሰው ያልተያዙ መሆናቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Via:- BBC
@YeneTube @Fikerassefa

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የአከፋፋይና የቸርቻሪ ነጋዴዎች የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ተገለፀ፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሲሚንቶ ግብይት ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ በማስወጣት እየናረ የመጣውን የሲሚንቶ ዋጋ ለማስተካከል የመሸጫ ዋጋ በመተመን ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶችና የግል ነጋዴዎች ተመርጠው በቅርቡ ወደ ስራ መግባታቸው ይታወሳል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አላስፈላጊ የሲሚንቶ ዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ዋጋ በመተመን የኮንስትራክሽን ዘርፉ እንዳይዳከም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም ከፋብሪካዎች ተረክበው የሚሸጡ አከፋፋዮች የአንድ ኩንታል ዋጋ እንደየ ርቀቱ ከ245.60 ብር እስከ 388.10 ብር ሲሆን የቸርቻሪ ነጋዴዎች የሚሸጡበት ዋጋ ከ260.20 ብር እስከ 408.10 ብር ነው፡፡ከዚህ በላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ የሚሸጥ ንግድ ድርጅት ካለ በቢሮው ነፃ ስልክ መስመር 8588 ላይ በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ጥቆማ በመስጠት ህገ-ወጥነትን በጋራ መከላከል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታውቋል ፡፡
Via Addis Ababa City PS Office

YeneTube
Photo
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰሞኑን ከአልጄዚራ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለይ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ከአልጀዚራ አረብኛ ስርጭት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ትናንት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓም ማምሻዉን በጣቢያዉ ተላልፏል።በዚሁ መሰረት በጣቢያዉ የኢትዮጵያ ቢሮ ሃላፊ መሀመድ ጣሃ ተወኩል በኩል ለቀረበላቸው ጥያቄዎች አቶ ገዱ ምላሽ ሰጥተዋል።ግብጽ በጎረቤት አገሮች ላይ የጦር ካምፕ ለመመስረትና የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገዉን ጥረት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ግብጽ የተለያዪ ሙከራዎችን በመጠቀም ላይ መሆኗን፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሁሉም ጎረቤት አገረቿ ጋር ማለትም ከሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላት በመሆኑ ሙከራው የማይሳካ ህልም ነው ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ የጎረቤት አገሮች ግንኙነታቸውን በማጠናከር ወደ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ውህደት እያመሩ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ ሲመዘን አገራቱ ግብጽን በመደገፍ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ይንቀሳቀሳሉ ብለዉ እንደማያምኑም አቶ ገዱ ገልጸዋል።በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለዉ ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ በከፍተኛ ደረጃ እየተጠናከረ እንደመጣ የገለጹት አቶ ገዱ፤ ከእርሻ መሬት ጋር በተያያዘ በድንበር አካባቢ የሚነሳው ችግር ለዘመናት የቆየ በመሆኑ ችግሩን በዘለቄታው ለመፍታት ሁለቱ አገራት በጋራ እና በትብብር እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰተውን ሰሞነኛ ክስተት የግብጽ ሚዲያዎች እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመራ በስፋት ሲሰሩ መቆየታቸውንም አቶ ገዱ አብራርተዋል።የግብጽ ሚዲያዎች ሃላይብ ትሪያንግል በመባል የሚታወቀውን የሱዳን መሬት ግብጽ በወረራ መያዟን በተመለከተ አንድም ቀን ሳይተነፍሱ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ጉዳይ እንደ ትልቅ አጀንዳ አንስተው ሰፊ ሽፋን መስጠታቸው ያላቸውን ተዓማኒነት ትዝብት ውስጥ እንደሚከትም የተናገሩት።ግብጾች ግድቡን ከእስራኤል ጋር ለማገናኘት መሞከራቸው ስህተት ብቻ ሳይሆን ወንጀል መሆኑንም አቶ ገዱ በነበራቸው ቃለ ምልልስ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
#ETV

የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በርካታ አባላቱ ከሕግ ውጪ ታሰሩብኝ አለ!
የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ)፣ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሰላማዊ መንገድ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንደተፈጠረበትና በርካታ አባላቱ እንደታሰሩበት አስታወቀ፡፡የቁጫ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ሰላም በር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ አብርሃም ቡሄ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባል በመሆኑና የፓርቲ ሥራ በመሥራቱ የታሰረም ሆነ የተከለከለ አንድም ሰው እንደሌለ በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
#Reporter

ማራቶን ሞተር በኮቪድ-19 ምክንያት 200 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ!
የኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሃዩንዳይ ተሸርካሪዎች አስመጪ እና መገጣጠሚያ ኩባንያው ማራቶን ሞተርስ 200 ሚሊዮን ብር ማጣቱን አስታወቀ።የማራቶን ሞተርስ ባለቤት የሆኑት አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከትንሽ እስከ ትልቅ የሚባሉ የንግድ ተቋማት ገቢያቸው እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ እና ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግም ኮቪድ በኢትዮጵያ ከተገኘበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ጀምሮ አስካሁን 200 ሚሊዮን ብር ገቢ ማጣቱን አስታውቋል፡፡
Via Addis Maleda

በቤት እጦት ምክንያት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዝቅተኛ ነዋሪዎች ቤት ለመገንባት መዘጋጀቱን በባህር ዳር ከተማ የአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አስታወቀ፡፡
የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ካሴ እንደገለጹት ግንባታው በ2 ዙር የሚሰራ ሆኖ የመጀመሪያው ዙር በ6 ወር የሚጠናቀቅ 7 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልገውና ለ56 እማውራና አባውራ ወገኖቻችን የሚውል ሲሆን በክፍለ ከተማችን የሚገኙ ልዩ ልዩ ተቋማትና ባለሀብቶች እየተሳተፉ ይገኛል ብለዋል፡፡
ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ኮምኒኬሽን ቢሮ

አንዳንድ ሰዎች ያለ አግባብ አስክሬን በመንካት ለኮሮና ቫይረስ እየተጋለጡ ስለሆነ ለእድሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በመላው ዓለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9.2 ሲደርስ ከእነዚህ መካከል 477 ሺህ መሞታቸው ተገለፀ። የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በላቲን አሜሪካ ብቻ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ ደርሷል።
#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
#BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳኑ ጠ/ሚንስትር አብደላ ሃምዱክ በሶስትዮሹ ድርድር በታዛቢነት ሲሳተፍ ለነበረው የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ዋና ጸሐፊ ስቴፈን ማኑቺን በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ዙሪያ ሁሉንም አካላት የሚያረካ ስምምነት ላይ ለመድረስ በውይይቱ ሀገራቸው እንደምትገፋበት ነግረዋቸዋል ተብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ይካሄዳል።
በነገው ስብሰባም የምክር ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እንዲሁም የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመትን መርምሮ ያጸድቃል።በተጨማሪም የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለመመደብ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብን፣ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።
እንዲሁም የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል መንግስት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ስርዓትን ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃልም ነው የተባለው።በተጨማሪም የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የልዩ የመንግስት ዕዳ ሰነድ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት ጨምሮ በ15 አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ያጸድቃል።
#FBC

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራን ለማቆም የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢዝነስ አማራጮቹን በመጠቀም ላይ መሆኑን አስታውቋል።በአየር መንገዱ የካርጎና ሎጀስቲክስ ማነኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ፍፁም አባዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኮሮና ፈተናዎችን ለመቋቋም ፊቱን ወደ ካርጎ ጭነት አገልግሎት ማዞሩን ተናግረዋል፡፡አቶ ፍፁም እንዳሉት በኢትዮጵያ ሰኔ መጨረሻ በጀት አመቱ የሚዘጋ በመሆኑ አየር መንገዱ ከካርጎ ብቻ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ያገኛል ብለዋል፡፡
Via Ethio FM

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 186 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4034 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት (186) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5034 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4034 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት (186) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5034 ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፣ ባጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 78 ደርሷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ሁኔታ
1.በህክምና ላይ የነበረ የ38 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
2.በጤና ተቋም የነበረች የ19 አመት የሶማሊ ክልል ነዋሪ
3.በጤና ተቋም የነበረች የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
@YeneTube @FikerAssefa
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ሁኔታ
1.በህክምና ላይ የነበረ የ38 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ (ወንድ)
2.በጤና ተቋም የነበረች የ19 አመት የሶማሊ ክልል ነዋሪ
3.በጤና ተቋም የነበረች የ40 አመት የአዲስ አበባ ነዋሪ
@YeneTube @FikerAssefa
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 186 ሰዎች ሲሆኑ ከአምስቱ በስተቀር ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። በፆታ ሲታይ ደግሞ ወንድ(73) ሴት(113) ናቸው!
➡️ዕድሜያቸው ከ6 ወር-75 አመት የሆኑ
➡️ተጨማሪ 74 ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 1 ከሐረሪ ክልል እና 2 ከደቡብ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1486 ነው።
➡️የተገኙት ከአዲስ አበባ(147)፣ ከኦሮሚያ ክልል(4)፣ከሶማሊ ክልል(16)፣ ከአፋር ክልል(10)፣ ከደቡብ ክልል(1) እና ከድሬዳዋ(8) በድምር 186 ሰዎች ናቸው።
➡️በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5034 ደርሷል።
➡️በጠና የታመሙት ቁጥር ደግሞ 38 ነው።
➡️በ24 ሰዓት ውስጥ 3 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፣ እስካሁን በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 78 ነው።

በዛሬው እለት፣በሶማሌ ክልል የአይሻ ወረዳ፣ ደወንሌ ኮሪደር በሚገኝ ኬላ ከጅቡቲ ለሚገቡ አሽከርካሪዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ ለመመርመር የሚያስችል ናሙና መውሰድ ተጀመረ፡፡
ናሙናውን ለመውሰድ የሚያስችልና ለማቆያ የሚያገለግል የድንኳን አልጋ በማዘጋጀት ስራው መጀመሩም ተገልጿል።የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የዲሜሬጅ ህግና ሎጅስቲክ ድጋፍ ዳይሬክተርና የደወንሌ የኮሮና መከላከል ግብረሀይል አስተባባሪ አቶ አበበ እሸቱ እንደተናገሩት የተጀመረው ናሙና የመውሰድ ስራ ከጅቡቲ የተለያዩ እቃ ጭነው የሚገቡ አሽከርካሪዎችን ናሙና ወስዶ ልየታ በማድረግ ቫይረሱ የተገኘባቸው ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።የናሙና ምርመራው ኮንቴኔር የሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ ነው የተጀመረው፡፡
ምንጭ:SRTV