YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኦነግ
በኤርትራ በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ #ከ1300 እስከ 1500 ያህል የኦነግ #ታጣቂዎቹ ዛሬ ጠዋት #በዛላንበሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ፡፡
@yenetube @mycase27
የተጠናከረ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ለዋልታ ቲቪ የተናገሩት ቅንጫቢ⤵️

📌"ኦነግ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር ትጥቁን #ፈቶ #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ተብሎ የሚነገረው መሰረተ ቢስ ወሬ ነው"

📌"እኛ ትጥቅ እንድንፈታ የተስማማንበት #ስምምነት_የለም። የታጠቀው ኣአካል ትጥቅ ይዞ እያለ እኛ ትጥቅ የምንፈታበት ምክን ያት የለም።"

📌"ትጥቅ መፍታት የሚባል #sensitivity ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈቱ መባልም አንፈልግም። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ኦነግ ያለው ሚና ምን እንደሚሆን ነው የተስማማነው።"

📌አቶ ዳውድ #ሰኔ_16 በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ ድርጅታቸው እንዳልተሳተፈ ገልፀዋል። #በቡራዩና_በአዲስ አበባ በተፈጠሩ ግጭቶችም ኦነግ #አለመሳተፉን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

📌#በቤኒሻንጉል#በወለጋና #በከፋ በተፈጠሩ ግጭቶች #ኦነግ መሳተፉንና አለመሳተፉን ለማረጋገጥ ማጣራት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

📌አቶ ዳውድ በበደኖና በአርባ ጉጉ #በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ #በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የኦነግ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
#update ኦነግ⤵️⤵️

#ኦነግ ትጥቅ አልፈታም በማለት ለተጀመረው ስላማዊ የፖለቲካ ሂደት እንቅፋት መሆን የለበትም መንግስትም በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ማቅረብ አለበት ሲሉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ #ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

አዲስ አበባ በሚገኘው አሐዱ በተባለው ሬድዮ ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ ሌንጮ ለታ በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ሁሉን አካታችና የማይቀለበስ እንዲሆን ሁሉም አካል በሀላፊነት መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከኦነግ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ይፋ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምን ተነስተው ትጥቅ አንፈታም እንዳሉ መረዳት ይቸግረኛል ብለዋል።

" ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ? አሁንስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ማንን ለመውጋት ነው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

የትጥቅ ትግል የትም እንደማያደርስና ስላማዊና ህዝባዊ እምቢተኝነት የተሻለ የትግል ስልት መሆኑን ከተገነዘብኩ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል፣ አሁን የሚያስፈልገን በስላምና በመግባባት ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲ ሽግግር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27
የአጣዬ እና አካባቢውን ሰላም እያወኩ ያሉት “የተደራጁ ኃይሎች” መሆናቸው ሲገለጽ ቢቆይም የሰሜን ሸዋ ዞን የአስተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ግን “#ማሽሞንሞን_አያስፈልግም#ኦነግ_ነው” ሲሉ ወንጅለዋል።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
#ኦነግ #OLF #ABO

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከ350 በላይ የሚሆኑ አባሎቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታወቀ።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ከ350 በላይ አባሎቼ እና ደጋፊዎቼ በጅምላ ታስረውብኛል ብሏል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገበሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህ የጅምላ እስር መፈጸሙ አሳስቦኛል የተጀመረውን የዲሞክራሲ ጭላንጭልም ያከስማል ብሏል።

ሰሞኑን ባልታወቀ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የጅምላ እስራት በዘመቻ መልኩ በኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ ይህን የጅምላ እስራት እየፈጸመ የለዉ አካል የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ፓርቲው አስታውቋል።

የጅምላ እስሩ በተለይም ከአንድ ሳምንት ወድህ ብቻ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች (በ7 የኦሮሚያ ዞኖች እና በ26 ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች) በጅምላ ከታሰሩት አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን መካከል እስከ አሁን ባገኛነዉ መረጃ መሰረት ወደ 350 የሚጠጉ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ታስረውብኛል መንግስት በአስቸኳይ ይፍታቸው ሲል አሳስቧል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
#OLF #ABO #ኦነግ መግለጫ

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

የክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን። በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም። በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ። ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

ስለሆነም፣ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ አስፈሪና ዘግናኝ የሆነ የስጋት ደመናን አንዣቦ ያሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ልያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ሁሉም ወገኖች ኃላፍነትና ግዴታቸዉን በላቀ የተጠያቂነት/responsibility መንፈስ እንዲወጡ ኦነግ አጥብቆ ይማጸናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግሥት የዜጎች ነፃነትና ደህንነት ልረጋገጥበት የሚችለዉ ሁለንተናዊ መፍትሄ ልገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደመንግሥት የተረከበዉን ታሪካዊ ኃላፍነትና ተጠያቂነት መወጣቱ የወሳኝነት ሚና እንዳለዉ ተገንዝቦ ይህንን ኃላፊነቱን በገንቢ ሁኔታ እንዲወጣ በአፅንዖት እናሳስባለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
@YeneTube @Fikerassefa
ቃል ሳይሆን ተግባር እንሻለን #ኦነግ #OLF

የኦሮሞ ነጳነት ግንባር የምክርቤቱን ውሳኔ በጥርጣሬ አይን እንደሚያየው እና አስታውቋለ እንዲሁም።

#የፊንፊኔና #ድሬዳዋ በህግ በታሪክ መሬቱ የኦሮሞ ህዝብ ሀብትና የኦሮሞ አካል ስለሆነ የነዚህን ሁለቱን የኦሮምያ ከተማዎች ጉዳይ በአስቸኮያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ፍታሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ ጠይቋል።

#OLF
@YeneTube @Fikerassefa
በምዕራብ #ኦሮሚያ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም እየተወሰደ ባለው እርምጃ፣ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የ-#ኦነግ #ሸኔ አባላት እጃቸውን እየሰጡ እና እየተያዙ ነው ተብሏል፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa