YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኦነግ #OLF #ABO

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከ350 በላይ የሚሆኑ አባሎቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታወቀ።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ከ350 በላይ አባሎቼ እና ደጋፊዎቼ በጅምላ ታስረውብኛል ብሏል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገበሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህ የጅምላ እስር መፈጸሙ አሳስቦኛል የተጀመረውን የዲሞክራሲ ጭላንጭልም ያከስማል ብሏል።

ሰሞኑን ባልታወቀ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የጅምላ እስራት በዘመቻ መልኩ በኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ ይህን የጅምላ እስራት እየፈጸመ የለዉ አካል የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ፓርቲው አስታውቋል።

የጅምላ እስሩ በተለይም ከአንድ ሳምንት ወድህ ብቻ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች (በ7 የኦሮሚያ ዞኖች እና በ26 ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች) በጅምላ ከታሰሩት አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን መካከል እስከ አሁን ባገኛነዉ መረጃ መሰረት ወደ 350 የሚጠጉ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ታስረውብኛል መንግስት በአስቸኳይ ይፍታቸው ሲል አሳስቧል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
#OLF #ABO #ኦነግ መግለጫ

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

የክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን። በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም። በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ። ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

ስለሆነም፣ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ አስፈሪና ዘግናኝ የሆነ የስጋት ደመናን አንዣቦ ያሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ልያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ሁሉም ወገኖች ኃላፍነትና ግዴታቸዉን በላቀ የተጠያቂነት/responsibility መንፈስ እንዲወጡ ኦነግ አጥብቆ ይማጸናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግሥት የዜጎች ነፃነትና ደህንነት ልረጋገጥበት የሚችለዉ ሁለንተናዊ መፍትሄ ልገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደመንግሥት የተረከበዉን ታሪካዊ ኃላፍነትና ተጠያቂነት መወጣቱ የወሳኝነት ሚና እንዳለዉ ተገንዝቦ ይህንን ኃላፊነቱን በገንቢ ሁኔታ እንዲወጣ በአፅንዖት እናሳስባለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
@YeneTube @Fikerassefa