YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከ|#ኦሮሚያ ክልል ፣ ቡሌሆራ አካበቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያ የሚኖሩ የቡርጂ ብሔረሰብ አባላት መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ብበሰልፍ ጠየቁ።
@YeneTube @Fikerassefa
#ኦሮሚያ_ክልል

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ ከ500 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል:-
⊙ በጉጂ ዞን በቄሮ ስም መሬት ወረራ የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ፣ ህገ ወጥ ኬላ በማቋቋም የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ያስተጓጎሉ፣ መንግስት የሚሰጠውን ስልጣን ሁሉ በቄሮ መረጋገጥ አለበት በሚል ያነሳሱ ሰዎች።

⊙ በባሌ ዞን የእርሻ ኢንቨስትመንት ያደናቀፉ።

⊙ በቡኖ በደሌ ዞን በአካባቢው የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆችን የቡና እና የጫት ምርቶች የመነጠሩ።

⊙ በጂማ ዞን የሰዎችን ቡና በመመንጠር ብሎም ቡዳ ነው በሚል ሰው የገገደሉ እና ያስገደሉ ይገኙበታል።
©FBC
@Yenetube @Fikerassefa
#አቶ_ኩማ_ደመቅሳ_ለቢቢሲ ⤵️

በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ባለፈው ሳምንት ኦዴፓ (የቀድሞው ኦህዴድ) በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኩማ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ አወዛጋቢ ስለነበሩና እርሳቸው በከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ስለታቀዱና ተግባራዊ ስለተደረጉ ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

«ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም»

በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላንን በተመለከተ የተሳሳተ አመለካከት እንዳለ ተናግረዋል።

ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ «ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ» በማለት የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተመሳሳይ #ኦሮሚያ ውስጥ ለጠንካራ ጥያቄና ተቃውሞ ምክያት የነበረው የአዳማ ከተማን የኦሮሚያ ክልል መዲና እንድትሆንና የክልሉ መስሪያ ቤቶች ወደዚያው እንዲዘዋወሩ መደረጋቸው ይጠቀሳል።

ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አቶ ኩማ ውሳኔው ስህተት እነደሌለበት ያምናሉ። አሁንም ወደኋላ መለስ ብለው ሲመለከቱ «አሁንም ያኔ የነበረኝ አቋም ስህተት ነው ብዬ አላምንም» ካሉ በኋላ፤ «አዳማ የክልሉ ዋና ከተማ ሆና እንደተቀየረች ብትዘልቅ ኖሮ ከተማዋ ታድግ እንደነበር» ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም ዋና ከተማን በመምረጥ ረገድ ሁሉንም እንቅስቃሴ ተቆጣጥሮ ሥራ ለማከናወን የተሻለው እንደሚመረጥ ጠቁመዋል። በውሳኔው ውስጥም ግፊት እንዳልተደረገባቸው ሲያስረዱም «ያኔ ይህንን ያደረገው ሌላ ኃይል ነው የተባለው ውሸት ነው። ውሳኔውን የወሰነው እኔና ከእኔ ጎን የነበሩት ናቸው» ብለዋል።

ይህም ሆኖ የኦሮሞ ህዝብን መብት የሚነካ ውሳኔ አስተላልፈው እንደማያውቁ «በግሌ የኦሮሞ ህዝብ ፋይዳና መብት ላይ ተደራድሬ አላውቅም» በማለት አስረግጠዋል ተናግረዋል። ከሰው የሚያገኙትን የድጋፍ ወይም የነቀፋ ምላሽ እንደማያስቡ ተናግረው «የኦሮሞን ህዝብ የሚጠቅም ሀሳብ ሁሌም አራምዳለሁ» ብለዋል።


አቶ ኩማ ደመቅሳ የቀድሞው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ያሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በክብር ካሰናበታቸው መስራችና ነባር አባላቱ መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በእሳቸው እይታ ትግል የሚካሄደው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ሆኖ ብቻ ስላልሆነ፤ ከኮሚቴው መሸኘታቸው ከትግል እንደማያግዳቸው «ትግል በተለያየ ደረጃ ይካሄዳል» በማለት ገልጸዋል።

የስንብት ሥነ ሥርዓቱ ሲካሄድ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው የሚናገሩት አቶ ኩማ፤ ለረዥም ጊዜ የቆዩበትን የትግል ጊዜ በማስታወስ «ከእኛ ጎን የነበሩና የተሰዉ ሰዎች ይህንን እድል አላገኙም። እኔ ይህንን እድል ስላገኘሁ ደስታዬ ወሰን የለውም» ብለዋል።

አቶ ኩማ ደመቅሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም በተለያዩ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ጊዜ ሰርተዋል።

©BBC
@YeneTube @Fikerassefa
በቤኒሻንጉል #ጉሙዝና በምዕራብ #ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን #ግጭት ለማስቀረት የሚካሄዱ የሰላም ጉባኤዎች ቀጥለዋል። የሰላም ጉባኤው በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ቀሽማንዶ በተባለ ቦታ ሰሞኑን ተካሂዷል።

የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ባለመው በዚህ ስብሰባም ከምዕራብ ወለጋ ቤጊ እና ቆንዳላ ወረዳዎች፤ ከአሶሳ ዞን ደግሞ ባምባሲ እና የማኦ-ኮሞ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከአሶሳ ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ያላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ምንጭ:-Dw
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ #ኦሮሚያ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለማስቆም እየተወሰደ ባለው እርምጃ፣ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የ-#ኦነግ #ሸኔ አባላት እጃቸውን እየሰጡ እና እየተያዙ ነው ተብሏል፡፡

Via:- Sheger FM
@Yenetube @Fikerassefa
ትኩረት #Share ይደረግ የኤልያስ መሰረት መልዕክት ነው።

#ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት እና በታጣቂዎች መሀል ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች ንፁሀን ዜጎች ለሞት፣ መቁሰል፣ መፈናቀል እና መራብ እየተዳረጉ ነው።

በተለይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደረጉ ውጊያዎች እና የአየር ጥቃቶች በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ እና እንደቆሰሉ የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የ11ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸውን ያጡ አባት እንዲሁም በአየር ጥቃት ከ15 በላይ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን የቀበሩ አንድ የሀይማኖት አባት (ሁለቱም ከ ቢላ ከተማ) ይህን በስልክ አረጋግጠውልኛል።

ጉዳዩን የአለም አቀፍ ሚድያ ችላ ብሎታል፣ የሀገር ውስጥ ሚድያው ረስቶታል፣ መንግስትም መረጃ እየሰጠበት አይደለም። ታጥቆ የሚዋጋው በፍላጎቱ ሊሆን ይችላል... በንፁሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን ሁላችንንም ሊያሳስብ ይገባል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ ለነበረው ጦርነት የተገኘው መፍትሄ ወደ ኦሮሚያ ክልልም እንዲዘልቅ ጥረት ማድረግ ይገባል፣ ህዝብ እያለቀ ነው።

#Peace #Ethiopia

Via:-EliasMeseret
"ለአጋቾቹ የምንከፍለው ገንዘብ ስለሌለን በየገበያው እና በየመንደሩ እየለመንን ነው የምንገኘው" -የታጋቾች ቤተሰቦች

ከሁለት ሳምንት በፊት በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ፤ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ ለመክፍል የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ በልመና ላይ እንደሚገኙ የታጋቾች ቤተሰቦች ገለጹ።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የታጋቾች ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ የተጠየቁትን ክፍያ ከፍለው የተለቀቁ ተማሪዎች ቢኖሩም ገንዘቡን መክፈል ያልቻሉ ግን እስከአሁን ድረስ በታጣቂዎች ተይዘው እንደሚገኙ አስታውቀዋል::

“እህቴን ትላንትም ዛሬ ጠዋትም አውርቻታለሁ:: ታስራ ነው ያለችው::ከእሷ ጋራ የነበሩ 4 የሚሆኑ ሰዎች የተጠየቁትን እስከ አንድ ሚሊየን የሚደርስ ገንዘብ ከፍለው ወጥተዋል:: እኛ የምንከፍለው ስለሌለን ከወረዳው የድጋፍ ደብዳቤ አጽፈን በየገበያው እና በየመንደሩ እየለመንን ነው የምንገኘው” ሲሉ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የታጋች እህት ገልጸዋል።

“ገንዘቡ የሚሞላልን ከሆነ አጋቾቹ የሚያዘጋጁት ሰው አለ::ለእሱ ሄደን እናስረክባለን::ከዛ ልጅቷን ወደ እኛ ያመጣሉ::ይህን እንድናደርግ ነው አጋቾቹ መመሪያ የሰጡን::” ሲሉ አክለው ገልፀዋል::

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
😭58👍226
ገርበ ጉራቻ አካባቢ ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ተለቀቁ፤ በታጋቾች ላይ ጾታዊ ጥቃትና ድብደባ ተፈጽሟል ተብሏል‼️
#ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ገርበ_ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ ከ167 በላይ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፉት ቀናት 16ቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸው ተገለጸ።

በታጋቾቹ ላይ ግርፋት፣ ድብደባ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን የተማሪዎቹን እገታ ከቤተሰብ ጋር ሆነው በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። 

አንድ የታጋች ተማሪ ቤተሰብ “ታጣቂዎቹ በተማሪዎቹ ፊት ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን እያለቀሱ ነግረውናል” ብለዋል።

ከ30 በላይ ይሆናሉ የተባሉት ታጣቂዎቹ ‘ፀጉራቸውን የተሰሩ፣ የሲቪል ልብስ የለበሱ እና የተማሩ’ መሆናቸውን ተማሪዎቹ አመልክተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭42👍19
#ኦሮሚያ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት የወባ በሽታ እየተባባሰ መሆኑና የጤና አገልግሎቶች መስተጓጓላቸው ተዘገበ

ለማ ተፈራ የተባሉ የምዕራብ ኦሮሚያ አርሶ አደር በአንድ ወር ውስጥ አራት ልጆቻቸውን በወባ በሽታ በሞት መነጠቃቸውን ገልጸው እየተካሄደ ያለው ግጭት ባይኖር ኖሮ አደጋውን መከላከል ይቻላል ብለው እንደሚያምኑ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ተናግረዋል።

አርሶ አደሩ "በግጭት ምክንያት መንደራችን ውስጥ የወባ መድሃኒት እና ህክምና እንዳልነበርም" ገልጸዋል።

#ኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትና በመንግስት ኃይሎች መካከል በመካሄደ ላይ የሚገኘው ግጭት የጤና አገልግሎቶችን ማቋረጡን በመቀጠሉ ቀውሱ እየተባባሰ መምጣቱን የጤና ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

የኦሮሚያ ሀኪሞች ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ገመቹ ቢፍቱ "በክልሉ ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የተዘጋጀ ጸረ-ወባ መድሃኒት አቅርቦት ተስተጓጉሏል" ብለዋል።

በአካባቢው የሚገኙ ሐኪሞች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ሪፖርት አድርገዋል። በምዕራብ ወለጋ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ዳይሬክተር ለገሰ ቡልቻ "ከዚህ ቀደም ካለው በተለየ መልኩ አሁንም በድርቅ ወቅት በርካታ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው" ብለዋል። ዳይሬክተሩ በፈረንጆቹ 2023-2024 በሆስፒታሉ ከታከሙ 26,000 ታካሚዎች ውስጥ 70% የሚሆኑት በወባ በሽታ የተያዙ ናቸው ነው ያሉት።

በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ በሽታው ወደ አዳዲስ አካባቢዎች እንዲሰራጭ ሁኔታዎችን በመፍጠር ቀውሱን እያባባሰው ነው ሲሉም ተናግረዋል።

Via AS
@Yenetube @Fikerassefa
👍23😭92
#ጅማ ዞን በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

#ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ሚርጋኖ በሶ ቀበሌ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በጣለው ከባድ ዝናብ በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን 2017 በሚርጋኖ ባሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገሬ ኦጎደማ በተባለ ቦታ ላይ ለሌት 6 ሰዓት በጣለው ዝናብ መከሰቱን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የሸቤ ሶምቦ ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤቱ አክሎ ገልጿል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ዩሱፍ አባ ማጫ እና የሚርጋኖ በሶ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ምስጋና ለታ ተጎጂዎችን በመጎብኘት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል ተብሏል።

ባሳለፍነው አመት ሀምሌ 15 ቀን በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።

በተመሳሳይ ወቅት በ #ሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ 11 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሽኮ ዞንም የአራት ሶዎች ህይወት በመሬት መንሸራተት አደጋ ማለፉም ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍12😭64