YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በኢ/ር ታከለ ኡማ የቀረበለትን የሁለት ቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል!

በዚህ መሰረት:-
1.ወ/ሪት ፋይዛ መሐመድ ኡመር- የባህል ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ
2.ወ/ሪት ሓዳስ ኪዱ ትዓራ - የሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2013 በጀት ዓመት የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሀብት ሊመዘግብ መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከ2013 በጀት ዓመት ጀምሮ ቀደም ሲል ሲመዘግብ ከነበረው የተሿሚዎችና የህዝብ ተመራጮች በተጨማሪ የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሀብት ለመመዝገብ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል።የምዝገባውን ሥርዓት የሚያስተባብረውና የሚያስፈጽመው ደግሞ በየተቋማቱ የተሰየሙዉ የሥነምግባር መኮንኑ ሲሆን÷ የእያንዳንዱ መንግስት ሰራተኛ ሀብት ምዝገባ የሚከናወነው ሰራተኛው በሚሰራበት ተቋም መሆኑም ነው የተገለጸው።ይህንንም ስራ ለማከናወን የሚያስችል ሥልጠናም ከሐምሌ 14 እስከ 18 ቀን 2012 ዓ.ም ለ213 የሥነምግባር መኮንኖች መሰጠቱ ተገልጿል።ኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባ ሥራ ከጀመረበት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የ220 ሺህ ተሿሚዎች፣የህዝብ ተመራጮችና የተወሰኑ የመንግስት ሰራተኞችን ሀብት መመዝገቡ ታውቋል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ሜጀር ጄ/ል ከፍያለው አምዴ በሱዳን አብዬ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ጦር አዛዥ ሆነው ተሾሙ!

ሰላም አስከባሪ ሠራዊቱ ከ9 አመት በፊት ወደ ስፍራው ከገባ ጊዜ አንስቶ ሜጀር ጄ/ል ከፍያለው ሲሾሙ 8ኛው ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አውስቶ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። አዲሱ ተሿሚ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ለ30 አመታት ያህል ማገልገላቸውም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የአዲስአበባ ከተማ ምክር ቤት ኢ/ር ታከለ ኡማ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ኣንስቶ ላከናወኗቸው ውጤታማ ስራዎች የዕውቅና ሽልማት አበርከተላቸው።

ምክር ቤቱ ኢ/ር ታከለ በተለይም የሚሰሩ ስራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራዎችን በመከናወናቸው ነው ሽልማቱን ያበረከተላቸው።በተለይም አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የዕውቅና ሽልማቱ ከምክር ቤቱ ተበርክቶላቸዋል።በተጨማሪም የከተማዋን ታሪካዊና የቱሪዝም መስህብነት የሚያጎሉ እንዲሁም የነዋሪዎችን ችግር የሚፈቱና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ታላላቅ ፕሮጀክችን ማስጀመራቸው በታሰበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማስቻላቸው ነው የእውቅና ሽልማት የተበረከተላቸው።

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa1
ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች በአቅራቢያ ወደሚገኙ የአየር ማረፊያዎች ተመልሰው ለማረፍ መገደዳቸውን አስታወቀ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ምክንያት ለተከሰተው መጉላላት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ሁኔታውን እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa1
አልጀሪያ መስጊዶችን ልትከፍት ነው!

የአልጀሪያ ፕሬዚዳንት አብደልማድጂድ ቴቡን መስጊዶች ቀስ በቀስ የሚከፈትበቱን ሁኔታ እንዲያጠኑ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን አዘዙ።ከፍተኛ የፀጥታ አካካላት ስብሰባ ላይ ነው ፕሬዚዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብደላዚዝ ድጀራድን ከአንድ ሺህ ሰዎች በላይ ሰዎች መያዝ የሚችሉ ትልልቅ መስጊዶች ላይ እንዲያተኩሩም ነግረዋቸዋል።ፕሬዚዳንቱ ትልልቅ መስጊዶችን የመረጡበት ምክንያትም ሲያስረዱ " አስፈላጊ የሚባለውን አካላዊ ርቀት መጠበቅ ስለሚያስችሉ" ነው ብለዋል።የፊት ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው ተብሏል።

#BBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ባለፉት አሥራ አንድ ቀናት ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ስማርት ስልኮች፣ የብር ጌጣጌጥ ፣ ካናቢስ ተብሎ የሚጠራ አደንዛዥ ፤ ልባሽ ጨርቆች ፣ሺሻ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት የተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መሆናቸውን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1
በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን አስታወቀ!

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን የምርመራ ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ።ምርመራው መጠናቀቁን ተከትሎ እስካሁን ሲታይ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ የምርመራ ሰነድ ተዘግቶ አዲስ ወደተከፈተው ቀዳሚ ምርመራ እንዲዛወርለት ጠይቋል። የቀዳሚ ምርመራ ችሎት የሚባለው ዐቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ተቀብሎ ተጠርጣሪው ላይ የተደረገው ምርመራ ተአማኒ መሆኑን ሲያረጋግጥ የማስረጃ ጥበቃ ለማድረግ የሚከተለው ሥርዓት ነው።

በዚህ መሠረት ሕጉን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ያስከፈለ በመሆኑ፣ ይህ የጊዜ ቀጠሮ ሲመለከት የነበረው ችሎት መዝገቡን ዘግቶ ወደ ቀዳሚ ምርመራ ችሎት እንዲመራው የምርመራ ቡድኑ እና ዐቃቤ ሕግ ጠይቋል። የምርመራ ቡድኑ በአቶ በቀለ ገርባ በተሰጠው ጊዜ የተለያዩ የምርመራ ሥራዎች ማከናወኑን ለአራዳ ምድብ ችሎት አስታውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢዋ እንዲሁም በሻሸመኔ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም በነበረው ብጥብጥ የደረሰውን ውድመት አስመልክቶ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘርፉን የተመለከተ 45 ገጽ ያካተተ ማስረጃ ማቅረቡን ጠቅሷል።ተጠርጣሪው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን በአስገዳጅ መልኩ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ 10 ቀናት በማስለቀስ የምኒልክ ሐውልት ማፍረስ እና ቤተ መንግሥቱን መቆጣጠር ይቻላል የሚል ትእዛዝ መስጠቱን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።
ከተጠርጣሪው የተገኙት ሁለት ሽጉጦች ሕገ ወጥ መሆናቸውንም ፖሊስ ጠቅሷል።የተጠርጣሪው ጠበቆች ደንበኛቸው ፈጸሙ የተባለው ወንጀል አመላካች ነገር አልሰማንም፤ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን አቅርቦ እንዲመረምር እና ይህ የምርመራ መዝገብ ተዘግቶ ጉዳዩ በቀዳሚ ምርመራ ይታይ ቢባል እንኳን ተጠርጣሪው የዋስ መብታቸው እንዲከበር አመልክተዋል። አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው የፈጸምኩት ወንጀል የለም፤ እኔ የፖለቲካ መሪ እንጂ የምመራው ሠራዊት የለም፤ በመሆኑም በብሔር እና በሃይማኖት ግጭት የተከፈተብኝ ወንጀል እኔን የሚመለከት አይደለም ብለዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበከሉ በተጠርጣሪው ላይ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት በመቀስቀስ እና በሌሎች ወንጀሎች ተጨባጭ ማስረጃ ማግኘቱን በማስታወቅ፣ ይህንን ማድረግ የሚቻለው በጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሳይሆን በመደበኛ ክርክር ነው ብሏል።አቶ በቀለ የተጠረጠሩበትም ወንጀል የሰው ሕይወት የጠፋበት እና ከባድ በመሆኑ የዋስትና መብታቸው ሊጠበቅ አይገባም ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል።ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የፖሊስን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለሐምሌ 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በሌላ በኩል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በ14 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል በሌላ ችሎት ማስከፈቱን ገልጿል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
አዲስ አበባ ዛሬ ጠዋትና አመሻሹን በጉም ተሸፍና ታይታለች።

በአብዛኞቹ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጭፍግግ ያለ አየር የተስተዋለ ሲሆን ፎቆችና ዛፎች አንዲሁም አስፋልትና መንደሮች በጉም ሲሸፈኑ ውለዋል።ነዋሪዎች ወፈር ያለ ልብስ ለብሰው " የዘንድሮ ክረምት " በማለት ክረምቱን ከበድ አንዳላቸው ሲያወሩ ተስምተዋል ።ይሄ ፎቶ አፍንጮ በር አካባቢ ዛሬ ሐምሌ 28,2012 ከቀኑ 11 ሰዓት የተነሳ ነው።

#FidelPost
@YeneTube @FikerAssefa1
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 44ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሀምሌ 29 እና 30/2012 ያካሂዳል፡፡

በነገው እለት በሚካሄደው ጉባኤ የ2012 የአስፈፃሚ አካላት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ፣ የ2013 በጀት እና የበጀት አመቱ የስራ እቅድ ላይ እንደሚወያዩ እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቁ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።

ምንጭ: የከተማ መስተዳደሩ መ/ኮምኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa1
ብሄራዊ ባንክ ለብድር እና ተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የምጣኔ ፖሊሲ ሊያወጣ እንደሆነ ፎርቹን አስነብቧል፡፡ምጣኔው ወቅታዊ የገንዘብ የመግዛት አቅምን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡ፖሊሲው አሁን ያለውን አሠራር በ3 ዐመታት ውስጥ ይተካል፡፡አዲሱ ፖሊሲ ለቁጥጥር አመች ቢሆንም፣ አስገዳጅ ግን እንደማይሆን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ እስካሁን ባለው አሠራር ባንኮች ለቁጠባ የሚሰጡት ዝቅተኛው ወለድ 7 በመቶ ሲሆን፣ የብድር ወለድ ደሞ በባንኮች እንደ ሁኔታው የሚወሰን ነው፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 588 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ8201 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 588 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡309 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19,877፣ ያገገሙት 8240፣ የሟቾች ቁጥር 343 ሲደርስ ፣በፅኑ ህክምና ክፍል ያሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 187 ከፍ ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa1
በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,826 ደረሰ፡፡

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 4,516 የላብራቶሪ ምርመራዎች 329 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ድረስ በተደረጉ 270,263 የላቦራቶሪ ምርመራዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,826 ደርሷል፡፡በተጨማሪም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#AMN
@YeneTube @FikerAssefa1
አማራ ክልል ከትግራይ ክልል ላይ ምንም ሊያነሳ የሚችለው የግዛት ጥያቄ እንደሌለ ባይቶና የተሰኘው የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲ ዛሬ በፈስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ገልጧል፡፡እንዲያውም በአማራ ክልል ስር ያሉ አንዳንድ የትግራይ ግዛቶችን ለማስመለስ እታገላለሁ- ብሏል ፓርቲው፡፡ፓርቲው አክሎም፣ ትግራይ ዘንድሮ የምታካሂደው ክልላዊ ምርጫ የሕዝበ ውሳኔ አንድምታ ያለው በመሆኑ፣ ማንም ሊያሰናክለው እንደማይችል እና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ለክልሉ ምክር ቤት የጻፉት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም ተቀባይነት እንደሌለው አውስቷል፡፡

#Wazema
Photo: VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
የአሜሪካ ተራዕዶ ድርጅት (USAID) ለኢትዮጵያ 250 ቬንትሌተርና ኦክሲጂኔተሮች እንዲሁም ሌሎች በፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።ድጋፉንም የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተገኝተው መረከባቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሊባኖስ ቤሩት ዋናው ወደብ ዛሬ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። በተጨማሪም በርካታ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፣ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ይኑሩ አይኑሩ የታወቀ ነገር የለም። የፍንዳታው ምክንያት ምን እንደሆነ የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ፣ ከርችት ዴፖ የተነሳ ሳይሆን እንዳልቀረ ብሉምበርግ የሀገሪቱን ማዕከላዊ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እስካሁን 200 ያህል አባላቶቼ ታሰረቡኝ ሲል አማረረ።

በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በአንዳንድ ዞኖች ጽ/ቤታቸዉ በመዘጋቱ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና አደጋ ላይ መዉደቁን አስታዉቀዋል። የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የፓርቲ አባላት እስራት ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በፊትም ነበረ ሲሉ ተናግረዋል።በተለይ በወረዳ የሚገኙ ጽ/ቤቶቻችን ተዘግተዉብናል ያሉት ዶ/ር መረራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የታሰሩ አባላቶቻችን ጉዳይ ይጣራልን ብለን ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃለ አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የኦነግ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ አባልት በመታሰራቸዉ፤ ፓርቲዉ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1