YeneTube
መብራት በመላ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑም…
#Update
በመላ ሀገሪቱ የተቋረጠው ኃይል መልሶ መገናኘት ጀምሯል
በዚህም መሰረት አብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል እና የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች መልሰው ኃይል ማግኘት ችለዋል።
የተቀሩትን አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ጥረቱ ቀጥሏል።
@Yenetube @Fikerassefa

👍24😭10😁8❤2
#Update
የኢራኑን ፕሬዚዳንት ጨምሮ አራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ!
የኢራን መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆሴን አሚር አብዶላያንን አሳፍራ የነበረች ሄሊኮፕተር ባጋጠማት አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
ራይሲ ከኢራን-አዘርባጃን ድንበር አካባቢ ከተመለሱ በኋላ ወደ ታብሪዝ ከተማ እያመሩ ነበር። በኢራን ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢ ይህው አደጋ ያጋጠመ ሲሆን በመጥፎ የአየር ሁኔታ ምክንያት ግዙፍ የፍለጋ ስራው ተስተጓጉሏል።የራይሲን ሄሊኮፕተር ፍለጋ የተቀላቀለው የቱርክ ሰው አልባ አውሮፕላን በሰሜናዊ ምእራብ ኢራን ወጣ ገባ የመሬት አቀማመጥ በበረራ መከታተያ ድረ-ገጾች ላይ ታይቷል።
ከፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በተጨማሪ በሄሊኮፐተሩ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ 8 ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አብራሪዎችም ህይወታቸው አልፏል።የፕሬዝዳንቱን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ህልፈት ተከትሎም የኢራን መንግስት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱም ነው የተነገረው።
@YeneTube @FikerAssefa

😭96👍30😁9👀9❤5
YeneTube
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ተስፋዬ ወፍጮ ቤት እየተባለ በሚጠራ አካባቢ እየተገነባ ባለ ህንጻ የአፈር ናዳ መከሰቱ ተነገረ፡፡ ህንጻ ለመገንባት የአፍር ቁፋሮ እያደረጉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞች አፈር እንደተናደባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ከአፈር ናዳው እስካሁን ድረስ አንድ ሰው ብቻ ማውጣት እንደተቻለ የገለጹት ነዋሪዎቹ በቦታው ያለው ነገር የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡ የእሳት እና…
#Update
በደረሰው አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ፡፡
ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏል ተብሏል፡፡
አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ በስራ ላይ እንዳሉ ስራዉ ከሚከናወንበት አጠገብ የነበረና አፋፍ ላይ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉሀ ልክና አፈር በሰራተኞቹ ላይ በመናዱ የደረሰ አደጋ ነው ሲል የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ከተጫነበት አፈርና ድንጋይ ስር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት እየተገነባ ያለው ህንጻ እና የተደረመሰው ቤት የአንድ ግለሰብ መሆናቸው ነግረውናል፡፡
በማናቸዉም የግንባታ ስራዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ አለመስራት መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የግንባታ ፈቃድ ሰጪ አካላትም ተገቢዉን ክትትል ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
Via Ethio FM

👍25😭11❤3
YeneTube
በአዲስ አበበ ከተማ የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፣ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ሥር ዋሉ የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት፦ 1ኛ. አቶ ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. አቶ ዮሴፍ ባቡ…
#Update
የግብር መጠንን በመቀነስ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ መርማሪ ያቀረበውን የጥርጣሬ መነሻንና የተጠርጣሪ ጠበቃ መከራከሪያ ነጥቦችን ተመልክቷል
ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው የታዩት ተጠርጣሪዎች የአ/አ ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ ሃብታሙ ግዲሳ፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ስምረት ገ/እግዚአብሔር፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ዮሴፍ ባቡ፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር አቤኔዘር ቶሎሳ፣ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ለሚ ሲሌ እና ገንዘብ ተቀባይ ባለሙያ ወ/ሮ መቅደስ አረጋዊ ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹ የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ከግብር ከፋይ ግለሰቦች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ከግብር ከፋይ ድርጅቶች “ግብር እንቀንስላችኋለን” በማለት በመደራደር ከ100 ሚሊየን ብር የግብር መጠንን ወደ 13 ሚሊየን ብር ዝቅ በማድረግ ግብርን በመቀነስ ከተለያዩ ድርጅቶች በተለያዩ መጠኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ ተቀብለዋል በማለት መርማሪ ፖሊስ የጥርጣሬ መነሻውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።
መርማሪ ፖሊስ በባንክ ሂሳባቸው የጉቦ ገንዘብ ገቢ የተደረገላቸው ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ መሰብሰቡን በማመላከት ተጨማሪ ግብረ አበር ለመያዝና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች አሰባስቦ ለመቅረብ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ በበኩሏ ደንበኞቿ በመርማሪ ፖሊስ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት “አልፈጸሙም ” በማለት በመከራከር የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቃለች።
መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ በማለት በጠበቃቸው የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ በመጠየቅ ተከራክሯል።
የፖሊስ የጥርጣሬ መነሻን እና ግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርመራ መዝገቡ ጅምር በመሆኑ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ለፖሊስ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በማመን የተጠርጣሪ የዋስትና ጥያቄን በማለፍ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።
በታሪክ አዱኛ

👍44❤8
YeneTube
የእስራኤል ጦር የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ በቤይሩት ጥቃት መገደሉን አስታውቋል። @YeneTube @FikerAssefa
#Update
የሄዝቦላህ መሪ ሃሰን ናስራላህ መሞቱ ተረጋገጠ!
የእስራኤል አየር ኃይል በቤሩት በወሰደው ጥቃት የሄዝቦላህ ሃሰን ናስራላህ መገደሉን ቡድኑ አረጋግጧል።
እስራኤል በበኳሏ ናስራላህ እስከወዳኛው ተሸኝቷል ብላለች።
ሃሰን ናስራላህ የተገደለው የእስራኤል ጦር ትናንት ምሽት በቤሩት ከተማ በወሰደችው መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ነው።

👍24😭12❤1⚡1
YeneTube
ኢራን በእስራኤል ላይ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀች ነው ተባለ። ኢራን በእስራኤል ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀች ነው ሲሉ የዋይት ሀውስ ባለስልጣን ተናግረዋል።እኚው ባለስልጣን ኢራን ይህንኑ የምታደርግ ከሆነ ከባድ መዘዝ ይዞባት ይመጣል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። @YeneTube @FikerAssefa
#Update
ኢራን ከ100 በላይ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች። ይህንንም ተከትሎ የእስራኤል መንግስት ዜጎች ወደ ቦምብ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲገቡ መልዕክት አስተላልፏል።
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን ከ100 በላይ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች። ይህንንም ተከትሎ የእስራኤል መንግስት ዜጎች ወደ ቦምብ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲገቡ መልዕክት አስተላልፏል።
@YeneTube @FikerAssefa
👍50👀34😁9👎5❤3😭3
YeneTube
የሃማሱ መሪ ያህያ ሲንዋር ሳይገደል አልቀረም ተባለ! የሃማሱ መሪ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተሰማ።የእስራኤል ጦር በፈጸምኩት ጥቃት "ሶስት ሽብርተኞች ተገድለዋል" ያለ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንደኛው የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ነው ብሎ እንደሚያምን እና ተጨማሪ ማጣራት እያደረገ እንደሆን አስታውቋል። ሲንዋር ከ2017 ጀምሮ በጋዛ የሃማስ መሪ የነበረ ሲሆን ባለፈው ሐምሌ የቡድኑ…
#Update
የእስራኤል መንግስት የሃማስ አለቃ ያህያ ሲንዋር መሞታቸውን አረጋግጫለው አለ!
የሳራኤሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሀማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ወታደራዊ ሃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።
እስራኤል ቀደም ሲል በጥቅምት 7 በሃማስ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በማቀነባበር ሲንዋርንበመወንጀል የእስራኤል መንግስት በጋዛ ሰርጥ አጸፋዊ ጥቃት ሰነዝራ ነበር::
በጋዛ ስትሪፕ ውስጥ የሃማስ መሪ የነበረው እስማኤል ሃኒዬህ በነሀሴ ወር ላይ በኢራን መገደሉን ተከትሎ ያህያ ሲንዋር መረከባቸው ይታወሳል::

🔥26👍22👎8😭6❤2⚡1
YeneTube
የኬንያው ምክትል ፕሬዝደንት ሆስፒታል ተኝተው ሳለ ከሥራቸው ተሰናበቱ! የኬንያ ሴናተሮች ምክትል ፕሬዝደንቱ ሪጋቲ ጋሻጉዋን ለሕክምና ሆስፒታል ሳሉ ከሥልጣን አሰናብተዋቸዋል።የምክትል ፕሬዝደንቱ ጠበቃ እንዳሉት ጋሻግዋ ሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተገኝተው ከሥልጣን የተነሱበትን ምክንያት ማዳመጥ ያልቻሉት ሆስፒታል በመግባታቸው ነው። በድራማ የታጀበ በተባለለት ቀን ነው ጋሻግዋ ባልተገኙበት ከመንበራቸው የተነሱት።…
#Update
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሴኔቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓን ከስልጣን ለማባረር ያሳለፈውን ውሳኔ ለጊዜው አግዶታል።ውሳኔው የተላለፈው የፓርላማ አባላቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ ካፀደቁ በኋላ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሴኔቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓን ከስልጣን ለማባረር ያሳለፈውን ውሳኔ ለጊዜው አግዶታል።ውሳኔው የተላለፈው የፓርላማ አባላቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሾሙ ካፀደቁ በኋላ ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
👍11❤1
#Update
ዶናልድ ትራምፕ ሶስተኛውን ወላዋይ ግዛት፣ 19 ድምጽ ያላትን የፔንስሌቫኒያ ግዛት አሽንፈዋል። ይህም ማለት ከተቀሩት አራት ወላዋይ ግዛቶች አንዱን ካሸነፉ፣ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።

❤39👍5
#Update
በምስራቅ ኢትዮጵያ የተቋረጠው ኃይል መልሶ ተገናኝቷል!
የድሬዳዋ - ሀረር- ጅግጅጋ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የምስራቅ አንድ ሪጅን የኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ እንደገለፁት ለሀረር፣ ጅግጅጋ እና ለሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል የተቋረጠው የማስተላለፊያ መስመሩ አንዱ ፌዝ በመበጠሱ ምክንያት ነበር።
ችግሩን ለመለየት አስቸጋሪውን የደንገጎን ተራራ በእግር በመጓዝ ፍተሻ መከናወኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የተበጠሰውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመጠገን አገልግሎቱን ዳግም መመለሱን ገልፀዋል።በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትግዕስት ስለጠበቁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

👍28❤3
YeneTube
የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት ማስተካከያ በተደረገ በቀናት ውስጥ የሦስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚቀርብላቸው ምግብ "ጥራት እና መጠን" ቀንሷል በማለት ተቃውሞ አነሱ። ከሁለት ሳምንት በፊት ትምሕርት ሚኒስቴር በምግብ ዋጋ ንረት ምክንያት "የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ በጀት" ላይ ማሻሻያ መደረጉን ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።በዚህም 22 ብር የነበረው የአንድ ተማሪ ዕለታዊ የምግብ በጀት…
#Update
ወደ መቶ ብር ከፍ ያለው የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት የተለየ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም ተባለ
የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 100 ብር ሆነ ማለት ድሮ ተማሪዎች ሲመገቡ ከነበረበት የምግብ አይነት የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት በቀን ከ22 ብር ወደ 100 ብር መሻሻሉን ተከትሎ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ተመኑ ሲያድግ በተቃራኒው ግን የሚቀርበው የምግብ አይነትና መጠን ያነሰ በመሆኑ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡አሐዱም ይሄንን የተማሪዎች ቅሬታ በመያዝ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል።
በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ በሰጡት ምላሽ፤ የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው፣ "የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም" ሲሉ ገልጸዋል።
ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ እንዳልቆዩ የሚገልጹት ዶ/ር ሰሎሞን፤ "ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል" ብለዋል።
አሐዱም "የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ማሻሻያ በቂ ነው ወይ? አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርስ ተመጣጣኝ ነው?" ሲል ዩኒቨርስቲዎችን ጠይቋል።
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ የትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች የቀን ምግብ 22 ብር ቢመደብ፤ ከዛ በላይ ወጪ እንደበረው እና ተቋማቱ ለሌላ ሥራ የሚያገኙትን ገንዘብ ለምገባ የሚያውሉበት ሁናቴ መኖሩን ገልጸዋል።
"ዩንቨርስቲዎች በሚመደው 22 ብር ብቻ ተማሪዎቻቸውን አይመግቡም ነበር" ሲሉ ዶ/ር ሰሎሞን ያነሱትን ሃሳብ ተጋርተዋል።
"አሁን የተሻሻለው በጀት በተወሰነ ደረጃ ችግርን ይቀርፋል ተብሎ የሚጠብቅ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የተደረገው ማሻሻያ ቁጥሩ ትልቅ ቢመስልም ቀድሞ ሲወጣ ከነበረው ወጪ አንጻር ሲታይ አሁንም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በአንጻሩ ሌላው አሐዱ ያነጋገራቸው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ቶሎሶ ዳኒ፤ "አሁን ካለው የዋጋ ንረት አንጻር 22 ብር ተማሪዎችን መመገብ አይችልም ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት መሰረት ወደ መቶ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ የተመደበው በተማሪ 100 ብር በቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ ከነበረው 22 ብር ወደ መቶ ብር ከፍ መደረጉ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ መሆኑን አንስተዋል።
ዶ/ር ሰሎሞን የዩንቨርስቲዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሃሳብ ሲያጠናክሩ፤ ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ እንደነበረ ጠቅሰው፤ "ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር" ሲሉ አክለዋል።
በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ሀላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።
Via Ahadu

👍37👀3👎2❤1😁1
#Update
- ኃፍረት የማይታይባቸው ናቸው በጥቂት ግለሰቦች ጥቅም ሲባል የትግራይ ህዝብ መጎዳት የለበትም
የትግራይ ህዝብ ወደ ባሰ መከራ ለማስገባት ርብርብ ላይ ናቸው።
- ትግራይ ህዝብ ሰላም ነው የሚሻው ድጋሚ ጦርነት አይፈልግም። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲቀባ ጠይቀዋል።
- ይህ ቡድን ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቀን ከለሊት አየደወሉ ስልጣን የሚለምኑ ኃይል ነው።
- የኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት መሻከር የጀመረው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ብኃላ ነው። አላማቸው ትግራይን ከካርታ ላይ ማስወጣት ነው እንዲሁም አንድ አንድ ጀነራሎች ከኤርትራ ጋር ተስማምተው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያስቡ ቡድኖች አሉ ይህ ጤነኛ መንገድ አይደለም።
-

👍20😁15🔥1
YeneTube
Photo
#Update
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በመኖሪያ ቤታቸው ተአቅበው እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወሳኔ አሳለፈ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬ መደበኛ ጉባኤ ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት ውይይት ካደረገ በኋላ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ፦
1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያኗን አባቶች፣ ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።
ቋሚ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ ወስኗል።
2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ ወንሷል።
3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ ወስኗል።
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ እንዲደረግ ወስኗል።
መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

👍98😁25👎15❤4
#Update
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስራ ማስታወቂያ አውጥቷል።
አዲስ ተመራቂዎች ኑ እና አመልክቱ ከነገ ጀምሮ የሚል ማስታወቂያ አውጥቷል።
ይህ ያስቆመው ይሆን ?

😁131👎58👍25🔥3
#Update
የተቋረጠው የኃይል አቅርቦት እየተመለሰ ነው!
ሲስተም ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባደረገው ርብርብ የቴክኒክ ብልሽቱ ተቀርፎ በአብዛኛው አከባቢዎች አገልግሎቱ መመለስ ጀምሯል፡፡
[EEU]

👍7❤6