YeneTube
120K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሸገር የዳቦ ፋብሪካ ከማምረት አቅሙ በግማሽ በመቶ ቀንሶ ዳቦ እያመረተ መሆኑን አስታወቀ።

በተመጣጠነ ዋጋ ዳቦ ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ እንዲችል ታስቦበት ሥራ የጀመረው ይህ ፋብሪካ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ ያመርታል በሚል ነበር፡፡ባለፈው ሰኔ ወር ተመርቆ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ የሚገኘው ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት የታሰበውን ያክል እያመረተ እንደሆነ የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ ቡልቡላ ተጠይቀው ፋብሪካው በሰዓት 80 ሺህ የማምረት አቅም ቢኖርም በአሁኑ ሰዓት እያመረተ ያለው ግን በሰዓት ከ30-35 ሺህ ነው ብለዋል፡፡

ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን 700 ሺህ ገደማ ዳቦ በማምረት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል።የምርት ሂደቱ የታሰበውን ያክል በፍጥነት ያልሄደበት ምክንያት የኮሚሽን ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው መሆኑን ተናግረዋል።በቅርቡም ከውጪ በሚገቡ ባለሙያዎች አማካኝነት ይህንን ሂደት ለማጠናቀቅ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውና ይህ ሲጠናቀቅ ፋብሪካውም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ስራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የሸገር ዳቦ በሚሰራጭባቸው የመሸጫ ሱቆች ከነዋሪዎች ውጪ ዳቦ ቸርቻሪዎች በዝቅተኛ ዋጋ ገዝተው ዋጋ ጨምረው የሚሸጡ ነጋዴዎች እንዳሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም የሰጡ ሸማቾች ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
ቻይና እና የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ የሚገነባውን የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና መሥሪያ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ለመጀመር ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የፈረሙት የቻይና የንግድ ምክትል ምኒስትር ኪያን ኬሚንግ እና የአፍሪካ ኅብረት ማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኤልፋዲል ናቸው።መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና መሥሪያ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 23 ሺሕ 244 ስኩዌር ሜትር ይሸፍናል። ዋና መሥሪያ ቤቱ ሁለት የቢሮ ሕንፃዎች፣ ሁለት የቤተ ሙከራ ሕንፃዎች፣ የድንገተኛ ማዕከል፣ የመረጃ ማዕከል እና ላብራቶሪ ይኖረዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 90,000 ስኩዌር ሜትር ቦታ ለዋና መሥሪያ ቤት ግንባታው አቅርቧል። የኅብረቱ መረጃ እንደሚጠቁመው የሕንፃ ግንባታው 40,000 ስኩዌር ሜትር ላይ ይከናወናል።ግንባታውን ለማስጀመር ስምምነቱ ሲፈረም የአፍሪካ ኅብረት የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኤልፋዲል የአፍሪካ ኅብረት ፕሮጀክቱን በፍጥነት ለማስጨረስ ከቻይና ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።

#DW
@YeneTube @FikerAssefa1
የርብ ወንዝ በመሙላቱ የፎገራና አካባቢው ነዋሪዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ ገጠማቸው።

ከወረታ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ፎገራ አካባቢ ያለው ድልድይ በመሙላቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሎ ውሏል።የዞን አስተዳደሩ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ ከክልሉ መንግስት ጋር በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ የክረምት ዝናቡ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ምክንያት ችግሩን መከላከል አልተቻለም።ከጧቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ ከጎንደር መስመር እንዲሁም ከወረታና ደብረታቦር መስመር የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሉን የገለጹት የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ሀላፌ ኢንስፔክተር ክንዱ እንደገለፁት የርብ ድልድይ በመሙላቱ የአስፓልት መንገዱ በጎር በመሞላቱ ተሳፋሪዎች እየተጉላሉ መሆኑን በመግለፅ በቦታው ተገኝተው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን በመግለጽ ከ500 በላይ ተሽከርካሪዎች ከሁለቱም አቅጣጫ መቆማየውን በመግለጽ በእግራቸው መሻገር የሚችሉ ተሳፋሪዎይች በእግራቸው እንዲያልፍ በማድረግ ትልልቅ መኪኖች በገመድ እየተሳቡ እንዲያልፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።በርካታ የአርሶ አደር ቤቶች በጎርፍ መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ: የደቡብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ያካሄዱት ውይይት ጋር በተያያዘ ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa1
ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ በኦላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈታኝ አይነ ስውራን ተማሪዎች ስልጠና በአዲስ አበባ በመስጠት ላይ ይገኛል።የዩንቨርሲቲ መግቢያ ወይም የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመወሰድ ስልጠኛው ላይ የተሳፉ አይነ ስውራን ተማሪዎችም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከዚህ በፊት ምንም የኮምፒተር እና የቴክኖሎጂ እውቀት ሳይኖረን በ 5 ሳንምት ስልጠና ብቻ ብሄራዊ ፈተና በኦላይን ተፈተኑ መባሉ ተገቢ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ምንም አይነት የቴክኖሎጂ እና የኮምፒውተር እውቀት የሌለን አይነ ስውራን ተማሪዎች በወረርሽኙ ምክንያት በኦንላይን እንድንፈተን መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ፣ በበኩላቸው አይነ ስውራን ተማሪዎች በሚኖራቸው የ5 ሳንምት የስልጠና ቆይታ ለፈተና የሚያበቃ መሰረታዊ የኮምፒተር ስልጠና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ስልጠናው አይነ ስውራን ተማሪዎች በራሳቸው ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፈተናውን እንዲወስዱ ለማስቻል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡ተፈታኝ ተማሪዎቹ ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ቅሬታ ካላቸው ተጨማሪ ስልጠና ወይም ሌላ መፍትሔዎችን እንደሚፈልጉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በ2012 የትምህርት ዘመን የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 400 የሚሆኑት አይነ ስውራን ተማሪዎች ናቸው። ሚኒስቴሩም ለእነዚህ 400 ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን መወሰድ የሚያስችላቸውን ስልጠና ለመስጠት ለሁሉም ተማሪዎች ጥሪ ቢያደርግም 250 ተማሪዎች ብቻ ስልጠና ላይ ተገኝተዋል።በመሆኑም በ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ አይነ ስውራን ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መፈተን የሚያስችላቸውን ስልጠና እንዲወስዱ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በማየት 12 ቀን ፈቅዶ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።ሁከት እና ብጥብጥ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተሰማራው የምርመራ ቡድን በርካታ የሰው ሞት እና የንብረት ውድመት የተመለከተ መረጃ መላኩንም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።አቶ ጃዋር በበኩሉ የተከሰተው ወንጀል እሱን እንደማይመለከት እና ሚዲያዎች ችሎቱን እንዳይዘግቡ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።ተጠርጣሪው አቶ ጃዋር ያቆማቸው 9 ጠበቆች የምርመራ ሥራው አዲስ አለመሆኑንና ፖሊስ የጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ እንዲሆን ወይም ጥቂት ቀን እንዲሆንም ጠይቀዋል።ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ቀደም ሲል በተሰጠው 13 ቀናት ውስጥ ምርመራውን በአግባቡ በማከናወኑ እና ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ አይቶ 12 ቀን በመፍቀድ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#ETV
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 610 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰአታት ለ7760 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 610 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡159 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 15,810፣ ያገገሙት 6685፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 253 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa1
የዘንድሮው ሃጅ ተጀመረ!

ከእስልምና አበይት አዕማደ ሥርዓት አንዱ የሆነው ሃጅ ዛሬ በሜካ፤ ሳውዲ አረብያ ተጀምሯል።የኮሮናቫይረስ መዛመት ባሳደረው ሥጋት ምክንያት ዘንድሮ የሃጅና ዑምራ ተጓዦች ቁጥር ከወትሮ ያነሰ እንደሆነ ተነግሯል። በእስልምና እምነት አንድ ሙስሊም በህይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሜካ ሂዶ ሥርዓቱን እንዲያደርስና አረፋን ወይም ኢድ አል አድሃን እንዲያከብር የሚጠበቅበት ሲሆን በዚሁ መሠረትም በየዓመቱ ከሁለት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ምዕመናን ወደ ሜካ ይሄዳሉ። በዚህ ዓመት ግን በኮቪድ 19 ምክንያት ሃገር አቋራጭ መንገደኞች እንዳይገቡ ሳዑዲ አረቢያ በማገዷ በሥርዓቱ ላይና ለኢዱም የሚገኙት አንድ ሺህ የሚሆኑ የሃገሪቱ ተወላጆችና ከሣምንታት በፊት የተመረጡ የውጭ ተወላጅ ነዋሪዎች መሆናቸው ታውቋል።

በበአሉ ላይ የሚገኙት ዕድሜአቸው ከሃያ እስከ ዓመት ባለው ክልል ውስጥ ያሉ ሲሆኑ ወደ ሜካ ከመሄዳቸው በፊት የኮሮናቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል። የሃጅ ሥርዓቱ ከመጀመሩ በፊትም፣ በየሆቴሎቻቸው ተወስነው እንዲቆዩ ተደርጓል።ለአምስት ቀናት የሚዘልቀው ሥርዓትና ኢድ በኋላም ለአንድ ሣምንት ያህል ተለይተው ወይም ኳራንቲን ላይ ሆነው መቆየት ይጠበቅባቸዋል።ሳውዲ አረብያ ከሁለት መቶ ሰባ ሺህ በላይ የኮቪድ 19 ህሙማን እንዳሏትና ወደ 2,800 የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሰው በወረርሽኙ ምክንያት እንደሞተባት ታውቋል።

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
ለሽብርተኞች መረጃ በማቀበል የተጠረጠሩት የሕወሃት አባላት ተወልደ ገ/ጻዲቅ እና ተስፋለም ይኸድጎ ትናንት ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደቀረቡ የዋዜማ ሪፖርተሮች ከሥፍራው ዘግበዋል፡፡ተስፋለም በሚመሩት የሕግ ጥናት እና ምርምር ማዕከል የሚሰሩ ሁለት ሹፌሮችም አብረው ቀርበዋል፡፡ ፖሊስ በተስፋለም መኖሪያ ቤት ያገኘሁት ክላሽንኮቭ መሳሪያ በፌደራል ፖሊስም ሆነ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዕውቅና የለውም- ብሏል ለችሎቱ፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ እና የጀመራቸውን ምርመራዎች ለማጠናቀቅ 14 ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፤ ችሎቱ ብይን ለመስጠጥ ለነገ ቀጥሯል፡፡

#Wazema
@YeneTube @FikerAssefa1
በዛሬው የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ "መንግስት በቅርቡ የተከሰተውን ሁከትና ግርግር ምክንያት በማድረግ የፓርቲ አመራሮቻችንን እያሰረብን ነው" ሲሉም የተለያዩ ፓርቲ ተወካዮች ላነሱት ሀሳብ
ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ምላሽ በሁከትና ግርግር እጃቸው ያለበት የገዥውም ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላቶችን በህግ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። በቅርቡ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ በርካታ የብልጽግና አመራሮች መታሰራቸውን ለአብነት በማንሳት።ሽማግሌዎችን አደራጅቶ በመላክ በህግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎችን ለማስፈታት የሚደረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል።ህግን እንደፈለጉ የሚጥሱ ሰዎችን በሽምግልና ስም የማስፈታት ስልጣን የለኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሂደቱ በራሱ የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት ልምምድን እንደሚያቀጭጭው አብራርተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa1
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተከተለው አመጽና ሁከት ተጠርጥረው የታሰሩት አቶ እስክንድር ነጋ ከመንግሥትና ለመንግሥት ቅርበት ካላቸው መገናኛ ብዙሀን ውጭ ሌሎች ጋዜጠኞች ችሎት እንዳይገቡ መከልከሉ ተገቢ እንዳይደለ ዛሬ ላቀረቡት አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ የቀጠሮ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ችሎቱ ለመገናኛ ብዙሀን ክፍት እንደሆነ በመግለጽ ፖሊስ እንዳይከለክል ማዘዙን የእስክንድር ጠበቃ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ችሎቱ ፣ ፖሊስ በአቶ እስክንድር ጉዳይ ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ አድርጎ 9 ቀናት ፈቅዷል።ለነሐሴ አንድ 2012 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#DW
@YeneTube @FFikerAssefa1
በትግራይ በሚካሄደው ምርጫ የባይቶና ፓርቲ እንደሚሳተፍ ገለፀ!

በትግራይ ክልል ለሚካሄድ ምርጫ ፍፁም የሚያሰራ ሁኔታ ባይኖርም እንሳተፋለን ሲል በክልሉ የሚንቀሳቀስ የባይቶና ፓርቲ አስታወቀ።ፓርቲው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት በክልሉ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም ከማጠልሸትና ከማደናቀፍ ወጥቶ በቀረው የምርጫ ግዜ የፖለቲካ ምህዳሩ ለማስፋት ሊሰራ ይገባል ብሏል።

#VoA
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ 17ኛው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በአሶሳ ተከፈተ!

የኢፌዴሪ ጉሙሩክ ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ የከፈተው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በይፋ ስታ ጀመረ።ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የገቢዎች ሚንስትር አቶ ላቀ አያሌው እችና የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በትናንትናው ዕለት በይፋ ሥራ የጀመረው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በኢትዮጵያ 17ኛው የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ሆኖ መከፈቱ እንደተገለፀም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

#FBC
@YeneTube @FikerAssefa1
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልእክተኛ ተቀብለው አነጋገሩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልእክተኛ የሆኑትን፣ ኒሃል ዴንግ ኒሃልን ዛሬ ከሰዓት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አመለከተ። ውይይታቸውም በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በተለይም ደግሞ ከኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ሰላም እና ደህንነት አኳያ በመተባበር ላይ፣ እንዲሁም ቀጣናዊ የትስስር ጥረቶች ላይ አተኩሯል።

#Walta
@YeneTube @FikerAssefa1
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ተጨማሪ አራት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ተጨማሪ የኮቪድ ምርመራ ማዕከላት ለመክፈት ማሰቡን ቢሮው አስታውቋል።የቢሮው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዋሌ በላይነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የአማራ ክልል በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ከሆኑ ክልሎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።እስካሁንም በሰምንት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከላት እስከ ትናንት ድረስ 28 ሺህ 621 ናሙናዎች የመረመረ ሲሆን 504 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

በኮሮና ከተጠቁ 504 ሰዎች ወስጥም 398 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ የአምሰት ሰዎች ህይወት ማለፉን ሃላፊው ተናግረዋል።በክልሉ የውጭ አገራት የጉዞ ታሪክ እና በቫይረሱ ከተጠቁ ሰዎች ጋር ንኪኪ ያላቸው ሰዎች ቁጥር መጨመር እንዳለ ሆኖ የቫይረሱ ስርጭት በማህበረሰብ ደረጃ እየተስፋፋ በመምጣቱ ተጨማሪ የኮሮና ምርመራ ማዕከላትን ማቋቋም የግድ ማስፈለጉንም አቶ ዋለ ገልጸዋል። በዚህም በደብረ ማርቆስ፣ደብረታቦር እና መተማ አዲስ የምርመራ ማዕከላትን ለማቋቋም መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ላይ መሆናቸውን ነግረውናል።

በመቀጠልም በከሚሴ ከተማ አራተኛ የኮቪድ ምርመራ ማዕከል ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩንም አቶ ዋሌ ነግረውናል። በኢትዮጵያ ዕለታዊ የኮቪድ ናሙና የመመርመር አቅምን በ52 የምርመራ ማዕከላት 13 ሺህ ለማድረስ እየተሰራ ሲሆን አሁን ላይ ከ10 ሺህ በታች ነው።በአማራ ክልል ደግሞ በእያንዳንዱ የኮቪድ መመርመሪያ ማዕከላት በየዕለቱ 300 ናሙናዎችን ለመመርመር ቢታቀድም አሁን ላይ ግን ከ100 ናሙናዎች በላይ ማለፍ አለመቻሉን ከክልሉ ጤና ቢሮ ተሰምቷል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1
ሰሞኑን በኮንሶ እና በአሌ ድንበር ላይ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ21 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደረሰ!

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ትናንት በሰጡት መግለጫ፥ ሰሞኑን በኮንሶ እና በአሌ ድንበር ላይ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ21 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል ብለዋል።የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን የማጣራት ስራ እየሰራ ሲሆን፥ ለጸጥታው መደፍረስ ምክንያት የሆኑ አካላትን ለህግ የማቅረብ ስራ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።እስካሁንም በችግሩ ተሳታፊ ናቸው በሚል የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ላይ ሲሆኑ፥ ቀሪ ተጠርጣሪዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa1
ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝተናል ብለዋል።ከትርፉ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግብር ከፍያለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 318 ነጥብ 4 ሚሊየን እዳንም ከፍያለሁ ብሏል።እንደ ወ/ት ፍሬህይወት የተገኘው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ31 ነጥብ 4 መቶ ብልጫ አለው። በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ደርሷልም ብለዋል።የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.5 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 23.8 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ደንበኞች ብዛት 212.2 ሺ እንዲሁም የመደበኛ ስልክ 980 ሺ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa1