YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 88ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሃገራችን ወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።

ምክር ቤቱ በሃገራችን የተቃጡ፣ የከሸፉ እና ጉዳት ያደረሱ የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶችን በዝርዝር ዳስሷል።በአሁኑ ወቅት ያሉ ወቅታዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይም በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በቀጣይ ስጋቶቹን በተቀናጀ መልኩ መግታት የሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይቷል።በዚህም የሃገርን ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት ቁርጠኝነት እንደሚሰራ በመግለፅ ይህን እውን ለማድረግም መከላከያን ጨምሮ ሁሉም የደህንነትና ጸጥታ ተቋማት እስካሁን እያደረጉት ያለውን ጥረትና መስዋዕትነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ምክር ቤቱ አረጋግጧል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ሰበር ዜና!! ኢትዮጵያ ነባሮቹን የብር ኖቶች ቀየረች! ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ…
የኢትዮጵያ መንግሥት አዳዲስ የደህንነት ገጽታዎች እና ሌሎችም መለያዎች የተካተቱባቸው የገንዘብ ዓይነቶችን ለግብይት እንደሚያውል በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

ነባሮቹ የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ የሚተኩ ይሆናል። አዲስ የ200 ብር ገንዘብም በተጨማሪነት ለግልጋሎት ይውላል።የ5 ብር ገንዘብ ባለበት ቀጥሎ፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል። ይህ የገንዘብ ቅያሪ መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲሁም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ የሚዘዋወረውን ገንዘብ ለመሰብሰብ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ የታለመ ነው።የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም ያግዛል።በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት ይገኛል።

የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት የሚተገበር ይሆናል። በገንዘብ ቅያሬው ሂደት የጸጥታ ማስከበር አካላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ያስፈጽማሉ። ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ፣ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።የክልል መንግሥታትም ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑም ይጠበቃል።ኢትዮጵያ ገንዘቧን የሚወክል ምልክት እንዳልነበራት ይታወቃል።በቅርቡ ለብር መለያ የሚሆን አዲስ ምልክት ተዘጋጅቶ በጥቅም ላይ ይውላል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 89ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን፥ በዚህም ከዚህ ቀደም በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር የነበሩና በብረታብረት፣ በአውቶሞቲቭ፣ በእርሻ መሳሪያዎች ምርት፣ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪና ፕላንት እንዲሁም የፖሊመር ምርት ዘርፎች የተሰማሩትን ተቋማት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር በማደራጀት የሃብት አጠቃቀሙን ውጤታማ ለማድረግ እና ወደ አትራፊነት እንዲሸጋገር ለማስቻል የማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ለውሳኔ ቀርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ የተሰጡ ግብአቶች ተካተው ረቂቅ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ፌዴሬኝን መካከል የኒኩሌር ሀይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የተደረገ የትብብር ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ሁለቱ ሀገራት የ1968ቱ የኒኩሌር መሳሪያዎች እሽቅድምድምን የሚከለክለውን ዓለም አቀፍ ስምምነት እና ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የገቡትን ስምምነት ባከበረ መልኩ የኒኩሌር ኢነርጂን ለሰላማዊ ዓላማዎች ጥቅም ላይ ማዋላቸው በሀገራቱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን በመግለፅ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጁን አዘጋጅቶ አቅርቧል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

#PMOEthiopia
Photo: EPA
@YeneTube @FikerAssefa
"እስካሁን 69 ወረዳዎች የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። 12 ያህል መለስተኛ ከተማዎች የሶላር ኃይል አገልግሎት ተጀምሮባቸዋል። ከመደበኛው የኃይል ማመንጫ አሠራር በተለየ፣ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የኃይል አቅርቦትን ማስፋፋት እንቀጥላለን።"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
"ኢትዮጵያ በፈጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት። ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም። "

"ማንም ገዝቶን አያውቅም።ወደፊትም ማንም አይገዛንም።ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም። ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም"

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በትናንትናው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛቻ አዘል ንግግር ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) 1495ኛው ልደት በዓል በተመለከተ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ!

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ከዚህ በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል:-

1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል
3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
👆👆

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች:

-አቶ ደመቀ መኮንን ም/ል ጠ/ሚርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
-ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም
-ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ሀይሎች ም/ል ኢታማዦር ሹም
-አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
-ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ወቅት ከዓመታት በፊት አባይ የተባለ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያለው የመገናኛ ብዙሀን ተቋም መኖሩን ጠቅሰዋል።የተጠቀሰው ተቋም በዩቲዩብ ሥራውን በመከወን ላይ ከሚገኘው እና በቅርቡ የቴሌቪዥን ስርጭት ከሚጀምረው #አባይ_ሚዲያ ጋር አንድነት እንደሌለውና ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ እና ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እየተወያዩ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በተገኙበት የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ውይይት እያካሄዱ ነው።ከውይይቱ አስቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የምርጫ ተዋናዮች ሚና እና የተለያዩ አገሮች የምርጫ ስርዓቶችን የሚመለከት የውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ 16 ምሁራንን የያዘ ነው።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 94ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የነገውን የምርጫ ቀን አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ከብሔራዊ ምርጫ ደህንነት ስትራቴጂ ማዘዣ ጋር ተወያይተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማዕከላዊ ዕዝ የሁኔታ ክትትል ክፍል ውስጥ ይፋ የተደረገው የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት አገልግሎት የምርጫ ደህንነት መድረክ በምርጫ ደህንነት ዘርፍ የተከናወነውን ዝግጁነት አጉልቶ ያሳያል። የደህንነቱ ዝግጁነት በሁሉም የሀገሪቱ ማእዘናት ላይ አካላዊ ኃይል ማሰማራትን እንዲሁም የሳይበር ደህንነት ማሻሻያዎችን የተመለከቱ ስጋቶችን ማክሸፍን ያጠቃልላል።በመላው የፌዴራል እና የክልል ማዘዣ ጣቢያዎች ባሉ የመረጃ መጋራት መሳሪያዎች፣ የሳተላይት ቁጥጥር ስርዓቶች እና የድሮን ቴክኖሎጂ ለዚሁ ዝግጅት ተሰማርተዋል። በመግለጫው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን አዲስ አካሄድና ከብሔራዊ ቁልፍ ተግባራት ቀድሞ ብሔራዊ ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ የተፈጠረውን አቅም ተመልክተዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa