አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ሐምሌ 20 ቀን ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!
በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁከት በማደራጀትና በገንዘብ በመርዳት ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተነገራቸው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራር አቶ ልደቱ አያሌው፣ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ታወቀ፡፡ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተለይ በቢሾፍቱ ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ፣ አቶ ልደቱም ሁከቱን በገንዘብ በመደገፍ መጠርጠራቸውን እንደ ነገሯቸው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተናግረዋል፡፡
አቶ ልደቱ በቢሾፍቱ የነበረውን ሁከት በገንዘብ ከመርዳታቸው ባለፈ፣ በሁከቱ ስለተፈጸመው የወንጀል ድርጊትና ስለደረሰው የጉዳት ዓይነት እንዳልተገለጸላቸው የተናገሩት አቶ አዳነ፣ አቶ ልደቱ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉበት ሒደትም ተናግረዋል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ደውሎላቸው እንደሚፈለጉ ነግሯቸው ወደ ፌዴራል ፖሊስ መሄዳቸውን እንደ ነገሯቸው አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡በቢሮአቸው የጠበቋቸው የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተጻፈ የመያዥያ ደብዳቤ እንዳሳዩዋቸው፣ ምክንያቱ ደግሞ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል መጠርጠራቸው መሆኑን ነግረዋቸው ወደ ቢሾፍቱ እየወሰዷቸው እንደሆነ፣ በስልክ እንደገለጹላቸው አስታውቀዋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት የመያዥያ ትዕዛዝ የወሰደው፣ ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. መሆኑንም አቶ አዳነ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡አቶ ልደቱ ለበርካታ ዓመታት መኖሪያቸው ከነበረው አዲስ አበባ ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ቢሾፍቱ በመቀየር፣ አዲስ በገነቡበት ቤት እየኖሩ እንደነበርም አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡ የድምፃዊ ሃጫሉ ሞትን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሁከት ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቤታቸውን ፖሊስ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦ ሲጠብቅ ካደረ በኋላ፣ በማግሥቱ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ‹‹ለደኅንነትህ›› በማለት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳመጣቸውም አስረድተዋል፡፡አቶ ልደቱ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባና በሰሜን ወሎ ላሊበላ ከተማ ልዩ መጠሪያው ‹‹መካነ ልዕልት›› በሚባለው ሥፍራ፣ ከ12 ጓደኞቻቸው ጋር እየገነቡት ያለውን የሪዞርት ፕሮጀክት ለማየት ሄደው እዚያው ቆይተው ሐምሌ 11 ቀን 2012 ዓ.ም. መመለሳቸውን አቶ አዳነ ገልጸዋል፡፡
#Reporter
@YeneTube @FikerAssefa1

የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ 'የመተላለፍ ዕድሉ ዝቅተኛ ነው!'
የኮሮናቫይረስ ላለባቸው እናቶች አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረገ በወሊድ ጊዜ ወደ ህጻናቱ የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።አሜሪካ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ሆስፒታሎች ኮሮናቫይረስ ካለባቸው እናቶች ከተወለዱ 120 ህጻናት ውስጥ አንዳቸውም በበሽታው አለመያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤት የተገኘው ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ ባለው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከተወለዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አንዳንዶቹ የእናታቸውን ጡት የመጥባት እድል ካገኙና በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከቆዩ በኋላም ጭምር ነው።ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚሉት የተገኘው ውጤት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ተጨማሪ ሰፋ ያለ ሙከራዎች ማድረግ ያስፈልጋል።
በእርግዝናና በጡት ማጥባት ወቅት የበሽታውን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታን በተመለከተ ያለው መረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚሰጠው ምክርም የተለያየ እንዲሆን አድርጎታል።የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች እናቶች ጡት ማጥባት የሚፈልጉ ከሆነ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ተደርጎላቸው ልጆቻቸውን ጡት ማጥባትም ሆነ አንድ ክፍል ውስጥ መሆን ይችላሉ ብለዋል።ባለሙያዎቹም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚሉት በኮሮናቫይረስ የመያዝ ስጋት የበለጠ ጡት ማጥባት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል የቫይረሱን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድልን ለመቀነስ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ለተወሰነ ጊዜ ከእናታቸው ተለይተው እንዲቆዩ የማድረግ ሃሳብን ተግባራዊ ለማድረግ እያሰበ ነው።ኮሮናቫይረስ ያለባት እናት ከወለደችው ልጅ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ የሚደረግና ጡት እንድታጠባ የሚፈቀድላት ከሆነ፤ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንድትጠቀምና በተደጋጋሚ እጇን መታጠብ እንደሚኖርባት በጥናቱ ተመልክቷል።ጥናቱን የመሩት ዶክተር ክርስቲን ሳልቫቶሬ እንዳሉት "ጥናታችን ወረርሽኙ ያለባቸው እመጫት እናቶች ቫይረሱን ወደ ልጃቸው የማስተላለፍ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።ነገር ግን ሁኔታውን የበለጠ ለመረዳት አሁንም ሰፋ ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ ቅኝትን የመሩት ፕሮፌሰር ማሪያን ናይት እንደገለጹት ጥናቱ በአገሪቱ ያለውን መመሪያ የሚደግፍና የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።ጨምረውም "በዩናይትድ ኪንግደም ከአንድ ሺህ በላይ ኮቪድ-19 ያለባቸው እናቶች የወለዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ1 እስከ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ላይ ብቻ ነው ቫይረሱ የተገኘው። በሽታውም በህጻናቱ ላይ የከፋ ህመምን አላስከተለም።"በአሜሪካ የተደረገው አነስ ያለ ጥናትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል መጠቀመን የመሰሉ ቀላል የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታ እንዳይከሰት ማድረግ መቻሉን ፕሮፌሰሯ ጠቅሰዋል።የጥናቱ ውጤት የህጻናትና የአዋቂዎች ጤና ጉዳይ ላይ በሚያተኩረው የላንሴት የህክምና ሙያዊ መጽሔት ላይ ታትሟል።
#BBC

በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ!
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የትራፊክ አደጋን በ17 በመቶ መቀነሱን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።አዲስ አበባ- አዳማ የፍጥነት መንገድ መግቢያ ላይ “የትራፊክ አደጋ ሰለባዎችን እያሰብን አረንጓዴ አሻራችንን እናኑር!” በሚል መሪ ቃል ደም የመለገስ የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሐ ግብር ተከናውኗል።በመርሐ ግብሩ የትራፊክ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት በ2011 በጀት ዓመት የተመዘገበው 4ሺህ 597 ሞት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ 3ሺህ 400 ቀንሷል ብለዋል።
#ENA

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡን የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ገዳ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ መሰማራቱን ከፖሊስ መስማታቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት መከበብን ለቢቢሲ ያረጋገጡት አቶ ገዳ የታጠቁ ኃይሎች በመኖሪያ ቤቱ ዙሪያ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።ኃላፊው፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትና መግባት እንዳልቻሉና ወደ ውጪ የሚወጡ ከሆነም በጸጥታ ኃይሎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ስጋተቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የግንባሩ ለቀ መንበር አቶ ዳውድ ከሦስት ቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ከአንድ ቀን በኋላ መፈታታቸውን አቶ ገዳ ገልጸዋል።"ዋና ሊቀመንበራችን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት።እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው የዕለተ ዕለት ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም" ሲሉ አቶ ዳውድ ከቤታቸው መውጣት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።አቶ ገዳ እንደሚሉት አቶ ዳውድ ብቻ ሳይሆኑ በቤታቸው ውስጥ ያሉ የቤተሰባቸው አባላትም ከመኖሪያ ግቢው መውጣትናም ሆነ ከውጪ መግባት ተከልክለዋል።
አቶ ገዳ ካሉት የእንቅስቃሴ ገደብ በተጨማሪ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ስልክ ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ እየሠራ አይደለም።የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት ለምን እንደተከበበ የሚያውቁት ነገር አለ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ገዳ፤ ፖሊስ ይህን ያደረገው ለእሳቸው [አቶ ዳውድ] ደኅንነት ሲባል እንደሆነ ተነግሮኛል ይላሉ።ይሁን እንጂ "ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ እየከለከሉ ደኅንነት ለመጠበቅ አይመስልም" ይላሉ። "የአቶ ዳውድ ስልክ ስለማይሰራ ከራሳቸው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልቻልንም" ሲሉ ከሊቀመንበሩ ጋር መገናኘት አዳጋች እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
ቢቢሲም ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ የሞባይል ስልክ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ በተደጋጋሚ በመደወል ሊያገኛቸው ጥረት ባደረገበት ጊዜ ማግኘት እንደማይቻል እንዲሁም የኔትወርክ መጨናነቅ እንዳለ መልዕክት ብቻ ነበር የሚሰማው።ሁኔታውን ለማጣራት ቢቢሲ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ የተየቀ ሲሆን እሳቸውም ስለጉዳዩ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላትም በእስር ላይ ይገኛሉ።ከእነሱም መካከል የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቶ ሚካኤል ቦረን፣ አቶ ኬነሳ አያና፣ የፓርቲው አማካሪ ዶክተር ሽጉጥ ገለታና ኮሎኔል ገመቹ አያና በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቀደም ሲል ፓርቲው አሳውቋል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰአታት ለ9527 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 720 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡250 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 13,968፣ ያገገሙት 6216፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 223 ደርሷል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባ ጉለሌ በሚገኘው ጽ/ቤቱ እየተደረገ ያለው ስብሰባ ከግንባሩ መሪም ሆነ ከግንባሩ ጉባዔ እውቅና ውጭ መሆኑን አንድ የግንባሩ አመራር አባል ገለጹ።
የዛሬው የጉለሌ ስብሰባ በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራ እና ከአርባ የጉሚ ሰባ የኮሚቴ አባላት አስራ አንዱን እንዲሁም ከጉሚ ሸኔ አባላት ደግሞ አምስቱን ብቻ በማሳተፍ አስራ ስድስት ሰዎች ብቻ እየተሳተፉበት መሆኑንንም የግንባሩ የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቴ ዑርጌሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እየተመራ ነው የተባለው ይኸው ቡድን የግንባሩን ሊቀመንበር ጨምሮ ዋነኞቹ የግንባሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሌሉበት የሚያደርገው ውይይት እና የሚወስናቸው ውሳኔዎች በእስር ላይ የሚገኙትን የግንባሩን አመራሮች የከእስር የሚያስለቅቅ እስካልሆነ እና አመራር ለመቀየር የሚደረግ ጥረት ከሆነ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።የቡድኑ አባላት ስብሰባውን ለማካሄድ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታግዘው ወደ ጽህፈት ቤቱ መምጣታቸው መንግስት ግንባሩን ለመቆጣጠር በሚያመቸው መንገድ እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።
«የፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ከበቀደም ጀምረው ያንን አካባቢ ከበው ነበር። ዛሬ ደግሞ የጽ/ቤት ጠባቂያችንን በግዴታ አስከፍተው ከመንግሥት ነው የተላክነው እዚህ ስብሰባ እንድናደርግ ተፈቅዶልናል።በሰላም ጉዳይ ላይም አብረን እንሰራለን ከፍታችሁ አስገቧቸው ብለው ጠባቂዎቻችንን አስገድደው አስገብተዋቸው አሁንስብሰባ እያደረጉ ነው።»የግንባሩ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖርያ ቤታቸው እንዳይወጡ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ጥበቃ ስር መውደቃቸውንም አቶ በቴ ተናግረዋል።ቀደም ሲል የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎም ሆነ ከዚያ በፊት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው የግንባሩ የስራ አስፈጻሚም ሆነ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የት እንደታሰሩ እና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ እንማይታወቅ አቶ በቴ አስረድተዋል።
«እነዚህ አመራሮች ታሰሩ እንጂ የታሰሩበት ቦታ ፣ ለምን እንደታሰሩ ፣ፍርድ ቤት መቼ እንደሚቀርቡ የሚታወቅ ነገር የለም። ቤተሰቦቻቸውም ሊጠይቋቸው አልቻሉም። በዚህም እኛም እንደ ድርጅት እነዚህን ሰዎች ስናፈላልግ ነበር። ለምን ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ የተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎችን ስናስስ ነበር። የፌዴራል፣ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፖሊስን ብንጠይቅም ልናገናቸው አልቻልንም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አጠቃላይ ጉባዔውን ሊያካሂድ ከአራት እስከ አምስት ወራት ቀርተውት ነበር ያሉት አቶ በቴ አሁን በጥቂት ሰዎች አማካኝነት የሚካሔደው ስብሰባ አላማው እና ግቡ እንደማይታወቅም ገልጸዋል።የግንባሩን ቀጣይ አቅጣጫ ለመናገር ግን ከስብሰባው በኋላ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ይወስናሉ ሲሉም አቶ በቴ ዑርጌሳ ተናግረዋል።
#DW

ጠ/ ሚ ዐቢይ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሠራ እና የሀዩንዳይ ኩባንያ አካል በሆነው ማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ የተገጣጠመች የመጀመሪያ መኪና በስጦታነት ተበረከተላቸው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀዩንዳይ ፕሬዚዳንት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የመገጣጠም ሥራ ተጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሠራውን እና የካርበን ልቀት የማያስከትለውን መኪና በተቀበሉበት ወቅት፣ ይህን የመሳሰሉ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት የሚያስገኙ ሥራዎች በሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለአረንጓዴ ልምላሜ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።መኪናውን የኃይል ማደያ ሳያስፈልግ በየትኛውም ቦታ ባትሪውን መሙላት እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
#FBC

በያዝነው ዓመት በኮቪድ-19 ምክንያት በወባ በሽታ የሚከሰት ሞት በዕጥፍ ሊጨምር ይችላል-የአለም ጤና ድርጅት
በአፍሪካ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመቆጣጠር ጥረት በሚያደርግበት በአሁኑ ወቅት በወባ በሽታ የሚከሰት የሞት መጠን እየጨመረ እንደሆነ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡በተለይ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት በአህጉሪቱ በወረርሺኙ ሳቢያ ከወባ በሽታ ጋር ተያያዥነት ያለው የሞት መጠን ከእጥፍ በላይ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡በወረርሺኙ ምክንያት በአለም አቀፍ ደረጃ የወባ በሽታን ለማከምና ለመከላከል የሚረዱ ሰፋፊ መርሃ-ግብሮች መዘጋታቸው በሽታው የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቆጣጠር አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ተነግሯል፡፡ለአብነትም በኬንያ በወባ በሽታ የተያዙ ታማሚዎች በኮሮና ቫይረስ እጠቃለሁ በሚል ፍርሃት ወደ ጤና ጣቢያዎች ለህክምና እንደማይመጡም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦አልጃዚራ/ETV

በኮሮናቫይረስ መያዙ የተጠረጠረው የመጀመሪያው ሰሜን ኮሪያዊ ነጻ መሆንኑን በምርመራ ማረጋገጧን ደቡብ ኮሪያ ገለፀች።
ግለሰቡ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሦስት ዓመታት በፊት መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ግን ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ነበር።ግለሰቡ ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተሻገረው በደቡባዊ ደሴቲ አካባቢ በሚገኝ የቱቦ ማስተላለፊያ ውስጥ በመሹለከለክና በመዋኘት ነበር።ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ-19 የተጠረጠረ ሰው ማግኘቷን አሳውቃ ነበር።

አቶ ልደቱ አያሌው ለተጨማሪ 14 ቀን በፖሊስ ቁጥጥር ስር በማረሚያ እንዲቆዩ ተወሰነ።
የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዛሬ ረፋዱን በነበረው የችሎት ውሎው፤ የኦሮሚያ ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ምርመራ ለማካሄድ የጠየቀውን የ14 ቀናት ጊዜን ፈቀደ።ፖሊስ "ሰኔ 23 እና 24 በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከት በማስተባበር እና በገንዘብ በመደገፍ አቶ ልደቱን ጠርጥሬያችኋለሁ" ሲል ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።ባለፈው አርብ ሐምሌ 17፤ 2012 በአዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ልደቱ በዚያኑ ቀን መኖሪያቸው ወደሚገኝበት ቢሾፍቱ ከተማ ተወስደዋል።ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው አስቀድሞ ያሉትን ሁለት ቀናት በእስር ያሳለፉት በከተማይቱ በሚገኝ ሶስተኛ ተብሎ በሚታወቀው የፖሊስ ጣቢያ ውስጥ መሆኑን አባል የሆኑበት የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ተናግረዋል።
Via Ethiopia Insider

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ሊቀመንበር አብድርሃማን መህዲ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ኦመር፣ የሶማሊ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በተገኙበት የቁርስ ግብዣና ውይይት ተካሂዷል። በዚህም የክልሉን ሰላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ በጋራ ለመስራት እንዲሁም ከሁለቱ ፓርቲዎች የተወጣጣው የጋራ ኮሚቴ የክልሉን ሰላምና ልማት ለማጠናከር እንደሚሰራ መገለጹን ኦብነግ በይፋዊ የትዊተር አካውንቱ አስፍሯል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
ባለፈው በጀት ዓመት ሕግን በማስከበር በኩል አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የክልሉን 2012 በጀት ዓመት ሪፖርት በምክር ቤቱ 5ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ጊዜ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ለክልሉ ሰላምና ጸጥታ ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል።
በክልሉ ሰላም እንዳይኖር በማኅበራዊ ሚዲያ ሲለቀቁ የነበሩ የሀሰት ትርክቶች አሉታዊ ሚና እንደነበራቸውም ጠቁመዋል። በጎንደር ከተማም ከመንግስት የጸጥታ መዋቅር ውጭ በብርጌድና በሻለቃ በማደራጀት ሰው በማገትና ሃብትና ንብረት ዘረፋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ቡድኖችን ስርአት ለማስያዝ መሠራቱን አብራርተዋል። በህገ ወጥ አደረጃጀት ተደራጅተው ከነበሩት ውስጥ 215 በምኅረት፣ 405 ሰላማዊ በሆነ መንገድ እጅ እንዲሰጡ፣ ፈቃደኛ ያልነበሩ 686 ሰዎች ደግሞ በኃይል እጅ እንዲሰጡ በማድረግ ሕግና ስርአት የማስከበር ሥራ ተሠርቷል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።
ትህነግ በጸብ አጫሪነት ባህሪው እንደገፋበትና እንቅስቃሴውን ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚያሻም ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ተናግረዋል።
#AMMA

ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን መጠቀም ጀመረች!
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ እንዳደረገው ድርጅቱ የታጁራ ወደብን በይፋ መጠቀም ጀምሪያለው ብሏል፡፡የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት ወደቡ ከተገነባ ባኋላ ላለፉት 3 አመት አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቷል ሆኖም ባሳለፍነው ሳምንት የመጀመሪያዋ መርከብ የኢትዮጵያን ጭነት ይዛ በወደቡ መህልቋን መጧሏን እና የያዘችውንም የድንጋይ ከሰል ጭነት በጥሩ ሁኔታ እያራገፈች ነው ብለዋል፡፡
ወደቡ በዋናነት በአፋር ክልል ለሚመረተው የፖታሽ ማእድን መውጫነት የተገነባ ቢሆንም የፖታሽ ምርቱ እስካሁን መመረት እንዳልጀመረ ይታወሳል፡፡ሆኖም ወደቡ ለጥቅል ጭነት/ general cargo እንቅስቃሴ ማገልገል ቢችልም በጅቡቲ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ከ 3 አመት በፊት የተገነባው ወደብ ወደስራ መግባት ሳይችል ቆይቶ ነበር፡፡ሆኖም ባለፈው ህዳር 120 ኪ.ሜ የሚረዝመው እና ታጁራን ከ ኢትዮጵያ ድንበር በበልሆ በኩል የሚያገናኘው የመንገድ ግንዳታ መጠናቀቁ ወደቡን ወደስራ እንዲገባ ማድረግ አስችሏል፡፡
አቶ ሮባ ስለወደቡ እንቅስቃሴ ሲያስረዱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እቃ ማራገፍ የተቻለ መሆኑን ገልፀው እስከ 4 ሺ ሜትሪክ ቶን የድንጋይ ከሰል በአንድ ቀን እስከማራገፍ ተችሏል ብለዋል፡፡ ይህም ከፍተኛ መጠን ነው ሲሉ አክለዋል፡፡በቀን ከ 50 እስከ 100 ተሽከርካሪዎች ምርቱን ይዘው ወደ አገር መግባት መቻሉን ማወቅ የተቻለ ሲሆን፡፡ በተለይ ከታጁራ እስከ በልሆ የተሰራው መንገድ አዲስ በመሆኑ ተሸከርካሪዎች በፍጥነት መመላላስ እንዲያስችላቸው አድርጓል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለካፒታል ገልፀዋል፡፡
#Capital

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ [ፎቶ] እና አቶ ኮርሳ ደቻሳ፤ በኮሮና በሽታ ተይዘው በሆስፒታል ህክምና ላይ በመሆቸው፤ ዛሬ በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን ጠበቆቻቸው ገለጹ።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
ሁለት ተቋማት ግምታዊ ዋጋቸው 34 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለተፈናቃዮች አደረጉ!
የገቢዎች ሚኒስቴር ና የጉምሩክ ኮሚሽን ግምታዊ ዋጋቸው 34 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቃዮች ዛሬ አደረጉ።ድጋፉ የተደረገው በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለሚያሰባስበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አማካይነት ነው።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌውና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቀበታ ተገኝተዋል።ድጋፉ የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ ምስር፣ ፓስታና አልባሳት እንደሆነም በርክክቡ ወቅት ተጠቅሷል።
አፈ ጉባዔ ታገሰ ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ድጋፉ የተደረገው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽንና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ከደሞዛቸው በማዋጣትና በቁጥጥር በኮንትሮባንድ ከተያዙ ቁሳቁስ እንደሆነ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተከሰተው የፀጥታ ችግር በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታችው ተፈናቅለዋል። የመንግሥትና የግል ድርጅቶችም ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ድጋፍ እያደረጉ ናቸው።
ምንጭ: ኢቲቪ

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ባልደረባ የነበሩት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20፤ 2012 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው እንደነበር ጠበቃቸው ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 8 የምርመራ ቀናት ተፈቅዶለታል።
በተያያዘ የችሎት ዜና ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20፤ 2012 ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፤ ሂሩት ክፍሌ፤ በጠበቃቸው በኩል ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ፓርቲያቸው አስታወቀ።ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቅቆ እንዲያቀርብ ለሐምሌ 28 ቀጠሮ ሰጥቷል።የኢዜማ የሙያ ማኅበራት ተጠሪ የሆኑት ሂሩት በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት "በአዲስ አበባ ከተማ ከቅድስተ ማሪያም እስከ ግንፍሌ አካባቢ ያሉ ወጣቶችን በማስተባበር፤ ሁከት በማስነሳት ተሳትፈዋል" በሚል ተጠርጥረው ነው። ሂሩት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን መጀመሪያ ችሎት ፊት የቀረቡት ሐምሌ 9 ቀን 2012 ነበር።ፖሊስ በመጀመሪያው የችሎት ውሎ 14 ቀናት የምርመራ ቀናት ጠይቆ 10 ቀናት ተፈቅዶለታል። በዛሬው ችሎትም ተመሳሳይ የምርመራ የጊዜ ጥያቄ ከፖሊስ የቀረበለት ፍርድ ቤቱ 8 ቀናት ብቻ መፍቀዱን ኢዜማ ገልጿል።

ጉግል እ.አ.አ እስከ 2021 ክረምት ድረስ ሰራተኞቹ ወደ መስሪያ ቤት እንደማይመለሱ አስታውቋል። የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሱንዳር ፒቻይ ለቫራይቲ እንደገለፁት በመስሪያ ቤት መገኘት አስፈላጊ ከሆነባቸው ዘርፎች ውጭ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰራተኞች እስከ ጁን 30, 2021 በቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት አማካኝነት ስራቸውን ያከናውናሉ።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ "ከህመምተኛ ልጃቸው ጋር እንዳይገናኙ በመከልከላቸው" ለ3 ቀናት የረሃብ አድማ አድርገው እንደነበር፤ ዛሬ በነበራቸው የፍርድ ቤት ውሎ መናገራቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ተናገሩ።
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa1
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 579 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰአታት ለ7009 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 579 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡170 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 14,547፣ ያገገሙት 6386፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 228 ደርሷል።

ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የአመራር ለውጥ አድርጓል በሚል የሚሰራጨው ዜና ሀሰት መሆኑን የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አረጋግጠዋል። ዜናው በዋነኝነት 'ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ በምክትላቸው አቶ አራርሶ ቢቂላ ተተክተዋል' የሚል የነበረ ሲሆን፣ አቶ አራርሶ አሁንም የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እንደሆኑና የተደረገ የአመራር ለውጥ እንደሌለ፣ ከትናንት ጀምሮ ጉለሌ በሚገኘው የኦነግ ጽ/ቤት ሲደረግ የነበረው ውይይትም በቅርቡ በታሰሩባቸው አባላት ዙሪያ መሆኑን እንደተናገሩ የሮይተርስ ጋዜጠኛ የሆነው ዳዊት እንደሻው ፅፏል።
@YeneTube @FikerAssefa1
@YeneTube @FikerAssefa1