ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሃሌ ሉያ ” הַלְּלוּיָהּ ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ሂልሌል” הַלְּלוּ ማለትም “እልልታ” ወይም “ምስጋና” ሲሆን “ያህ” בְּיָ֥הּ ደግሞ የያህዌህ ምጻረ-ቃል ነው፤ “ያህን አመስግኑት” ማለት ነው፤ “ያህ” የሚለው ቃል 50 ጊዜ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ሲሆን ለሰዎች ስም በመነሻና በመድረሻ ቅጥያ ያገለገለ ሲሆን በሃሌ-ሉያህ ላይ ደግሞ መድረሻ ቅጥያ ሆኖ አገልግሏል፣ ይህም የያህዌህ ምጻረ-ቃል የሆነ ስም ነው፦
መዝሙረ ዳዊት 68፥4 ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” בְּיָ֥הּ ነው፥

“ያህ” አርኪኦሎጂስቶስ በቁፋሮ ያገኙት የአፍሮ-አሲአቲክ ጽሁፉ ሲሆን ከሙሴ በፊት በግብጽና በከነአን ውስጥ ጣኦታውያን የግብጹን የጨረቃ አምላክ ለመጥራት ይጠቀሙበታል፣ ታዲያ “ያህ” ከሙሴ በፊት በግብጽና በከነአን ውስጥ ጣኦታውያን ስለሚጠቀሙበት የጣኦቶቻቸው ስም ነበረን?፦ Biblical Archaeology Review 1975 monthly magazine.
ምን እርሱ ብቻ እንደሚታወቀው የአቃሮንን አምላክ “ብዔልዜቡል” בַּעַל זְבוּב‌‎, ነው፤ “ዜቡል” ማለት “ዝንቦች” ማለት ሲሆን “ቤል” בעל ማለት ደግሞ “የዝንቦች ጌታ” ነው፦
2ኛ ነገሥት 1፥2 አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዓይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም፦ ሂዱ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ ብሎ መልእክተኞችን ላከ።
2ኛ ነገሥት 1፥3 የእግዚአብሔርም መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን፦ ተነሣ፥ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣና፦ የአቃሮንን አምላክ “ብዔልዜቡልን” בַּעַל זְבוּב‌‎, ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን?
2ኛ ነገሥት 1፥6 እነርሱም፦ አንድ ሰው ሊገናኘን መጣና፦ ሂዱ፥ ወደ ላካችሁም ንጉሥ ተመልሳችሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ “ብዔልዜቡልን” בַּעַל זְבוּב‌‎, ትጠይቅ ዘንድ የላክህ በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በሉት አለን አሉት።
2ኛ ነገሥት 1፥16 ኤልያስም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ “ብዔልዜቡልን” בַּעַל זְבוּב‌‎, ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም አለው።

ታዲያ “ቤል” בעל ማለት “የዝንቦች ጌታ” ከሆነ ለምንድን ነው የእኔ “ቤል” בַּעְלִֽי ብለሽ አትጠሪኝም ያለው? ቤል ተብሎ ይጠራ ነበርን? “ባል” እና “ሚስት” የሚለው አምልኮ ጣኦታውያን ለያህዌህ እና ለሚስቱ ለአሸራ ይጠቀሙ ነበር፦
ሆሴዕ 2፥18 በዚያ ቀን “ባሌ” ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ “በኣሌ” בַּעְלִֽי ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል ያህዌህ፤

በዚህ ቢቆም ጥሩ ነበር የሚገርመው እስራኤላዊ ሰማያስ ልጁን “በዓልያህ” בְּעַלְיָה ብሎታል ትርጉሙ “ያህዌህ በዓል ነው” ማለት ነው፦
1ኛ ዜና መዋዕል 12:5 ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ “በዓልያ” בְּעַלְיָה፥ ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥

“በኣል” הַבַּ֖עַל ማለት “ቤል” ነው፤ ጣዖት ነው፦
1ኛ ነገሥት 18፥21 ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፦ እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ “በኣል” הַבַּ֖עַל ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
1ኛ ነገሥት 18፥26 ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፥ ከጠዋትም እስከ ቀትር ድረስ፦ “በኣል ሆይ” הַבַּ֣עַל ፥ ስማን እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፥ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር።

ታዲያ ያህዌህ ጣዖት ነውን? እረ በፍፁም ባይብል ምኑ ይታመናል? የሰው ንግግር እና እጅ ገብቶበታል፤ የነብያት አምላክ አላህ “በዕል” بَعْل ከሚባለው ጣዖት እጅጉን ይለያል፦
37፥125 *በዕልን ትጠራላችሁን?* ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን? أَتَدْعُونَ بَعْلًۭا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ ٱلْخَٰلِقِينَ

አምላካችን አላህ በቁርአን የተጠቀሱ “አስማኡል ሁስና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “የተዋቡ ስሞች” አሉት፦
59:24 እርሱ አላህ ፈጣሪው ከኢምንት አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለእርሱ “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤
20:8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም ለእርሱ “መልካም የሆኑ ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት።
17:110 ፦አላህን ጥሩ፤ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤ ማንኛውንም ብትጠሩ፣ መልካም ነው፤ ለእርሱ “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉትና በላቸው፤
7:180 ለአላህም “መልካም ስሞች” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ አሉት፤ ስትጸልዩ በርሷም ጥሩት እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤

ከእነዚህ ስሞች ታላቁ ስሙ “አል-ሐዩል ቀዩም” الْحَيُّ الْقَيُّومُ ሲሆን ትርጉሙ “ሕያው አስተናባሪ አሊያም ሕያው ሆኖ የሚኖር ነገሮችን ሁሉ የሚያስሆን” ማለት ነዉ፤ ይህ “ኢስሙል አእዘም” ማለትም “ታላቁ ስም” ነው፤ ይህ ታላቅ ስሙ በሶስት ሱራዎች ላይ ይገኛል፦
3:2 አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም እርሱ *ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ* الْحَيُّ الْقَيُّومُ ነዉ።
20:111 ፊቶችም ሁሉ፣ *ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ* الْحَيُّ الْقَيُّومُ ለሆነው አላህ ተዋረዱ፤ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ።
2:255 አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ *ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ* الْحَيُّ الْقَيُّومُ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡

ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር አያተል ኩርሲይን ሲፈስር እንዲህ ይላል፦
አቡ ኡማማህ እንደተረከው ነብዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የአላህ ታላቁ ስም በእርሱ አላህን ከተማፀኑት ተማፅኖውን ይመልሳል፤ ይህም በሱረቱል በቀራ፣ በሱረቱል አለ-ኢምራን እና በሱረቱ አጥ-ጣሃ ውስጥ ይገኛል።
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 30
አል-ቃሲም እንደተረከው፦ “የአላህ ታላቁ ስም በእርሱ አላህን ከጠሩት ጥሪውን ይመልሳል፤ ይህም በሱረቱል በቀራ፣ በሱረቱል አለ-ኢምራን እና በሱረቱ አጥ-ጣሃ ውስጥ ይገኛል። عَنِ الْقَاسِمِ، قَالَ اسْمُ اللَّهِ الأَعْظَمُ الَّذِي إِذَا دُعِيَ بِهِ أَجَابَ فِي سُوَرٍ ثَلاَثٍ الْبَقَرَةِ وَآلِ عِمْرَانَ وَطَهَ ‏.‏

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
በአረቢኛ ድምጽ ያላቸው “ተነባቢ ፊደላት”sound letters” 28 ሲሆኑ “አጫዋች ፊደል”stretch letter” ደግሞ 1 ሲሆን እርሱም “አሊፍ” ا ነው። በመካከላቸው ስናነባቸው የሚቀጥን ፊደል 19 ሲሆን “ተርቂቅ” ይባላል፣ የሚወፍር ፊደል ደግሞ 7 ሲሆን “ተፍሂም” ይባላል፣ ነገር ግን ተርቂቅና ተፍሂም የሆኑ ሁለት ሃርፎች “ራ” ر እና “ላም”ل ናቸው፤ “ራ” ر በፈትሃና በደማ ይወፍራል በከስራ ይቀጥናል፣ “ላም” ل ደግሞ በለፍዙል ጀላላ ማለትም በአላህ ስም ላይ ትወፍራለች። ይህንን እሳቤ ይዘን የአላህ ስምን ስናጠና “አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው” ማለት ነው፤ አላህ ኢስሙል ዛት” ማለትም “የህላዌው ስም” ነው፤ “ዛት” ذات ማለት “ምንነት” ሲሆን አላህ በምንነቱ የሚመለክ ነው፤ ይህ ስም በሙያ እንዲህ ተቀምጧል፤ “ኢዕራብ” إﻋﺮﺍﺏ ማለት “ሙያ”case” ማለት ሲሆን ይህ ሙያ “ፈትሐ” فَتْحَة “ከስራ” كَسْرَة “ደማ” ضَمَّة በሚባሉ አጭር አናባቢ ሃርፎች ላይ ያገለግላሉ፦
“መንሱብ”፦ በፈትሐ የሚያገለግለው ሙያ “መንሱብ” المنصوب ማለትም ተሳቢ ሙያ”accusative case” ሲሆን አሏህ በፈትሐ ስንጠቀም “አሏሀ” اللَّهَ ይሆናል።
“መጅሩር”፦ በከስራ የሚያገለግለው ሙያ “መጅሩር” المجرور ማለትም አገናዛቢ ሙያ”genitive case” ሲሆን አሏህ በከስራ ስንጠቀም “ሊሏሂ” اللَّهِ ይሆናል።
“መርፉዕ”፦ በደማ የሚያገለግለው ሙያ ደግሞ “መርፉዕ” المرفوع ማለትም ባለቤት ሙያ”nominative case” ሲሆን አሏህ በደማ ስንጠቀም “አሏሁ” اللَّهُ ይሆናል። ለምሳሌ፦ “አሏሁ-ማ” ٱللَّهُمَّ ማለት “ያ-አሏህ” ياالله ማለት ነው።

ይህ ስም የፈለግነውን ሃርፍ ከላዩ ላይ ቢቀነስ ትርጉም አለው፦
@ አሏህ በሚለው መነሻ የመጀመሪያውን አንድ ሀርፍ ስንቀንሰው “ሊሏህ” لله የሚል ይሆናል፡፡ ትርጉሙም “የአላህ” ማለት ነው።
@ አሏህ በሚለው የመጀመሪያዎቹን ሁለት ሃርፎች ስንቀንሰው ደግሞ ውጤቱ “ለሁ” لَهُ የሚል ይሆናል፡፡ ትርጉሙም “የእርሱ” የሚል ነው፡፡
@ አሏህ በሚለው የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሃርፎች ስንቀንሰው ደግሞ ውጤቱ “ሁ” هُ የሚለው ይሆናል፡፡ ትርጉሙም “እርሱ” የሚል ነው፡፡
@ አሏህ በሚለው ሀርፎች ከመሀል ከሁለቱ የላም ሃርፎች አንዱን ስንቀንሰው ውጤቱ “ኢላህ” إِلَٰه የሚለው ይሆናል፤ ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፤ “ኢላህ” የሚለው ቃል 147 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ተባታይ ነው፤ አንስታይ ሲሆን ደግሞ “ኢላሃህ” إلاهة ነው፤ የኢላህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አሊሀህ” آلِهَةٌ ነው፤ “ኢላህ” በተለያየ አገናዛቢ ተውላጠ ስም ላይ ሲመጣ፦
“ኢላሂ” إِلَٰهي “አምላኬ”
“ኢላሁና” إِلَٰهُنَا “አምላካችን”
“ኢላሀከ” إِلَٰهَكَ “አምላክህ”
“ኢላሀኩም” إِلَٰهُكُمْ “አምላካችሁ”
“ኢላሀሁ” إِلَٰهَهُ “አምላኩ”
“ኢላሀሁም” إِلَٰهَهُمْ “አምላካቸው” ይሆናል።
“ኢላህ” ማለት “አምላክ” ተብሎ በትርጉም መጠቀም ይቻላል፤ ግን “አላህ” የተፀውዖ ስም ስለሆነ እራሱ ነው የሚቀመጠው፦
17:22 “ከአላህ” ጋር ሌላን “አምላክ” አታድርግ፤ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና لَّا تَجْعَلْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقْعُدَ مَذْمُومًۭا مَّخْذُولًۭا ፤
28:88 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ وَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ ۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَىْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُۥ ۚ لَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ፡፡
26:213 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና فَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْمُعَذَّبِينَ ፡፡
ነጥብ አንድ
“አሏህ እና ሴማዊ ዳራ”
አሏህ በዕብራይስ አሁንም “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን ከውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל ሲኖረው አንዱን ስንቀንስ እና በፈትሃ ስንጨርሰው “ኤሎሃ” אלוהּ ይሆናል፤ ትርጉሙም “አምላክ” ማለት ነው፤ የኤሎሃ ብዜት ደግሞ “ኤሎሂም” אלהים ነው፤ “ኤል” אֵל የኤሎሃ ምፃረ-ቃል ሲሆን የኤል ብዜት ደግሞ “ኤሊም” אֵלִ֑ים ነው፤ “ያ-አሏህ” יַאלְלָה “አሏህ ሆ” እና “ወ-ሏህ” וַאלְלָה “በአሏህ” ይባላል።
አሏህ በአረማይክ አሁንም “አሏህ” ܐܲܠܵܗܵܐ
ሲሆን ከውስጡ “ኤላህ”ܐܠܗܐ ማለትም “አምላክ” የሚል ቃል አለ፤ ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Bergsträsser, Gotthelf. 1995. Introduction to the Semitic Languages: Text Specimens and Grammatical Sketches.
2. Fitzmyer, J. (1997), The Semitic Background of the New Testament, Eerdmans Publishing.
3. Bennett, Patrick R. 1998. Comparative Semitic Linguistics:
4. Moscati, Sabatino. 1969. An introduction to the comparative grammar of the Semitic languages: phonology and morphology.

እንግዲህ ኢየሱስ፣ ሔኖክ፣ ኖህ እና አብርሐም የሚጠቀሙበት ዘዬ አረማይክ ከነበረ እና ሌሎች የእስራኤል ነብያት የዕብራይስጥ ዘዬ ሲጠቀሙ ከነበረ “አሏህ” የሚለውን ስም መጠቀማቸው ግድ ይላል፤ ነገር ግን አሁን በዘመናችን የአላህ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ኪታባት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ የታሪክ ምሁራን ያትታሉ፣ ለምሳሌ የእስራኤል ልጆች ውስጥ የነበሩት ነቢያት ሲናገሩበት የነበረው ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን እነርሱ የተናገሩበት መጽሐፍት የሉም፣ በጣም ቀደምትነት አለው የሚባለው የነቢያት መጽሐፍት ግልባጭ በግሪክ ሰፕቱአጀንት የተዘጋጀው ሲሆን ከሰፕቱአጀንት በኋላ የተዘጋጁት የሙት ባህር ጥቅል፣ ማሶሬቲክ፣ ሰመሪያን ይህንኑ የግሪኩን መሰረት አድርገው ነው የተተረጎሙት፣ ከሰፕቱአጀንት በፊት የነበረው የነቢያት መጽሐፍት ዛሬ የለም፣ ከሌለ አላህ የሚለው ቃል ይጠቀሙ አይጠቀሙ ምንም ምንጭ የለም ማለት ነው፣ ወደ ኢየሱስም ስንመጣ ኢየሱስ ሲናገርበት የነበረ ቋንቋ አረማይክ ሲሆን ሃዋርያቱም ሲናገሩበት የነበረው ይህን ቋንቋ ነው፣ ነገር ግን ወደ ሁለተኛው ትውልድ ይህ የኢየሱስ ትምህርት ሲገባ የተጻፈው ኮይኔ በሚባል የግሪክ ቋንቋ ነው፣ ስለዚህ ነቢያት አምላካቸውን ማን ብለው እንደነበር የሚያሳይ የቋንቋ መረጃ በዛሬ ጊዜ የለም። አላህ የሚለውን ስም ነቢያቶች ተናግረውት አያውቁም የሚለው አሉባልታ ምንጭ አልባና ሰነድ አልባ ነው፣ ይህን ደፍሮ ለመናገር ስረ-መስረት ያለው አንጓ፣ ቋንቋ፣ ምጥቀት ሆነ ልቀት ያስፈልጋል፣ በተረፈ “”እግዚአብሔር፣ ቴኦስ፣ ጋድ፣ ጉድ”” የሚሉት ቃላት ባዕደ-ቃላት እና ኢላህ ለሚለው ቃል ትርጉም ናቸው እንጂ አሏህ ለሚለው ቃል ትርጉም አይደሉም።
ነጥብ ሁለት
“አሏህና ነብያቱ”
አላህ ጥንት ነቢያቶች የሚያመልኩት የነቢያት አምላክ መሆኑን የምናውቀው ከጥንቶቹ ነቢያት ጋር የነበረውን መስተጋብር ለመግለጽ፦
“ቁልና” قُلْنَا *አልን* ፣
“አርሰልና” أَرْسَلْنَا*ላክን*፣
“አውሃይና” أَوْحَيْنَا *አወረድን*
በማለት ጥንትም ነቢያትን ሲልክ የነበረው፣ ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲያወርድ የነበረውና በተለያየ መንገድ ሲያናግራቸው የነበረው እርሱ መሆኑን ይገልጻል፦

1. አልን፦
20:116 ለመላእክትም፣ ለአዳም ስገዱ፣ *ባልን* ጊዜ አስታውስ፤
2:35 «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» *አልንም*፡፡
11:40 ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ፣ በርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት፣ ወንድና ሴት ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን *አልነው*፤
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ *ባልነው* ጊዜ አስታውስ።
2:125 ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
2:60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡
17:2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፤ ከኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ *አልናቸውም*።

2. ላክን፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ *ልከናል*፤
57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ *ላክን*፤
23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት *ላክን*፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤

3. አወረድን፦
4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድን*፣ ወደ አንተም *አወረድን*፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው።
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ *የምናወርድለት* ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
12:109 ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደ እነርሱ ራዕይ *የምናወርድላቸው* የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤
21:7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ *የምናወርድላቸው* የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፤
16:43 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን *የምናወርድላቸውን* ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤

አላህ የነቢያት አምላክ ነው፤ ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊህ፣ ኢብራሒም፣ ሹዐይብ፣ ሙሳ እና ኢሳ አላህ እያሉ ይጠቀሙ እንደነበር ቃሉ ይነግረናል፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን” አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤

“ኑሕ”
11:25-26 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፤ አላቸውም ፦ እኔ ለናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ። አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።

“ሁድ”
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

“ሷሊህ”
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም፤ .. አላቸው።

“ኢብራሒም”
19:48 እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግዙትንም እርቃለሁ፤ ጌታየንም እግዛለሁ፤ ጌታየን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ።

“ሹዐይብ”
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፤ እኔም በናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።

“ሙሳ”
7:104-105 ሙሳም አለ፦ፈርኦን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፤ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፤ ከጌታችሁ በታምር በእርግጥ መጣኋችሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከኔ ጋር ልቀቅ።

ኢሳ”
3:51 አላህ ጌታየና ጌታችሁ ነዉ፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነዉ አላቸዉ።
ነጥብ ሶስት
“አሏህና ታሪካዊ ፍሰት”
አሏህ የሚለው ስም ነብያችን ነብይ ሆነ ከመላካቸው በፊትና ቁርአን ከመውረዱ በፊት በሴመቲክ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ-እውቀቶች*Encycolopedias* ሆኑ ታሪካዊ ፍሰቶች ያትታሉ፦
1. የሃይማኖት መድብለ-እውቀት 1987: “አላህ የሚለው ስም ስረ-መሰረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.
2. የክርስትና መድብለ-እውቀት 2001: “ ቅድመ-ቁርአን አረብ ተናጋሪ ክርስቲያንና አይሁድ እንዲሁ አላህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.
3. የኢስላም መድብለ-እውቀት 1913: “አረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሃመድ በነበሩት ዘመናት አላህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.
4. የብሪታኒካ መድብለ-እውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርአን በነበሩት አረቢያን መጽሐፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

ከነዚህ ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ ተነስተን የምንደመድመው ነገር ቢኖር አላህ የሚለው ስም ነቢያችን የገለጡት አሊያም ቁርአን የገለጠው ስም ብቻ ሳይሆን ስረ-መሰረቱ ቀዳማይ መሆኑን ነው፣ የትኛውም ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ አላህ የጣኦት ስም ነው ብሎ ያሰፈረ የለም፣ አለ የሚል ሰው ካለ ተግዳሮትና ጋሬጣ ሆኖ መቅረብ ይችላል። ቁሬሾች አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ እንጂ ከጣኦቶቻቸው መካከል አንዱ ጣኦት ነበር የሚል የቡና ዲቃላ ወሬ የላቸውም፦
31:25 ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፤ ምስጋና ለአላህ ይገባው፣ በላቸው፤ ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
29:61 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
43:87 ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው፣ በእርግጥ አላህ ነው፣ ይላሉ።ታዲያ ከእምነት ወዴት ይዞራሉ።
39:38 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ ይሉሃል።
29:63 ከሰማይም ውሃን ያወረደና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋት ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ይሉሃል።
23:84-89 «ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ ንገሩኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን» በላቸው፡፡«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ» በላቸው፡፡

ማጠቃለያ
አላህ ህያው የሆነ ሁሉን የሚያውቅ፣ የሚያይ፣ የሚሰማ እና በእኔነት የሚናገር አምላክ ነው፦

1. ሁሉን የሚያውቅ ነው፦
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤

2. ሁሉ ተመልካች ነው፦
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

3. ሁሉን የሚሰማ ነው፦
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

4. እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው፦
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።
2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጥንቧ ዘረኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

“ዘረኝነት”racism” ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን ክፉ በሽታ ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ዝንባሌ ደግሞ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦
25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ዘረኝነት ምንጯ ዝንባሌ ከሆነ ታዲያ ከዘረኝነት በሽታ ለመገላገል መፍትሔው ምንድን ነው? አዎ አምላካችን አላህ የሚናገረውን በጥሞና ሰምቶ መተግበር ነው፦
4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

“ነፍሥ” نَفْس የሚለው ቃል አደምን ያሳያል፤ “መቀናጃዋ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል ”ዘውጀሃ” زَوْجَهَا ሲሆን የአደም ጥንድን ያሳያል፤ ይህቺም ጥንድ ሐዋ ናት፤ “ነፍሥ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደም መፈጠራችንን ያሳያል፤ “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን ሙተና ማለትም ሁለትዮሽ”dual” የሚያሳይ ነው፤ “እነርሱም” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደምና ከሐዋ መፈጠራችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ታዲያ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ከሆንን አንዱን ዘር ማብለጥ ሌላውን ማሳነስ ጠባብነት አይደለምን? አንድ ሙስሊምስ እንዲህ አይነት ውዝግብ ውስጥ መግባት የእምነትን ገመድ የሚበጥስ አይደለምን? አላህ ሁላችንንም ከአንድ አባትና እናት ነው የፈጠረን፦
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

“ወንድ” እና “ሴት” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ሰዎች ከወንድና ከሴት መፈጠራቸውን ያሳያል፤ አላህ ነገድ እና ጎሳ ያደረገን ብዙ ስለሆንን ለትውውቅ የትውልድ መዝገብ እንጂ አላህ ዘንድ ማነስ እና መተለቅ አላህ በመፍራት ብቻ ነው።
አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

ቋንቋዎች ይዘውት የመጡት ባህል፣ ትውፊት፣ ክህሎት ነገድ እና ጎሳ እንዲሆን አድርጎታል፤ ይህ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶችና መተዋወቂያ ነው። ደሃ ሃብታም ሳንል፤ ዘመድ ባዕድ ሳንል፣ ዝንባሌ ተከትለን ሳናዳላ ለአላህ ብለን ለሰው ሁሉ በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች መሆን አለብን፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
ስለዚህ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ እንጂ መኩሪያ ወይም ማብጠልጠሊያ አይደለም፤ ዘረኝነት በዲንያም በአላህ ዘንድ ዋጋ ያሳጣል በአኺራም ለጀሃነም ይዳርጋል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَفَخْرَهَا بِالآبَاءِ مُؤْمِنٌ تَقِيٌّ وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ‏”‏

የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150
ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*። عَنْ جُنْدُبِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عُمِّيَّةٍ يُقَاتِلُ عَصَبِيَّةً وَيَغْضَبُ لِعَصَبِيَّةٍ فَقِتْلَتُهُ جَاهِلِيَّةٌ ‏”‏

“ጃህሊያህ” جَاهِلِيَّةٌ ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ ይባላል፤ በእርግጥም ዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 32, ሐዲስ 6255
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦ “ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን? አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*። جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ يَقُولُ كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزَاةٍ فَكَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ يَا لَلأَنْصَارِ وَقَالَ الْمُهَاجِرِيُّ يَا لَلْمُهَاجِرِينَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا بَالُ دَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ ‏
‏ ‏
የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162
ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል አይቀጣም*። وَلاَ يُؤْخَذُ الرَّجُلُ بِجَرِيرَةِ أَبِيهِ وَلاَ بِجَرِيرَةِ أَخِيهِ ‏”

አንድ ሰው ባጠፋው ብዙኃኑን ዘር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 2661 ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ أَعْظَمَ النَّاسِ فِرْيَةً لَرَجُلٌ هَاجَى رَجُلاً فَهَجَا الْقَبِيلَةَ بِأَسْرِهَا
እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዘረኝነት የሚጣራ፣ በዘረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ሰው ከነብያችን”ﷺ” ሱናህ ውጪ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349
ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ አይደለም*። عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ مِنَّا مَنْ دَعَا إِلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ قَاتَلَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ مَاتَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ ‏”‏

በድንበር፣ በክልል፣ በወሰን የከፋፈሉን ሰዎች ናቸው። ምድር እኮ የአላህ ናት፤ ተቸግረን ብንሰደድ ሰፊ ናት፤ ዋናው ይህቺ አንድ የተውሒድ መንገድ ሃይማኖታችን ናትና አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ*፡፡ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ أَرْضِي وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ
21፥91 *ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ*፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ

እንግዲህ ዲነል ኢስላምን የመሰለ ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በዘረኝነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠርዘኝነት፣ በቡድንተኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታዘዝ ነው። በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ ጠበኞችም በነበርን ጊዜ በእኛ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ እናስታውስ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማን፤ በጸጋውም ወንድማማቾች ሆንን፥ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ በነበር ጊዜ አዳነን፦
3፥103 *የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ*፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

በተሰጠን ጸጋ ልክ ወንድማማች መሆን ሲገባን ዛሬ በመሃይምነት አራንቋ የተያዝን በማህበራዊ ሚድያ ዘረኝነትን ስናራግብ እንውላለን፤ ኢስላም ዓለም-ዐቀፍ ሆኖ ሳለ ምነው ጠበብንሳ? ምነው ይህ ያህል ኢማናችን ወረደሳ? አላህ ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዘረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

ቅጥፈት አንድ
የሐዋርያት ሥራ 7:15-16 ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ “አባቶቻችንም”፤ ወደ ሴኬምም አፍልሰው #አብርሃም #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በብር በገዛው መቃብር “ቀበሩአቸው”።

በአብርሃምና በሴኬም መካከል የትውልድ ልዩነት አለ፤ ሴኬም ይቅርና የሴኬም አባት ኤሞር የነበረው በአብርሃም ጊዜ ሳይሆን የአብርሃም የልጅ ልጅ በሆነው በያዕቆብ ጊዜ ነው፦
ዘፍጥረት 34:4-6 #ሴኬምም አባቱን #ኤሞርን ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው። #ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። #የሴኬም #አባት #ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ #ያዕቆብ ወጣ።

ልብ በሉ ሴኬም የያዕቆብን ልጅ ዲናን ሲያስነውር ማለት ሲደፍራት አይደለም አብርሃም አያቱ ይቅርና አባቱ ይስሐቅ ሞቷል፤ ታዲያ አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር መቃብር የገዛው መቼ ነው? ይህ እልም ያለ ቅጥፈት ነው፤ ታዲያ ማን ነው መቃብሩን ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች የገዛው? ስንል የዘፍጥረት ዘጋቢ ያዕቆብ ነው ይለናል፦ ዘፍጥረት 33:18-19 #ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ #ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ፤ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የእርሻውን ክፍል #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር #ልጆች #በመቶ #በጎች ገዛው።

ውሸት ሁሌም ውሸት ነው፤ ልብ በሉ አብርሃም በህይወት ሳይኖር ያልገዛውን ገዛ ማለቱ ሲገርመን አብርሃም ገዛ የተባለው #በብር ሲሆን ያዕቆብ ግን #በመቶ #በጎች ነው፦
ኢያሱ 24:32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት #ያዕቆብ #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በመቶ #በግ በገዛው #እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።

የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ሉቃስ ወይም እስጢፋኖስ አሊያም የግሪክ እደ-ክታባትን ገልባጮች ቀጥፈዋል፤ አብርሃም በእርግጥም የመቃብር ስፍራ ገዝቷል የገዛው ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች ሳይሆን ከኬጢያዊ ከኤፍሮን እርሻ ላይ ነው፤ የገዛውም በመቶ በግ ሳይሆን #በአራት #መቶ #ሰቅል ነው፦
ዘፍጥረት 23፥16-17 *አብርሃምም* የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን #አራት #መቶ #ሰቅል መዝኖ #ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና።
ዘፍጥረት 49፥29-30 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው። እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ #አብርሃም ለመቃብር ርስት #ከኬጢያዊ #ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።

ቅጥፈትን በጋራ እንከላከል፤ ኢንሻላህ ይቀጥላል……

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ቅጥፈት ሁለት 1ኛ ነገሥት 6፥1 የእስራኤል ልጆች #ከግብጽ #ምድር #ከወጡ #አራት #መቶ #ሰማንያ ዓመት #በሆነ #ጊዜ#ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት እንደሆነ ይህ የነገሥት ፀሐፊ አስፍሮታል፤ እውን የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት ነው ወይ? ይህንን ቅጥፈት አብረን እንይ፦

ነጥብ አንድ
“አርባ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ወጥተው ከነዓን እስኪገቡ ድረስ 40 ዓመት በምድረ-በዳ ቆይተዋል፦ ዘጸ 16:35 የእስራኤልም ልጆች #ወደሚኖሩባት #ምድር #እስኪመጡ ድረስ #አርባ #ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ። ዘዳ 29:5 #አርባ #ዓመት በምድረ በዳ መራኋችሁ፤ ልብሳችሁም አላረጀባችሁም፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ላይ አላረጀም።

ነጥብ ሁለት
“አርባ ዓመት”
ካሌብ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ሲወጡ የአምስት እመት ልጅ ነበረ፤ የምድረ-በዳው 40 ዓመት ሲጨመር 45 ዓመት ሆኖት ነበር፤ በከነዓን 40 ዓመት ሲቀመጥ 85 ዓመት ሆነው፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ወጥተው በምድረ-በዳ 40 ዓመት አሳልፈው ከነዓን ከገቡ በኃላ 40 ዓመት ሲቆዩ 80 ዓመት ይሆናል፦ ኢያ 14:10፤ አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል #በምድረ #በዳ #ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን #አርባ #አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ #ሰማንያ #አምስት ዓመት ሆነኝ።

ነጥብ ሶስት “አራት መቶ አምሳ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከካሌብና ከኢያሱ ሞት በኃላ እስከ ነብዩ ሳሙኤል መሳፍንትን ለአራት መቶ አምሳ ዓመት አስነስላቸው፦
መሳ 2:16 እግዚአብሔርም #መሳፍንትን #አስነሣላቸው፥ ከሚማርኩአቸውም እጅ አዳኑአቸው።
ሐዋ 13:20 ከዚህም በኋላ #እስከ #ነቢዩ #እስከ #ሳሙኤል #ድረስ #አራት #መቶ #አምሳ #ዓመት ያህል #መሳፍንትን ሰጣቸው።

ነጥብ አራት
“አርባ ዓመት”
በነብዩ ሳሙኤል ጊዜ የቂስን ልጅ ሳኦል ነገሠ፤ ይህም ንግሥና 40 ዓመት ቆየ፦ ሐዋ 13:21 ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን #አርባ #ዓመት ሰጣቸው፤

ነጥብ አምስት
“አርባ ዓመት”
ከሳኦል ንግሥና በኃላ ንጉሥ ዳዊት ለአርባ ዓመት ነገሰ፦ 1ነገ 2:11 ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠው ዘመን #አርባ #ዓመት ነበረ፤ በኬብሮን ሰባት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።

ነጥብ ስድስት
“አራት ዓመት”
ከዳዊት በኃላ ሰለሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ሰለሞን ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ፦ 1ነገ.6:1፤ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው #ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

አሁን ነው ጉድ የሚፈላው፤ ከግብፅ መውጣት ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ያለው የጊዜ እርዝመት እስቲ እንደምራቸው፦
40 ዓመት
40 ዓመት
450 ዓመት
40 ዓመት
40 ዓመት
4 ዓመት
=======
614 ዓመት ይሆናል።
እሺ እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ሲጀምር የነበረው የጊዜ ቆይታ 614 ወይስ 480? ማን ነው የቀጠፈው? ይህ ታሪክ ከመነሻው የታሪክ ጸሐፊዎች ቃል እንጂ የአምላክ ንግግር አይደለም፤ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እንደ የፈጣሪ ቃል ቢወስዱትም የፈጣሪ ንግግር አይደለም። አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው ፅፈው ከአላህ ሳይሆን “ይህ ከአላህ ዘንድ ነው” ብለው እውነትን በውሸት እንደሚቀላቅሉ በተከረው ከሊማ ነግሮናል፦
2:79 ለነዚያም *መጽሐፉን* *በእጆቻቸው* ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «*ይህ* *ከአላህ* *ዘንድ* *ነው*» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ #እጆቻቸው #ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የሙሐመድ"ﷺ" ሸፋዓ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥79 ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ *ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል*፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا

"ሐምድ" حَمْد ማለት "ሐመደ" حَمَّدَ ማለት "አመሰገነ" ከሚል ሥርወ-ቃል። የመጣ ሲሆን "ምስጋና" ማለት ነው፤ ሐምድ የአምልኮ አይነት ነው፤ በቁርኣን ውስጥ ከተዋቡ የአላህ ስሞች አንዱ "አል-ሐሚድ" الْحَمِيد ሲሆን "እጅግ በጣም የተመሰገነ" ማለት ነው፦
31፥26 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ *አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው*፡፡ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

አላህ አምላኪዎች "ሓሚዱን" حَٰمِدُون ማለትም "አመስጋኞች" ይባላሉ፦
9፥112 እነርሱ ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ *"አመስጋኞች"*፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡ التَّائِبُونَ الْعَابِدُونَ الْحَامِدُونَ السَّائِحُونَ الرَّاكِعُونَ السَّاجِدُونَ الْآمِرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَالنَّاهُونَ عَنِ الْمُنكَرِ وَالْحَافِظُونَ لِحُدُودِ اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِين

ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ሙሐመድ" مُحَمَّ በሚል ስም አራት ጊዜ በቁርኣን ተዘክረዋል፤ የስማቸውም ትርጉም "ምስጉኑ" ማለት ነው፦
3፥144 *ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل
33፥40 *ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
47፥2 እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ *በሙሐመድ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል*፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَآمَنُوا بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَهُوَ الْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ ۙ كَفَّرَ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَأَصْلَحَ بَالَهُمْ
48፥29 *የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው*፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

"አሕመድ" أَحْمَد የሚለው ቃል የሙሐመድ ተለዋዋጭ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተመስጋይ" ማለት ነው፤ ይህም ስም በቁርኣን አንድ ጊዜ ተወስቷል፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና *ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 163
ኢብኑ ጁበይር ከአባቱ አግኝቶ እንደተረከው፤ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *“እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ "እኔ አሕመድ ነኝ"፣ እኔ ማሒ ማለትም ያ ከሃዲ ሲያጠፋ የምገስጽ ነኝ፣ እኔ ሰዎች በሚሰበሰቡት ጊዜ ሐሺር(ሰብሳቢ) ነኝ፣ ከዚህ በኃላ ነቢይ የለም፤ እኔ ዓቂብ(መጨረሻ) ነኝ*። بْنَ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” أَنَا مُحَمَّدٌ وَأَنَا أَحْمَدُ وَأَنَا الْمَاحِي الَّذِي يُمْحَى بِيَ الْكُفْرُ وَأَنَا الْحَاشِرُ الَّذِي يُحْشَرُ النَّاسُ عَلَى عَقِبِي وَأَنَا الْعَاقِبُ ” . وَالْعَاقِبُ الَّذِي لَيْسَ بَعْدَهُ نَبِيُّ .

በታሪክ ላይ ሙሐመድ"ﷺ" በሚል ስም የተጠራ ከእርሳቸው በፊት ማንም ፍጡር የለም። ይህንን ስም ኢብኑ ሠዐድ ባዘጋጀው ሲራህ "ኪታብ ጠበቃተል ኩብራህ መጽሐፍ 1" ላይ መልአኩ ጂብሪል ለእናታቸው ለአሚናህ በህልም ያወጣው ስም ነው።
አንዳንድ ኀያሲ አላህ ምስጉን ተብሏልና ለነቢያችን"ﷺ" "ምስጉን" መባሉ ማሻረክ አይሆንም ወይ? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፤ ሲጀመር አላህ ምስጉን የተባለበት ቃል "አል-ሐሚድ" الْحَمِيد እንጂ "ሙሐመድ" مُحَمَّ አይደለም፤ ሲቀጥል አላህ ምስጉን የተባለው ፍጡራን ስለሚያመልኩት ነው፤ ነቢያችን"ﷺ" ምስጉን የተባሉበት ግን አላህ ስላከበራቸው ነው፤ ሢሰልስ ኢብራሂም እና ቀጥተኛው መንገድ "ምስጉን" ተብለዋል፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን *እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና*» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
22፥24 ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ፡፡ *ወደ ምስጉንም መንገድ ተመሩ*፡፡ وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَىٰ صِرَاطِ الْحَمِيدِ
እንግዲህ ኢብራሂም እና ቀጥተኛው መንገድ "ምስጉን" ከተባሉ ነቢያችን"ﷺ" "ምስጉኑ" ወይም "ተመስጋኙ" መባላቸው አያስደንቅም፤ አይ "ምስጉን" የሚለው ቃል "መሽኩር" مَّشْكُور በሚል ቀመር እና ስሌት እንረዳዋለን ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ስሌት ተረዱት። እንኳን ነቢያችን"ﷺ" በትንሳኤ ቀን የሚቆሙበት ስፍራ "መሕሙድ" ተብሏል፤ "መሕሙድ" مَّحْمُود ማለት "ምስጉን" ማለት ሲሆን ለስፍራ ገላጭ ሆኖ የመጣ ቃል ነው፦
17፥79 ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የኾነችን ሶላት በእርሱ በቁርኣን ስገድ፡፡ *ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል*፡፡ وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3430
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ *"አላህ በቃሉ፦ "ጌታህ ምስጉን በኾነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል"። ስለዚህ አንቀጽ ተጠይቀው "ይህ ሸፋዓ ነው" ብለው መለሱ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فِي قَوْلِهِ ‏:‏ ‏(‏ عَسَى أَنْ يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَحْمُودًا ‏)‏ سُئِلَ عَنْهَا قَالَ ‏"‏ هِيَ الشَّفَاعَةُ ‏

“ሸፋዓ” شَفَٰعَه ማለት “ምልጃ” ማለት ሲሆን የነቢያችን"ﷺ" ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም" ያለ ሰው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *"እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆትታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም" ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏"‌‏.‏

በአላህ አምልኮ ላይ ሌላ ማንነትን እና ምንነት ያላሻረከ ነገር ግን ዐበይት ወንጀሎችን የሠራ በነቢያችን"ﷺ" ምልጃ ከጀሃነም ቅጣት ነጻ ወጥቶ ወደ ጀነት ይገባል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2622
አነሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"የእኔ ምልጃ ከእኔ ኡማህ ዐበይት ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ነው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ شَفَاعَتِي لأَهْلِ الْكَبَائِرِ مِنْ أُمَّتِي
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ"ﷺ" ምልጃ ይገባሉ፤ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏

አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን በነቢያችን"ﷺ" ሸፋዓ ተጠቃሚ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማንን እንመን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ክፍል ሁለት
ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ ነገር ግን እርሱ እንደተናገረ ተደርጎ በስሙ የተቀጠፉ ብዙ ጭማሬዎችን ከዚህ ቀደም አይተን ነበር፤ አንድ ቅጥፈት ቅጥፈት ከሆኑበት መገለጫዎቹ አንዱ የእርስ በእርስ ግጭት ነው፤ እስቲ ኢየሱስ በጴጥሮስ ዙሪያ የተናገረውንና በጴጥሮስ ዙሪያ የተደረገውን ክንውን የተለያየ ትረካና ዘገባ እንይ፦

ነጥብ አንድ
“ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም”
ጴጥሮስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ እስኪደው ድረስ ዶሮ እንደማይጮህ ተናግሮ ነበር፦
ዮሐ 13:38 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት። ነፍስህን ስለ እኔ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ “”ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም””።
ሉቃ22:34 እርሱ ግን። ጴጥሮስ ሆይ፥ እልሃለሁ፥ እንዳታውቀኝ “”ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዛሬ ዶሮ አይጮኽም”” አለው።
ማቴዎስ 26:34 ኢየሱስ፡- እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት “”ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”” አለው።

ነገር ግን ጴጥሮስ በመጀመሪያው ክህደቱ ዶሮ ጮኸ፦
ማርቆስ 14:66-68 ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፥ ጴጥሮስም እሳት ሲሞቅ አይታ ተመለከተችውና። አንተ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው።
እርሱ ግን። የምትዪውን አላውቅም አላስተውልምም ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ “”ዶሮም ጮኸ””።

ማነው የዋሸው ኢየሱስ ወይስ ተራኪዋቹ?

ነጥብ ሁለት
“ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”
ይህ ደግሞ ሌላ ዘገባ ነው፤ ጴጥሮስ ኢየሱስን ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ተናግሮ ነበር፦
14:30 ኢየሱስም። እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”” አለው።

የቅድሙ ዶሮ ምንም ሳይጮህ ነው፤ ይህ ደግሞ ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ነው፤ ለመሆኑ የቱን ነው ኢየሱስ በትክክል የተናገረው? “ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም” ወይስ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”?
ቀጥሎስ ለምን ዶሮ እስከ ሶስተኛው ክህደት ምንም አልጮኸም?
ማቴዎስ 26:69-75 ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ፡- አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው። እርሱ ግን፡- የምትዪውን አላውቀውም ብሎ በሁሉ ፊት ካደ። ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፡- ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች። ዳግመኛም ሲምል፡- ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ካደ። ጥቂትም ቈይተው በዚያ ቆመው የነበሩ ቀርበው ጴጥሮስን፡- አነጋገርህ ይገልጥሃልና በእውነት አንተ ደግሞ ከእነርሱ ወገን ነህ አሉት። በዚያን ጊዜ፡- ሰውየውን አላውቀውም ብሎ ሊራገምና ሊምል ጀመረ። ወዲያውም “”ዶሮ ጮኸ””። ጴጥሮስም፡- “”ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ”” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።

ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማንን እንመን?

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

በቀደሙት ሁለት ክፍሎች ስለ ጴጥሮስና ድርጊቱ የተገለፁት ዘገባዎች እርስ በእርስ እንዴት እንደሚፋለሱ አይተን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለ ኢየሱስ፣ ስለ ሁለቱ ሃዋርያት ስለ ጴጥሮስና እንድሪያስ እና ስለ መጥምቁ ዮሃንስ የተዛባውን ትረካ እንመለከታለን፦

ነጥብ አንድ
“ኢየሱስ”
የማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ከተጠመቀ በኃላ ወዲያውኑ ወደ ምድረ በዳ ወጥቶ አርባ ቀን ሰነበተ የለናል፦
ማርቆስ 1:12-13 “ወዲያውም””immediately” መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው። በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት።

በተቃራኒ የዮሃንስ ዘጋቢ ግን ኢየሱስ በዮሃንስ እጅ ተጠመቀ ይለን እና በሁለተኛው ቀን ሁለት ደቀመዛሙርቱ ቆመው ነበር ይለንና በሶስተኛ ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ላይ ነበረ ይለናል፦
1. የመጀመሪያው ቀን ፦
ዮሐ 1:32-33 ዮሐንስም እንዲህ ብሎ መሰከረ። መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ፤ በእርሱ ላይም ኖረ። እኔም አላውቀውም ነበር፥ ዳሩ ግን በውኃ አጠምቅ ዘንድ የላከኝ እርሱ። መንፈስ ሲወርድበትና ሲኖርበት የምታየው፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው አለኝ።
2. በሁለተኛው ቀን፦
ዮሐ 1:35 “በነገው”the next day” ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ቆመው ነበር፤
3. በሶስተኛው ቀን፦
ዮሐ 2:1 “በሦስተኛውም ቀን” በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ጥያቄአችን ኢየሱስ ከተጠመቀ በኃላ ወዲያውኑ ወደ ወደ ምድረ-በዳ 40 ቀን ፆመ ወይስ በሶስተኛው ቀን ቃና ዘገሊላ ሰርግ ላይ ተገኘ?

ነጥብ ሁለት
“ሁለቱ ሃዋርያት”
ሁለቱ ሃዋርያት ጴጥሮስና እንድርያስ ወንድማማቾች ሆነው ኢየሱስ ከተጠመቀ በኃላ መጥምቁ ዮሐንስ እርስ ቤት ከገባ በኃላ በገሊላ ባህር ላይ አሳ ሲያጠምዱ ኢየሱስ ለደቀመዝሙርነት እንደመለመላቸው የማርቆስ ዘጋቢ ይነግረናል፦
ማርቆስ 1:14-18 “”ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ”” ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ “”ወደ ገሊላ”” መጣ። “በገሊላ ባሕርም” አጠገብ ሲያልፍ “ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን” መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና። ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። “ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት”።

የዮሐንስ ዘጋቢ ግን በተቃራኒው ኢየሱስ ኢየሱስ ለደቀመዝሙርነት የመለመላቸው መጥምቁ ዮሃንስ እስር ቤት ሳይገባ ዮሃንስ አጠገብ ቆመው መጀመሪያ እንድርያስን መልምሎ ቀጥሎ ወንድሙን ጴጥሮስን መለመለ፦
ዮሐ 1:35-45 በነገው ደግሞ ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት “ቆመው” ነበር፥ ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ። እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ። ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት። ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት “ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ” ነበረ። እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም “ስምዖንን አገኘውና”። መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው። ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ። አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው።

ጥያቄአችን፦ የቱ ነው እውነተኛ ትረካ? ኢየሱስ ሁለቱን ሃዋርያት የመለመላቸው ከመጥምቁ ዮሃንስ በኃላ የሚለው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ሁለቱን ሃዋርያት የመመመላቸው መጥምቁ ዮሃንስ ቆሞ ነው የሚለው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሶስት
“መጥምቁ ዮሃንስ”
ኢየሱስ 40 ቀን ፆሞ ሲጨርስና ማስተማር ሲጀምርና ሁለቱን ደቀመዛሙርት ሲመለምል መጥምቁ ዮሃንስ እስር ቤት ታስሮ ነበር፦
ማርቆስ 1:14-15 “”ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ”” ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

ነገር ግን የዮሃንስ ዘጋቢ እንደሚተርክልን ደግሞ ኢየሱስ ሁለቱን ደቀመዛሙርት ከመለመለ በኃላ መጥምቁ ዮሃንስ እስር ቤት አልገባም፣ ጭራሽ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ያጠምቅ ነበር ይለናል፦
ዮሐ.3:22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “”ከደቀ መዛሙርቱ”” ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር። “ዮሐንስም” ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና “”ያጠምቅ” ነበር፥ እየመጡም ይጠመቁ ነበር “””ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና”””።

ጥያቄአችን፦ የቱ ነው እውነተኛ ትረካ? ኢየሱስ ሁለቱን ሃዋርያት ከመመልመሉ በፊት መጥምቁ ዮሃንስ ታስሮ ነበር የሚለን የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ሁለቱን ሃዋርያት ከመለላቸው በኃላ መጥምቁ ዮሃንስ እስር ቤት አልገባም የሚለው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ኢንሻላህ ይቀጥላል……

✍🏼ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማንን እንመን?

ክፍል አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

በዚህ ክፍል እንደ ቀድሞ ክፍሎች በኢየሱስና በሃዋርያት መካከል ያለውን መስተጋብር የሚተርከው ዘገባ የእርሰ በእርስ አለመስማማት የምናይበት ነው፦

ነጥብ አንድ
“ሃዋርያት”
የዮሃንስ ተራኪ ኢየሱስ አስሩን ሃዋርያት ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ ተሰብስበው በነበሩበት ቤት እንዳገኛቸውና አስራ አንደኛው ቶማስን በኃላ እንዳገኘው ይናገራል፦
ዮሐ 20:19 ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።
ዮሐ 20:24 ነገር ግን “ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ” ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም።

ከዚህ በተቃራኒ የማቴዎስ ተራኪ ደግሞ ሃዋርያት ኢየሱስን ያገኙት በሴቶቹ ጥቆማ ወደ ገሊላ ተራራ ሲሆን እዛ ያገኘው ደግሞ አሥራ አንዱንም ደቀ መዛሙርት እንደሆነ ይነግረናል፦
ማቴዎስ 28:10 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ፡- አትፍሩ፤ ሄዳችሁ “ወደ ገሊላ” እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፥ በዚያም “ያዩኛል” አላቸው።
ማቴዎስ 28:16 “”አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ””፥ ባዩትም” ጊዜ ሰገዱለት፤

ጥያቄአችን፦ ኢየሱስ ከትንሳኤው በኃላ ሃዋርያትን ያገኘው የት ነው? አስሩን በተዘጋ ቤት ወይስ አስራ አንዱን በገሊላ? ቶማስ ነበረ ወይስ አልነበረም?
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ግርም የሚለኝ አንድ ነገር አለ፤ ኢየሱስ ለምን መቅደላዊት ማርያም አትንኪኝ አላት? ስንል መልሱ፦ “ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ” የሚል ነው፤ እንዳትነካው የፈለገው ስላላረገ ከሆነ ማቴዎስ ለምንድን ነው መቅደላዊት ማርያምና ሌሎች ሴቶች “እግሩን ይዘው” ሰገዱለት” ብሎ ያለው? ያኔስ እግሩን ከመንካትም አልፈው ሲይዙት አርጎ ነበርን?
ማቴዎስ 28፥9-10 እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና። ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው “እግሩን ይዘው” ሰገዱለት። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ። አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፥ በዚያም ያዩኛል አላቸው።
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ”፤

ነጥብ ሁለት
“ይሁዳ”
የሉቃስ ዘጋቢ ሰይጣን ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ የገባው ከፋሲካ እራት በፊት እንደሆነ ይተርካል፦
ሉቃስ 22፥3 “ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ”፤
ሉቃስ 22፥7 ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ፤

የዮሃንስ ዘጋቢ በተቃራኒው ሰይጣን ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ የገባው በእራት ጊዜ እንደሆነ ይተርካል፦
ዮሐንስ 13 26-27 ኢየሱስም፦ እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው ብሎ መለሰለት። ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው፤
ቍራሽም ከተቀበለ በኋላ “”ያን ጊዜ”” ሰይጣን ገባበት።

ጥያቄአችን፦ የትኛው ትረካ ነው ትክክል? ሰይጣን ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ የገባው ከእራት በፊት የሚለው የሉቃስ ዘጋቢ ወይስ ሰይጣን ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ የገባው በእራት ጊዜ ነው የሚለው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማንን እንመን?

ክፍል አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

መግቢያ
የአዲስ ኪዳን ምሁር ሄርማን ቻርለስ በ 1890 AD ሲናገሩ፦ 5,800 የሚደርሱ የአዲስ ኪዳን ግሪክ እደ-ክታባት ይገኛሉ፤ እነዚህ እደ-ክታባት እርስ በእርሳቸው የቃላት ሆነ የትርጉም ልዩነት አላቸው፤ ለምሳሌ በሳይናቲከስና በቫቲካነስ እደ-ክታባት መካከል የ 3,036 የቃላትና የትርጉም ልዩነት አላቸው ብለዋል፤ ይህ ልዩነት የመጣው የአዲስ ኪዳን ስረ-መሰረት”orgion” ስለሌለና አሁን ያለት እደ-ክታባት የቅጂዎች ቅጂ ስለሆነ እንደሆነ ምሁራን ይናገራሉ፤ ይህ ልዩነት ጤናማ አለመሆን ብቻ ሳይሆን የክርስትናን ዶግማ ክፉኛ ይፈታተናል፤ ምክንያቱም እነዚህን አራት ወንጌላት ሃዋርያት አለመፃፋቸው ብቻ ሳይሆን በእነርሱ የዳቦ ስም የገለበጡት ፅሁፍም ችግር ስላለበት ነው፤ እስቲ ይህንን ልዩነት ዛሬ በስቅለቱ ዙሪያ ያሉትን ዘገባዎች እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የቤተ መቅደስም መጋረጃ”
የሉቃስ ዘጋቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ ይተርካል፦
ሉቃስ 23፥45-46 “የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ተቀደደ”። ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።

የማቴዎስ ዘገቢ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ ይተርካል፦
ማቴዎስ 27፥ 50-51 ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ “የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ”፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከተቀደደ በኃላ እንደሆነ የሚተርክልን የሉቃስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ ህይወቱን የሰጠው የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከመካከሉ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ከመቀደዱ በፊት እንደሆነ የሚተርክልን የማቴዎስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሁለት
“በሰቀሉትም ጊዜ”
ቅድሚያ የአራቱ ወንጌላት ተራኪዎች ጊዜን የሚቆጥሩት በዕብራውያን አቆጣጠር ብቻ መሆኑ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ ነው፤ የሮማውያን አቆጣጠር አንዳንዶች ይጠቀሙ ነበር የሚለው ቅጥፈት የታሪክ፣ የአውድና የባህል ማስረጃ የለውም፤ ይህ ቅጥፈት ግጭትን ለመደበቅ ሆን ብሎ ግምታዊ ነው፤ ለምሳሌ ማርቆስ የዕብራዊያን አቆጣጠሩ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለበት በዕብራውያን 3 ሰአት ነው ይለናል፦
ማርቆስ 15፥25 “”በሰቀሉትም ጊዜ” “”ሦስት ሰዓት”” ነበረ።
ማርቆስ 15፥33 “ስድስት ሰዓትም”” በሆነ ጊዜ፥ እስከ “”ዘጠኝ ሰዓት”” በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
34 “”በዘጠኝ ሰዓትም”” ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤

በዚህ ሁለም ይስማማል፤ ኢየሱስ ተሰቀለ የተባለው ከ ቀኑ ጠዋት 3 ሰአት ነው፤ ከዮሃንስ ዘገባ ጋር ፍጭቱን ከማየታችን በፊት ዮሃንስ የሚጠቀመው የዕብራውያን አቆጣጠር መሆኑን በአፅንኦትና በአንክሮት እንመልከት፦
ዮሐንስ 1፥40 መጥታችሁ እዩ አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ፥ በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ፤ “አሥር ሰዓት” ያህል ነበረ።
ዮሐንስ 4፥6 በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ “”ጊዜውም ስድስት ሰዓት”” ያህል ነበረ።

ድካም ያለበት ቀትር ስድስት ሰአት የዕብራውያን አቆጣጠር እንጂ የሮማውያን አቆጣጠር አይደለም፤ ምክንያቱም የሮማውያን ስድስት ሰአት የዕብራውያን ከምሽቱ 12 ሰአት አሊያም ከጎህ 12 ሰአት ነው፤ ይህን ሃቅ ይዘን የዮሃንስ ዘጋቢ ጋር ኢየሱስ ስድስት ሰአት ላይ እንኳን ሊሰቀል ይቅርና ገና ህዝቡ ስቀለው እያሉ ይጮኹ እንደነበር ይተርካል፦
ዮሃንስ 19፥14-15 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ “ስድስት ሰዓትም” የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ እነሆ ንጉሣችሁ አላቸው። እነርሱ ግን፦ አስወግደው፥ አስወግደው፥ “”ስቀለው”” እያሉ ጮኹ።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? በሰቀሉት ጊዜ 3 ሰአት ነበረ ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ 6 ሰአት ላይ ገና አልተሰቀለም ብሎ የሚተርከው የዮሃንስ ዘጋቢ?

ነጥብ ሶስት
“ሶስት ቀን”
ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።

የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?
መደምደሚያ
እንግዲህ ከላይ የዘረዘርናቸው የተለያዩ ትረካዎች የመጡት ከመለኮት ሳይሆን የሰው ንግግር መሆናቸውንም የክርስትና ምሁራንን ይስማሙበታል፤ ነገር ግን ይህ እርስ በእርስ የሚጋጨው ትረካ ከአምላክ ዘንድ የተገለጠ ግህደተ-መለኮት ነው ብለው በእጅ አዙር ይናገራሉ፤ ይህንን ነጥብ አምላካችን አላህ እንዲህ ይናገራል፦
79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡

በዚህም ከአላህ የወረደውን እውነት ካልተወረደው ውሸት ቀላቅለውታል፤ ይህም መበረዝ ይባላል፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን “ትቀላቅላላችሁ”? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን “ትደብቃላችሁ”?

መጽሐፍትና ከሰው መጽሐፍት ተቀላቅለው እያለ ቁርአን በነቢያችን ላይ ወረደ፣ ቁርአን ከጌታ የመጣውን እውነት ሊያረጋግጥ የየቀጠፉትን ደግሞ ሊያርም የወረደው፦
5:48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” مُصَدِّقًا እና በርሱ ላይ “ተጠባባቂ” وَمُهَيْمِنًا ሲሆን በውነት አወረድን፤

ቁርአን “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا “አረጋጋጭ” ሲሆን የቀድሞቹን መጽሐፍት ከአላህ ዘንድ የወረዱትን እውነትነት ያላቸው መሆኑን ሲያረጋግጥ የሰዎች ጽሁፍ የገቡበትን ደግሞ የምንመዝንበት “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ነው፣ ሙሃይሚን የሚለው ቃል “አራሚ”correcter” አሊያም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ፍቺ አለው፣ የቀድሞ ነቢያት የትምህርታቸው ጭብጥ ምን እንደነበረ የመጽሃፉን አስኳል ያስቀምጣል በዚህም የሰው ትምህርትን ከመለኮት ትምህርት የምንለይበት ሚዛን ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቀደር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

54፥49 *እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው*፡፡ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

የኢማን መሰረቶች ስድስት ሲሆኑ፤ እነርሱም፦ በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር ማመን ናቸው፤ ከስድስቱ የኢማን መሰረቶች ስድስተኛው በቀደር ማመን መሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ይህ በሐዲሰል ጂብሪል ተገልጿል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ "አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ"ﷺ" እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *"ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ "በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው" አሉ*።
قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏"‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏"‏

“ቀደር” قَدَر የሚለው ቃል “ቀደረ” قَدَرَ ማለትም “ቻለ” ወይም “ወሰነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውሳኔ” ማለት ነው፤ “ቀድር” قَدْر ማለት ደግሞ “ችሎታ” ማለት ነው፤ “አል-ቀዲር”  القَدِير ማለት “ሁሉን ቻይ” “ከሃሊ ኩሉ” ማለት ሲሆን ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ነው፤ “ተቅዲር” تَقْدِير ማለትም “ሁሉን ቻይነት” የአላህ ባህርይ ነው፤ አላህ “ሁሉን ቻይ” ነው ማለት “ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል” ማለት ነው፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
35፥1 *በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አምላካችን አላህ ሁሉን ቻይ ስለሆነ ነገርን ሁሉ በቀደር ፈጥሮታል፦
54፥49 *እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው*፡፡ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

"ልክ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ቀደር” قَدَر ሲሆን አላህ ነገርን ሁሉ አስቀድሞ በዕውቀቱ፣ በኪታቡ፣ በፈቃዱ እና በሥራው ቀድሮታል፤ የአላህ ቀደር የተለያየ "መራቲብ" مراتب ማለትም "ደረጃ"Degree" አሉት፤ እነዚህ መራቲበል ቀደር የሚባሉት፦ መርተበቱል ዒልሚያህ፣ መርተበቱል ኪታባህ፣ መርተበቱል መሺያህ እና መርተበቱል ኸልቅ ይባላሉ። እነዚህ ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እናያለን፦
ነጥብ አንድ
"የአላህ ዕውቀት"
በቁርአን ከተገለፁት የአላህ መልካም ስሞች መካከል “አል-ዐሊም” الْعَلِيم ወይም “አል-ዓሊም” الْعَٰلِم ሲሆን “ሁሉን ዐዋቂ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን ነገር ዐዋቂ ነው፦
33፥54 ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁ በእርሱ ይመነዳችኋል፤ *አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና*። إِن تُبْدُوا شَيْئًا أَوْ تُخْفُوهُ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

“ዒልም” عِلْم ማለት “ዕውቀት” ማለት ሲሆን የአላህ ዕውቀት የአላህ የራሱ ባህርይ ነው፤ ይህ የአላህ ዕውቀት በመሃይምነት ተቅድሞ መነሻ እና በመሃይምነት ተደምድሞ መዳረሻ የለውም፤ የአላህ ዕውቀት በጊዜ እና በቦታ እንደ ፍጡራን አይገደብም፤ ዕውቀቱ አይሻሻልም አይለወጥም።
ይህ የአላህ ዕውቀት በቁርአን ውስጥ የተገለፀው በሁለት መልኩ ነው፤ አንደኛው “ዒልሙል ገይብ” ሲባል ሁለተኛው “ዒልሙዝ ዛሂር” ይባላል።

“ዒልሙል ገይብ” عِلْمٌ الْغَيْب ማለት “ስውር ወይም እሩቅ አሊያም ረቂቅ ዕውቀት”subjective knowledge” ማለት ነው፤ “ገይብ” غَيْب ማለት “ባጢን” بَاطِن “ስውር” ወይም “እሩቅ” ማለት ሲሆን አላህ አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት፣ ከተከሰተ በኃላ እና በተከሰተ ጊዜ ያለውን ዕውቀት ነው፦
19፥64 «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ *”በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው”* ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፡፡ وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا

“ገይብ” በሶስት ይከፈላል፦
አንደኛው “አል-ገይቡል ማዲ” الغيبه المادي ሲሆን ያለፈ ክስተት ነው።
ሁለተኛው “አል-ገይቡል ሙዷሪዕ” الغيب المضارع ሲሆን እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ በአሁኑ ሰዓት ቀጣይነት ያለው ነገር ነው፤ አላህ በመካከል ማለትም ከህዋስ ባሻገር ለምሳሌ በልብ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል።
ሶስተኛው “አል-ገይቡል ሙስተቅበል” الغيب المستقبل ሲሆን መጪው ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚሆን ነው፤ ከፍጡራን በኃላ ወደ ፊት ምን እንሚከሰት ያውቃል።

“አል-ገይቡል ሙስተቅበል” ሁለት ደረጃ አለው አንዱ አላህ ብቻ የሚያውቀው ሲሆን “አል-ገይቡል ሙጥለቅ” الغيب المطلق ሲባል፣ ሁለተኛው ደግሞ አላህ ለሚልከው ነቢይ ሲያሳውቅ ያ የሚያሳውቀው የሩቅ ነገር ምስጢር “አል-ገይቡ አን- ኒስቢይ” الغيب النسبي ይባላል፤ አላህ ወደፊት የሚከሰተውን ክስተት አስቀድሞ ለሚወደው ነቢይ ይገልጥለታል፦
72፥26-27 «እርሱ *”ሩቁን ምስጢር”* ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡» عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
*ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

ስለዚህ አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት ያለው ዕውቀት “ዒልሙል ገይብ” ሲባል ከተከሰተ በኃላ የሚገልጠው ዕውቀት “ዒልሙዝ ዛሂር” ይባላል።
ዒልሙዝ ዛሂር” عِلْمٌ الظَهِير ማለት “ግልፅ ወይም ቅርብ አሊያም ተጨባጭ ዕውቀት”objective knowledge” ማለት ነው፤ “ዛሂር” ظَهِير ማለት “ሸሀደት” شَهَٰدَة “ግልፅ” ወይም “ቅርብ” ማለት ሲሆን አንድ ነገር ሲከሰት ነው።
አምላካችን አላህ ሁሉንም ነገር ማለትም መልካሙ ይሁን መጥፎ ነገር ከመከሰቱ በፊት ያውቀዋል፦
59፥22 *እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ "ሩቁን እና ቅርቡን ዐዋቂ የኾነ ነው"፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ ነው*፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۖ هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

ኢንሻላህ ስለ ቀደር ሁለተኛ ደረጃ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም