ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.2K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ወደ አዲስ ኪዳን ስንማትር የጌታ መልአክ ወደ ዘካርያስ የተላከ መልአክ ነው፥ ይህም መልአክ "እኔ በአምላክ ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" ብሎአል፦
ሉቃስ 1፥11 የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
ሉቃስ 1፥19 መልአኩም መልሶ፦ “እኔ በአምላክ ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር።

ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" የተባለውን ሁሉ ለኢየሱስ የሚሰጡ ሰዎች አዲስ ኪዳን ላይ ገብርኤል "የጌታ መልአክ" መባሉን ሲያውቁ ምን ይውጣቸው ይሆን? ይህ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም የታየው ነው፦
ማቴዎስ ፥1፥20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው።

ይህ ጥቅስ የጌታ መልአክ ኢየሱስ ሳይሆን ሰማያዊ ፍጡር የሆነ መልአክ ነው፥ የጌታ መልአክ ኢየሱስ ሲወለድ ለማብሰር መጥቶ ነበረ፦
ሉቃስ 2፥9 እነሆም "የጌታ መልአክ" ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።

የጌታ መልአክ ሰብአ ሰገል ከሄዱ በኋላ እና ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶታል፦
ማቴዎስ 2፥13 እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦
ማቴዎስ 2፥19 ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦

ኢየሱስ በሚያገለግልበት ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበር፦
ዮሐንስ 5፥4 አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና።

የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ ሐዋርያትን አወጣቸው፣ የጌታም መልአክ ፊልጶስን አናገረው፣ የጌታ መልአክ ጴጥሮስን አናገረው፣ የጌታ መልአክ ሄሮድስን መታው በትልም ተበልቶ ሞተ፦
የሐዋርያት 5፥19 የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና።
የሐዋርያት 8፥26 የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ "ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ፡፥" አለው።
የሐዋርያት 12፥7 እነሆም የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፥ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና፦ "ፈጥነህ ተነሣ" አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።
የሐዋርያት 12፥23 ለአምላክ ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ።

ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ ኢየሱስ ነው" የሚል በቀጥታ ሆነ በተዛዋዋሪ ማስረጃ እና መረጃ የለም፥ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊያን "ብሉይ ኪዳን ላይ "የጌታ መልአክ" የተባለው ኢየሱስ ነው" ብለው በቀጥታ ሆነ በተዛዋዋሪ ስላልተናገሩ "የጌታ መልአክ ኢየሱስ ነው" የሚለው ንግግር ምናባዊ ቅዠት እንጂ ነባራዊ እውነታ አይደለም። በቁርኣን "የጌታ መልአክ" ጂብሪል ነው፦
19፥19 «ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፥ እኔ የጌታሽ መልእክተኛ ብቻ ነኝ» አላት፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا

ጂብሪል መልእክተኛነቱ ለጌታ ከሆነ ልጅን የሚሰጥ አሏህ ስለሆነ ከጌታ ይዞት የመጣው መልእክት፦ "ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ" የሚል ነው፥ "መልአክ" مَلْأَك የሚለው ቃል "ለአከ" لَأَكَ ማለትም "ላከ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው። የጌታ መልአክ "ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ" "አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና" የሚል መልእክት ከጌታው ይዞ እንደመጣ የጌታ መልአክ ጂብሪልም "ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ" የሚለውን የጌታን መልእክት ከጌታ አሏህ ይዞ የመጣ ነው። ሊአሀበ" لِأَهَبَ የሚለው የግሥ መደብ "ፊዕሉል ሙዷሪዕ" فِعْل ٱلْمُضَارِع ሲሆን የሚጠጋው ወደ አሏህ ነው፦
42፥49 የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ

ተግባባን? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የያህዌህ መልአክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አሏህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

"የሰውን ልጅ የሚመስል" የሚል ቃል እንደየ ዐውዱ ለተለያየ ፍጡር ይውላል፥ ለምሳሌ፦ ለዳንኤል የተገለጠለት መልአክ "የሰው ልጅ የሚመስል" ተብሎአል፦
ዳንኤል 10፥16 እነሆም "የሰው ልጅ የሚመስል" ከንፈሬን ዳሰሰኝ።

ራእይ ላይም አንድ በስም ያልተገለጠ መልአክ "የሰውን ልጅ የሚመስል" ተብሎአል፦
ራእይ 14፥14 አየሁም እነሆም ነጭ ደመና፥ በደመናውም ላይ "የሰውን ልጅ የሚመስል" ተቀምጦአል፥ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው።

ይህ መልአክ በስም ያልተገለጠ ፍጡር መሆኑን የምናውቀው ሌላ ፍጡር መልአክ በትእዛዛዊ ግሥ፦ "ስደድ" "እጨድ" ብሎ ያዘዋል፦
ራእይ 14፥15 "ሌላ" መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ "የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድ እና እጨድ! የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና" ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። Καὶ ἄλλος ἄγγελος ἐξῆλθεν ἐκ τοῦ ναοῦ, κράζων ἐν φωνῇ μεγάλῃ τῷ καθημένῳ ἐπὶ τῆς νεφέλης Πέμψον τὸ δρέπανόν σου καὶ θέρισον, ὅτι ἦλθεν ἡ ὥρα θερίσαι, ὅτι ἐξηράνθη ὁ θερισμὸς τῆς γῆς.

እዚህ አንቀጽ "ሌላ" የሚለው የገባው ቃል "አሎስ" ἄλλος ሲሆን "ሌላ ተመሳሳይ ዓይነት"Another the same kind" ማለት ነው፥ ስለዚህ ታዛዡ መልአክ እና አዛዡ መልአክ ሁለቱም ተመሳሳይ ተፈጥሮ ያላቸው ፍጡራን መላእክት ናቸው። "ሄቴሮስ" ἕτερος እራሱ ተመሳሳይ ተፈጥሮ ላላቸው ይገባል፦
ማቴዎስ 8፥21 ከደቀ መዛሙርቱም "ሌላው"፦ “ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፡” አለው። ἕτερος δὲ τῶν μαθητῶν εἶπεν αὐτῷ Κύριε, ἐπίτρεψόν μοι πρῶτον ἀπελθεῖν καὶ θάψαι τὸν πατέρα μου.

"ሄቴሮስ" ἕτερος በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ተመሳሳይ ተፈጥሮ ላላቸው ውሏል፥ ዘፍጥረት 29፥10 ዘፍጥረት 30፥24 ተመልከት!
ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ዘካሪያስ ጋር የመጡት ሁለት መላእክት ተመሳሳይ ተፈጥሮ ያላቸው ፍጡራን መላእክት ናቸው፦
ዘካርያስ 2፥3 እነሆም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው "መልአክ" ወጣ፥ "ሌላም" መልአክ ሊገናኘው ወጣ። וְהִנֵּ֗ה הַמַּלְאָ֛ךְ הַדֹּבֵ֥ר בִּ֖י יֹצֵ֑א וּמַלְאָ֣ךְ אַחֵ֔ר יֹצֵ֖א לִקְרָאתֹֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሌላ" ለሚለው ገላጭ ቅጽል የገባው ቃል "አኼር" אַחֵ֔ר ሲሆን ሁለቱም ተመሳሳይ ተፈጥሮ ያላቸው ፍጡራን መላእክት መሆናቸውን አመላካች ነው፥ "ሌላ ሰው ይመጣል" ብል ፊተኛው ሰው እና ሌላው ሰው ተመሳሳይ ተፈጥሮ ያላቸው ፍጡራን ሰዎች አመላካች እንደሆነው ማለት ነው። ሌላይኛው መልአክ ፊተኛውን መልአክ፦ "ሩጥ" "በለው" በማለት በትእዛዛዊ ግሥ ያዘዋል፦
ዘካርያስ 2፥4 እንዲህም አለው፦ “ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎች እና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች"።

"እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ" ባዩ ያህዌህ ስለሆነ ሁለተኛው መልአክ፦ "እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ" ይላል ያህዌህ" በማለት ይናገራል፦
ዘካርያስ 2፥5 "እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ" ይላል ያህዌህ።

ሁለተኛው መልአክ "ይላል ያህዌህ" ማለቱ በራሱ ያህዌህ ሲናገር የሚያስተላልፍ ፍጡር መልአክ መሆኑ ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል፥ መልአኩም፦ "አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ! ኰብልዪ" ያህዌህ እንዳለ ይነግረናል፦
ዘካርያስ 2፥7 “አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ! ኰብልዪ” እንዲህ ይላልና ጸባዖት ያህዌህ። הֹ֥וי צִיֹּ֖ון הִמָּלְטִ֑י יֹושֶׁ֖בֶת בַּת־בָּבֶֽל׃ ס כִּ֣י כֹ֣ה אָמַר֮ יְהוָ֣ה צְבָאֹות֒

"እንዲህ ይላልና ጸባዖት ያህዌህ" ቁጥር 8 ላይ ቢኖርም ቁጥር 7 ላይ ያለውን መልአኩ "ይላልና" በማለት እየተናገረ ነው፥ መልአኩ በመቀጠል፦ "ልኮኛል" በማለት የያህዌህ መልእክተኛ መሆኑን ይናገራል፦
ዘካርያስ 2፥8 ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ "ልኮኛል"፤ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።
ዘካርያስ 2፥9 እነሆ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፤ ጸባዖት ያህዌም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

"ጸባዖት" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሰባኡት" צְבָא֖וֹת ከሚል የዕብራይስጥ የተገኘ ሲሆን "ሠራዊት" ማለት ነው፥ ያህዌህ የሠራዊቱ የመላእክት ጌታ መሆኑን ለማሳየት የገባ ነው። መልአኩም "ይላል ያህዌህ" በማለት ንግግሩን ይቀጥላል፦
ዘካርያስ 2፥10 "የጽዮን ልጅ ሆይ! እነሆ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና ዘምሪ ደስም ይበልሽ" ይላል ያህዌህ።

"በመካከልሽ እኖራለሁ" የሚለው ያህዌህ ነው፥ በቀጣይ "በመካከልሽም እኖራለሁ" የሚለው ሁለተኛው ፍጡር መልአክ ነው፦
ዘካርያስ 2፥11 በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ ያህዌህ ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፤ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ ጸባዖት ያህዌህም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።
ይህ የሚያሳየው መልአኩ ያህዌህ መሆኑን ሳይሆን የያህዌህ መልአክ የያህዌህ ወኪል፣ ልኡክ፣ እንደራሴ መሆኑን ነው። ለምሳሌ፦ የያህዌህ ታቦት የሰው እጅ ሥራ ፍጡር ነው፥ ግን ታቦቱ የያህዌህ መገኘት እንደ ራሴ ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥2 ንጉሡ ነቢዩን ናታንን፦ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፥ የያህዌህ ታቦት ግን በመጋረጆች ውስጥ እንደ "ተቀመጠ" እይ" አለው።

በመጋረጃ ድንኳን የተቀመጠው የያህዌህ ታቦት ሆኖ ሳለ ያህዌህ ግን "በድንኳን እና በማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት "አልተቀመጥሁምና" ብሎአል፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥5 ሂድ፥ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው፦ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳን እና በማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት "አልተቀመጥሁምና" አንተ የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም"።

የያህዌህ ታቦት የያህዌህ መገኘት እንጂ ታቦቱ ያህዌህ እንዳልሆነ ሁሉ የያህዌህ መልአክም የያህዌህ መገኘት እንጂ ያህዌህ በፍጹም አይደለም። የያህዌህ ታቦት ወደ ሰፈሩ በገባ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን፦ "አምላክ ወደ ሰፈሩ ገብቷል" አሉ፦
1 ሳሙኤል 4፥6 የያህዌህም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አስተዋሉ። וַיֵּ֣דְע֔וּ כִּ֚י אֲרֹ֣ון יְהוָ֔ה בָּ֖א אֶל־הַֽמַּחֲנֶֽה׃
1 ሳሙኤል 4፥7 ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው፦ "አምላክ ወደ ሰፈሩ ገብቷል" አሉ። וַיִּֽרְאוּ֙ הַפְּלִשְׁתִּ֔ים כִּ֣י אָמְר֔וּ בָּ֥א אֱלֹהִ֖ים אֶל־הַֽמַּחֲנֶ֑ה

ሁለቱም ጥቅስ ላይ "ገባ" ለሚለው የገባው ቃል "ባ" בָּ֖א ሲሆን "መጣ" ማለት ነው፥ ወደ ሰፈሩ የመጣው ማን ነው? ታቦት ወይስ አምላክ? የታቦቱ መምጣት የአምላክ መምጣት እንጂ ታቦቱ አምላክ ካልሆነ የመልአኩ መኖር የአምላክ መኖር እንጂ መልአኩ አምላክ አይደለም። ሙሴ በታቦቱ መጓዝ እና ማረፍ ጊዜ ያህዌህን ያነጋግር ነበር፦
ዘኍልቍ 10፥35 ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ ያህዌህ ሆይ! ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ" ይል ነበር። ባረፈም ጊዜ፦ ያህዌህ ሆይ! ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ" ይል ነበር።

ሙሴ "ተነሳ" "ተመለስ" እያለ በሁለተኛ መደብ ታቦቱን አላኮ እና አስታኮ መናገሩ ታቦቱ ያህዌህ ነው ወይስ የያህዌህ ነው? ታቦቱ እኮ የሙሴ የእጅ ሥራ ነው፦
ዘዳግም 10፥3 ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ።

"መልአክ" በዕብራይስጥ "ማላህ" מֲלְאָךְ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ "መላሆት" מַלְאֲכוּת ማለት "መልእክት" ማለት ሲሆን መልእክተኛው ከላኪው ተቀብሎ የሚናገረው መልእክት የላኪው እስከሆነ ድረስ "በመካከልሽ እኖራለሁ" የሚለውን መልእክት መልአኩ ቢናገርም እንኳን የሚያስረዳው መልአኩ ላኪው ያህዌን መሆኑን ሳይሆን መልአኩ መልእክት አድራሽ መሆኑን ብቻ ነው እንጂ ፍጡር መልአክ ፈጣሪ አይሆንም። ፈጣሪ ፈጣሪ ከላከ ሁለት ፈጣሪ ይሆናልና አያስኬድም፥ ፈጣሪ ግን አንደ ነው። አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፦
22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አሏህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

"ለዘካሪያስ የተገለጠው ሁለተኛው መልአክ ኢየሱስ ነው" የሚለው ትምህርት እንዲህ ድባቅ ይገባል፥ ኢየሱስን ብሉይ ኪዳን ላይ አስገብቶ መልአክ የማድረግ አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች ለአሁኑ አልተሳካላቸውም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ለመጪው ትውልድ የሚሆን መተግበሪያ"Application" እና ድረ ገጽ"Website" ሁለት ወንድሞች ሠርተው አበርክተዋል። በዱዓችሁ አትርሷቸው!

ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=net.wahidcom&pli=1

ለiOS ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/wahid-islamic-apologist/id6743720489?platform=iphone
ብዙ ባል በባይብል

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

"ሞኖስ" μονός ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን "ጋሞስ" γάμος ማለት "ጋብቻ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ሞኖ ጋሞስ" μονό γάμος ማለት "የአንድ ለአንድ ጋብቻ"Monogamy" ማለት ነው።
"ፖሎስ" πολλός ማለት "ብዙ" ማለት ሲሆን "ጋሞስ" γάμος ማለት "ጋብቻ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ፖሎ ጋሞስ" πολλό γάμος ማለት "የአንድ ለብዙ ጋብቻ"Polygamy" ማለት ነው።
የአንድ ለብዙ ጋብቻ እራሱ ለሁለት ይከፈላል፥ አንዱ "ፖሎ ጉኔ" πολλό gunḗ ሲሆን "አንድ ወንድ ብዙ ሚስት"Polygyny" ማለት ነው። በቁርኣን የተፈቀደው ፖሎ ጉኔ ነው፦
4፥3 ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስት፣ አራት አራት አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

አለማስተካከልን ከተፈራ ሞኖ ጋሞስ ይበረታታል። በባብይል ፖሎ ጉኔ የተፈቀደ ነው። ይህንን መጣጥፍ ይመልከቱ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/2964

የአንድ ለብዙ ጋብቻ ሁለተኛው ደግሞ "ፖሎ አነር" πολλό ሲሆን "አንድ ሴት ብዙ ባል"Polyandry"ማለት ነው፥ ፖሎ አነር በቁርኣን ክልክል ሲሆን በጳውሎስ ትምህርት የተፈቀደ ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥12 ዲያቆናት የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ። διάκονοι ἔστωσαν μιᾶς γυναικὸς ἄνδρες,

"የአንዲት ሴት ባሎች"Let the deacons be the husbands of one wife" የሚለው ይሰመርበት! "ባሎች" የሚለው ቃል በግሪኩም በነጠላ "አኔር" ἀνήρ ሳይሆን በብዙት ቁጥር "አንድሬስ" ἄνδρες ነው፥ "አንዲት ሴት" ብዙ ዲያቆናት ባሎች ማግባትን ጳውሎስ ስለፈቀደ በባይብል ፖሎ አነር አለ ማለት ነው። ፖሎ ጉኔን የምትቃወሙ ምን ይውጣችሁ ይሆን?
ባል እና ሚስት እያወሩ ነው...

ሚስት፦ "ፍቅሬ ሴት ከብዙ ወንዶች ጋር ስትዘወጅ ሐራም ነው፥ ወንድ ግን ከአራት ሴቶች ጋር ሲዘወጅ ሐላል ነው። ለምንድ ነው?

ባል፦ "አየሽ ፍቅሬ አንድ የቁልፍ ጋን በአራት የተለያየ ቁልፍ የሚከፈት ከሆነ ጋኑ ችግር አለበት ማለት ነው፥ አንድ ቁልፍ ግን አራት የተለያዩ ጋኖችን መክፈት ከቻለ ምርጥ ቁልፍ ነው ማለት ነው"።
አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኩፋሮች የሚያነሱትን ጥያቄዎች ከበቂ መልስ እና ከበቂ ማብራሪያ ጋር እንዲሁ የእኛን በጨዋ ደንብ ያቀረብነውን ሙግት ይጎብኙት፦
ክፍል አንድ
ክፍል ሁለት
ክፍል ሦስት
ክፍል አራት
ክፍል አምስት
ክፍል ስድስት
ክፍል ሰባት

ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆን ዘንድ ኢንሻላህ ሼር አርጉት!
ስም ሰጠው

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

በመጻሕፍቱ ማመን ከእምነት ማዕዘናት አንዱ ነው፥ መርየም በጌታዋ መጻሕፍት አምናለት። "ሶደቀት" صَدَّقَتْ የሚለው "አመነት" آمَنَتْ በሚል የመጣ ነው፦
66፥12 በጌታዋ ቃላት እና በመጻሕፍቱ አረጋገጠች፥ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِينَ

መርየም በጌታዋ ቃላት አምናለች፥ የጌታዋ ቃላት "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" የሚል ነው፦
3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

መርየም ከአሏህ በኾነው ቃላት ከተበሠረችበት ቃላት አንዱ ልጇ ስሙ "አል መሢሕ ዒሣ" መባሉ ነው፥ "ዒሣ" عِيسَى የሚለው ስም የልጇ የተጸውዖ ስሙ"Proper Name" ሲሆን "አል መሢሕ" الْمَسِيح ደግሞ የማዕረግ ስሙ"Generic Name" ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ የሚለው ስም "ያህ" יָהּ እና "ሹዋ" יָשַׁע ከሚል ሁለት የዕብራይስጥ ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ያህ" יָהּ የሐሸም ምጻረ ቃል ሲሆን "የሻ" יָשַׁע ማለት ደግሞ "መድኃኒት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ ማለት "ያህ መድኃኒት ነው" ማለት ነው፥ "ኤልየሻ" אֱלִישָׁע ማለት "ኤል" אֵל እና "የሻ" יָשַׁע ከሚል ቃል የተዋቀረ ሲሆን "ኤል መድኃኒት ነው" ማለት ነው። በግዕዝ "ኢየሱስ" የተባለው "ያህሹዋ" እና "ኤልሳዕ" የተባለው "ኤልየሻ" የፍጡራን ስም ሲሆኑ "ያህ" እና "ኤል" ለፍጡራን በመነሻ ወይም በመዳረሻ ምጻረ ቃል ሆነው ይገባሉ፥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ የሚል ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የያዘው የነዌ ልጅ ኢየሱስ ነው፦
ኢያሱ 1፥1 እንዲህም ሆነ የያህዌህ ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ ያህዌህ የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ያህሹዋን እንዲህ ብሎ ተናገረው። וַיְהִ֗י אַחֲרֵ֛י מֹ֥ות מֹשֶׁ֖ה עֶ֣בֶד יְהוָ֑ה וַיֹּ֤אמֶר יְהוָה֙ אֶל־יְהֹושֻׁ֣עַ בִּן־נ֔וּן מְשָׁרֵ֥ת מֹשֶׁ֖ה לֵאמֹֽר׃

የነዌ ልጅን በዐማርኛ ላይ "ኢያሱ" ብለው ስም ያወጡለት "ኢየሱስ" የሚባለው የማርያም ልጅ የፍጡር ስም መሆኑን ለመደበቅ እንጂ ግዕዙ ላይ የመጽሐፉ ስም እራሱ "መጽሐፈ ኢያሱ" ሳይሆን "ኦሪት ዘኢየሱስ" ነው፥ ግዕዙ ላይ "እግዚአብሔር ተናገሮ ለኢየሱስ ወልደ ነዌ" ይለዋል። በ 280 ቅድመ ልደት ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ኮይኔ የተረጎሙትም ሰባው ሊቃናት ያስቀመጡት "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብለው ነው፥ ሉቃስ የነዌ ልጅ ኢየሱስን "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብሎ አስቀምጦታል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥45 አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው አምላክ በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ "ከ-"ኤሱስ" ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። ἣν καὶ εἰσήγαγον διαδεξάμενοι οἱ πατέρες ἡμῶν μετὰ Ἰησοῦ ἐν τῇ κατασχέσει τῶν ἐθνῶν, ὧν ἐξῶσεν ὁ Θεὸς ἀπὸ προσώπου τῶν πατέρων ἡμῶν ἕως τῶν ἡμερῶν Δαυείδ·
ይህንን የፍጡር ስም መልአኩ ገብርኤል ለማርያም በዕብራይስጥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ ሲላት ሉቃስ በዘገባው ደግሞ "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብሎ አስቀምጦታል፦
ሉቃስ 1፥31 እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም "ኤሱስ" ትዪዋለሽ። καὶ ἰδοὺ συλλήμψῃ ἐν γαστρὶ καὶ τέξῃ υἱόν, καὶ καλέσεις τὸ ὄνομα αὐτοῦ Ἰησοῦν.

በዕብራይስጥ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ በግሪክ ኮይኔ "ኤሱስ" Ἰησοῦς የተባለው ስም አንዱ አምላክ በመልአኩ ለማርያም ልጅ የሰጠው ስም ነው፦
ፊልጵስዩስ 2፥9 በዚህ ምክንያት ደግሞ አምላክ ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው።

ጥቅሱ "ስሙን ሰጠው" አይልም፥ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን "ኢየሱስ የአብ ሲሆን ለወልድ ሰጠው" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ።
፨ ሲጀመር "ስም ሰጠው" ስለተባለ የተሰጠው ስም "የሰጪውን ነው" ማለት አይደለም። ለምሳሌ፦
ዳንኤል 2፥37 አንተ ንጉሥ ሆይ! የሰማይ አምላክ መንግሥትን፣ ኃይልን፣ ብርታትን እና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።

አምላክ ለናቡከደነጾር "ክብር ሰጠው" ማለት የናቡከደነጾር ክብር "የአምላክ ክብር ነው" ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም አምላክ "ክብሬን ለሌላ አልሰጥም" ብሎአልና፦
ኢሳይያስ 42፥8 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ስሜ ይህ ነው። ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።

በተመሳሳይ አንዱ አምላክ ለማርያም ልጅ የሰጠው ስም የራሱን ስም ሳይሆን ፍጡራን ሲጠቀሙበት የነበረውን የሰው ስም እንጂ መለኮታዊ ስሙን ለማንም ፍጡር አይሰጥም።

፨ ሲቀጥል "በዚህ ምክንያት" የሚል አመልካቻዊ ምክንያት እራሱን ዝቅ በማድረጉ ያገኘው ስም ወይም ዝና ነው። ለምሳሌ፦
1ኛ ነገሥት 1፥47 የንጉሡም ባሪያዎች ገብተው፦ "አምላክ የሰሎሞንን ስም ከስምህ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ" ብለው ጌታችንን ንጉሡን ዳዊትን ባረኩ፤ ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።

የሰሎሞንን ስም ከስም የበለጠ መሆኑን ዝነኛ መሆንን እንጂ በባሕርይ ሰው ከመሆን እንደማያዘልል ሁሉ የኢየሱስ ስም ከስም የበለጠ መሆኑ ዝነኛ መሆንን እንጂ በባሕርይ ሰው ከመሆን አያዘልለውም፦
1ኛ ነገሥት 3፥12 እኔ እንደ ቃል አድርጌልሃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም የሚመስልህ ከአንተ በፊት እንደሌለ ከአንተም በኋላ እንዳይነሣ አድርጌ ጥበበኛ እና አስተዋይ ልቡና ሰጥቼሃለሁ።

ሰሎሞንን የሚመስል ከሰሎሞን በፊት እንደሌለ ከሰሎሞን በኋላ እንደማይነሳ መነገሩ ሰሎሞን በባሕርይ ሰው ከመሆን ዘሎ መልአክ አሊያም አምላክ እንዳማያደርገው ሁሉ አምላክ ኢየሱስን ያለ ልክ ከፍ ከፍ ማድረጉ ኢየሱስን በባሕርይ ሰው ከመሆን ዘሎ መልአክ አሊያም አምላክ አያደርገውም። ከዚህ ይልቅ "ከፍ ከፍ" ለማለት የገባው ሥርወ ቃል "ሁፕሶ" ὑψόω ሲሆን በአምላክ ቀኝ ከፍ ማለቱ ለማሳየት የገባ ቃል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥33 ስለዚህ በአምላክ ቀኝ "ከፍ ከፍ" አለ። τῇ δεξιᾷ οὖν τοῦ θεοῦ ὑψωθεὶς
የሐዋርያት ሥራ 5፥31 አምላክ ይህን ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ "ከፍ ከፍ" አደረገው። τοῦτον ὁ Θεὸς Ἀρχηγὸν καὶ Σωτῆρα ὕψωσεν τῇ δεξιᾷ αὐτοῦ τοῦ δοῦναι μετάνοιαν τῷ Ἰσραὴλ καὶ ἄφεσιν ἁμαρτιῶν.

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "ከፍ ከፍ" አለ ለሚል የገባው የግሥ መደብ በተመሳሳይ "ሁፕሶ" ὑψόω ነው፥ በእርግጥ ራሱንም የሚያዋርድ አማኝ ሁሉ ከፍ ይላል፦
ማቴዎስ 23፥12 ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።
መዝሙር 37፥34 ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ኤፌሶን 2፥7 በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

ተግባባን አይደል? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ ሆይ! ሙሥሊም ያልሆኑ አካላትን ወደ ኢሥላም በንጽጽር ለመጣራት "የተደበቀው እውነት" እና "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" የተባሉት መጻሕፍት በድጋሚ እንዲታተም በጠየቃችሁን እና በወተወታችሁን መሠረት አንብቡ እና ለክርስቲያኖች አስነብቡ!

መጻሕፍቱን የምትፈልጉ አገር ውስጥ ያላችሁ ሆነ ከአገር ውጪ ያላችሁ በ +251928444408 ዐብዱ መርካቶ ብላችሁ በቀጥታ አሊያም በዋትሳፕ ታገኙታላችሁ፥ እንዲሁ በቴሌ ግራም ይህንን ዩዘር ኔም በመጠቀም http://tttttt.me/merkatozon ማግኘት ትችላላችሁ።

እንዲሁ ቤተል ተቅዋ መሥጂድ ሥር ስለሚገኝ ኩብራ ብላችሁ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፦ +251911663699

አየር ጤና አንሷር መሥጂድ ሥር፦ 0963796354

ለብዙዎች ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ሁሉም ቦታ ሼር አርጉት!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" "መገዛት" "እራስን መስጠት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም "ታዘዝ" ሲለው እርሱም፦ "ታዘዝኩ" አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ "ታዘዝ" ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ "ታዘዝኩ" አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዝ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊም" أَسْلِمْ ሲሆን "ታዘዝኩ" ለሚለው ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፥ "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ለአንድ አምላክ ብቻ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ "ታዘዙ"፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام በግንባር እና በጥሬ ትርጉም ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአሏህ ሰጠው፥ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ሰጡ» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ወጅህ" وَجْه የሚለው ቃል "ወጁሀ" وَجُهَ ማለት "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "ፊት" "ማንነት"Person" ማለት ነው፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ"Person" ማለት ነው። "Person" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ከሚል የግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ሲሆን "ፊት" ማለት ነው፥ ስለዚህ "ፊት" ሲባል "ማንነት" "መለያ" ማለት ከሆነ "ፊቴን ለአሏህ ሰጠው" ማለት "እራሴን ለአሏህ ሰጠው" "አካሌን ለአሏህ ሰጠሁ" ማለት ነው። "ሰጠው" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፦
2፥112 አይደለም፤ እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "የሰጠ" ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام ለሚለው ቃል ሥርወ ቃል ነው፥ እራስን ለአንዱ አምላክ መስጠት የኢብራሂምንም መንገድ ነው፦
4፥125 እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "ከሰጠ" እና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ከሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው። "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "ደነገገ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ" "ሃይማኖት" ማለት ነው፥ "ሃይማኖት" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሃይማነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሥርወ እምነት" "አንቀጸ እምነት" ማለት ነው። ከአንዱ አምላክ በግልጠተ መለኮት የሚመጣው መርሕ፣ ሥርወ እምነት፣ አንቀጸ እምነት በአምልኮ ለአንዱ አምላክ "መታዘዝ" ብቻ እና ብቻ" ነው፥ በአምልኮ ለአንዱ አምላክ ከመታዘዝ ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፥ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ
በባይብል አንድ ሃይማኖት እንዳለ እና ይህም ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ እንደተገለጠ ይናገራል፦
ኤፌሶን 4፥5 አንድ ጌታ "አንድ ሃይማኖት" አንዲት ጥምቀት።
ይሁዳ 1፥3 ለቅዱሳን "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት" እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

ቅዱሳን የተባሉት ቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ናቸው፥ የመጀመሪያው ነቢይ አዳም ነው፦
ኤፌሶን 3፥6 "ለቅዱሳን ሐዋርያት እና ለነቢያት" በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።
ቀሌምንጦስ 1፥40 በዚህ ጊዜ ንጉሥነትን እና ነቢይነትን ሠጠው በክብር መንበር ላይም አስቀመጠው።
ቀሌምንጦስ 1፥43 በዚህ ጊዜ መላእክት የእግዚአብሔር ቃል፦ "አዳም ሆይ! እነሆ ንጉሥ፣ ካህን እና "ነቢይ" መስፍን ለፍጥረት ሁሉ ገዢ ስላንተ በፈጠርሁት ሁሉ እንድትሆን አደረግሁ...ሲል ሰሙ።

ከ 451 እስከ 521 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ያዕቆብ ዘሥሩግ"Jacob of Serugh" በእንተ ወላዲተ አምላክ በሚል መጽሐፉ ላይ አዳም ነቢይ እንደነበረ ተናግሯል፦
"አዳም ድንግል ሔዋንን አስገኝቷል፥ "የሕይወት እናት" ብሎ ጠርቷታል። እርሱ ነቢይ ነበረ"።
On the Mother of God (Jacob of Serugh) Homily (I)1 Number 634

ከአዳም ጀምሮ በመገለጥ የተሰጠ አንድ ሃይማኖት አለ፥ ይህንን ሃይማኖት ባይብል በግልጽ ስለማያስቀምጥ አይሁዳውያን ከኪሳቸው "የሁዲ ሃይማኖት" ሲሉ ክርስቲያኖች ከኪሳቸው "የክርስትና ሃይማኖት" ይላሉ። ነገር ግን የሁዱ በይሁዳን ነገር የመጣ "አይሁድ" የሚል ዘር እንጂ ሃይማኖት አይደለም፥ "ክርስትና" የሚለውንም ቃል ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያት የማያውቁት ሲሆን "ክርስትና" ብሎ ለመጀመርያ ጊዜ ያሰፈረው አግናጥዮስ ዘአንጾኪያው"Ignatius of Antioch" በ 110 ድኅረ ልደት ነው።
ስለ ኢሥላም ግን በግሥ መደብ ደረጃ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ይገኛል፦
መዝሙር 56፥12 አምላክ ሆይ! እኔ የምስጋና ስእለት "የምሰጥህ" ከእኔ ዘንድ ነው። עָלַ֣י אֱלֹהִ֣ים נְדָרֶ֑יךָ אֲשַׁלֵּ֖ם תֹּודֹ֣ת לָֽךְ׃

"የምሰጥ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አሻሌም" אֲשַׁלֵּ֖ם ሥርወ ቃሉ "ሸለም" שָׁלַם ሲሆን "ታዘዘ" "ተገዛ" የሚል ነው፥ በዐረቢኛ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ ሲባል እራስን ለአሏህ መስጠት ነው፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አሏህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

"የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! አንድ ሰው "ከአንዱ አምላክ ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ሲል ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፥ "ስእለት" ማለት "ብፅዓት" "ስጦታ" ማለት ሲሆን ለአምላክ የሚሰጠው ትልቁ ስእለት ውስጥን መስጠት ነው፦
ሉቃስ 11፥40 እናንት ደንቆሮዎች የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።

"በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ" ሲል ለአምላክ ውስጥን መስጠት ኢሥላም ይባላል። አምላክ ያለውን ሁሉ ማድረግ እና መታዘዝ ኢሥላም ይባላል፦
ዘጸአት 24፥7 የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፦ “አምላክ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም" አሉ።

ለአንዱ አምላክ በአምልኮ መገዛት ኢሥላም ከሆነ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ነፍስን ለአምላክ የማስገዛት እሳቤ አለ፦
መዝሙር 62፥1 ነፍሴ ለአምላክ የምትገዛ አይደለችምን?
መዝሙር 2፥11 ለአምላክ በፍርሃት ተገዙ! በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
መዝሙር 100፥2 በደስታም ለአምላክ ተገዙ! በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ።
ያዕቆብ 4፥7 እንግዲህ ለአምላክ ተገዙ! ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።

ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል........

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام ማዕዘናቱ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ናቸው፥ ለምሳሌ፦ ጦም ከነቢያችን"ﷺ" በነበሩት ነቢያት እና ሕዝቦቻቸው እንደተደገገ አሏህ ይናገራል። ወደ ነቢያት መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረደ፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጦም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
21፥73 በትእዛዛችንም ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው፡፡ ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን፡፡ ለእኛ ተገዢዎችም ነበሩ፡፡ وَجَعَلْنَاهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا وَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِمْ فِعْلَ الْخَيْرَاتِ وَإِقَامَ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءَ الزَّكَاةِ ۖ وَكَانُوا لَنَا عَابِدِينَ

"በትእዛዛችን" የሚለው ይሰመርበት! ይህም ትእዛዝ ኢሥላም ሲሆን በኢሥላም ማዕቀፍ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ከአሏህ የተወረደ ግልጠተ መለኮት ስለሆነ "ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን" ይለናል፥ ይህንን መመሪያ የተከተሉት ለአሏህ ተገዢዎችም ነበሩ። ከሰው ወገን ለመጀመርያ አሏህ ወሕይ ያወረደው ወደ አደም ነው፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን ጊዜን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ "ከዚህ በፊት" አሏህ በአደም ጊዜ "ታዛዦች" ብሎ ሰየመ፦
22፥78 "እርሱ "ከዚህ በፊት" "ሙሥሊሞች" ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን የአደምን ጊዜ ያስታውሰናል። "እርሱ" የተባለው "አሏህ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ተውላጠ ስም ነው፥ አሏህ ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን ሲያወርድ "ሙሥሊሞች" ብሎ የጠራን ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት አንዱን አምላክ በአምልኮ "ታዛዥ" ማለት ነው፦
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፥ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን»። وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት እራሱ ለአሏህ በአምልኮ የሚታዘዙ ናቸው፦
3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድም በግድም ለእርሱ "የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአሏህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች በግዴታ አሏህ ላስቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ የታዘዙ ሲሆኑ በውዴታ ደግሞ ለሸሪዓው ሕግ ይታዘዛሉ። "ከርህ" كَرْه ማለት "ግዳጅ" ማለት ሲሆን "ጦውዕ" طَوْع ማለት ደግሞ "ፈቃደኝነት" ማለት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች ለአሏህ በግዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَام كَوْنِيّ ሲባል በውዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَام شَرْعِيّ ይባላል። "ሰው ሲወለድ ሙሥሊም ነው" የሚባለው አል ኢሥላም ከውኒይ ሲሆን አምላካችን አሏህ በሸሪዓህ "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲለን አል ኢሥላም ሸርዒይ ነው፦
5፥44 እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን "የታዘዙ" ማለት ነው። ኢብራሂም ወደ ጌታው በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ነው፦
37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ!፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 ወደ አሏህ "በ-ንጹሕ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ንጹሕ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠሊም" سَلِيم ነው፥ አንድ በኢሥላም ልቡን ሢያሠልም ልቡ ውስጥ "ሠላም" سَلَام ስላለ ልቡ ሠሊም ስትሆን እርሱ ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ይሆናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 17027
ዐምር ኢብኑ ዐባሣህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ኢሥላም ምንድን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም"ﷺ"፦ "ልብህን ለአሏህ ዐዘ ወጀል ማሥለም ነው" አሉት"። عَنْ عَمْرِو بْنِ عَبَسَةَ قَالَ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَا الْإِسْلَامُ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُسْلِمَ قَلْبُكَ لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

አንድ ሰው ልቡን ለአሏህ ካሠለመ ጀነት ይገባል፥ ልቡን ለአሏህ ያሠለመ ሰው ከጀሀነም ይድናል፦
አል አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 260
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው፥ እስካልሠለማችሁ ድረስ ጀነት አትገቡም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لاَ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ حَتَّى تُسْلِمُوا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 163
ዐምር ኢብኑ አል ዓስ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠለመ ዳነ"። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ قَدْ أَفْلَحَ مَنْ أَسْلَمَ ‏"‏ ‏.‏

"ሠሊመ" سَلِمَ ማለት "ታዘዘ" "ሰጠ" "ሰላም ሆነ" ሲሆን በዕብራይስጥ "ሸሊመ" שׁ־ל־ם ነው፥ በዕብራይስጥ "ሙሽሊም" משלם ማለት "ታዛዥ" "ሠላማዊ" "እራሱን የሰጠ" ማለት ነው፦
ኢዮብ 22፥21 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። הַסְכֶּן־נָ֣א עִמֹּ֑ו וּשְׁלם בָּ֝הֶ֗ם תְּֽבֹואַתְךָ֥ טֹובָֽה׃

"ሰላምም ይኑርህ" የግሥ መደብ "ዩሻልም" וּשְׁלם ሲሆን ሥርወ ቃል "ሸለም" שָׁלַם ነው፥ ባይብል ሀብ"Bible Hub" ይህንን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦ "በዐረቢኛ "ሠሊም" سَلِمَ ሲሆን "ደህና መሆን" "አስተማማኝ" "ከጥፋት ነጻ" "የበላይ" "መስጠት" "መስጠት ወይም ራስን ማስረከብ በተለይ ለአምላክ" በሥማዊ ግሥ "ሙሥሊም" እና በግሥ መሠረት "ኢሥላም" በመደበኛ ለአምላክ መታዘዝ ነው"Arabic سَلِمَ be safe, secure, free from fault, make over, resign to, resign or submit oneself, especially to God, whence participle Muslim, and infinitive Islam properly submission to God."

በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ዓይነት ቃል እና አሳብ ከቀረ ነቢያቱ ከአምላክ በቀጥታ በመጣላቸው በሥርወ መሠረቱ ምን ሊኖር እንደሚችል መገመት አያዳግትም፥ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ግልጠተ መለኮት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልእክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት የተላለፈበት ሰነድ በዚህ ዘመን የለም። ጌታዬ ሆይ! ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፥ በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን፦
12፥101 «ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፡፡ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፡፡ ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፡፡ በመልካሞቹም አስጠጋኝ» አለ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ ۚ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ
7፥126 «የጌታችንም ተአምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን» وَمَا تَنقِمُ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِآيَاتِ رَبِّنَا لَمَّا جَاءَتْنَا ۚ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ሙሥሊም አርጎ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በቅርብ ቀን ኢንሻ አሏህ!
ማንም ሚሽነሪ ተነስቶ "ኢየሱስ ያድናል" በማለት የኩፍር እና የሺርክ ጎጆ ሠርቶ አይፈለፍላትም።
ሸምሥ እና ቀመር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ

"ሸምሥ" شَّمْس ማለት "ፀሐይ" ማለት ሲሆን "ሸምሥ" شَّمْس የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በሡረቱል በቀራህ ምዕራፍ 2 ቁጥር 258 ላይ ነው፦
2፥258 ወደዚያ አሏህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን? ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል፥ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ እና መልስ አጣ፥ አሏህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

"ሸምሥ" شَّمْس የሚለው ቃል ለመጨረሻ ጊዜ የተጠቀሰው በሡረቱ አሽ ሸምሥ ምዕራፍ 91 ቁጥር 1 ላይ ነው፦
91፥1 በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا

በሡረቱል በቀራህ ምዕራፍ 2 ቁጥር 258 ላይ እና በሡረቱ አሽ ሸምሥ ምዕራፍ 91 ቁጥር 1መካከል ያለው የአናቅጽ ብዛት 5778 ነው፥ የፀሓይ የሙቀት መጠን"Temperature" በኬልቪን"kelvin" ሲለካ 5778 k የገጽታ ምስል"Photosphere" ይሆናል።

"ቀመር" قَمَر ማለት "ጨረቃ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ በቁርኣን "ቀመር" قَمَر የሚለውን ቃል የተጠቀመው "27" ጊዜ ብቻ ነው፥ የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው።
"ሠናህ" سَنَة ማለት "ዓመት" ማለት ሲሆን "ሠናህ" سَنَة የሚለው ቃል በቁርኣን የተጠቀሰው "19" ጊዜ ብቻ ነው፥ ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ አሏህ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና "ነገሩን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ" ሲሆን የጌታቸውን መልእክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

ፀሐይ እና ጨረቃ የዓለማቱ ጌታ አሏህ ለመኖሩ ከምልክቶቹ ናቸው። ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፦
41፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው። ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

አምላካችን አሏህ እነዚያ ቆመው እና ተቀምጠው፣ በጎኖቻቸው ተጋድመው እርሱ የሚያወሱ እና በበፈጠረው ፍጥረት አፈጣጠር የሚያስተነትኑ ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሏህ ታማኝ ነው!

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥23 እርሱ አሏህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ ከጉድለት ሁሉ የጠራ፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኃያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ከአሏህ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም። "አል መሊክ" الْمَلِك ማለት "ንጉሡ" ማለት ነው፣ አል ቁዱሥ" الْقُدُّوسُ ማለት "ቅዱሱ" "ከጉድለት ሁሉ የጠራ" ማለት ነው፣ "አሥ ሠላም" السَّلَام ማለት "የሰላም ባለቤት" ማለት ነው፣ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "ታማኝ" "ጸጥታን ሰጪው" ማለት ነው፣ "አል ሙሀይሚን" الْمُهَيْمِن ማለት "ጠባቂው" ማለት ነው፣ "አል ዐዚዝ" الْعَزِيز ማለት "አሸናፊው" ማለት ነው፣ "አል ጀባር" الْجَبَّار ማለት "ኃያሉ" ማለት ነው፣ "አል ሙተከቢር" الْمُتَكَبِّر ማለት "ታላቁ" "ኩሩው" ማለት ነው፦
59፥23 እርሱ አሏህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ ከጉድለት ሁሉ የጠራ፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኃያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጸጥታን ሰጪው" ለሚለው የገባው ቃል "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲሆን "ታማኝ"Faithful" ማለት ነው፥ አሏህ የተናገረው ነገር፣ የገባውን ኪዳን እና የሰጠውን ተስፋ በመፈጸም ታማኝ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "አማኝ" ማለት ነው፥ አሏህ አማኝ ነው" በማለት ለፍጡር የሚውለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
16፥97 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ "አማኝ" ኾኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً

እዚህ አንቀጽ ላይ "አማኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ሙእሚን" مُؤْمِن ሲሆን ለአሏህን ግን "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "ታማኝ" እንጂ "አማኝ" የሚለውን አያሲዝም። ለምሳሌ፦ አሏህ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፦
22፥17 አሏህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዐዋቂ" ለሚለው የገባው ቃል "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፥ አሏህ "ምስክር" ነው፦
6፥19 «በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው?» በላቸው፡፡ ሌላ መልስ የለምና «አሏህ ነው፡፡ በእኔ እና በእናንተ መካከል "መስካሪ" ነው» በላቸው። قُلْ أَيُّ شَيْءٍ أَكْبَرُ شَهَادَةً ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ شَهِيدٌ بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምስክር" ለሚለው የገባው ቃል "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፥ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ማለት "ሰማዕት" በሚል ይመጣል፦
4፥69 አሏህን እና መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አሏህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃን፣ ከሰማዕታት፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا

"ሹሀዳእ" شُّهَدَاء ማለት "ሰማዕታት" ማለት ሲሆን "ሸሂድ" شَهِيدٌ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ሲባል አሏህ "ዐዋቂ" "ምስክር" በሚል እንጂ "ሰማዕት" በሚል እንደማንረዳው ሁሉ በተመሳዳይ አሏህ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲባል አሏህ "ጸጥታን ሰጪው" "ታማኝ" በሚል እንጂ "አማኝ" በሚል አንረዳውም። ተጨማሪ ምሳሌ፦ አሏህ "አት ተዋብ" التَّوَّاب ነው፦
2፥160 እኔም "ጸጸትን በጣም ተቀባይ" አዛኙ ነኝ፡፡ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጸጸትን በጣም ተቀባይ" ለሚለው የገባው ቃል "አት ተዋብ" التَّوَّاب ሲሆን "ይቅር ባይ" ማለት ነው። ነገር ግን "ተዋብ" تَّوَّاب የሚለው ቃል "በንስሓ ወደ አሏህ ተመላሽ" በሚል ቃል ይመጣል፦
2፥222 "አሏህ "ከኃጢአት ተመላሾችን" ይወዳል፥ ተጥራሪዎችንም ይወዳል" በላቸው፡፡  إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ التَّوَّابِينَ وَيُحِبُّ الْمُتَطَهِّرِينَ

"ተዋቢን" تَّوَّابِين ማለት "ከኃጢአት ተመላሾችን" ማለት ሲሆን "ተዋብ" تَّوَّاب ሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ "ተዋብ" تَّوَّاب ሲባል አሏህ "ጸጸትን ተቀባይ" "ይቅር ባይ" በሚል እንጂ "በንስሓ ወደ አሏህ ተመላሽ" በሚል እንደማንረዳው ሁሉ በተመሳዳይ አሏህ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲባል አሏህ "ጸጥታን ሰጪው" "ታማኝ" በሚል እንጂ "አማኝ" በሚል አንረዳውም።

ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው እሙን ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹ ምህዋር፣ የምዕራፉ አውታር፣ የመጽሐፉ ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው።
እሩቅ ሳንሄድ አምላክ በባይብል "ምስክር" ተብሎአል፦
ኤርምያስ 29፥22 እኔም አውቃለሁ "ምስክርም" ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
1ኛ ሳሙኤል 20፥23 አንተ እና እኔ ስለ ተነጋገርነው እነሆ እግዚአብሔር ለዘላለም በመካከላችን "ምስክር" ነው። καὶ τὸ ρῆμα ὃ ἐλαλήσαμεν ἐγὼ καὶ σύ, ἰδοὺ Κύριος μάρτυς ἀνὰ μέσον ἐμοῦ καὶ σοῦ ἕως αἰῶνος.

እዚህ ጥቅስ ላይ "ምስክር" ለሚለው በግሪክ ሰፕቱአጀንት የገባው ቃል "ማርትይስ" μάρτυς ነው፥ ነገር ግን "ማርትይስ" μάρτυς የሚለው ቃል "ሰማዕት" በሚል ይመጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 22፥20 "የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር" አልሁ። καὶ ὅτε ἐξεχύννετο τὸ αἷμα Στεφάνου τοῦ μάρτυρός σου, καὶ αὐτὸς ἤμην ἐφεστὼς καὶ συνευδοκῶν καὶ φυλάσσων τὰ ἱμάτια τῶν ἀναιρούντων αὐτόν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰማዕት" ለሚለው የገባው ቃል "ማርትይስ" μάρτυς ነው። እና ያህዌህ ሰማዕት ነውን? "አይ "ማርትይስ" μάρτυς ለያህዌህ "ምስክር" ማለት ነው፥ ለእስጢፋኖስ ደግሞ "ሰማዕት" ማለት ነው" ከተባለ እንግዲያውስ እኛም፦ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ለአሏህ "ታማኝ" ማለት ነው፥ ለሰው "ሙእሚን" مُؤْمِن ደግሞ "አማኝ" ማለት ነው" እንላለን። አምላክ ደግሞ "ታማኝ" ነው፦
ኤርሚያስ 42፥5 እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛ እና "ታማኝ" ምስክር ይሁን።

ስለዚህ "አሏህ አማኝ ነው፥ የሚያምነው ምንድን ነው" ብላችሁ ላፀፃችሁት አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of Equivocation" መልሱ ይህንን ይመሳል፥ "አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚለውን"Two different things by the same word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ አሻሚ ሕፀፅ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም