ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥያቄ ለህዝበ ክርስቲያኑ

1ኛ. እንደ ባይብሉ ፉሲካ የሰንበት ዋዜማ ላይ ከሆነ ይህንን ፋሲካ ኢየሱስ ሀሙስ ፀሀይ ከጠለቀች በኃላ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አክብሯል፦
ዘሌዋውያን 23፥5 በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን #ሲመሽ የእግዚአብሔር #ፋሲካ #ነው
ዘኁልቅ 28፥16 በመጀመሪያው ወር ከወሩም ""በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ"" ነው።
ማቴዎስ 26፥19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ ፋሲካንም አሰናዱ።
ማርቆስ 14፥16 በዚያም አሰናዱልን። ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ።
ሉቃስ 22፥13 ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ።

ጥያቄአችን ፋሲካ ከሀሙስ ማታ እስከ አርብ መአልት ከነበረ ፋሲካ እሁድ የሚከበርበት ቀን ከየት አመጣችሁት?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

2ኛ. እንደ ባይብሉ ከሆነ ሶስት ቀንና ሌሊት የሚሸፍነው በምድር ልብ ማለትም በመቃብር ውስጥ ነው፦
ማቴዎስ 12፥40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ #በምድር #ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

እንደ ባይብሉ ከሆነ ወደ መቃብር የገባው አርብ ምሽት የቅዳሜ ሌሊት ከሚጀምርበት ነው፦
በማለት በመቃብር ያለውን ጊዜ የሚሸፊን መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ መቃቢር የገባው ደግሞ በምሽት ነው፦
ማርቆስ 15፥42-46 አሁንም """#በመሸ #ጊዜ""" የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። ጲላጦስም አሁኑን እንዴት ሞተ ብሎ ተደነቀ፥ የመቶ አለቃውንም ጠርቶ ከሞተ ቆይቶአልን? ብሎ ጠየቀው፤ ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው። በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው፥ በመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ።

""በመሸ ጊዜ""" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ አይሁድ የሚያከብሩት በኣል ከ 12 ሰኣት በኃላ የነገው ነው፤ ቀኑም የሚጀመረውም ከሚሽቱ 12 ነው፤ ምሽት የሌሊት መጀመሪያ ነው፤ ሲመሽ ደግሞ ፀሀይ ትጠልቃለች ቀጣዩ ቀን በሌሊት ይጀመራል፦
ዘጸአት 12፥18 በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን "በመሸ ጊዜ" ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን #በመሸ #ጊዜ የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።
ማርቆስ 1፥32 "#ፀሐይም #ገብቶ #በመሸ ጊዜ"፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

እንግዲህ ከዚህ ከሰንበት ማለት ከቅዳሜ ዋዜማ ምሽቱ የቅዳሜ ከሆነ ከዚያ ጀምራችሁ ቁጠሩት። ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ለማክሰኞ ጅማሬ ላይ ይመጣል። ጥያቄአችን ሶስት መአልትና ሌሊት በመቃብር ከነበረ ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ጅማሬ ትንሳኤ ከሆነ እንዴት እሁድ ሌሊት ተነሳ ይባላል?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

3ኛ. ኢየሱስ የአላህ ነብይ ነው አይዋሽም፤ መቼም አራቱ ወንጌላት ላይ ያሉት ቃላት አይደለም የኢየሱስ ይቅርና የመጀመሪያዎቹ ፀሃፊያን ያልሆኑ ንግግሮች በእማኝነትና በአስረኝነት ማቅረብ ይቻላል፤ ነገር ግን ነጥባችን እርሱ አይደለም፤ ኢየሱስ ተናገረ ተብሎ የተቀጠፈበት ነገር እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ እንደ ማርቆስ ዘጋቢ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በኃላ” የሚለው መስተዋድድ በአራተኛው ቀን አሊያም በአምስተኛው ቀን ሊሆን ይችላል፤ ግን ሶስኛውን ቀን አይጨምርም፦
ማርቆስ 8፥31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ሊነሣ” እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።

የማቴዎ ዘጋቢ ደግሞ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ተብሎ ነው፤ ልብ አድርጉ “በ” የሚለው መስተዋድድ ሶስተኛውን ቀን ብቻ የሚያመለክት ነው፦
ማቴዎስ 16፥21 ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ “”በሦስተኛውም ቀን” ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

ጥያቄአችን፦ የቱ ትረካ ነው ትክክል? ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “ከሦስት ቀንም “”በኋላ”” ነው ብሎ የሚተርከው የማርቆስ ዘጋቢ ወይስ ኢየሱስ ይነሳል የተባለው “በ”ሦስተኛውም ቀን”” ነው ብሎ የሚተርከው የማቴዎስ ዘጋቢ?
መረጃዋን ከባይብል ቁጭ ቁጭ አርጓት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ቅጥፈት ሁለት 1ኛ ነገሥት 6፥1 የእስራኤል ልጆች #ከግብጽ #ምድር #ከወጡ #አራት #መቶ #ሰማንያ ዓመት #በሆነ #ጊዜ#ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት እንደሆነ ይህ የነገሥት ፀሐፊ አስፍሮታል፤ እውን የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት ነው ወይ? ይህንን ቅጥፈት አብረን እንይ፦

ነጥብ አንድ
“አርባ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ወጥተው ከነዓን እስኪገቡ ድረስ 40 ዓመት በምድረ-በዳ ቆይተዋል፦ ዘጸ 16:35 የእስራኤልም ልጆች #ወደሚኖሩባት #ምድር #እስኪመጡ ድረስ #አርባ #ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ። ዘዳ 29:5 #አርባ #ዓመት በምድረ በዳ መራኋችሁ፤ ልብሳችሁም አላረጀባችሁም፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ላይ አላረጀም።

ነጥብ ሁለት
“አርባ ዓመት”
ካሌብ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ሲወጡ የአምስት እመት ልጅ ነበረ፤ የምድረ-በዳው 40 ዓመት ሲጨመር 45 ዓመት ሆኖት ነበር፤ በከነዓን 40 ዓመት ሲቀመጥ 85 ዓመት ሆነው፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ወጥተው በምድረ-በዳ 40 ዓመት አሳልፈው ከነዓን ከገቡ በኃላ 40 ዓመት ሲቆዩ 80 ዓመት ይሆናል፦ ኢያ 14:10፤ አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል #በምድረ #በዳ #ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን #አርባ #አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ #ሰማንያ #አምስት ዓመት ሆነኝ።

ነጥብ ሶስት “አራት መቶ አምሳ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከካሌብና ከኢያሱ ሞት በኃላ እስከ ነብዩ ሳሙኤል መሳፍንትን ለአራት መቶ አምሳ ዓመት አስነስላቸው፦
መሳ 2:16 እግዚአብሔርም #መሳፍንትን #አስነሣላቸው፥ ከሚማርኩአቸውም እጅ አዳኑአቸው።
ሐዋ 13:20 ከዚህም በኋላ #እስከ #ነቢዩ #እስከ #ሳሙኤል #ድረስ #አራት #መቶ #አምሳ #ዓመት ያህል #መሳፍንትን ሰጣቸው።

ነጥብ አራት
“አርባ ዓመት”
በነብዩ ሳሙኤል ጊዜ የቂስን ልጅ ሳኦል ነገሠ፤ ይህም ንግሥና 40 ዓመት ቆየ፦ ሐዋ 13:21 ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን #አርባ #ዓመት ሰጣቸው፤

ነጥብ አምስት
“አርባ ዓመት”
ከሳኦል ንግሥና በኃላ ንጉሥ ዳዊት ለአርባ ዓመት ነገሰ፦ 1ነገ 2:11 ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠው ዘመን #አርባ #ዓመት ነበረ፤ በኬብሮን ሰባት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።

ነጥብ ስድስት
“አራት ዓመት”
ከዳዊት በኃላ ሰለሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ሰለሞን ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ፦ 1ነገ.6:1፤ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው #ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

አሁን ነው ጉድ የሚፈላው፤ ከግብፅ መውጣት ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ያለው የጊዜ እርዝመት እስቲ እንደምራቸው፦
40 ዓመት
40 ዓመት
450 ዓመት
40 ዓመት
40 ዓመት
4 ዓመት
=======
614 ዓመት ይሆናል።
እሺ እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ሲጀምር የነበረው የጊዜ ቆይታ 614 ወይስ 480? ማን ነው የቀጠፈው? ይህ ታሪክ ከመነሻው የታሪክ ጸሐፊዎች ቃል እንጂ የአምላክ ንግግር አይደለም፤ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እንደ የፈጣሪ ቃል ቢወስዱትም የፈጣሪ ንግግር አይደለም። አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው ፅፈው ከአላህ ሳይሆን “ይህ ከአላህ ዘንድ ነው” ብለው እውነትን በውሸት እንደሚቀላቅሉ በተከረው ከሊማ ነግሮናል፦
2:79 ለነዚያም *መጽሐፉን* *በእጆቻቸው* ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «*ይህ* *ከአላህ* *ዘንድ* *ነው*» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ #እጆቻቸው #ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም