ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሶስት
“አሏህና ታሪካዊ ፍሰት”
አሏህ የሚለው ስም ነብያችን ነብይ ሆነ ከመላካቸው በፊትና ቁርአን ከመውረዱ በፊት በሴመቲክ ዳራ ደግሞ ከሁሉ በላይ የሆነው አንዱ አምላክ ሲጠራበት የነበረ ስም እንደነበር የተለያየ መድብለ-እውቀቶች*Encycolopedias* ሆኑ ታሪካዊ ፍሰቶች ያትታሉ፦
1. የሃይማኖት መድብለ-እውቀት 1987: “አላህ የሚለው ስም ስረ-መሰረት የጋራ በሆኑ በተለያዩ ጥንታዊ የሴም ቋንቋዎች ይገኛል” ገጽ 27.
Encycolopedia of religion 1987: “the orgin of Allah is found in a root common to various ancient semetic languages” p27.
2. የክርስትና መድብለ-እውቀት 2001: “ ቅድመ-ቁርአን አረብ ተናጋሪ ክርስቲያንና አይሁድ እንዲሁ አላህ ለታላቁ አምላክ ይጠቀሙበት ነበር” ገጽ 101.
Encyclopedia of Christianity 2001: “before Quran Arabic-speaking Christians and Jews also refer to supreme God as Allāh” page 101.
3. የኢስላም መድብለ-እውቀት 1913: “አረቦች ቅድመ-ነቢዩ ሙሃመድ በነበሩት ዘመናት አላህ የሚባል ታላቅ አምላክ ያመልኩ ነበር” ገጽ 302.
Encyclopedia of Islam 1913: “Before prophet Muhammad Arabian was worshiping supreme God who is Allah” page 302.
4. የብሪታኒካ መድብለ-እውቀት 1996: “ቅድመ-ቁርአን በነበሩት አረቢያን መጽሐፍት ውስጥ አላህ የሚለው ቃል ይገኛል” ገጽ 106.
Encyclopedia of britannica 1996: “Before Quran The word Allah was in the Arabic books” page 106.

ከነዚህ ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ ተነስተን የምንደመድመው ነገር ቢኖር አላህ የሚለው ስም ነቢያችን የገለጡት አሊያም ቁርአን የገለጠው ስም ብቻ ሳይሆን ስረ-መሰረቱ ቀዳማይ መሆኑን ነው፣ የትኛውም ምሁራዊና እውቀታዊ መረጃ አላህ የጣኦት ስም ነው ብሎ ያሰፈረ የለም፣ አለ የሚል ሰው ካለ ተግዳሮትና ጋሬጣ ሆኖ መቅረብ ይችላል። ቁሬሾች አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው ብለው ያምናሉ እንጂ ከጣኦቶቻቸው መካከል አንዱ ጣኦት ነበር የሚል የቡና ዲቃላ ወሬ የላቸውም፦
31:25 ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፤ ምስጋና ለአላህ ይገባው፣ በላቸው፤ ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
29:61 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
43:87 ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው፣ በእርግጥ አላህ ነው፣ ይላሉ።ታዲያ ከእምነት ወዴት ይዞራሉ።
39:38 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ ይሉሃል።
29:63 ከሰማይም ውሃን ያወረደና በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋት ማን እንደ ሆነ ብትጠይቃቸው አላህ ነው፣ይሉሃል።
23:84-89 «ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ ንገሩኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን» በላቸው፡፡«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡ «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡ «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ» በላቸው፡፡

ማጠቃለያ
አላህ ህያው የሆነ ሁሉን የሚያውቅ፣ የሚያይ፣ የሚሰማ እና በእኔነት የሚናገር አምላክ ነው፦

1. ሁሉን የሚያውቅ ነው፦
60:1 #እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን #የማውቅስሆን ወደ እነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤

2. ሁሉ ተመልካች ነው፦
34:11 #እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

3. ሁሉን የሚሰማ ነው፦
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ #እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

4. እኔነት ያለው ተናጋሪ ነው፦
21:92 “#እኔም” ጌታችሁ #ነኝ እና “አምልኩኝ”።
2:160 እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ #እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ #ነኝ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም