ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?

ቅጥፈት አንድ
የሐዋርያት ሥራ 7:15-16 ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ “አባቶቻችንም”፤ ወደ ሴኬምም አፍልሰው #አብርሃም #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በብር በገዛው መቃብር “ቀበሩአቸው”።

በአብርሃምና በሴኬም መካከል የትውልድ ልዩነት አለ፤ ሴኬም ይቅርና የሴኬም አባት ኤሞር የነበረው በአብርሃም ጊዜ ሳይሆን የአብርሃም የልጅ ልጅ በሆነው በያዕቆብ ጊዜ ነው፦
ዘፍጥረት 34:4-6 #ሴኬምም አባቱን #ኤሞርን ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው። #ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። #የሴኬም #አባት #ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ #ያዕቆብ ወጣ።

ልብ በሉ ሴኬም የያዕቆብን ልጅ ዲናን ሲያስነውር ማለት ሲደፍራት አይደለም አብርሃም አያቱ ይቅርና አባቱ ይስሐቅ ሞቷል፤ ታዲያ አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር መቃብር የገዛው መቼ ነው? ይህ እልም ያለ ቅጥፈት ነው፤ ታዲያ ማን ነው መቃብሩን ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች የገዛው? ስንል የዘፍጥረት ዘጋቢ ያዕቆብ ነው ይለናል፦ ዘፍጥረት 33:18-19 #ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ #ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ፤ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የእርሻውን ክፍል #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር #ልጆች #በመቶ #በጎች ገዛው።

ውሸት ሁሌም ውሸት ነው፤ ልብ በሉ አብርሃም በህይወት ሳይኖር ያልገዛውን ገዛ ማለቱ ሲገርመን አብርሃም ገዛ የተባለው #በብር ሲሆን ያዕቆብ ግን #በመቶ #በጎች ነው፦
ኢያሱ 24:32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት #ያዕቆብ #ከሴኬም #አባት #ከኤሞር ልጆች #በመቶ #በግ በገዛው #እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።

የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ሉቃስ ወይም እስጢፋኖስ አሊያም የግሪክ እደ-ክታባትን ገልባጮች ቀጥፈዋል፤ አብርሃም በእርግጥም የመቃብር ስፍራ ገዝቷል የገዛው ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች ሳይሆን ከኬጢያዊ ከኤፍሮን እርሻ ላይ ነው፤ የገዛውም በመቶ በግ ሳይሆን #በአራት #መቶ #ሰቅል ነው፦
ዘፍጥረት 23፥16-17 *አብርሃምም* የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን #አራት #መቶ #ሰቅል መዝኖ #ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና።
ዘፍጥረት 49፥29-30 እንዲህ ብሎም አዘዛቸው። እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ #አብርሃም ለመቃብር ርስት #ከኬጢያዊ #ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።

ቅጥፈትን በጋራ እንከላከል፤ ኢንሻላህ ይቀጥላል……

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ?

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ቅጥፈት ሁለት 1ኛ ነገሥት 6፥1 የእስራኤል ልጆች #ከግብጽ #ምድር #ከወጡ #አራት #መቶ #ሰማንያ ዓመት #በሆነ #ጊዜ#ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት እንደሆነ ይህ የነገሥት ፀሐፊ አስፍሮታል፤ እውን የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ እስከ ሰለሞን 4ኛ ዓመት ንግሥና 480 ዓመት ነው ወይ? ይህንን ቅጥፈት አብረን እንይ፦

ነጥብ አንድ
“አርባ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ወጥተው ከነዓን እስኪገቡ ድረስ 40 ዓመት በምድረ-በዳ ቆይተዋል፦ ዘጸ 16:35 የእስራኤልም ልጆች #ወደሚኖሩባት #ምድር #እስኪመጡ ድረስ #አርባ #ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ። ዘዳ 29:5 #አርባ #ዓመት በምድረ በዳ መራኋችሁ፤ ልብሳችሁም አላረጀባችሁም፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ላይ አላረጀም።

ነጥብ ሁለት
“አርባ ዓመት”
ካሌብ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ሲወጡ የአምስት እመት ልጅ ነበረ፤ የምድረ-በዳው 40 ዓመት ሲጨመር 45 ዓመት ሆኖት ነበር፤ በከነዓን 40 ዓመት ሲቀመጥ 85 ዓመት ሆነው፤ ስለዚህ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ወጥተው በምድረ-በዳ 40 ዓመት አሳልፈው ከነዓን ከገቡ በኃላ 40 ዓመት ሲቆዩ 80 ዓመት ይሆናል፦ ኢያ 14:10፤ አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል #በምድረ #በዳ #ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን #አርባ #አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ #ሰማንያ #አምስት ዓመት ሆነኝ።

ነጥብ ሶስት “አራት መቶ አምሳ ዓመት”
የእስራኤልም ልጆች ከካሌብና ከኢያሱ ሞት በኃላ እስከ ነብዩ ሳሙኤል መሳፍንትን ለአራት መቶ አምሳ ዓመት አስነስላቸው፦
መሳ 2:16 እግዚአብሔርም #መሳፍንትን #አስነሣላቸው፥ ከሚማርኩአቸውም እጅ አዳኑአቸው።
ሐዋ 13:20 ከዚህም በኋላ #እስከ #ነቢዩ #እስከ #ሳሙኤል #ድረስ #አራት #መቶ #አምሳ #ዓመት ያህል #መሳፍንትን ሰጣቸው።

ነጥብ አራት
“አርባ ዓመት”
በነብዩ ሳሙኤል ጊዜ የቂስን ልጅ ሳኦል ነገሠ፤ ይህም ንግሥና 40 ዓመት ቆየ፦ ሐዋ 13:21 ከዚያም ወዲያ ንጉሥን ያነግሥላቸው ዘንድ ለመኑ፥ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን የሚሆን ሰው የቂስን ልጅ ሳኦልን #አርባ #ዓመት ሰጣቸው፤

ነጥብ አምስት
“አርባ ዓመት”
ከሳኦል ንግሥና በኃላ ንጉሥ ዳዊት ለአርባ ዓመት ነገሰ፦ 1ነገ 2:11 ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠው ዘመን #አርባ #ዓመት ነበረ፤ በኬብሮን ሰባት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።

ነጥብ ስድስት
አራት ዓመት”
ከዳዊት በኃላ ሰለሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ሰለሞን ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ፦ 1ነገ.6:1፤ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ #በአራተኛው #ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።

አሁን ነው ጉድ የሚፈላው፤ ከግብፅ መውጣት ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ያለው የጊዜ እርዝመት እስቲ እንደምራቸው፦
40 ዓመት
40 ዓመት
450 ዓመት
40 ዓመት
40 ዓመት
4 ዓመት
=======
614 ዓመት ይሆናል።
እሺ እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ሲጀምር የነበረው የጊዜ ቆይታ 614 ወይስ 480? ማን ነው የቀጠፈው? ይህ ታሪክ ከመነሻው የታሪክ ጸሐፊዎች ቃል እንጂ የአምላክ ንግግር አይደለም፤ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እንደ የፈጣሪ ቃል ቢወስዱትም የፈጣሪ ንግግር አይደለም። አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው ፅፈው ከአላህ ሳይሆን “ይህ ከአላህ ዘንድ ነው” ብለው እውነትን በውሸት እንደሚቀላቅሉ በተከረው ከሊማ ነግሮናል፦
2:79 ለነዚያም *መጽሐፉን* *በእጆቻቸው* ለሚጽፉ እና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «*ይህ* *ከአላህ* *ዘንድ* *ነው*» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ #እጆቻቸው #ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡
3፥71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም