ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
፨ሲቀጥል "ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር" በሚል አንቀጽ ውስጥ "ሲቀር" "በቀር" ለሚለው የገባው ቃል "ኢላ" إِلَّا ሲሆን ኢሥቲስናእ ነው። "ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء‏ የሚለው ቃል "ኢሥተስና" اِسْتَثْنَى ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "በስተቀረት"exception" ማለት ነው፥ ኢሥቲስናእ በሁለት ይከፈላል። አንዱ "ኢሥቲስናኡል ሙተሲል" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُتَّصِل ሲሆን "ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት "የተያያዘ"attached" ማለት ነው፦
43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢላ" إِلَّا የሚለው ኢሥቲስናኡል ሙተሲል ስለሆነ ተመሳሳይ ጥንተ ተፈጥሮን ያሳያል፥ ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት የሚሆነው እና አሏህን ፈሪዎች ጥንተ ተፈጥሯቸው ተመሳሳይ ነው። ተጨማሪ ይህንን ጥቅስ መመልከት ይቻላል፦
103፥2 ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡ إِنَّ الْإِنسَانَ لَفِي خُسْرٍ
103፥3 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ

ሁለተኛው ደግሞ "ኢሥቲስናኡል ሙንቀጢዕ" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُنقَطِع ሲሆን "ሙንቀጢዕ" مُنقَطِع ማለት "ያልተያያዘ"detached" ማለት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፥ ግን የዓለማት ጌታ "ሲቀር"»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም "እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው" ያላቸው እና "ሲቀር" ያለው "የዓለማት ጌታ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች እንደሆኑ ሁሉ በተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር "መላእክት" እና "ኢብሊሥ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች ናቸው። በተጨማሪ አንድ ጥቅስ እንመልከት፦
17፥67 በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው ሁሉ ይጠፋሉ፥ እርሱ(አላህ) "ሲቀር"፡፡ وَإِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فِي الْبَحْرِ ضَلَّ مَن تَدْعُونَ إِلَّا إِيَّاهُ

ጣዖታዊያን በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛቸው ጊዜ የሚጠሩዋቸው ጣዖታታት የሰው እጅ ሥራዎች ሲሆኑ ይጠፋሉ፥ አሏህ ግን ሕያው ፈጣሪ ስለሆነ አይጠፋም። ስለዚህ "በቀር" "በስተቀር" ስለተባለ ዐውዱ እና አጠቃላይ አሳቡ ሳይታይ "አንድ ምድብ ነው" ማለት ስህተት እንዳለው ከተረዳን ዘንዳ "በቀር" ስላለ ኢብሊሥን የመላእክት ጥንተ ተፈጥሮ ውስጥ ማካተት ስህተት ነው።
ኢብሊሥ ከጂን እንጂ ከመላእክት አለመሆኑ ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ከሲር በመቀጠል በተፍሢሩ ላይ አድ-ደሓክ፣ ሠዒድ ኢብኑ ጀቢር፣ ኢብኑ ኢሥሐቅ ወዘተ "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" ያሉት ከኢሥራዒልያት ትርክት እንደሆነ ተናግሯል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው፦ "ኢብሊሥ ከመላእክት አይደለም፥ ለአንዲት ቅጽበት እንኳን አልነበረም። ልክ አደም"ዐ.ሠ." ለሰው ሥረ-መሠረት እንደሆነ ሁሉ ኢብሊሥም ለጂን ሥረ-መሠረት ነው"። ይህ በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው። قال الحسن البصري : ما كان إبليس من الملائكة طرفة عين قط ، وإنه لأصل الجن ، كما أن آدم ، عليه السلام ، أصل البشر . رواه ابن جرير بإسناد صحيح
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"በእርግጥ በዚህ ሪዋያህ ከቀደምቶቹ የተተረከው ዘገባ አብዛኛውን ከኢሥራኢልያት እንደሆነ ይጤናል"። وقد روي في هذا آثار كثيرة عن السلف ، وغالبها من الإسرائيليات التي تنقل لينظر فيها

፨ሢሰልስ መላእክት የተፈጠሩበት ንጥረ ነገር ብቻ ሳይሆን ባሕርያቸውም ይለያል፥ መላእክት ፆታ የላቸውም፦
43፥19 "መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ"፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው "መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ

ከመላእክት መካከል ሴቶች ቢኖሩ ኖሮ ቁሬሾች፦ "መላእክት ሴቶች ናቸው" ማለታቸውን አይቃወምም ነበር፥ አሏህ መላእክትን ሴቶች አድርጎ አልፈጠረም። ጂኒዎች ግን ጾታ አላቸው፥ ዝርያ ስላላቸው የሚራቡ ወንድ እና ሴት ናቸው፦
18፥50 "እርሱን እና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲኾኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ! أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ ۚ بِئْسَ لِلظَّالِمِينَ بَدَلًا
72፥6 እነሆም "ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጂኒ ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ"፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡  وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፥ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ "አሏህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው" ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏
ኢብሊሥ ከጂን ስለሆነ አሏህን የማመጽ እና የመታዘዝ ነጻ ፈቃድ ስላለው በጌታው ላይ አምጾ ኮራ፥ መላእክት ግን የማመጽ እና የመታዘዝ ነጻ ፈቃድ ስለሌላቸው በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም። አሏህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፥ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፦
38፥74 ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር፡፡ "ኮራ"፤ ከከሓዲዎቹም ሆነ፡፡ إِلَّا إِبْلِيسَ اسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ
16፥49 "እነርሱም አይኮሩም" وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

፨ሲያረብብ መላእክት በአሏህ ላይ አምጸው የሚገቡበት ጀሀነም ሆነ ታዘው የሚገቡበት ጀነት የለም። ጂኒዎች ግን በምርጫቸው አምነው ጀነት ወይም ክደው ጀሀነም መግባት ይችላሉ፦
11፥119 የጌታህም ቃል፦ "ገሀነምን ከጂኒዎ እና ከሰዎች ሁሉ በእርግጥ እሞላታለሁ" በማለት ተፈጸመች። وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ
55፥45 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَان
55፥46 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

ሱረቱር ረሕማን ዐውዱ ላይ ያሉት ሰው እና ጃን ናቸው፥ "ጌታችሁ" የሚለው ቃል "ረቢኩማ" رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙሰና ሰውን እና ጃንን ያመለክታል። “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙሰና ሰውን እና ጃንን ያመለክታል፦
55፥14 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ خَلَقَ الْإِنسَانَ مِن صَلْصَالٍ كَالْفَخَّارِ
55፥15 "ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው"፡፡ وَخَلَقَ الْجَانَّ مِن مَّارِجٍ مِّن نَّارٍ

የትንሳኤ ቀን ለሁለቱም የተቀጠረ ቀጠሮ ነው፥ የዚያን ቀን የተውበት በር ስለተዘጋ ሰው ሆነ ጂን ከኃጢኣቱ አሏህን ይቅርታ እንዲጠይቅ አይጠየቅም። ከዛ ይልቅ "የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልእክተኞች አልመጧችሁምን" በመባል ፍርድ ያገኛሉ፦
44፥40 የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ
55፥39 በዚያም ቀን ሰው እና ጃን ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ
6፥130 የጂኒዎች እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልእክተኞች አልመጧችሁምን? ይባላሉ፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا

ለጂኒዎች ጀነት እና ጀሃነም እንዲሁ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ እንዳላቸው እና የተፈጠሩበት አላማ ካየን ዘንዳ በነጻ ምርጫቸው አምነው ሙሥሊም አልያም ክደው ኩፋር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 «እኛም ከእኛ ውስጥ ሙሥሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሠለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡» وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ስለዚህ "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" የሚለው ትርክት ቁርኣን ላይ ሆነ ሐዲስ ላይ የለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁርአን ኢየሱስን ብቻ ንጹህ ይለዋልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

19:19 ፦ እኔ *ንጹሕን* زَكِيًّا ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፣ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት።

መግቢያ
ብዙ ሚሽነሪዎች ይህ ጥቅስ ተመርኩዘው የኢየሱስን ልዩ መሆን አሊያም አምላክ መሆን ያሳያል ብለው እንደ በቀቀን ሲደጋግሙት ይሰማል፣ ዘኪይ زَكِيّ የሚለው ቃል *ንጹሕ* ማለት ሲሆን ይህም ቃል ለኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሰዎችም ጥቅም ላይ ውሏል፦

አንደኛ ለየሕያህ፦
19:13 ከኛም የኾነን ርኅራኄ፣ ንጽሕናንም وَزَكَاةً፤ ጥንቁቅም ነበር።

ሁለተኛ ለወጣቱ ልጅ፦
18:74 ወርደው ተጓዙም፤ ወጣትንም ልጅ ባገኙና በገደለው ጊዜ ያለ ነፍስ መግደል ንጹሕን زَكِيَّةً ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎ ነገር ሠራህ አለው።
18:81 ጌታቸውም በንጹሕነት زَكَاةً ከርሱ በላጭን፣ በእዝነትም ከርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን።

ሶስተኛ ለአህለል ጀና፦
20:76 ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አሏቸው፤ ይህም የተጥራራ تَزَكَّىٰ ሰው ምንዳ ነው።
87:14 የተጥራራ تَزَكَّىٰ ሰዉ በእርግጥ ዳነ፤

ዘኪይ زَكِيّ *ንጹሕ* ማለት ልዩ መሆንን አሊያም አምላክ መሆንን ካሰኘ ለምን ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ልዩና አምላክ አልሆኑም? ከቁርአኑ በተቃራኒው ባይብሉ ከሴት የተወለደ ንጹህ ሊሆን አይችልም ብሎ ይሞግታል፣ እንኳን ከሴት የተወለደ ብስብስ የሆነ ሰውና ትልም የሆነ የሰው ልጅ ይቅርና ሰማያት፣ ከዋክብት፣ መላእክት ንጹሃን እንዳልሆኑ ይነግረናል፦
ኢዮብ 25:4-6 ከሴትስ የተወለደ *ንጹሕ* ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል? እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ *ንጹሐን* አይደሉም። ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
ኢዮብ 14:1 *ከሴት የተወለደ* ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።
ኢዮብ 14:4 *ከርኩስ ነገር ንጹሕን* ሊያወጣ ማን ይችላል?
ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው?
ኢዮብ 14:14-15 ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በፊቱ *ንጹሐን* አይደሉም።
ኢዮብ 4:17-18 በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥ ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት *ሊነጻ* ይችላልን? እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤ መላእክቱንም *ስንፍና* ይከስሳቸዋል፤

በባይብሉ መስፈርት መሰረት ታዲያ ከሴት የተወለደ ብስብስ የሆነ ሰውና ትልም የሆነ የሰው ልጅ ንጹህ ካልሆነ ኢየሱስም ንጹህ አይደለም ማለት ነው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ከሴት የተወለደ ሰውና የሰው ልጅ ነው፦

አንደኛ ከሴት የተወለደ ነው፦
ገላትያ 4:4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር *ከሴት የተወለደውን* ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

ሁለተኛ ሰው ነው፦
ዮሐንስ 8:40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን *ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ *ሰው* ነበረ፤
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 25 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

ሶስተኛ የሰው ልጅ ነው፦
ማቴዎስ 11፥19 *የሰው ልጅ* እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል።
ዮሐንስ 5፥27 *የሰው ልጅም* ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።
ዮሐንስ 13፥31 ኢየሱስ እንዲ አለ፦ አሁን *የሰው ልጅ* ከበረ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ከበረ፤

ወሰላሙ አለይኩም
ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው፥ አላህ የሚሰጠው "ነቢይነት" ደግሞ "ኑቡዋህ" نُبُوَّة ይባላል፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

ይህ ለአንድ ነቢይ የሚሰጠው ነቢይነት የተጠናቀቀው በመጨረሻው ነቢይ በነቢያችን”ﷺ” ነው፥ ነብያችን”ﷺ” የነቢያት ሁሉ መደምደሚያ ናቸው፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ ነው*፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

በተለያየ ጊዜ የሚመጡት የአላህ ነብያት ከኣደም ጀምሮ ተከታታይ ግህደተ-መለኮት ይወርድላቸው ነበር፥ እንዲሁ አላህ የወሰነላቸው የራሳቸው ዘመነ-መግቦትም ነበራቸው። ነገር ግን አንድ ዕድገት ጅማሬ እና ድምዳሜ እንዳለው ሁሉ ነብይነትም በኣደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ተጠናቋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከነቢይነት የተቋጨ የለም ከሙበሺራት በስተቀር። እነርሱም፦ "ሙበሺራት ምንድን ናት? አሉ። እርሷቸውም፦ "መልካም ሕልም ናት" አሉ"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ لَمْ يَبْقَ مِنَ النُّبُوَّةِ إِلاَّ الْمُبَشِّرَاتُ ‏"‌‏.‏ قَالُوا وَمَا الْمُبَشِّرَاتُ قَالَ ‏"‏ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል፥ ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም። አነሥም፦ "ሰዎችም ስለዚያ ጉዳይ አጢነው ነበር" አለ። እርሳቸውም፦ "ሙበሺራት ትሆናለች" አሉ። እነርሱም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሙበሺራት ምንድን ናት? አሉ። እርሳቸውም፦ "የሙሥሊም ሕልም፥ እርሷም ከነቢይነት ክፍል ናት" አሉ"*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ فَشَقَّ ذَلِكَ عَلَى النَّاسِ فَقَالَ ‏"‏ لَكِنِ الْمُبَشِّرَاتُ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ وَمَا الْمُبَشِّرَاتُ قَالَ ‏"‏ رُؤْيَا الْمُسْلِمِ وَهِيَ جُزْءٌ مِنْ أَجْزَاءِ النُّبُوَّةِ

"ሪሳላህ" رِسَالَة ማለት "መልእክት" ማለት ሲሆን "ረሱል" رَسُول ማለት ደግሞ "መልእክተኛ" ማለት ነው። ለነቢይ የሚሰጠው ነቢይት እንደተዘጋ ሁሉ ለመልእክተኛ የሚሰጥ መልእክትም ተዘግቷል። ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የሚመጣ ነቢይ ሆነ የሚላክ መልእክተኛ እንደሌለ ነቢያችን”ﷺ” እዚህ ሐዲስ ላይ ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነግረውናል። ነቢይነት ቢዘጋም ሙበሽራት ግን አለ፥ "ሙበሺራት" مُبَشِّرَات ማለት የሙሥሊም ሕልም ነው። የሷሊሕ ሙሥሊም መልካም ሕልም ከአርባ ስድስቱ የኑቡዋህ ክፍል አንዱ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 2
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *"የሷሊሕ ሰው መልካም ሕልም ከአርባ ስድስቱ የነቢይነት ክፍል አንዱ ነው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الرُّؤْيَا الْحَسَنَةُ مِنَ الرَّجُلِ الصَّالِحِ جُزْءٌ مِنْ سِتَّةٍ وَأَرْبَعِينَ جُزْءًا مِنَ النُّبُوَّةِ
መልአኩ ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” ከመምጣቱ በፊት ነቢያችን”ﷺ” ወሕይ በሕልም ይመጣላቸው ነበር፥ ይህም የእርሳቸው ሕልም ቆይታ 6 ወር ሲሆን የነቢይነት አንድ ክፍል ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 1 , ሐዲስ 3
የምእመናት እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"በእንቅልፍ ውስጥ ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከወሕይ መጀመሪያ ልክ እንደ ጎህ ንጋት ግልጽ ብሎ መልካም ሕልም ቢሆን እንጂ አይመጣላቸው ነበር። ከዚያም በራሳቸው መገለልን ይወዱ ነበር፥ በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና ቀጥ ይሉ ነበር። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህን ያመልኩ ነበር፥ ለቆይታም የጉዞ ምግብ ይይዙ ነበር። በሒራእ ዋሻ ሐቁ ወደ እሳቸው እስኪመጣላቸው ድረስ ወደ ባለቤታቸው(ኸዲጃህ) በመመለስ እንደዚሁ በድጋሚ ምግባቸውን ይወስዱ ነበር። ከዚያም መልአኩ ወደ እርሳቸው መጥቶ፦ "ኢቅራእ" አላቸው"*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ، وَيَتَزَوَّدُ لِذَلِكَ، ثُمَّ يَرْجِعُ إِلَى خَدِيجَةَ، فَيَتَزَوَّدُ لِمِثْلِهَا، حَتَّى جَاءَهُ الْحَقُّ وَهُوَ فِي غَارِ حِرَاءٍ، فَجَاءَهُ الْمَلَكُ فَقَالَ اقْرَأْ‏

በእንቅልፍ ከመልካም ሕልም ጅማሬ እስከ ጂብሪል ቁርኣንን "ኢቅራእ" ማለት ድረስ ስድስት ወር ያክል ነበር፦
የኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ ፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 1 ኪታቡ አት-ተዕቢር ባብ 2
"አሏህ ወደ ነቢዩ ለስድስት ወራት በሕልም ወሕይ አውርዷል"*። أَنَّ اللَّه أَوْحَى إِلَى نَبِيّه فِي الْمَنَام سِتَّة أَشْهُر

አንድ የእርሳቸው የነቢይነት ክፍል 6 ወር ከሆነ ሁለት ክፍል ደግሞ 6×2= 12 ወር ወይም አንድ ዓመት ነው፥ የእርሳቸው የነቢይነት ክፍል በአንድ ዓመት ሁለት ክፍል ከሆነ በ 23 ዓመት 46 ክፍል ይሆናል ማለት ነው። 23×2=46 ይሆናል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏

13+10=23 ይሆናል። 23 ዓመቱ በሁለት ክፍል ሲሆን 46 ከሆነ እንግዲያውስ መልካም ህልም ከአርባ ስድስቱ የነቢይነት ክፍል አንዱ ነው። አምላካችን አላህ ለሷሊሕ ሙሥሊም በሕልማቸው የሚያሳውቃቸው ዕውቀት "ኢልሃም" ነው፥ "ኢልሃም" إِلْهَام የሚለው ቃል "አልሀመ" أَلْهَمَ ማለትም "አነቃቃ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መነቃቃት" ማለት ነው። አላህ በነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት ተጠቃሚ ያድርገን! ኢልሃም ከሚሰጣቸው ሷሊሕ ሙሥሊም ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የነብያችን ጉብኝት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ከሓዲዎች በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህ ግን ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አፈልግም፤ ከዚያም ባሻገር ነብያችንን”ﷺ” በቅን መንገድ እና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርጋቸው ዘንድ የላከቸው ነው፦
9፥32-33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም يُرِيدُونَ أَن يُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَيَأْبَى ٱللَّهُ إِلَّآ أَن يُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸውን በመዞር በአንድ ሌሊት ይጎበኙ ነበር፤ ይህንን ጉብኝት ከሓዲያን በመገልበጥ መሳለቂያ አድርገው ብዙ ጊዜ እንደ በቀቀን ሲደጋግሙት ይደመጣል፤ ይህንን ገላባ ጥያቄ እስቲ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 5 , ሐዲስ 36:
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” እንደተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር፤ ለእርሳቸው በዚያን ጊዜ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩ أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُمْ أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَطُوفُ عَلَى نِسَائِهِ فِي اللَّيْلَةِ الْوَاحِدَةِ، وَلَهُ يَوْمَئِذٍ تِسْعُ نِسْوَةٍ‏.‏ ።

ይህ ዘገባ በኢማም ቡኻሪይ ውስጥ በተመሳሳይ አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከበት ብዙ ቦታ ሰፍሯል፤ ይህንን ዘገባ ጥልል እና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦

ነጥብ አንድ
“ጉብኝት”
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር” ብሎ ነው፤ “ይዞሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጡፉ” يَطُوفُ ሲሆን “ጣፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ኢሽቲቃቀል ከቢር ወይንም “ጠዋፍ” طَواف ማለትም “ዙረት” ከሚለው ኢሽቲቃቅ አሰጊር የመጣ ነው፤ በምን ቀመርና ስሌት ነው “ዙረት” ሲተረጎም “ተራክቦ” የሚሆነው? አላህ በሐጅ ጊዜ ቤቴንም “ለሚዞሩት”፣ ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ብሎ የለ እንዴ? ያ ማለት ተራክቦ ያድርጉ ማለት ነው እንዴ? ይህ የሌለ ፉርሽ ኢሥነ-አመክንዮ ነው፦
2:125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ” እና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን وَإِذْ جَعَلْنَا ٱلْبَيْتَ مَثَابَةًۭ لِّلنَّاسِ وَأَمْنًۭا وَٱتَّخِذُوا۟ مِن مَّقَامِ إِبْرَٰهِـۧمَ مُصَلًّۭى ۖ وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ፡፡
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም “ለሚዞሩት” እና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ አስታውስ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ።
22:29 ከዚያም ትርፍ አካላችቸንን እና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ثُمَّ لْيَقْضُوا۟ تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا۟ نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا۟ بِٱلْبَيْتِ ٱلْعَتِيقِ ።

ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” ይዞሩ የነበሩት ጉብኝት እንጂ ተራክቦ የሚል አልሰፈረም፤ ይጎበኙ ነበር ማለት ተራክቦ ነው ቢባልስ ችግሩ ምንድን ነው? አላህ የሰጣቸው ችሎታና ፀጋ ቢሆንስ? በክርስትናው አስተምህሮት ተራክቦ የኃጢአት ውጤት ነው ተብሎ የሚታመነው ኢስላም ጋር አይሰራም።
ምክንያቱም ተራክቦ ሰው የሚረካበትና አይኑን በአይኑ የሚያይበት የአብራኩ ክፋይ ነው፤ ለማንኛውም የሚቀጥለው ነጥብ “ይዞሩ” ነበር ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ዓኢሻ”ረ.ዓ.” ትነግረናለች፦
ነጥብ ሁሉት
“መነካካት”
በቁርአን አገላለፅ “መነካካት” የሚለው በግልፅና በማያሻማ ተራክቦን ነው፤ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት መርየም ለመላኩ የመለሰችው መልስ እና አላህ ስለ ሴቶች የተናገረውን ማየት ይቻላል፦
3፥46 ፡-ጌታዬ ሆይ! “ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” አለች قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ ፡፡
19፥20 « ሰው “ያልነካኝ” ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّۭا ፡፡
2፥236 ሴቶችን “ሳትነኳቸው” ወይም ለእነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةًۭ ۚ ፡፡

“ሰው ያልነካኝ” እና “ሳትነኳቸው” የሚለው ቃል “ተራክቦን” ካመለከተ ይህንን ነጥብ ይዘን ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደነገረችን እያንዳንዳቸው የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸው የየራሳቸው ቀናት እንዳላቸውና ግን በቀን ውስጥ ሁሉንም ሴቶች “ያለ ንክኪ” ማለትም ያለ ተራክቦ “ይዞሩ” እንደነበር ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12 , ሐዲስ 90:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” አለች፦ የእህቴ ልጅ ሆይ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እኛ ጋር በሚቆይበት ጊዜ አንደኛችን ከሌላኛችን ጋር አያበላልጡም ነበር፤ ትንሽ ወቅት ሁላችንም ጋር “ይዞሩ” يَطُوفُ ነበር፤ ቀኑዋ የደረሰበት ሴት እስከሚደርስ እና እስከሚያድር ድረስ ሁላችንም ሴቶች ጋር “ያለ ንኪክይ” غَيْرِ مَسِيسٍ ይቀርቡን ነበር قَالَتْ عَائِشَةُ يَا ابْنَ أُخْتِي كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لاَ يُفَضِّلُ بَعْضَنَا عَلَى بَعْضٍ فِي الْقَسْمِ مِنْ مُكْثِهِ عِنْدَنَا وَكَانَ قَلَّ يَوْمٌ إِلاَّ وَهُوَ يَطُوفُ عَلَيْنَا جَمِيعًا فَيَدْنُو مِنْ كُلِّ امْرَأَةٍ مِنْ غَيْرِ مَسِيسٍ حَتَّى يَبْلُغَ إِلَى الَّتِي هُوَ يَوْمُهَا فَيَبِيتُ” ።

ምን ትፈልጋለህ? አንዱን አጠማለው ብትል በአንዱ ትያዛለህ፤ ሚሽነሪዎች የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ቢፈልጉም አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8-9 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፤ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው يُرِيدُونَ لِيُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ በእውነተኛው ሃይማኖትም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጽላት እና ታቦት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

"ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" "ፊደል" ማለት ነው፤ የጽሌ ብዙ ቁጥር "ጽላት" ሲሆን "ሰሌዳዎች" ወይም "ፊደሎች" ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ደግሞ "ላሁት" לֻחֹ֣ת ሲሆን በዐረቢኛ "ለውሕ" لَوْح ነው፣ አምላካችን አላህ ለሙሳ ቃላትን በፊደል ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ
7፥154 *ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ*፡፡ وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ

ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተምዝግቧል፦
ዘጸአት 24፥12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ *እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው*።

"ታቦት" ማለት "ማህደር" "ሰገባ" "ሳጥን" "ማደሪያ" ማለት ነው፣ በዕብራይስጥ ደግሞ "አሮውን" אֲר֖וֹן ሲሆን በዐረቢኛ "አት-ታቡት" التَّابُوتُ ነው፣ አምላካችን አላህ ስለ ታቡት እንዲህ ይለናል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- *«የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ "ሳጥኑ" ሊመጣላችሁ ነው*፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

"ሳጥኑ" ለሚለው ቃል የገባው "አት-ታቡት" التَّابُوتُ ነው፤ ይህ ቃል የሙሳ እናት ለጣለችው ሳጥን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
20፥39 *«ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ ጣይው*፡፡ እርሱንም ሳጥኑን በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ፡፡ أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ ታቦት የጽላቱ ማህደር ወይም ሰገባ ሲሆን ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተምዝግቧል፦
ዘጸአት 25፥10 *ከግራር እንጨትም "ታቦትን" ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን*።
ዘዳግም 10፥5 *ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ "ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው" እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ*።

ይህ እንዲህ ከሆነ ይህ ጽላት እና ታቦት የት ገባ? በተለይ የአገራችን ሰዎች እንደሚተርኩልን ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ አቢሲኒያ በዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን በሰለሞን ዘመነ-መንግሥት እንደገባ ይነገራል፣ ነገር ግን በዓለማችን ታሪክ ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፋና ከዚያ በፊት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደነበረ ተዘግቧል፤ በተጨማሪ የእዝራ ሱቱኤል ጽሐፊ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ ይዘግባል፦
እዝራ ሱቱኤል 9፥6-7 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም ግናይቱ እንደጠፍች ምስጋና እንደቀረ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ *ታቦተ ፅዮን እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ። ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ፅዮን እንደጠፍች ቀረች*፤ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን።

የአገራችን ታሪክ የተፋለሰ መሆኑን የምናውቀው ይህ ጥቅስ ታቦተ ጽዮን በባቢሎናውያን እንደጠፋች መናገሩ ነው። ከዚያም ባሻገር ከሰለሞን 400 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ በኢየሩሳሌም መኖሩን በዜና መዋዕል ላይ ተዘግቧል፦
ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ *ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ *አኑሩት*፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤

ታቦተ ጽዮን አክሱም ላይ አለች የሚለው ትረካ ከክብረ ነገሥት ውጪ የታሪክ፣ የባይብል እና የሥነ-ቅርፅ መረጃ ሆነ ማስረጃ የለም። ታቦቱ እና ጽላቱ ቢኖሩም እንኳን በአዲስ ኪዳን ጥቅም የላቸውም። የአዲስ ኪዳን ታላቁ ጸሐፊ ጳውሎስ እንደሚነግረን ከሆነ ሙሴ ንዋየ-ቅዱሳቱን የሚሰራው የሚመጣውን ነገር እያየ እንደነበር ተዘግቧል፦
ዕብራውያን 8፥5 እነርሱም *ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና*።
ዘጸአት 25፥40 በተራራ ላይ *እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ*።
የሐዋርያት ሥራ 7፥44 *እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች*፤

ይህንን ጳውሎስ ታቦትና ጽላት "ጥላ"typology" እንደሆነ ይናገራል፤ ብሉይ ላይ የነበረው ኪዳን በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፤ ይህም ኪዳን ጥላነቱ ታቦቱ የሰው አካል ሲሆን የሚጻፍበት ፊደል ደግሞ ለሰው ልብ ምሳሌ ሆኖ አዲሱ ኪዳን በልብ የሚጻፍ መሆኑኑን ይነግረናል፦
ኤርምያስ 31፥31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር *አዲስ ቃል ኪዳን* የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር *የምገባው ቃል ኪዳን ይህ* ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ*፥ *በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ዕብራውያን 8፥10-13 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። .. *አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል*።
ብሉይ ማለት አሮጌ ማለት ነው። አሮጌ ያሰኘው አዲሱ ነው፣ አሮጌው ኪዳን ህጉ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ሲሆን አዲሱ ደግሞ በልብ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ነው፣ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ኪዳን አሮጌና ውራጅ እንደተባለ አስተውሉ፣ ከዚያም ባሻገር በአዲሱ ኪዳን አሮጌው ኪዳን ተሽሯል ይላል፦
2ኛ ቆሮ 3፥3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ *ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት* እንጂ *በድንጋይ ጽላት* ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
2ኛ ቆሮ 3፥7 ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ *ተሻረው* ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ *ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት* በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
2ኛ ቆሮ 3፥13 *የዚያንም ይሻር* የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
2ኛ ቆሮ 3፥14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ *የተሻረ* ነውና።

ምን ትፈልጋለህ? በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸው ጽላት በልብ ጽላት ተሽሯል፣ ቤተመቅደሱም ሰው ሆኗል፦
1ኛ ቆሮ 3፥16-17 *የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ* የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም *የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ*።
1ኛ ቆሮ 6፥19-20 ወይስ *ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?*

አዲሱ ኪዳን ህጉ የተጻፈው በልብ ጽላት ላይ ከሆነ ቤተመቅደሱ የሰው አካል ከሆነ እግዚአብሔር ሰው በሰራው ቤተ መቅደስ አይኖርም ይለናል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም
የሐዋርያት ሥራ 7፥50 ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል *የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም*።
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ *የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?*
ኤርምያስ 3፥16 በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ *የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም* ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ *ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም*።

የሚገርመው የአገራችን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ስንጠቅስ "ተሽሯል" ይሉናል፣ የተሻረው ታቦቱትና ጽላቱ እንጂ ሕጉ አይደለም። ሕጉማ በልብ ተጽፏል ተብሏል። የአገራችን ክርስቲያኖች ሕጉ ተሽሯል ይሉና የተጻፈበት ድንጋይ ሆነ የሚቀመጥበት ታቦት አልተሻረም ብለው ድርቅ ይላሉ፣ እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ በግልጽ የድንጋይ ጽላት እንደተሻረና አምላክ ሰው በሰራው ቤተመቅደስ እንደማይኖር ተናግሯል፣ ነገር ግን ዛሬ ያሉት ያገራችን ሰዎች ዛርኒሽ በተቀባ እንጨት ቀርጸው ታቦት ነው ብለው ለታቦቱ ሲሰግዱ፣ ሲለማመኑ፣ ሲማጸኑ፣ ሲሳሉ፣ ዕጣን ሲያጨሱ ይታያል፣ ይህ በትንቢት ስለ እነርሱ የተነገረው እየተፈጸመ ነውና በተውበት ወደ አላህ ተመለሱና አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምልኩ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 *ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአክሱም ሙስሊሞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

አክሱም ላይ የአክሱም ሥልጣኔ በነበረበት ሰአት የተተከለው የ24 ሜትር ወይም 78 ጫማ ርዝመት እና 160 ቶን የሚመዝነው የአክሱም ሃውልት ነው። ይህ ሃውልት የወንድ ሃፍረተ-ስጋ ምስል ነው። ከኩሻይቲክ የሜሮይ አገዛዝ የተወሰደ ይህ ምስል ቅድመ-ክርስትና በአክሱም ላይ ይመለክ እንደነበረ ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ ያሰፈረው ጉዳይ ነው። ክርስትና አክሱም ሲገባ ይህንን ጣዖት ከማፍረስ ይልቅ አጠገቡ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን ይዞ በገባው በአቡነ ሰላማ ማለትም በፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃን ዘመን የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ተገንብቷል፤ አሁን ያለችውን ደግሞ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት የተሠራች ናት።

ዛሬ አክሱም ውስጥ ያሉት ሙስሊሞች መስኪድ እንዳይገነቡ የአክሱም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አግደዋል። ይህም የሆነው በሁለት ተልካሻ ምክንያት ነው። አንደኛው በአምልኮት ቦታቸው ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ ሲሆን ሁለተኛው ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚል ሁለት ተልካሻ ምክንያቶች ይዘዋል።

ምክንያት አንድ
በአምልኮት ቦታችሁ ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ቅድሚያ እዛው አክሱም ውስጥ ሲመለክ የነበረውን ጣዖት በቅርስነት ከጽዮን ቤተክርስቲያን ጋር ከመደበል ይልቅ አፈራርሶ ማቃጠል ይጠበቅባችሁ ነበር፦
ዘዳግም 7፥5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ *ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ*።

ሁለተኛ የሙስሊም አምልኮ ባዕድ አምልኮ ሳይሆን ጥንት የነበሩት ነብያት ሲያመልኩት የነበረው የዓለማቱ ጌታን አላህን ብቻ በብቸኝነት የሚመለክበት ነው። ሦስተኛ ጥንት የነበረው የሙሴ ታቦት ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የለም። ለምን ይዋሻል? አሁን አርስቱ ስላልሆነ "ጽላት እና ታቦት" የሚለውን የእኔን መጣጥፍ አንብቡት።

ሁለተኛው ምክንያት
ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ከመነሻው እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ዐረባውያን አይደለንም። ሲቀጥል ሳውዲ ቤተ-ክርስቲያን የማይገነባው ሳውዲ ውስጥ ክርስቲያን ስለሌለ እንጂ አሁን ከተለያዩ አገር ለሥራ የመጡ ዜጎች የአምልኮ ቦታ ያስፈልጋቸው ተብሎ ቤተ-ክርስቲያን ሊሰራላቸው ተፈራርመው ጨርሰዋል። በኢስላምም አህለል ዚማህ ማለትም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በኢስላም አገር ውስጥ ጂዚያህ እስከከፈሉ ድረስ የአምልኮ ነጻነት አለ።
ሢሰልስ ኢትዮጵያ የሁለቱም ሃይማኖት አገር ናት፤ የምትመራበት መርሕ በሕገ መንግሥት እንጂ በፍትሐ-ነገሥት ወይም በሲኖዶስ አሊያም በመጅሊስ አይደለም። ሕገመንግሥቱ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 2 እንዲህ ይላል፦
"የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት እና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማኖት ትምህርት እና ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ።"

ምን ትፈልጋለህ? አክሱም ላይ ያሉት ሙስሊሞች መስጊድ መገንባት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው። በመነጋገር ከማመን ይልቅ በዱላ እመን የሚለውን የአጼዎቹ ሥርዓት ናፋቂዎቹ፦ "አክሱም ላይ መስኪድ እሰራለው ያለ ደሙ ይፈሳታል" የሚል ቃለ ፉከራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለፈልፉ ይደመጣል፤ ክርስትና ፍቅር ናት፣ ክርስትና ቀኝህን ሲመታ ግራህን ስጠው ስብከት ላይ ብቻ ነው የሚሰራው። እናንተ እነማን ናችሁ? ምንስ ስለሆናችሁ ነው? የመከልከል ሞራሉም ብቃቱም የላችሁም። በዚህ ነጥብ ላይ ማንም ምንም ናችሁ። ሕገ-መንግሥቱን የማያከብር ግለሰብ ሆነ ተቋም ሕገወጥ ነው። አጼዎቹ አንዴ በግድ ካልተጠመቃችሁ፣ አንዴ የኢስላም ልጅ ትምህርት አያስፈልገውም እየተባለ ከትምህርት ገበታው ሲያባርር አባት ለሰራው ልጅ አይጠየቅም በሚል መርሕ በይቅርታ ስናልፋችሁ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ስትሞሉ ፈለጋችሁ? የአክሱም ሙስሊሞችን በደል የሚካሱበትን ቀን አላህ ያፍጥነው! አሚን። በዓለም ላይ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው በደል ታሪክ ይቁጠረው፤ አላህ የፍርዱ ቀን ለበደለኞች ቅጣት አዘጋጅቷል። አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ብቻ ነው፦
14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአላህ ባህርይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 53, ሐዲስ 32
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አዝዘ ወጀል አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا،

የቋንቋው ሊሂቃን "ሱራ" صورة ማለት "መልክ" image" ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ይህም "መልክ" ባህርይ ለማመልከት እንደሚመጣ ይናገራሉ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 ሐዲስ 2
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ የመጀመሪያው ግሩፕ በሌሊት ሙሉ እንደሆነች በጨረቃ "#መልክ" صُورَةِ ሆኖ ወደ ጀነት ይገባሉ። إِنَّ أَوَّلَ زُمْرَةٍ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ الْقَمَرِ لَيْلَةَ الْبَدْرِ،

በዚህ ሐዲስ ላይ መቼም የጨረቃ መልክ የጨረቃን ቅርፅና ክብደት ለማመልከት ነው ከተባለ የጨረቃ ቅርጷ 1958×1010 km3 እንዲሁ ክብደቷ 7.342×1022 kg ነው፤ ያ ማለት ሰው ጀነት የሚገባው በጨረቃ ቅርፅና ክብደት ነው ማለት ሳይሆን የጨረቃ ባህርይ የሆኑን ንፅህናዋን፣ ድምቀቷ እና ውበቷን ማለቱ ነው፤ እንግዲህ "ሱራ" صورة "መልክ" የአንድን ህላዌ ባህርይ ለማመልከት ከመጣ ይህም "መልክ" ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ የሚባሉትን ባህርያት ያቅፋል፤ አላህ ሁሉን ነገር ተመልካች፣ ሁሉን ነገር ሰሚ እና ሁሉን ነገር አዋቂ ነው፤ አላህ አደምን ሲፈጥረው በባህርያቱ የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ እና የሚያውቅበት ልብ"አንጎል" ሰቶታል ማለት ነው፦
67:23 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም "#መስሚያ" እና "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ያደረገላችሁ ነው፤ ጥቂትንም አታመሰግኑም በላቸው።
23፥78 እርሱም ያ "#መስሚያዎችንና" "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡

አላህ "የሚመስለው ምንም ነገር የለም" አላህ ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው፦
42:11"የሚመስለው" ምንም ነገር የለም፤ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው።

አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው እንደተባለ ሁሉ ሰውም ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው ተብሏል፦
76:2 እኛ ሰዉን፥ በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ "ሰሚ" "ተመልካችም" አደረግነዉ።

ነገር ግን አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው የተባለው ሰው ሰሚ" እና "ተመልካች" በተባለበት ሂሳብ አይደለም፤ ምክንያቱም አላህ ሁሉን ነገር ይሰማል ያያል፤ ይህ ባህርይ ጊዜና ቦታ አይገድበውም፤ ሰው ግን ያለ ብርሃን ማየት እና ያለ ድምፅ መስማት አይችልም፤ በተመሳሳይ አላህ ሁሉን አዋቂን ነው እውቀቱ በጊዜና በቦታ አይገደብም፤ ሰው ግን እውቀቱ ጊዜ እና ቦታ ይገድበዋል፦
58:6 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።
67:19 እርሱ በነገር ሁሉ ተመልካች ነው።
4:86 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።
39:62 እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።
33:27 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

የሰው መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም ከአላህ የሆኑ ፀጋ ሲሆኑ ከእንስሳ በተለየ መልኩ ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ተጠያቂ ናቸው፦
17:36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ #መስሚያ#ማያም#ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ #ተጠያቂ ነውና إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ።
102:8 ከዚያም #ከጸጋዎቻችሁ النَّعِيمِ ሁሉ በዚያ ቀን #ትጠየቃላችሁ ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ ።
16:93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ #ትጠየቃላችሁ" وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ ።

የአላህ ዛት የራሱ ሲፋ አለው ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ እና እጅ ግን ከፍጡራን ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ፣ መናገር እና እጅ ጋር አይመሳሰልም። ለምሳሌ የሰው እጅ ቀኝና ግራ ነው የአላህ እጆች ግን ቀኝ ናቸው፦
ኢማም ሙስሊም 33, ሐዲስ 21 ፍትኸኞች አላህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር-ረህማን በስ-ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፤ ሁለቱም እጆቹ #ቀኝ ናቸው። " ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻘْﺴِﻄِﻴﻦَ ﻋِﻨْﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻨَﺎﺑِﺮَ ﻣِﻦْ ﻧُﻮﺭٍ ﻋَﻦْ ﻳَﻤِﻴﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻭَﻛِﻠْﺘَﺎ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻤِﻴﻦٌ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﺪِﻟُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺣُﻜْﻤِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﻟُﻮﺍ "

አላህ በራሱ ባህርይ ፈጠረው ማለት ለምሳሌ አላህ አደምን በእጁ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *"በሁለት እጆቼ"* "ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ
36፥71 እኛ *"እጆቻችን ከሠሩት"* ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًۭا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ

እጅ የአላህ ባህርይ ነው፤ ኹን የሚለው ንግግሩ የራሱ ባህርይ ነው፤ በባህርይው አደምን ፈጥሮታል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ *ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*። وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ ፤

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን “ነገረኝ” ለሚለው ደግሞ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነቢይ ማለት ሁሉን ዐዋቂውና ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሙሳ ዘመን በኢስራኢል ልጆች የተነሱ ነቢያት ናቸው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

"በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ ጊዜ" የሚለው ይሰመርበት፤ እነዚህ ነብያት ነገዶቹ ናቸው፤ አላህ ወደ ነገዶቹ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ *ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ *በነገዶችም ላይ በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው፣ ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብ እና *ወደ ነገዶቹም በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

አላህ ወሕይ የሚወርድላቸውን እነዚህን ነገዶች አሥራ ሁለት አለቆች አድርጎ አስነሳቸው፤ ለአሥራ ሁለትም ሕዝቦች ከፋፈላቸው፦
5፥12 *አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን*፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا
7፥160 *አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው*፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ መታውም *ከእርሱ አሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ*፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا
ጥንት የአሥራ ሁለቱ አበው የቃልኪዳን መጽሐፍ የነበረ ሲሆን አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ውሳኔ የአፓክራፋ መጽሐፍ ብለው ቀንሰውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የመጽሐፉን ባለቤቶችን ጠይቁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ የምናወርድላቸው የኾነን *”ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም”*፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች *”ጠይቁ”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ ፡፡

ብዙ ሚሽነሪዎች ከላይ ያለውን አንቀፅ ሲመፃደቁበት ማየት የተለመደ ሆኗል፤ “እናንተ ሙስሊሞች እኛን ጠይቁ ተብላችኃል” እያሉ እንደበቀቀን ሲደጋግሙትም ይታያል፤ እልህ መርፌ ሊያስውጣቸው ከሚደርሱ መሃይማን ጋር ጊዜን፣ ጉልበትና እውቀትን ማባከን አግባብ አይደለም፤ ሳይገባቸው ስለሚናገሩ ሃሳባቸው ሲዝረከረክባቸው ማየት የተለመደ ነው፤ “ዱባና ቅል አበቃቀላቸው ለየቅል” ይላል ያገሬ ሰው፤ በየትኛው ቀመርና ስሌት ነው ሙስሊም እውቀት ፈልጎ ክርስቲያንን የሚጠይቀው? ይህንን አንቀፅ መንሃጅ ማለትም ቀደምት ሰለፎች እና ሙፈሲሪን የተረዱበትን ነጥብ በነጥብ ማየት አለብን፦

ነጥብ አንድ
“ተጠያቂዎች”
የመጽሐፉን ባለቤቶች የተባሉት ተጠያቂዎች ክርስቲያንና አይሁዳውያን እንደሆኑ እሙንና ቅቡል ነው፦
3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! *”እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ”* እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን *”ትደብቃላችሁ”*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ ።
5፥68 እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን”* እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَىْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ ۗ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًۭا مِّنْهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَٰنًۭا وَكُفْرًۭا ۖ فَلَا تَأْسَ عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ ፡፡
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም *”በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው”* አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ ፡፡

በተናጥል የመጽሐፉን ባለቤቶች የተባሉት አይሁዳውያን እንደሆኑ ይህ አንቀፅ ያስረዳል፦
4፥153 የመጽሐፉ ሰዎች በነሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል፡፡ ከዚያም የከበደን ነገር ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል፡፡ «አላህንም በግልጽ አሳየን» ብለዋል፡፡ በበደላቸውም መብረቅ ያዘቻቸው፡፡ ከዚያም ተዓምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ ከዚያም ይቅር አልን፡፡ ሙሳንም ግልጽ ስልጣንን ሰጠነው يَسْـَٔلُكَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ أَن تُنَزِّلَ عَلَيْهِمْ كِتَٰبًۭا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ ۚ فَقَدْ سَأَلُوا۟ مُوسَىٰٓ أَكْبَرَ مِن ذَٰلِكَ فَقَالُوٓا۟ أَرِنَا ٱللَّهَ جَهْرَةًۭ فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ بِظُلْمِهِمْ ۚ ثُمَّ ٱتَّخَذُوا۟ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ فَعَفَوْنَا عَن ذَٰلِكَ ۚ وَءَاتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَٰنًۭا مُّبِينًۭا ፡፡

በተናጥል የመጽሐፉን ባለቤቶች የተባሉት ክርስቲያኖች እንደሆኑ ይህ አንቀፅ ያስረዳል፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ «ሦስት ነው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا ፡፡
ነጥብ ሁለት
“ጠያቂዎች”
አላህ “ጠይቁ” ብሎ ያለው ማንን ነው የሚለውን ነጥብ ለመረዳት ቅድሚያ አውዱ መመልከት ግድ ይላል፤ አረብ ሙሽሪኪን፦ “ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን? በማለት ተናገሩ፦
21፥3 ልቦቻቸው ዝንጉዎች ኾነው እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ፡፡ *”ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን?”* እናንተም የምታዩ ስትኾኑ *”ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?”*» አሉ لَاهِيَةًۭ قُلُوبُهُمْ ۗ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ هَلْ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ ۖ أَفَتَأْتُونَ ٱلسِّحْرَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ፡፡

አረብ ሙሽሪኪን፦ “ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለምና ይህ መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን”* ምን አለው አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ እርሱ መልአክ አይወረድም ኖሯልን? አሉ፦
25፥7 ለእዚህም *”መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን”* ምን አለው ከእርሱ ጋር *”አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ አይወረድም”* ኖሯልን? *”አሉ”* وَقَالُوا۟ مَالِ هَٰذَا ٱلرَّسُولِ يَأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِى فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۙ لَوْلَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكٌۭ فَيَكُونَ مَعَهُۥ نَذِيرًا ፡፡
25፥21 እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት፦ *”በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም”*፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም *”አሉ”*፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا ۗ لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّۭا كَبِيرًۭا ፡፡

አላህም ከዚህ በፊት አስጠንቃቂ ይኾኑ ዘንድ ወህይ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፤ ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም፤ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ ብሎ ምላሽ ሰጠ፦
21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ የምናወርድላቸው የኾነን *”ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም”*፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች *”ጠይቁ”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ ፡፡
21፥8 *”ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም*”፡፡ ዘውታሪዎችም አልነበሩም وَمَا جَعَلْنَٰهُمْ جَسَدًۭا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَٰلِدِينَ ፡፡
25፥20 ከአንተ በፊትም *”ከመልክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۗ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍۢ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ ۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًۭا ፡፡

አላህ ጠይቁ ያለው ጠያቂዎች አረብ ሙሽሪኮችን መሆኑን ካየን ጠይቁ የተባሉት ጥያቄ፦ “ከነብያችን በፊት ወህይ ሲወርድላቸው የነበሩት ሰዎች ወይስ መልአክ” የሚለውን ነው፤ አረብ ሙሽሪኮች ከእነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው አላህ ወህይ ማውረዱ ድንቅ ስለሆነባቸው ያንን ወህይ ድግምት ነው፤ መልእክተኛውን ድግምተኛ ነው ብለው አስተባበሉ፦
10፥2 *”ሰዎችን አስጠንቅቅ”*፤ እነዚያንም ያመኑትን ለእነርሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን *”አብስር”*» በማለት *”ከእነርሱው”* ወደ ኾነ አንድ ሰው *”ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን”* ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» *”አሉ”* أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ رَجُلٍۢ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ قَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌۭ مُّبِينٌ ፡፡
38፥4 *”ከእነርሱ የሆነ አስጠንቃቂም”* ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም፦ *”ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው”*» *”አሉ”* وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌۭ كَذَّابٌ ፡፡
50፥2 ይልቁንም *”ከእነርሱ”* ጎሳ የኾነ *”አስጠንቃቂ”* ስለ *”መጣላቸው”* ተደነቁ፡፡ *”ከሓዲዎቹም”* «ይህ አስደናቂ ነገር ነው» *”አሉ*” بَلْ عَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَىْءٌ عَجِيبٌ ፡፡

አላህም ነብያችንን፦ “ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፤ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ” በላቸው በማለት ተናግሯል፦
6:50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ *”ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም”*፡፡ ወደ እኔ *”የሚወርድልኝን”* እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ፡፡
18፥110 «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ *”ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ”*፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”* قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا ፡፡
መደምደሚያ
ስለዚህ ቁርአን ላይ ሙስሊሞች በሁሉም ርእሰ ጉዳይ ላይ የመጽሓፉ ባለቤቶችን ጠይቁ ሳይሆን ያለው አረብ ሙሽሪኮችን ከእዚህ በፊት ግህደተ መለኮት ሲወርድላቸው የነበረው መልአክ ሳይሆን ሰዎች ነው፤ ይህንን የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሓፉ ባለቤቶችን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አስጠንቃቂ ለምን ሰው ይሆናል የሚል ሙግት ያቀረቡት እነርሱ ናቸው እንጂ ሙስሊሙማ በነብያችን ነብይነት በቁርአን የአላህ ቃል መሆን ያምናል፤ ምን ብሎ ይጠይቃል? በተጨማሪም ከነብያችን በፊት በነበሩት መልእክተኞች ሰው መሆናቸውን ያምናል፦
2፥285 መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፤ ምእምኖቹም እንደዚሁ፤ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ *”በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ”*፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን እንሻለን፡፡ መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው» *”አሉም”* ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّن رُّسُلِهِۦ ۚ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የተሳከረ ምልከታ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

መግቢያ
ትጉሃን ሃያሲ በስሙር ሙግት ሂስ ሲሰጡ ማዳመጥ አስተማሪ ከመሆን ባሻገር ያለንበትን እውነት እንድናጠናክር ያበረታታል፤ በተቃራኒው ሚሽነሪዎች ቧጠውና ሟጠው በጥላቻ ለሚያጠለሹአቸው ጥላሸት ኢስላማዊ አቃቤ-እምነት መሰረት አድርገን ድባቅ ማስገባት ግድ ይላል፤ የተሳከረ፣ የተውረገረገ፣ የደፈረሰና የተንሸዋረረ ምልክታ የሚመጣው ከእጥረተ-ንባብ እና ከጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው፤ በተለይ በአላህ ላይ የማያውቁትን መናገር ከሸይጧን ነው፤ ሰይጣን ወዳጆቹን የሚያዛቸው በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር በአላህም ላይ የማያውቁትን እንዲናገሩ ነው፦
2፥169 እርሱ(ሰይጣን) የሚያዛችሁ በኃጢኣትና በጸያፍ ነገር *”በአላህም ላይ የማታውቁትን እንድትናገሩ ብቻ ነው”*፡፡ إِنَّمَا يَأْمُرُكُم بِٱلسُّوٓءِ وَٱلْفَحْشَآءِ وَأَن تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
10፥68 *”በአላህ ላይ የማታውቁትን”* ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ሆን ተብሎ በአላህ ላይ ውሸትን ቀጣጥፎ አንቀጾቹን ማስተባበል ትልቅ በደል ነው፤ በደለኞች ደግሞ ከጀሃነም መዘውተር አይድኑም፦
6፥21 *በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው?”* እነሆ *”በደለኞች አይድኑም”*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ ۗ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلظَّٰلِمُونَ
10፥17 *በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው?”* እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡ فَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْمُجْرِمُونَ
29፥68 *”በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው?* በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን? وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِٱلْحَقِّ لَمَّا جَآءَهُۥٓ ۚ أَلَيْسَ فِى جَهَنَّمَ مَثْوًۭى لِّلْكَٰفِرِينَ

እንግዲህ እውነቱን እንገልጣለን ቅጥፈቱን እናጋልጣለን፤ አንድ ሰው ይህ እውነት በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ በደለኛ ከሃጂ ነው፤ ለከሓዲዎች ደግሞ መኖሪያ ገሀነም ነው፤ እስቲ ይህንን አለሌ እና ቅሪላ ምልከታ አንኮላ እና እንኩቶ መሆኑን እናሳያለን፦
ነጥብ አንድ
“ኢላህ”
“አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም 2699 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው””the Being Who worshiped” ማለት ነው፤ Lane’s Arabic-English Lexicon by Edward William Lane (London: Willams & Norgate 1863) ይመልከቱ።
“አሏህ” ኢስሙል ዛት” ማለትም “የህላዌው ስም” ነው፤ “ዛት” ذات ማለት “ምንነት” ሲሆን አላህ በምንነቱ የሚመለክ ነው፤ ማንነት እከሌ የሚባል ነው፤ ፈጣሪ ማን ነው? ጌታ ማን ነው? አስተናባሪ ማን ነው? ተብሎ ሲጠየቅ አላህ ነው፦
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡

አላህ ማንነት ሲሆን የህላዌ ስሙ ነው፤ የተጸውዖ ስም በየትኛውም ቋንቋ እራሱን ነው እንጂ በትርጉም አይጠራም፤ ለምሳሌ “ወሒድ” ስሜ ነው፤ ትርጉሙ “ብቸኛ” ማለት ነው፤ ኢትዮጵያ “ብቸኛ” ኢንግላንድ “only” ስውዲን “bara” ግሪክ “ሞኖ” እስራኤል “ያኺድ” እባላለውን? በፍፁም ይህ የተጸውዖ ስም የትም አገር አይቀየርም። እዚህ ድረስ ካየን አላህ የስሙን ትርጉሙ ከላይ እንዳየነው “የሚመለክ” ወይም “አምልኮ የሚገባው” ማለት ሲሆን አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ተቺዎች ጎግል ላይ በሚቃርሟት የለበጣ መረጃ አሏህ “አል” ال እና “ኢላህ” إِلَٰه ከሚል ቃላት የተዋቀረ ነው ይላሉ፤ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፤ “ኢላህ” إِلَٰه ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፤ “አል” የሚል አመልካች መስተአምር”definite article” ሲገባበት “አል-ኢላህ” الإِلَٰه “አምላክ”the-God” ይሆናል እንጂ ትርጉሙ “አሏህ” ٱللَّه ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም አሏህ ላይ ላም ተሽዲድ ሆና ትመጣለችና፤ “ኢላህ” ላይ ግን ሸዳህ የለውም። “ኢላህ” 147 ጊዜ በቁርአን የመጣ ሲሆን የኢላህ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አሊሀህ” آلِهَةٌ ማለትም “አማልክት” ነው፤ “ኢላህ” ማለት “አምላክ”God” ተብሎ በትርጉም መጠቀም ይቻላል፤ የማዕግረ ስም ስለሆነ፤ ግን “አላህ” የተፀውዖ ስም ስለሆነ እራሱ ነው የሚቀመጠው፦
17:22 “ከአላህ” ጋር ሌላን “አምላክ” አታድርግ፤ የተወቀስክ ረዳት የሌለህ ትሆናለህና لَّا تَجْعَلْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَقْعُدَ مَذْمُومًۭا مَّخْذُولًۭا ፤
28:88 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ وَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ ۘ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَىْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُۥ ۚ لَهُ ٱلْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ፡፡
26:213 “ከአላህም” ጋር ሌላን “አምላክ” አትጥራ፤ ከሚቀጡት ትኾናለህና فَلَا تَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ فَتَكُونَ مِنَ ٱلْمُعَذَّبِينَ ፡፡

በሰዋስው ሕግ “ያ” يا ማለት “ሆይ”O” ማለት ሲሆን ቃለ-አህስሮ”Vocative particle” ነው፤ በዚህ ሕግ “ያ ረብ” يا رَبِّ “ያ ኢላህ” يا إِلَٰه “ያ ረህማን” يا رَّحْمَٰنِ “ያ ረሂም” يا رَّحِيمِ ወዘተ በማለት “ነኪራህ” نكرة ማለትም “ኢ-አመልካች መስተአምር” በማድረግ መጠቀም እንችላለን፤ ነገር ግን “ማዕሪፋህ” معرفة ማለትም “አመልካች መስተአምር” የሆኑትን ቀመርያህ እና ሸምሲያህ ጨምረን “ያ አር-ረብ” “ያ አል-ኢላህ” “ያ አር-ረህማን” “ያ አር-ረሂም” ወዘተ ማለት አይቻልም። አሏህ ቃሉ አል-ኢላህ ቢሆን ኖሮ “ያ አሏህ” يا ٱللَّه የሚለው አይመጣም ነበር፤ አሏህ ላይ ግን “ቃለ-አህስሮ” በመነሻ “ያ አሏህ” يا ٱللَّه አሊያም በመዳረሻ “አሏሁ-ማ” ٱللَّهُمَّ ሆኖ ይመጣል፦
3:26 በል- የንግሥና ባለቤት የሆንክ *”አላህ ሆይ”*! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ በችሎታህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና። قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُ ۖ بِيَدِكَ ٱلْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ

ሌላው በቋንቋ ሕግ ያለው የሙህራን አቅዋል አንድ ቃል ከግስ መደብ እና ከስም መደብ ሲረባ “ሙሽተቅ” مُشتَق ማለትም “ሥርወ-ግንዳዊ ቃል”derivative word” ሲባል ነገር ግን አንድ ቃል ከግስ መደብ እና ከስም መደብ የማይረባ ከሆነ “ጃሚድ” جامِد ማለትም “ሥርወ-ግንድ አልባ”un-derivative word” ይባላል፤ በዐረቢኛ ቋንቋ ሕግ የአሏህ ስም ጃሚድ ነው። ስለዚህ አሏህ ከአል-ኢላህ ሥርወ-ግንድ የተገኘ ነው ማለት የተሳከረ፣ የተውረገረገ፣ የደፈረሰና የተንሸዋረረ ምልክታ ነው። ኢንሻላህ ሌላውን የተሳከረውን ምልከታ በክፍል ሁለት እናየዋለን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተሳከረ ምልከታ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ነጥብ ሁለት
“አላህ”
” አሏህ” በዕብራይስ “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን ይህንን ቃል በዕብራይስጥ የቁርአን ትርጉም ላይ እናገኘዋለን፤ ነገር ግን ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች ግልብ እና ድልብ ሃሳብ ይዘው ቃላትን በምላሶቻቸው ሲያጣምሙ ይታያሉ፤ “ኣላህ” אלה አንድ “ላሜድ” ל ብቻ ሲሆን ይላላል፤ ይህ ቃል 36 ጊዜ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ሲሆን፦
1ኛ. “መሃላ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 24:41የዚያን ጊዜ “ከመሐላዬ” אָלָה ንጹሕ ነህ፤ ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ባይሰጡህ ካማልሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆናለህ።”
2. “እርግማን” ማለት ነው፦
ዘኍልቍ 5:23 ካህኑም እነዚህን “መርገሞች” אָלָה በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤”

“አሏህ” የሚለው ቃል ግን ይለያል። አሏህ በዕብራይስ አሁንም “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን በውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל አለው። ነገር ግን አሏህ የሚለው አንድ “ላሜድ” ל በመቀነስና በማላላት አሏህ ማለት “እርግማን” አስተግፊሩላህ! ማለት ነው እያሉ ይሳለቃሉ፤ ሌላው “አክበር” أكبر ማለት “ታላቅ” ማለት ሲሆን “elative degree” ነው፤ ይህንን ቃል ወደ ዕብራይስጥ “ከ” የነበረውን ወደ “ኸ” ይቀይሩትና ያጣምማሉ፤ “አኽባር” עַכְבָּר ማለት “አይጥ” ማለት ነው፤ “አሏሁ አኽባር” ማለት “አሏህ አይጥ ነው” አስተግፊሩላህ! ብለው ንግግርን ከስፍራው ይቀይራሉ፤ ይህ ዛሬ ያሉት ከሃድያን ንግግሮችን ቢያጣምሙ አይደንቅም፤ ነብያችን”ﷺ” ነብይ ሆነው በተላኩበትም ጊዜ አይሁዳውን ቃላትን ያጣምሙ ነበር፤ “ራዒና” َرَٰعِنَا ማለት “ጠብቀን” ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ግን “ጅል” ማለት ነው፤ ለዛ ነው አላህ “አንዙርና” ٱنظُرْنَا ማለትም “ተመለከትን” በሉ ያለው፦
4፥46 ከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ፡፡ «ሰማንም አመጽንም የማትሰማም ስትኾን ስማ» ይላሉ፡፡ በምላሶቻቸውም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ *”ራዒና”* ይላሉ፡፡ እነሱም «ሰማን ታዘዝንም ስማም ተመልከተንም» ባሉ ኖሮ ለነሱ መልካምና ትክክለኛ በኾነ ነበር፡፡ ግን በክህደታቸው አላህ ረገማቸው፡፡ ጥቂትንም እንጅ አያምኑም፡፡ مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَٱسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍۢ وَرَٰعِنَا لَيًّۢا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًۭا فِى ٱلدِّينِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱسْمَعْ وَٱنظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًۭا
2፥104 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ራዒና”* አትበሉ፡፡ *”ተመለከትን”* በሉም፡፡ ስሙም፤ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقُولُوا۟ رَٰعِنَا وَقُولُوا۟ ٱنظُرْنَا وَٱسْمَعُوا۟ ۗ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌۭ

ሌላው አሏህ የሚለው ስም አሁን ባሉት የባይብል ቅጂዎች ውስጥ ለምን የለም? ብለው ይሞግታሉ፤ የነብያትን ግልጠተ-መለኮት “አስል” አሁን በዘመናችን የለም፤ “አስል” أصل ማለትም “ሥረ-መሰረት”origin” ማለት ሲሆን የአላህ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ኪታባት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት ማለት ነው፤ ለምሳሌ የእስራኤል ልጆች ውስጥ የነበሩት ነቢያት ሲናገሩበት የነበረው ቋንቋ ዕብራይስጥ ሲሆን እነርሱ የተናገሩበት መጽሐፍት የሉም፣ በጣም ቀደምትነት አለው የሚባለው የነቢያት መጽሐፍት ግልባጭ በግሪክ ሰፕቱአጀንት የተዘጋጀው ሲሆን ከሰፕቱአጀንት በኋላ የተዘጋጁት የሙት ባህር ጥቅል፣ ማሶሬቲክ፣ ሰመሪያን ይህንኑ የግሪኩን መሰረት አድርገው ነው የተተረጎሙት፣ ከሰፕቱአጀንት በፊት የነበረው የነቢያት መጽሐፍት ዛሬ የለም፣ ከሌለ አሏህ የሚለው ቃል አለመጠቀማቸው ማስረጃ አይሆንም፣ ወደ ኢየሱስም ስንመጣ ኢየሱስ ሲናገርበት የነበረ ቋንቋ አረማይክ ሲሆን ሃዋርያቱም ሲናገሩበት የነበረው ይህን ቋንቋ ነው፣ ነገር ግን ወደ ሁለተኛው ትውልድ ይህ የኢየሱስ ትምህርት ሲገባ የተጻፈው ኮይኔ በሚባል የግሪክ ቋንቋ ነው፣ ስለዚህ ነቢያት አምላካቸውን ማን ብለው እንደነበር የሚያሳይ የቋንቋ መረጃ በዛሬ ጊዜ የለም። አላህ የሚለውን ስም ነቢያቶች ተናግረውት አያውቁም የሚለው አሉባልታ ምንጭ አልባና ሰነድ አልባ ነው፣ ይህን ደፍሮ ለመናገር ስረ-መስረት ያለው አንጓ፣ ቋንቋ፣ ምጥቀት ሆነ ልቀት ያስፈልጋል። ታዲያ ነብያት አሏህ ብለው ይጠቀሙ እንደነበር መረጃ ከፈለጋችሁ ከአሏህ ንግግር ይኸው፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ *”አላህን አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ”*፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوتَ

ይህ ስሁት ሙግት ድባቅ ካስገባን እስቲ በባይብል ላይ የአምላክ ስም ተብሎ ስለሚባለው ስለ ያህዌህ በመጨረሻው ክፍል ኢንሻላህ እንቋጫለን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተሳከረ ምልከታ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ነጥብ ሶስት
“ያህዌህ”
“ያህዌህ” በተነባቢ ፊደላት ከቀኝ ወደ ግራ “ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ” יְהֹוָה እና በፈትሃ ስናነበው ደግሞ “የ-ሃ-ወ-ሃ” יְהֹוָה ነው፣ ይህ ፊደል “ቴትራ-ግራማቶን”Tetra-grammaton” ይሉታል፤ ትርጉሙ “ቴትራ” ማለት “አራት” ማለት ሲሆን “ግራማቶን” ማለት ደግሞ “ተነባቢ ፊደላት” ማለት ነው፤ ይህ ቴትራ-ግራማቶን በማሶሬቲክ እደ-ክታክ”manu-script” ላይ 6,518 ጊዜ ሰፍሮ ይገኛል፣ በተነባቢው ፊደላት በዮድ-ሄ-ዋው-ሄ ላይ “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ከሚለው አናባቢ ድምጽ “አ-ኦ-አ” ሲጨምሩበት “ያህዌህ” የሚል ስም ተፈጠረ እንጂ ይህ ታላቅ ስም አናባቢ ድምጹ ስለጠፋ በትክክል አይታወቅም፣ ስለዚህ ጉዳይ ለዘብተኛ ምሁራን በመድብለ-ዕውቀት ሲናገሩ፦
“ያህዌህ፦ ባዕድ ከሆነ ድምጽ ሰጪ ፊደላት ተዋቅሮ ያህዌህ በመባል በስህተት የተነበበ ነው፣”
Encyclopedia international volume 9, 1974 Edition.
“ያህዌህ፦ የቴትራ-ግራማቶን የተሳሳተ አነባነብ ነው፣”
The universal jewish encyclopedia volume 6, 1948 Edition.
“ያህዌህ፦ ለእስራኤል አምላክ የተሳሳተ ስም ነው፣”
Encyclopedia Americana volume 16, 1976 Edition.

አይሁዳውያን ይህንን ታላቅ ስም አናባቢ ድምጾችን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን 6,828 ጊዜ የነበረውን የእነርሱ “ጸሐፍት” ይህን ተነባቢ ፊደላት ከሌሎች የብሉይ እደ-ክታባት”manu-scripts” ላይ አሽቀንጥረው በማውጣት “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ማለትም “ጌታ” በሚል ለውጠውታል፣ ከዚያም ባሻገር በሰፕቱአጀንት”LXX” እና በሌሎች ቋንቋዎችም “ጌታ” በሚል ተለውጧል፣ የአዲስ ኪዳን የግሪክ ኮይኔ እደ-ክታባት አዘጋጆች ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ያህዌህ እየተባለ የሚጠቀሰውን “ኪርዮስ” κύριος ማለትም “ጌታ” በማለት ተክተውታል፤ ላቲኖቹ ደግሞ “የ” የሚለው “ጀ” እና “ወ” የነበረው “ቨ” በመለወጥ “ጆሆቫ” ብለውታል፤ ሆነም ቀረ እንደ ባይብሉ ይህ ታላቅ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠው ሙሴ ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ በተሰጠበት ጊዜ ነው፦
ዘጸአት 3፥13-15 ሙሴም አምላክን፦ እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ። የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ። ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው። አምላክም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር»אֶֽהְיֶ֑ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֖ה እኔ ነኝ አለው እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። « የሚኖር» אֶֽהְיֶ֑ה ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው። አምላክም ደግሞ ሙሴን አለው። ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ “ያህዌህ” יְהֹוָה ወደ እናንተ ላከኝ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።

“ኤህዬህ-አሸር-ኤህዬህ” אֶֽהְיֶ֑ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֖ה ማለት “እኔ ነኝ እርሱ እኔ ነኝ” I am who I am” ማለት ነው፤ ይህንን ስም የፈጣሪ ስም ነው ብሎ የሰበከ አንድ ነብይ የለም፤ “ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ” יְהֹוָה የሚለውም ቢሆን ሌሎች ከሙሴ በፊት የነበሩት ነብያት አያውቁትም፦
ዘጸአት 6:3 ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ “ያህዌህ” יְהֹוָה አልታወቀላቸውም ነበር።

“ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ” የሚለውን ከሙሴ በፊት ካላወቁት ለምንድን ነው? በአምስቱ ኦሪቶች ውስጥ አብርሃምና ሔዋን እንደተናገሩት ተደርጎ የገባው?
ዘፍጥረት 22:14 አብርሃምም ያንን ቦታ “ያህዌ” יְהֹוָה ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል።
ዘፍጥረት 4:1 አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም። ወንድ ልጅ “ከያህዌ” יְהֹוָה አገኘሁ አለች።

እስቲ ከሙሴ መጽሐፍ በፊት ያህዌህ የሚለውን ስም የጠቀሰ ነብይ ከነማስረጃው ቁጭ አድርጉልን፤ የለም። ልብ አድርጉ “ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ” ማለት “እንዲሆን የሚያደርግ”to cause to become” ማለት ነው፤ ቋንቋውም ዕብራይስጥ ነው፤ ሔዋን ሆነች አብርሃም ዕብራይስጥ ተናጋሪ አይደሉም፤ ታዲያ ጸሐፍት ልክ እንደተናገሩት አስመስለው ለምን አስገቡት? ይህ የብረዛ ውጤት ነው፤ “ስሜ “ያህዌህ” አልታወቀላቸውም ነበር” እያለን? የከርሰ-ምድር ጥናት እንዳስቀመጠው “ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ” የሚለውን ቃል ከሙሴ መወለድ በፊት የከነዓን ጣኦታውያን ለጣዖታቸው ይጠቀሙበት ነበር፤ “አሸራ” אֲשֵׁרָה ማለትም “አስታሮት” ሚስቱ ናት ብለው ያምኑ ነበር፦
1. Olyan, Saul M. (1988), Asherah and the cult of Yahweh in Israel, Scholars Press, p. 79,
2. Asherah – the Wife of God http://wifeofyahweh.com