ማዕከላዊ እስር ቤት⬆️
"ዛሬ ጠዋት ጀምሮ እስከ ረፋድ ድረስ በርካታ ሰዎች ማዕከላዊ እስር ቤትን እየጎበኙ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም መካከል አቶ #ጃዋር_መሀመድ የተገኙ ሲሆን ኦቦ #በቀለ_ገርባ ለOMN ሚዲያ ሠዎች እና በቦታው ለተገኙ ጎብኚዎች ስለ ቦታውና በዚያ ስላሳለፉአቸው አስከፊ ጊዜያት ገለፃ ሲያደርጉና ሲያስጎበኙ ነበር።"
📸በርካታ የTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ማዕከላዊን በመጎብኘት የሚያዩትን ነገር በፎቶ እያስቀሩ እየላኩን ይገኛሉ!
Via #Fasil/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia

2954 አሽከርካሪዎች ጉቦ ለመስጠት ሲሞክሩ ተይዘዋል!
በ2011 በጀት ዓመት ለትራፊክ ፖሊሶች ጉቦ ለመስጠት የሞከሩ 2954 አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣አሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ህግ በመተላለፍ ወንጀል ሲጠየቁ ለትራፊክ ፖሊስ አባላት የመማለጃ ገንዘብ ለመስጠት በመሞከራቸው ነው። እንደ ኮማንደር ፋሲካ አባባል ግለሰቦቹ ከሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ብር ጉቦ ለመስጠት የሞከሩ ናቸው። ድርጊታቸው በበቂ ማስረጃ በመረጋገጡም ጉዳያቸው ለዓቃቤ ህግ ተላልፎ በክስ ሂደት ላይ ይገኛል። እስካሁን ከአሽከርካሪዎች ገንዘብ ሲቀበሉ የተያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ያለመኖራቸውን ያረጋገጡት ኮማንደር ፋሲካ ድርጊቱ ካለፈው ተመሳሳይ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸርም ቁጥሩ በ 5 በመቶ ያህል መጨመሩን ተናግረዋል።
Via #EPA

አሳዛኝ ዜና!
በአንጎለላና ጠራ ወረዳ በተከሰተ ደራሽ ዉሀ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ!
በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ "አባ ወኔ" በተባለዉ ወንዝ ሀሙስ ነሀሴ 30/2011ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰአት በተከሰተ ደራሽ ዉሃ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። በደራሸ ዉሀዉ ተወስደዉ ህይወታቸዉ ካለፉት ሰባት ሰዎች መካከል አንድ የሁለት አመት ሴት ህፃን ልጅ ትገኝበታለች።
የአንጋዳ ቀበሌ ምድብተኛ ፖሊስ ረዳት ሳጅን ተፈራ ሀይሌ እንደገለፁት በደራሽ ዉሀዉ ህይወታቸዉ ያለፉት ግለሰቦች በአንጋዳ ቀበሌ በአንድ አካባቢ የሚኖሩና በእለቱ ወደ አቅራቢያቸዉ ወደሚገኝ የአሳባህር ቀበሌ ሀሙስ ገበያ ለገበያ ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ ሲመለሱ ከቀኑ 8:00 ሰአት ገደማ በጣለ ከባድ ዝናብ አማካኝነት በተከሰተ ደራሽ ዉሃ አደጋዉ የደረሰ ሲሆን ቤተሰቦቻቸዉና የአካባቢዉ ማህበረሰብ አደጋዉ መከሰቱን ካወቁ ምሽት 12:00 ሰአት ጀምሮ ፍለጋ በማድረግ የስድስቱ አስከሬን አርብ ጳጉሜ 12:00 ሰአት ገደማ ተገኝቶ ስርአተ ቀብራቸዉ ተፈፅሟል።
የ2 አመት ህፃኗ አስከሬን ቶሎ ሊገኝ ባለመቻሉ ፍለጋዉ በዚሁ እለት እስከ ቀኑ 8:00 ሰአት ድረስ ቀጥሎ የህፃኗን አስከሬን ማግኘት ተችሏል። ህይወታቸዉ ያለፉት ግለሰቦች ስድስቱ ከ35 እስከ 50 አመት ባለ የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸዉ።
Via Angolela Tera Woreda Government Communication Affairs Office

#እንዳይበሉ
እንዲህ ያለውም ማጭበርበር ተበራክቷል⬆️
"አንድ ሴትዮው በፌስቡክ ሪኬስት ልካልኝ ጓደኛዬ ሆነች ለረጅም ቀን አወራን። እና የካንሰር በሽተኛ መሆናን ነግራኝ የቀራት ትንሽ ቀን እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ ያላትን ሀብት ለእኔ ልታወረሰኝ እንደሆነ ነገረችኝ፤ ብዙ ነገር ነው ያወራችኝ። እና በመጨረሻም ብሩን ልላክ አለችኝ፡፡ እሺ አልኳት ብሩ ተልኳል ብላ ከላይ ያለውን ወረቀት ላከችልኝ፡፡ ለማንም ማሳየት የለብህም በሚስጥር ያዘው አለችኝ፡፡ ብሩ ዛሬ ይደርሳል እና ከዛ በፊት ግን 1500 ዶላር በአካውንቴ አስገባ አለችኝ፡፡ እኔ ደግሞ አሁን ስለሌለኝ ብሩን ስትልኪልኝ ከዛ ላይ ቆርጬ እለልክልሻለሁ ስላት አይቻልም ብላ ተወችው፡፡ በዚህ ነገር ብዙ ሰዎች እንዳይታለሉ አስጠንቅቅልኝ!"
🤔አንዳንዱ የ800 ብር ካርድ ላክልኝና ሽልማቱን ልስጥ ብሎ ይደውላል፤ አንዳንዱ ደግሞ 1500 ዶላር ላክልኝና ሀብቴን ላውርስህ ይላል!! ለማንኛውም ይህችን የማጭበርበሪያ ዘዴ ማወቁና መጠንቀቁ አይከፋም!!

#update የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በከተማው ከንቲባ በቀረበው ጥሪ መሠረት የከተማይቱን ሙስሊሞችን በማስተባበር ግምቱ 5,250,000 (አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ)ብር የሚያወጣ 520ሺህ ደብተርና 10ሺህ እስክሪብቶ በአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት በሼህ ሱልጧን ሀጂ አማን አማካኝነት ለከንቲባ ታከለ ዑማ አስረክቧል።
Via አህመዲን ጀበል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via አህመዲን ጀበል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2010 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች! የ2010 የውርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች የውጭ የትምህርት እድል እንደምናገኝ ተገልፆ ህዝቡም ስምቶት የነበረ ቢሆንም ምንም የትምህርት እድል አላገኘንም አሁንም እዚሁ ነው ያለነው አንዳንዶች በስራ ፍለጋ፡ አንዳንዶችም ተቀጥረን እየሰራን ነው ብለዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል እና የዓምና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ይህን ብሏል፦ …
ትላንት በተነሳው ጉዳይ...
"የ2010 ተመራቂ ነኝ ሚ... እባላለው። የGold Medalist ተሸላሚ ነበርኩኝ ዶ/ር አብይም ጋር ተጋብዤ ሄጄ ነበር። scholarship እንደሚሰጠን በኢትዮጲያ ህዝብ ፊትም ቃል ተገብቶልን ነበር። ግን እስካሁን ምንም ነገር የለም።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የ2010 ተመራቂ ነኝ ሚ... እባላለው። የGold Medalist ተሸላሚ ነበርኩኝ ዶ/ር አብይም ጋር ተጋብዤ ሄጄ ነበር። scholarship እንደሚሰጠን በኢትዮጲያ ህዝብ ፊትም ቃል ተገብቶልን ነበር። ግን እስካሁን ምንም ነገር የለም።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልዕክት
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ በቅድሚያ እንኳን ለ2012 ዓ.ም ዋዜማ እና ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ እያለ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ በበጎን በመደመር ስኬትን የምናስመዘግብበት እና እርስበርስ በመደጋገፍ ወደላቀ ደረጃ የምንሸጋገርበት የሥራ ዘመን እንዲሆን ይመኛል፡፡
የጋሞ ዞን ፖሊስ መረጃ ስልክ 046 882 0025
የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ መረጃ 046 881 4298
የሴቻ ክ/ከተማ ፖሊስ መረጃ 046 881 0095
የሲቃላ ክ/ከተማ ፖሊስ መረጃ 046 881 2637
የአባያ ክ/ከተማ ፖሊስ መረጃ 046 881 4312
የነጭ ሣር ክ/ከተማ ፖሊስ መረጃ 046 881 3381 የስልክ መረጃዎችን በመጠቀም ጥቆማዎችን በማድረስ ህገ-ወጥ ተግባራትንና ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል በየደረጃው ያለው ህብረተሰብ የድርሻውን እንዲወጣ ያሳስባል፡፡
#share #ሼር

በሀድያ ዞን #ሾኔ ከተማ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው በከተማው ወርልድ ቪዥን በተባለው አካባቢ የተርጋ ቁጥሩ ኮድ 1-14316 ደ.ሕ ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ከሻሸመኔ ወደ ወላይታ ሶዶ ይጓዝ ከነበረ ኮድ 3-05477 ደ.ሕ ከሆነ የጭነት አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ስራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ሳጅን አዲሴ በርገኖ እንደገለጹት ባጃጁ መስመሩን ስቶ በፍጥነት በመጓዝ ላይ ከነበረው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪው ጋር በመላተሙ አደጋው ሊደርስ ችሏል። በአደጋውም በባጃጁ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
#የሟቾቹ አስክሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ መደረጉንም አመልክተው የአይሱዙ አሽከርካሪ ለጊዜው ቢሰወርም ፖሊስ በክትትል ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ሳጅን አዲሴ የሰው ህይወትና ንብረትን ከጥፋት ለመታደግ አሽከርካሪዎች ርቀታቸውንና ፍጥነታቸውን በመቆጣጠር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

ሠላም ለራስ ነው!
ሶሪያ፣ሊቢያ፣የመን...በእነዚህ ሃገራት ሰዎች እንደዋዛ ህይወታቸውን ያጣሉ፤ በአሁን ቅጽበትና ባሉበት ስፍራ መኖራቸውን እንጂ የሚቀጥለው ትንፋሻቸው ይኑር አይኖር ማረጋጋጥ አይችሉም። በማንኛውም ስፍራና ጊዜ #ሞት አለ። ሰርቶ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት አይቻልም፤ ስራ የለም። ሃብት ማፍራት የሚባለው ነገር የማይጨበጥ ቅዠት ነው። እነዚህ ሃገራት #የተተረማመሱት ለፖለቲካዊ ነጻነቶች በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ነው ቢባልም አሁን ግን ፖለቲካዊ መብትና ነጻነት የሚባሉት ነገሮች ትርጉም አጥተዋል። አመለካከትን ማራመድ፣ መደራጀት፣ ሃሳብን መግለጽ፣ ምርጫ፣ የስልጣን ውክልና፣ መንግስት፣ የህግ የበላይነት የሚባሉት ነገሮች ማረፊያ መሬት አጥተዋል፤ ማረፊያቸው ሰላም ነበርና።
ሰላም ለሰዎች ተለጣፊ ነገር ሳይሆን መሰረታዊና የህልውና ጉዳይ ነው!

የፅሁፉ ባለቤት ኢብሳ ነመራ--TIKVAH-ETH ለዛሬው ቀን እንዲሆን መርጦ የወሰደው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትግራይ ክልል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እያስተማሩ ካሉ መምህራን መካከል 30 በመቶ የሚሆኑት የሚያስተምሩት ከሰለጠኑበት የሙያ መስክ ውጪ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የመምህራን ምደባው በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር መቆየቱም ተመልክቷል።
https://telegra.ph/ETH-09-07-12
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
https://telegra.ph/ETH-09-07-12
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ማዕከል ሊገነባ ነው!
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የኢትዮጵያ የሰላም ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ ዛሬ አፍሪካ ህብረት ቡልጋሪያ አካባቢ አስቀመጡ። 4.2 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው ማዕከሉ ሰላምን ለመኮትኮት ፣ የሰላም ባህልን ለማሣደግና ሰላምን ለማበልፀግ እንደሚዉል ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ማዕከሉ የማህበረሰቡን እምቅ ባህላዊ እሴቶች የሚንሸራሸሩበት እና ልጆችም የሰላምን ባህል ይዘዉ እንዲያድጉ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚከናወንበት ይሆናል። የማዕከል ግንባታዉ በ3 ወራት ዉስጥ የሚጀመር ሲሆን ዝርዝር ሂደቱ በቀጣይ እንደሚገለፅ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ምልመላ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የጀመረውን ውስጣዊ አደረጃጀት ሪፎርም በክልል ደረጃ በማስፋት በ9 ክልሎች የሚገኙት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን እንደአዲስ እያደራጀ ይገኛል፡፡ የዚህ ስራ ዋናው አካል የክልል የምርጫ ሃላፊዎችን እንደስራ አመራር ቦርዱ አባላት አመራረጥ ሁሉ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በዘጠኙ ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በእጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉና ከስር የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ግለሰቦች የአመላመል ሂደት እንዲሁም በመጨረሻ ይህን የክልል ቅርጫፍ መስሪያ ቤት ዋና ሃላፊነትን አስመልከቶ ቦርዱ የሚሰጠው የቅጥር ውሳኔ በሚዲያ በይፋ የተገለጸ እንዲሆን ማድረግ አስፈልጓል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07-13

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔን አፈጻጸም አስመልክቶ ከክልልና ዞን ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔን አፈጻጸም አስመልክቶ የተለያዩ አካላት ጋር የሚደረጉ የተለያዩ ውይይቶችን እንደሚያከናውን ባስቀመጠው የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት ነሃሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከደቡብ ክልል ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ምክር ቤት ተወካዮች፣ የክልሉ አመራር አባላትና ከዞኑ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሒዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አፈጉባኤ ሄለን ደበበ፣ ምክትል አፈጉባኤ መንግስቱ ሻንካ፣ የክልል መስተዳደር ጽ/ቤት ዋና አማካሪ አኒሳ መልኮ፣ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደስታ ሌዳሞ፣ ሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከቦርዱ አባላት ጋር ገንቢ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም ላይ፦
1. በተጠየቀው በጀት በኩል ምንም አይነት ችግር እንደማይኖር
2. በዞኑ የሚኖሩ እድሜያቸው ለመምረጥ የደረሰ ነዋሪዎች ሁሉ በህዝበ ውሳኔው እንደሚሳተፉ፣ ክልሉም በበኩሉ ለምርጫ ቦርድ ሎጀስቲክስ ዝግጅት ለማቀላጠፍ በዞኑ ስር የሚገኙ ህዝበ ውሳኔው የሚካሄድባቸውን ቀበሌዎች ዝርዝር እንደሚያሳውቅ
3. የህግ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎቹን ማውጣት ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ክልሉ ከመርሃግብሩ ከተጠቀሱት ቀናት ጥቂት ተጨምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 አ.ም ድረስ እንደሚቀርብ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ቦርዱ በማስከተል በመርሃ ግብሩ መሰረት ሌሎች ተመሳሳይ ውይይቶችን ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያከናውን ሲሆን በየጊዜው ሂደቱን የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️
ቴሌግራም፦
1. ኢትዮ-ቴሌኮም -- በዚህ ስም የተከፈተና 50,000 subscribers ያለው የቴሌግራም ቻናል የኢትዮ ቴሌኮም አይደለም። የኢትዮ ቴሌኮም ትክክለኛ የቴሌግራም ገፅ የ✅ምልክት ያደረኩበትና 47,000 subscribers ያሉት በእንግሊዘኛ "Ethio telecom" ተብሎ የተፃፈው ነው።
2. Elias Meseret ከTikvah-Eth ጋር በመተባበር--- ይህ በጋዜጠኛ ኤልያስና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም በጥምረት የተከፈተው የቴሌግራም ገፅ በኤልያስም ሆነ በTIKVAH የማይተዳደር ነው። ማወቁ አይከፋም!
ፌስቡክ፦
1. Takel Uma Banti--4,117 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገፅ አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የሳቸው አይደሉም። ኢንጂነሩ የሚያስተዳድሩት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና like page ያልሆነ ገፅ ነው።
2. የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል Ethiopian Defense Force - ይህ 40 ሺህ Like ያለው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃዎችን የሚያሰራጨው 25,000 like ባለው /የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ፅ/ቤት Defense Minister Office, Ethiopia/ የፌስቡክ ገፅ ነው።
3. Oromia Comunication Bureau--ይህ 18 ሺህ like ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። ትክክለኛው የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና ከ158 ሺህ በላይ like ያለው ነው።
#BONUS
የክቡር የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የፌስቡክ ገፅ 420,000 like ያለው ነው ሚኒስትሩ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያሰራጩት ይኸው በተጠቀሰው ገፅ ነው። በዚህ አጋጣሚ TIKVAH-ETH ክቡር ሚኒስትሩ ገፃቸውን በፌስቡክ #verify ቢያስደርጉት መልካም ነው ለማለት ይወዳል።
#TIKVAH_ETHIOPIA
በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

👍2
#ቺኩንጉንያ በድሬዳዋ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የህክምና መርሀ ግብር በተለያዩ ድሬዳዋ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል። በዚህ ወገንን የመርዳት መርሀ ግብር ላይ እየተካፈሉ ላሉና በቀጣይም ከመስከረም 2-4 ድረስ ለሚከናወነው የህክምና መርሀ ግብር ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች በራሳችንና በአጠቃላይ የድሬዳዋ ህዝብ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በመጀመሪያው ዙር የህክምና መርሀ ግብር እስከ 34 በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። ለዚህ መርሀ ግብር መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉልን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ አመራሮች እንዲሁም ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ተመራቂ ሀኪሞች ምስጋናችን የላቀ ነው።
በጋራ ሆነን የቺኩንጉንያን ወረርሽኝ ከውዷ ከተማችን ለማጥፋት እንረባረብ!
Dr. Miki Shawel
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋራ ሆነን የቺኩንጉንያን ወረርሽኝ ከውዷ ከተማችን ለማጥፋት እንረባረብ!
Dr. Miki Shawel
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፖሊስ አንድን ወጣት #ሲደበድብ የሚታይበት የዛሬው ቪዲዮ በበርካቶች ዘንድ #መነጋገሪያ ሆኗል!
ፖሊሶቹ የዋስ መብታቸው ተከብሮ ተለቀዋል!
ቪድዮ ላይ የታዩት ፖሊሶች #የዋስ_መብታቸው ተከብሮ ተለቀዋል፤ የማጣራት ሂደቱ ግን እንደቀጠለ ነው ሲሉ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ማምሻውን ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናገሩ።
የፖሊሶቹ መጨረሻ ምን ሆነ ተብለው በጋዜጠኛ ኤልያስ የተጠየቁት ኮማንደር ፋሲካ ተከታዩን መልስ ሰጥተዋል፦
"ፖሊሶቹ በዋስትና ከእስር ወጥተዋል ምክንያቱም የፈፀሙት ነገር ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም። ይሁንና አሁን ላይ የማጣራቱ ስራ እንደቀጠለ ነው። አንድ ፀብ ውስጥ ያልነበረ ሰው የችግሩ ዋና ተዋናይ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ ሰው ፖሊሶቹን በቴስታ መትቶ መሳርያ ለመቀበል እንደሞከረ ደርሰንበታል። ቪድዮውን የቀረፀውን ሰውም አናግረነው ነበር፣ ሙሉ ሁኔታውን አልቀረፅኩም፣ ለዛም ይቅርታ ብሏል።"
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት