TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. BBC አማርኛ -- ይህ የቴሌግራም ቻናል የቢቢሲ አይደለም። ቢቢሲ አማርኛ በፌስቡክና በትዊተር ላይ ካለው የመገናኛ አማራጭ ውጪ በቴሌግራም ምንም አይነት ገፅ የለውም!

2. ESAT TV --- የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ምንም አይነት ይፋዊ የሆነ የቴሌግራም ገፅ የለውም።

3. Jawar Mohammed --- የOMN ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ በቴልግራም መልዕክት የሚያሰራጭበት ምንም ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል የለውም። እንዲሁም በፌስቡክ ላይ ያለው የግል ገፁ በFACEBOOK #verify የተደረገው ብቻ ነው።

ፌስቡክ፦

1. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት--19,359 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የዲያቆን ዳንኤል አይደሉም።

2. ጉለሌ ፖስት -- 87 ሺህ Like ያለው ጉለሌ ፖስት በሚል የተከፈተው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የዋናው የጉለሌ ፖስት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 47 ሺ Like ያለው ነው። ይገርማል🤔ትክክለኛውን የሚከተለው እና ሀሰተኛውን ገፅ የሚከተለውን የሰው ቁጥር መልስ ብላችሁ ተመልከቱ!

ሌላው...

ከሰሞኑን በወዳጃች እና እጅግ በምናከብረው አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ስም ብዙ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል ጥንቄቄ ይደረግ!! ያልተናገረውን ተናግሯል፤ ያላለውንም ብሏል በሚል አንዳንድ ገፆች ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. Walta TV -- ይህ የቴሌግራም ቻናል የዋልታ ቴሌቪዥን አይደለም። ዋልታ ሚዲያ እስካሁን በይፋ ያሳወቀው የቴሌግራም ቻናል የለም።

2. ትምህርት ሚኒስቴር --- የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርን ስም የሚጠቀመው ቻናል ሀሰተኛ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ቴሌግራም ቻናል የለውም።

3. NEAEA/የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ/ --- ኤጀንሲው ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የለውም።

ፌስቡክ፦

1. አብን/የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/--24,00 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የአብን አይደሉም። ትክክለኛው የፌስቡክ ገፅ 153,422 like ያለው ነው።

2. OBN አማርኛ -- 20,236 ሺህ Like ያለው OBN አማርኛ በሚል የተከፈተው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የዋናው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 111 ሺህ Like ያለው ነው። ይህን የፌስቡክ ገፅ ተጠንቀቁት!

#Bonus

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በፌስቡክ #verify የተደረገ የፌስቡክ ገፅ አላቸው። ገፁ 97,017 Like ያለው ነው!

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. ኢትዮ-ቴሌኮም -- በዚህ ስም የተከፈተና 50,000 subscribers ያለው የቴሌግራም ቻናል የኢትዮ ቴሌኮም አይደለም። የኢትዮ ቴሌኮም ትክክለኛ የቴሌግራም ገፅ የምልክት ያደረኩበትና 47,000 subscribers ያሉት በእንግሊዘኛ "Ethio telecom" ተብሎ የተፃፈው ነው።

2. Elias Meseret ከTikvah-Eth ጋር በመተባበር--- ይህ በጋዜጠኛ ኤልያስና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም በጥምረት የተከፈተው የቴሌግራም ገፅ በኤልያስም ሆነ በTIKVAH የማይተዳደር ነው። ማወቁ አይከፋም!

ፌስቡክ፦

1. Takel Uma Banti--4,117 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገፅ አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የሳቸው አይደሉም። ኢንጂነሩ የሚያስተዳድሩት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና like page ያልሆነ ገፅ ነው።

2. የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል Ethiopian Defense Force - ይህ 40 ሺህ Like ያለው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃዎችን የሚያሰራጨው 25,000 like ባለው /የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ፅ/ቤት Defense Minister Office, Ethiopia/ የፌስቡክ ገፅ ነው።

3. Oromia Comunication Bureau--ይህ 18 ሺህ like ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። ትክክለኛው የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና ከ158 ሺህ በላይ like ያለው ነው።

#BONUS

የክቡር የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የፌስቡክ ገፅ 420,000 like ያለው ነው ሚኒስትሩ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያሰራጩት ይኸው በተጠቀሰው ገፅ ነው። በዚህ አጋጣሚ TIKVAH-ETH ክቡር ሚኒስትሩ ገፃቸውን በፌስቡክ #verify ቢያስደርጉት መልካም ነው ለማለት ይወዳል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍2
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. EBS TV -- በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ስም የተከፈተው እና 5770 subscribers ያሉት የቴሌግራም ቻናል የEBS አይደለም። EBS በይፋ ይህ ነው የኔ ቻናሌ ብሎ ያሳወቀው የቴሌግራም ቻናል የለም።

ፌስቡክ፦

1. National Education Assessment and Examination agency--ይህ 149,000 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ትክክለኛ ገፅ አይደለም። ይህ ብዙ ተከታይ ይለው ገፅ በርካቶችን ያደናግራል ተጠንቀቁ። የኤጀንሲው ትክክለኛው ገፅ 119,000 Like ያለው ነው። ኤጀንሲው ገፁን በፌስቡክ #verify ቢያስደርገው መልካም ነው።

2. Desalegn Chanie Dagnew- ይህ 7,740 ሺህ Like ያለው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በፌስቡክ ላይ Like Page የላቸውም። ጥንቃቄ ይደረግ!

3. BBC news Amharic/አማርኛ--ይህ ከ 4 ሺህ በላይ like ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። ትክክለኛው የBBC አማርኛ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገና ከ300 ሺህ በላይ like ያለው ነው።

4. Jawar mohammed--ይገርማል! ይህ ከ286,000 በላይ ህዝብ የሚከተለው ገፅ ሀሰተኛ ነው። ብዙ የሀሰት መረጃዎች የሚሰራጩበት በመሆኑ ጥንቃቄ ይደረግ። ትክክለኛው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ የፌስቡክ ገፅ #verify የተደረገ ነው። ልብ በሉ like page አይደለም!

#BONUS

DW ትግርኛ/ድምፂ ወያነ የትግርኛው አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች የሚከተሉት ነው። የአማርኛው አገልግሎት ገፅ ደግሞ ከ46 ሺህ በላይ Like ያለው ነው።

#ቲክቫህ
Verified! የዶክተር አሚር አማን የፌስቡክ ገፅ በፌስቡክ ድርጅት #verify ተደርጓል። #ETHIOPIA