TIKVAH-ETHIOPIA
ፖሊስ አንድን ወጣት #ሲደበድብ የሚታይበት የዛሬው ቪዲዮ በበርካቶች ዘንድ #መነጋገሪያ ሆኗል!
ፖሊሶቹ የዋስ መብታቸው ተከብሮ ተለቀዋል!
ቪድዮ ላይ የታዩት ፖሊሶች #የዋስ_መብታቸው ተከብሮ ተለቀዋል፤ የማጣራት ሂደቱ ግን እንደቀጠለ ነው ሲሉ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ማምሻውን ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተናገሩ።
የፖሊሶቹ መጨረሻ ምን ሆነ ተብለው በጋዜጠኛ ኤልያስ የተጠየቁት ኮማንደር ፋሲካ ተከታዩን መልስ ሰጥተዋል፦
"ፖሊሶቹ በዋስትና ከእስር ወጥተዋል ምክንያቱም የፈፀሙት ነገር ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም። ይሁንና አሁን ላይ የማጣራቱ ስራ እንደቀጠለ ነው። አንድ ፀብ ውስጥ ያልነበረ ሰው የችግሩ ዋና ተዋናይ ሆኖ አግኝተነዋል። ይህ ሰው ፖሊሶቹን በቴስታ መትቶ መሳርያ ለመቀበል እንደሞከረ ደርሰንበታል። ቪድዮውን የቀረፀውን ሰውም አናግረነው ነበር፣ ሙሉ ሁኔታውን አልቀረፅኩም፣ ለዛም ይቅርታ ብሏል።"
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia