TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማዕከላዊ እስር ቤት⬆️#የTIKVAH_ETH ቤተሰብ አባላት #ማዕከላዊ_እስር_ቤትን ተዘዋውረው እየጎበኙ እኛም በያለንበት የእስር ቤቱን ሁኔታ በስልካችን ላይ እንድናየው እያደረጉን ይገኛሉ።

ፎቶ📸CAN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
”የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ለእኛ #ኢትዮጵያዊያን ክብራችን ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ #ETH

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07-14
እንኳን አደረሳችሁ!

ህዝቡ #አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ። አቶ ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በ2012 ዓ.ም ለተሻለ ተጠቃሚነት ይሰራል ብለዋል። በ2011 ዓ.ም የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርም ለ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።

በቀጣዩ በጀት አመትም መንግስት ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አንስተዋል። አዲሱ አመት ስኬታማ ስራዎች የሚሰሩበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚሰራበት፣ ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የምናስቀጥልበት እና ስራ አጥ ዜጎች የተሻለ ስራ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ተናግረዋል። በፖለቲካው ዘርፍም በ2011 ዓ.ም የታዩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ስኬታማ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ!

በሀዋሳ ከተማ #የኮሌራ በሽታ በመከሰቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀድራላ አህመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማዋ ምልክቱ   ከታየባቸው 56 ሰዎች ውስጥ አራቱ በኮሌራ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በከተማዋ አዳሬ እና በሀዋሳ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ጊዜያዊ የህክምና ማዕከላት መቋቋማቸውን እንዲሁም በአዳሬ ጤና ጣቢያ በቋሚነት ህሙማን የሚስተናገዱበት ልዩ ስፍራ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በሽታው በንጽህና ጉድለት ምክንያት እንደሚመጣና በቀላሉ ተላላፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያልበሰሉ ምግቦችን ከመመገብና ንጽህናው ያልተጠበቀ ውሀ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ለመጠጥ የሚጠቀመውን ውሀ #አፍልቶ በማቀዝቀዝ አልያም  በማከሚያ ዘዴ  እንዲጠቀም የማይቆም #ተቅማጥና #ትውከት ሲገጥመውም በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም እንዲሄድም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄራዊ የኩራት ቀን በመስቀል አደባባይ በደማቅ ስነ-ስርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ፣ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰልፈኞች ወታደራዊ ሰልፍ አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሄራዊ ኩራታችን የሆኑ ልዩ ልዩ ትርዒቶች ቀርበዋል፡፡ በመድረኩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ፣ የፌደራል መንግስት እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሠላምና መረጋጋት እንዲመጣ የፖለቲካ ኃይሎች የሚጋጩ ሕልሞቻቸውን አስቀምጠው ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልጋቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና ፖለቲከኛው ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ገለፁ።

https://telegra.ph/ETH-09-08

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ እንዴት እያለፈ ነው? የት ከተማ ምን ምን በጎ ስራዎችን እየሰራችሁ ነው? ለኛ መማሪያ ይሆነን ዘንድ መልካም ስራችሁን አካፍሉን። እስካሁን የደረሱንን በያዝነው ሳምንት የተሰሩ በጎ ተግባራትን እናቀርባለን።

ምልዕክታቹን በዚህ አድራሻ ብቻ ነው ምትልኩት @tsegabtikvah
ኮምቦልቻ ላይ ለበጎነት እየተሮጠ ነው!

"Arhibu kombolcha/አርሂቡ ኮምቦልቻ በጎአድራጎት ማህበር ዛሬ እሁድ ጣት ባዘጋጀው እኔም ‘ለኮምቦልቻ እሮጣለሁ’ የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው። ለበጎ ስራ እንሩጥ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስቴ ከተማ⬆️

እስቴ ከተማ ክረምቱ እጅግ መልካም ስራዎች የተሰሩበት ሆኗል። የከተማይቱ ወጣቶች ከላይ የምትመለከቷቸውን ትንንሽ ውብ የሆኑ፤ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ሲያስተምሩ ነበር፤ በተጨማሪ በበጎ ፍቃድ የትራፊክ አደጋ መከላከል ስራ እና ደካሞችን የማገዝ ስራ እንደተሰራ ወጣቶቹ ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኩ⬆️በመልካም ስራቸው ሁሌም #የሚያኮሩን በየዕለቱ የሚሰሯቸውን መልካም ስራዎች የሚያጋሩን "የለኩ እኔም ለወገኔ የበጎ አድራጎት ማህበር" ዛሬ ደግሞ እሁድ በአካባቢ ፅዳት ስራ እያሳለፉ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ በኔጌሌ ቦረና⬆️

"ሰዉ አለ የአረጋውያን ማህበር" በነጌሌ ቦረና ወጣቶች የተመሠረተ ሲሆን የአረጋዊያንን እና የአቅም ደካሞችን ቤት በማደስ ላይ ይገኛሉ። መንፈሱ በጣም ደስ ይላል ብለዋል ወጣቶቹ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጤና ባለሞያዎቻችንን አመስግኑልን!

በድሬዳዋ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የህክምና መርሀ ግብር በተለያዩ ድሬዳዋ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እየተሰጠ ይገኛል። በዚህ ወገንን የመርዳት መርሀ ግብር ላይ እየተካፈሉ ላሉና በቀጣይም ከመስከረም 2-4 ድረስ ለሚከናወነው የህክምና መርሀ ግብር ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች በራሳችንና በአጠቃላይ የድሬዳዋ ህዝብ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

#ዶክተር_ሚኪ_ሻውል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኩራት ቀንዎ ነፃ ቡና እንሆ!

ቶሞካዎች ተመስግናችኃል!


አዲስ አበባ መስቀል ፍላወር የሚገኘው "ቶሞካ ቡና" የኩራት ቀንን ምክንያት በማድረግ ደንበኞቹን በነጻ ቡና እያጠጣ ነው፤ በቡናችሁ ኩሩ እያለ ይገኛል☕️

በነገራች ላይ...የሀገራችን ቡና #ኢትዮጵያን በዓለም ላይ እንድትታወቅ በማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ በሀዋሳ⬆️

ቤተሰቦቻቸው አቅም ላነሳቸው እና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ልጆች የሀዋሳው "አለን ኢትዮጵያ የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል" በቋሚነት ለሚያስተምራቸው ከ10 በላይ ህፃናት የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። በነገራችን ላይ ይህ ማዕከል ገና አንድ አመቱ ነው። በወጣቶች የሚንቀሳቀስ እና ትልልቅ ስራዎችን እየሰራ ያለ ማዕከል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክባሪያችሁ ነን!

"ዘመን ለኢትዮጲያ የበጎ አድራጎት ማህበር በላፍቶ ለሚኖሩ ለ100 የጎዳና ተዳዳሪዎች ምሳ ያበላን ሲሆን ለ20 ታዳጊዎች ሊስትሮ ድጋፍ አድርገናል ለ3 እናቶች የበአል ማሳለፊያ ዶሮ እንቁላል እና ዘይት አበርክተናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጳጉሜን ለጤና!

ዲላ የሚገኘው ዶ/ር ተስፋነው መካከለኛ ክሊኒክ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ነፃ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

አመስግነናል ዶክተር!

ፎቶ📸ሜላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማህበራዊ ሚዲያውን ጨለማ ያደረግብን እኮ መልካም ስራን የሚሰራ ወጣት፣ ጎልማሳ ስሌለን አይደለም!! ኢትዮጵያ ሀገራችን በሁሉም አካባቢ መልካም ስራዎችን የሚሰሩ ምርጥ ዜጎች አሏት። ብዙ ጊዜ ማህበራዊ ሚዲያውን የሚቆጣጠረው ግን ትንሽሽ ጉዳይ ናቸው። ለሀገር አድገት፣ ሰላም፣ አንድነት፣ አብሮነት የማይጠቅም መልካም ያልሆነ መልዕክት ነው። የወጣቶችን መልካም ስራ የመሰለ ትልቅ አጀንዳ ከየት ይመጣል??

ፌስቡክ ላይ ብዙ ጊዜ የምንታዘበውን ነገር እናካፍላችሁ፦

የሰዎችን እምነት፣ ባህል፣ ብሄር፣ ማንነት፣ አመለካከት ማንቋሸ መስድብ፣ ሀሰተኛ ዜና ማሰራጨት፣ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክት ማስተላለፍ፣ በህዝብ መካከል መከፋፈል ለመፍጠር የሚነገር መልዕክት፣ ሀገር ለማጥፋት፣ሰላም ለማደፍረስ ሲሆን ብዙ Like እና share ይደረጋል። ተነቦ የማያልቅ comment ይፃፋል ያውም ጥሩና መማሪያ ቢሆን ደግ ስድብ፣ ማንቋሸሽ...ብዙ ብዙ ነው አስተያየቱ።

በአንፃኑ ግን...

ወጣቶች የሚሰሩት መልካም ስራን ብዙ ሰው ሲጋራው አይታይም፣ Like የለውም፣ share አይደረግም። ብዙዎቹ ምስጋናም የላቸውም፣ ክብርም የላቸውም፣ ዞር ብሎ የሚያቸውም የለም። ሚዲያዎችም የሆነ ሰዓት ትዝ ሲሏቸው ነው የሚያቀርቡት ወይም የመንግስት ሰዎች ለሪፖርት ሲሉ ያሞጋግሷቸዋል።

ያለንበትን እንፈትሽ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አመስግነናል!

"እሁድን በጠዋት ተነስተን የሲዳማ ዞን አጠቃላይ አመራሮች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ባለፈው በንብረት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በዓሉን በድምቀት እንዲያሳልፉ በማሰብ ሰብስበናል። ገንዘቡም ከነገ ጀምሮ ወደ ተፈለገው ቦታ ይደርሳል። ከዚያ ወጥቼ ወደ ቤቴክርስቲያን እየሄድኩ ነው!" #DE

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እድሳት ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በክረምት ለተደረገለት እድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ሰጥተዋል። ሌሎችም የነዚህን በጎ ፈቃደኞች አርአያነት በመከተል ህዝብን በነፃ የማገልገልና የመደገፍ ተግባርን ባህል እንዲያደርጉ ዶ/ር ዐቢይ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጴጥሮስ ሆስፒታል ያስገነባውን አዲስ ህንፃም በዛሬው እለት መርቀዋል። የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉትም በጥቁር አንበሳ የተደረገው በጎ ተግባር ለሌሎች ሆስፒታሎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ ነው። በቀጣይ ሌሎች ሆስፒታሎችም እድሳት እንዲደረግላቸው ሚኒስቴሩ ከባለ ሃብቱና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌼🌼ስጦታዬ ለአዲስ አበባዬ🌼🌼
ጳጉሜ 1 ተጀምሯል እስከ ጳጉሜ 6 ይቀጥላል፡፡
ቦታ 1. በሚሊኒየም አዳራሽ
2. በኤግዚቢሽን ማእከል

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine

TIKVAH-ETH MAGAZINE👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ