TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንዳይበሉ

እንዲህ ያለውም ማጭበርበር ተበራክቷል⬆️

"አንድ ሴትዮው በፌስቡክ ሪኬስት ልካልኝ ጓደኛዬ ሆነች ለረጅም ቀን አወራን። እና የካንሰር በሽተኛ መሆናን ነግራኝ የቀራት ትንሽ ቀን እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ ያላትን ሀብት ለእኔ ልታወረሰኝ እንደሆነ ነገረችኝ፤ ብዙ ነገር ነው ያወራችኝ። እና በመጨረሻም ብሩን ልላክ አለችኝ፡፡ እሺ አልኳት ብሩ ተልኳል ብላ ከላይ ያለውን ወረቀት ላከችልኝ፡፡ ለማንም ማሳየት የለብህም በሚስጥር ያዘው አለችኝ፡፡ ብሩ ዛሬ ይደርሳል እና ከዛ በፊት ግን 1500 ዶላር በአካውንቴ አስገባ አለችኝ፡፡ እኔ ደግሞ አሁን ስለሌለኝ ብሩን ስትልኪልኝ ከዛ ላይ ቆርጬ እለልክልሻለሁ ስላት አይቻልም ብላ ተወችው፡፡ በዚህ ነገር ብዙ ሰዎች እንዳይታለሉ አስጠንቅቅልኝ!"

🤔አንዳንዱ የ800 ብር ካርድ ላክልኝና ሽልማቱን ልስጥ ብሎ ይደውላል፤ አንዳንዱ ደግሞ 1500 ዶላር ላክልኝና ሀብቴን ላውርስህ ይላል!! ለማንኛውም ይህችን የማጭበርበሪያ ዘዴ ማወቁና መጠንቀቁ አይከፋም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia