አሳዛኝ ዜና!
በሀድያ ዞን #ሾኔ ከተማ ዛሬ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው በከተማው ወርልድ ቪዥን በተባለው አካባቢ የተርጋ ቁጥሩ ኮድ 1-14316 ደ.ሕ ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ከሻሸመኔ ወደ ወላይታ ሶዶ ይጓዝ ከነበረ ኮድ 3-05477 ደ.ሕ ከሆነ የጭነት አይሱዙ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ስራ ሂደት አስተባባሪ ዋና ሳጅን አዲሴ በርገኖ እንደገለጹት ባጃጁ መስመሩን ስቶ በፍጥነት በመጓዝ ላይ ከነበረው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪው ጋር በመላተሙ አደጋው ሊደርስ ችሏል። በአደጋውም በባጃጁ ውስጥ የነበሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
#የሟቾቹ አስክሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ መደረጉንም አመልክተው የአይሱዙ አሽከርካሪ ለጊዜው ቢሰወርም ፖሊስ በክትትል ላይ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ሳጅን አዲሴ የሰው ህይወትና ንብረትን ከጥፋት ለመታደግ አሽከርካሪዎች ርቀታቸውንና ፍጥነታቸውን በመቆጣጠር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia