መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#ብጉር

#ብጉር እጅግ የተለመደ እና አብዛኞቻችንን የሚያጠቃ የቆዳ ችግር ነው የሚከሰተውም በቆዳችን የሚመነጭ ቅባት ወይንም የሞቱ ሴሎች የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ሲደፍኑ ነው
በአብዛኛው በጉርምስና ጊዜ የሚመጣው ብጉር የሆርሞን መለወጥን ተከትሎ ነው
#የብጉር #ምልክቶች #እንደ #አይነቶቻችው #ይለያያሉ
👉ቀዳዳዎቻቸው የተደፈኑ ( ነጭ የሚሆኑ ብጉሮች)
👉ቀዳዳዎቻቸው የተከፋቱ (ጥቁር ብጉሮች)
👉ቁስለት ያለው ብጉር ( የተቆጣ ብጉሮች)
👉መግል የያዙ ብጉሮች ( የባክቴርያ ኢንፌክሽን ያለው ብጉሮች)
👉ጠጣር ብጉር ( ትልቅና የህመም ስሜት ያላቸው ብጉሮች) ናቸው።
#ብጉርን #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?
👉የሆርሞኖች በሰውነታችን መለዋወጥ
👉መድሃኒቶች በተለይም ሆርሞኖችን የያዙ ከሆኑ
👉ቅባትነት ያላቸውን መዋቢያዎችን መጠቀም
👉ጭንቀት
👉የወር አበባ መምጣት ናቸው።
#ለብጉር #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?
👉እድሜ
ሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች የሚጠቁ ቢሆንም #የጉርምስና እድሜ ላይ ግን በብዛት ይስተዋላል።
👉በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።
👉ቅባቶች
ቅባቶችን መጠቀም ይህን ሊያስከትል ይችላል።
👉ጭንቀት
#ጭንቀት ብጉር እንዲባባስ ስለሚያደርግ ማስወገድ ተገቢ ነው።
#ብጉር #እንዳይባባስ #ለመቆጣጠር #ምን #ማድረግ #እንችላለን?
👉ብጉር የወጣበትን ቦታ በሰሱ ማጽዳት በውሃና በሳሙና መታጠብ (በቀን ሁለት ጊዜ)።
👉ቅባታማ የሆኑ የመዋቢያ ውጤቶችን መጠቀምን ያስውግዱ።
👉በብጉር የተጎዳ ቆዳዎን በእጅዎ አይነካኩ።
👉ከባድ የጉልበት ስራ ከሰሩ በሗላ ገላዎን እና ፊትዎን ይታጠቡ።
ብጉር ቆዳዎን እያጠቃ የሚያስቸግርዎ ከሆነ እና ከላይ በተጠቀሱት መከላከያ መንገዶች የማይሻሻል ከሆነ ወደ ሀኪም በመሄድ ብጉርን ለማከም የተዘጋጁ መድሀኒቶችን በትክክሉ መጠቀም ተገቢ ነው።

#መልካም #ጤና
#Herpes #zoster (አልማዝ-ባለጭራ)

በግማሽ የሰውነት ክፍል ላይ በድንገት የሚወጣ ሽፍታ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ሽፍታው መስመር ይዞ ውሀ ቋጥሮ በጣም ህመም ያለው ነው፡፡ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ ግን
👉በጀርባበማጅራት
👉በደረት ወይም
👉በፊት ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡
በአገራችን በተለምዶ #አልማዝ #ባለጭራ እየተባለ ይጠራል::
👉 #የአልማዝ #ባለጭራ #በሽታ #ዋና #መንስኤ ጉድፍን የሚያስከትለው ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ (Varicella Zoster Virus) ነው ህመሙ ምንም እንኳን ለህልፈተ ህይወት ባይዳርግም ከፍተኛ ስቃይ/ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡
#የህመሙ #ምልክቶች
ብዙዉን ጊዜ በአንዱ የሰዉነት ክፍል በኩል/በቀኝ ወይም በግራ በኩል/ የሚታይ ነዉ፡፡
👉የማቃጠል
👉ማሳከክ
👉የመደንዘዝ
👉መጠቅጠቅ ህመም
👉የጡንቻ ህመም (ድካም)
👉ህመሙ ከተከሰተ ከጢቂት ቀናት በኃላ በቫይረሱ የተጠቃዉ አካባቢ ቀይ ሽፍታ መከሰት/መጀመር
👉ትኩሳት
👉የራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው
#ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ነገሮች
👉ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች
👉የተወሰኑ የህመም አይነቶች እንደ #ካንሰር #ኤች #አይቪ #ስኳርና ሌሎች የሰዉነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚቀንሱ ህመሞች ካሉ
👉እድሜ ከ50 ዓመትና ከዚያ በላይ ሲሆን
#ህክምናዉ
👉ወደ ቆዳና አባለዘር ሐኪም መሄድ
👉ሕክምናው ከሐኪም ጋር በመነጋገር የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፤የአልማዝ ባለጭራ (ኸርፐስ) በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እንደመሆኑ ጨርሶ ከሰዉነት ዉስጥ የሚያስወጣ መድሃኒት የለም ቢሆንም አንዳንድ ሁኔታውን ለማቅለል የሚታዘዙ የፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ ፡፡ በአፍም ሆነ በቅባት መልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ቁስሉ ወዲያው እንደጀመረ ቶሎ መወሰድ አለባቸው፤ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ፡፡
በተጨማሪም - ህመምና ሽፍታ በአይን ዙሪያ ከወጣ ይህ አይነት እንፌክሽን ካልታከመ የማይመለስ ጉዳት በአይን ላይ ሊያመጣ ይችላል፡፡

#መልካም #ጤና
#በወር #አበባ #ጊዜ #የሚከሰት #ሕመም

ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ የሕመም ስሜት ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሴቶች ከወር አበባ መምጣት ጋር ተያይዞ የሆድ ቁርጠት ሕመም ይኖራቸዋል፡፡
የሕመሙ መጠን ከሰው ሰው የሚለያይ ሲሆን አንዳንዴም የእለት ኑሮን እስከማቃወስ ይደርሳል፡፡

#በወር #አበባ #ጊዜ #የሕመም #ስሜት #እንዲሰማ #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች

👉ዕድሜ ከ30 ዓመት በላይ
👉ጊዜውን ጠብቆ የማይመጣ ከሆነ
👉ልጅ ያልወለዱ ከሆነ
👉በወር አበባ ጊዜ ከፍተኛ ሕመም የሚሰማው የቤተሰብ አባል ካለዎት
👉ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ናቸዉ፡፡
በወር አበባ ጊዜ የሚከሰቱ የሕመም ምልክቶች?
👉የሆድ ቁርጠት
👉የማያቋርጥ ከዕምብርት በታች ያለ የሕመም ስሜት
👉ወደ ጀርባ ወደምጥ የሚሄድ ዓይነት ስሜት
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሴቶች
👉 የማቅለሽለሽ
👉ተቅማጥ
👉የራስ ምታት
👉ማዞር የመሳሰሉት ሊኖራቸው ይችላል፡፡

#በወር #አበባ #ጊዜ #የሚከሰትን #ሕመም #ለማስታገስ

👉የሞቀ ውኃ ያለበትን የውኃ መያዣ ላስቲክ
በሆድዎ አካባቢ ማስቀመጥ የሚሰማዎን ሕመም ያስታግሳል
👉የአልኮል መጠጦችንና ሲጋራ ማጨስን መስወገድ
👉ጭንቀትን በተቻለ መጠን መቀነስ
👉 ለሕመም ማስታገሻነት የሚጠቅሙ መድኃኒቶችንም መጠቀም ናቸው፡፡
የህመም ስሜቱ የበዛና በማስታገሻዎች ሊታገስ ካልቻለ ወደ ህክምና መሄዱ ተመራጭ ነው

#መልካም #ጤና
#ቃር (Heartburn)

#ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሀርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።
በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ ሲገባ ነው።

#ለቃር #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች

👉ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
👉ሽንኩርት
👉ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
👉ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
👉ቸኮሌት
👉የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
👉ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
👉ከጥጋብ በላይ መመገብ
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉ነፍሰጡርነት ናቸው።

#ምልክቶች

👉ደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት በተለይ ምግብ ከተመገብን በኋላ እንዲሁም ምሽት ላይ
👉በጀርባ በምንቸኛበት ወቅት የማቃጠል ስሜቱ መጨመር
👉አፋችን ላይ የመምረር ስሜት።

#ሃኪምዎን #ማማከር #የሚገባው #መቼ #ነው

#ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።
#ከዚህ #በተጨማሪ
👉 በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
👉 ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
👉 ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
👉 የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።

#ቃርን #ለማስታገስ #መደረግ #ያለባቸው #የአኗኗር #ዘይቤ #ለውጦች

👉የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
👉ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
👉የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
👉ሲጋራን አለማጤስ
👉በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።

መረጃዉ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ይቺን👍 አይንፈጉን

#ጤና #ይስጥልኝ
#የጥፍር #ፈንገስ #ኢንፌክሽን

#የጥፍር #ፈንገስ #ኢንፌክሽን የምንለው በፈንገስ ምክንያት የሚከሰት ህማምን ሲሆን ከአንድ በላይ ጥፍሮችንም ሊያጠቃ ይችላል።
የጥፍር ፈንገስ ጥፍራችን እንዲወፍርና የህመም ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። የጥፍር ፈንገስ ኢንፌክሽኑ በጣቶችዎ መካከል ሊዛመትም ይችላል።

#የጥፍር #ፈንገስ #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው

👉የጥፍር መወፈር
👉የጥፍር ቀለም ወደ ቢጫነት መለወጥ
👉የጥፍር ቅርጽ መለወጥ
👉መጥፎ ጠረን ማምጣት ናቸው።
የጥፍር ፈንገስ በአብዛኛው በእግር ጥፍሮች ላይ የሚከሰት ሲሆን አልፎ አልፎ በእጅ ጣት ጥፍሮች ላይም ይከሰታል።

#ለጥፍር #ፈንገስ #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉 እድሜ መጨመር
👉ከፍተኛ ላቦት መኖር
👉በባዶ እግር ውሀ ዋና ቦታ፣ በጂም እና የገላ መታጠቢያ ቦታዎች መራመድ
👉ስኳር ወይም በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳካሙ ህመሞች መኖር ናችው።

#የጥፍር #ፈንገስ #እንዴት #መከላከል #ይቻላል

👉እጅዎን እና እግርዎን በሚገባ መታጠብ እና ማድረቅ
👉በፈንገስ ያልተበከለ የጥፍር መቁረጫን መጠቀም ወይንም በሚገባ አጽድተን መጠቀም
👉ላቦትን የሚመጡ ካልሲዎችን መጠቀም
👉በየትኛውም ቦታ ጫማ ተጫምተው መንቀሳቀስ
👉የአየር ዝውውርን የሚፈቅዱ ጫማዎችን መጠቀም
👉ጥፍርዎን ለማስዋብ የሚጠቀሟቸው እቃዎች በሚገባ የጸዱ መሆናቸው ማረጋገጥ
👉የጥፍር ማስዋቢያ እቃዎችን ከሌሎች ሰዎች ጋር አለመጋራት ናቸው።

#ህክምናው

👉የጥፍር ፈንገስን ለመከላከል ዋናውና ቀላሉ መንገድ ጥፍሮቻችንን አጭርና ንፁህ አድርጎ መያዝ ነዉ በበሽታዉ ከተጠቃን በኋላ ግን በሀኪም ትዛዝ የሚሰጡ መድሀኒቶች አሉ ከነዚህም ውስጥም
በአፍ የሚወሰዱ የፈንገስ መድሀኒቶች
በቅባት መልክ የተዘጋጁ መድሀኒቶች ናቸው

#ሀኪምዎን #ማማከር #የሚገባው #መቼ #ነው

የጥፍር ፈንግስ ኢንፌክሽን በከፍተኛ ሁኔታ ከአንድ ጥፍር ወደ ሌላው ሊዛመት ስለሚችልና ተገቢው ጥንቃቄ ካልተወሰደ ደግሞ ሌሎች የቤተሰብ አባሎችንም ሊያጠቃ ስለሚችል ወደሀኪም በመሄድ ተገቢውን መድሀኒት በታዘዘው መሰረት በሚገባ በመጠቀም እንዲለቅ ማድረግ ይቻላል።

ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያከፍሉ አብሮነታችሁን በዚ 👍 አሳዩን


#መልካም #ጤና
#የጉበት #ስብ (Fatty liver)

የጉበት ስብ የምንለው በጉበት ውስጥ የሚገኘው የስብ መጠን ከ 5-10 በመቶ የሚሆነውን የጉበት ክፍል ከያዘ ነው።
#ጉበታችን ከሰውነታችን ክፍል ውስጥ ሁለተኛ ትልቁ አካል ሲሆን የምንመገበውንም የምንጠጣውን አና ማንኛውንም ለሰውነት ጠቃሚ ያልሆነ ነገሮችን ከደማችን ውስጥ ያጣራል። #የጉበት ይህን የማከናወን ስራ በጉበት ስብ መብዛት ሊዛባ ይችላል።
የጉበት ስብ ይህ ነው የሚባል የራሱ የሆነ ምልክት ላያሳይ ይችላል።

#የጉበት #ስብን #የሚያስከትሉ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?

👉በአብዛኛው የጉበት ስብ የሚከሰተው አብዝተው የአልኮል መጠጥ በሚያዘውትሩ ሰዎች ላይ ነው እስካሁንም ድረስ የአልኮል መጠጥ በማይወስዱ ሰዎች ላይ የሚከሰት የጉበት ስብ ምክንያቱ በውል ግልጽ አይደለም

#አራት #አይነት #የጉበት #ስብ #አይነቶች #ይገኛሉ እነዚህም

#በአልኮል #መጠጥ #ምክንያት #የሚመጣ
👉ይህ የጉበት ስብ ከአልኮል መጠጥ ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ የመጀመሪያ ምልክት ተደረጎ የወሰዳል።
ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መጠቀም ጉበት ላይ ጉዳትን ያስከትላል ይህም ጉበት ስብን እንዲከማች ያደርገዋል የአልኮል መጠጥን በማቆም የጉበት ስብ እንዲወገድ ማድረግ ይቻላል።
#ያለ #አልኮል #መጠጥ #የሚከሰት #የጉበት #ስብ
👉ይህ 10% በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን ጉበታችን በጤናማ ሁኔታ ስብን ማቅልውጥ ሲያቅተው በሚከማች ስብ ምክንያት ነው
#ያለአልኮል #መጠጥ #የሚከሰት Steatohepatitis
👉የስብ መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ምክንያት ጉበት እንዲያብጥ የሚያደርግ ነው። ይህ ህመም የጉበትን ስራ በእጅጉ ሊያውክ ይችላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ምልክቶች
👉 የምግብ ፍላጎት ማጣት
👉ማቅለሽለሽ
👉 ማስመለስ
👉የሆድ ህመም ስሜት
👉የሰውነት ቢጫ መሆን ናቸው።
#በእርግዝና #ጊዜ #የሚከሰት #የጉበት #ስብ
👉ይህ ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል አይነት የጉበት ስብ ሲሆን ምልክቱ በሶስተኛው የእርግዝና ክፍለ ጊዜ ማለትም ከ6-9ወራት ባለዉ ጊዜ የሚከሰት ነው
👉የሚያቋርጥ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
👉በቀኝ የሆድ ክፍል አከባቢ የህመም ስሜት
👉የሰውነት ቢጫ መሆን
👉የድካም ስሜት ናቸው ።
#ለጉበት #ስብ #ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች #ምንድን #ናቸው?
👉ከልክ ያለፈ ውፍረት
👉የስኳር ህመም
👉የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠጣት
👉እርግዝና
👉ከፍተኛ የስብ መጠን በደም ውስጥ መኖር
👉የስኳር ህመም
👉ፈጣን የሆነ የክብደት መቀነስ
👉የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች
👉ከፍተኛ የትራይግላይሴራይድ መጠን ናቸው።
#የጉበት #ስብ #እንዴት #ይታከማል?
👉ይህ ነው የሚባል የህክምና መድሀኒትም ሆነ ቀዶ ጥገና የሌለው የጉበት ስብ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል እንደሚኖርብዎ በሀኪምዎ ይነገሮታል እነዚህም
👉የአልኮል መጠጥ አለማዘውተር
👉የኮሌስቴሮል መጠንን መቆጣጠር
👉ክብደትዎን መቀነስ
👉የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር ናቸው።

እንደተለመደው መረጃዉ ከተመቾት ላይክ 👍 ማረጎን አይርሱ

#መልካም #ጤና