መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
#Herpes #zoster (አልማዝ-ባለጭራ)

በግማሽ የሰውነት ክፍል ላይ በድንገት የሚወጣ ሽፍታ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ሽፍታው መስመር ይዞ ውሀ ቋጥሮ በጣም ህመም ያለው ነው፡፡ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ ግን
👉በጀርባበማጅራት
👉በደረት ወይም
👉በፊት ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡
በአገራችን በተለምዶ #አልማዝ #ባለጭራ እየተባለ ይጠራል::
👉 #የአልማዝ #ባለጭራ #በሽታ #ዋና #መንስኤ ጉድፍን የሚያስከትለው ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ (Varicella Zoster Virus) ነው ህመሙ ምንም እንኳን ለህልፈተ ህይወት ባይዳርግም ከፍተኛ ስቃይ/ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡
#የህመሙ #ምልክቶች
ብዙዉን ጊዜ በአንዱ የሰዉነት ክፍል በኩል/በቀኝ ወይም በግራ በኩል/ የሚታይ ነዉ፡፡
👉የማቃጠል
👉ማሳከክ
👉የመደንዘዝ
👉መጠቅጠቅ ህመም
👉የጡንቻ ህመም (ድካም)
👉ህመሙ ከተከሰተ ከጢቂት ቀናት በኃላ በቫይረሱ የተጠቃዉ አካባቢ ቀይ ሽፍታ መከሰት/መጀመር
👉ትኩሳት
👉የራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው
#ተጋላጭነትን #የሚጨምሩ #ነገሮች
👉ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች
👉የተወሰኑ የህመም አይነቶች እንደ #ካንሰር #ኤች #አይቪ #ስኳርና ሌሎች የሰዉነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚቀንሱ ህመሞች ካሉ
👉እድሜ ከ50 ዓመትና ከዚያ በላይ ሲሆን
#ህክምናዉ
👉ወደ ቆዳና አባለዘር ሐኪም መሄድ
👉ሕክምናው ከሐኪም ጋር በመነጋገር የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፤የአልማዝ ባለጭራ (ኸርፐስ) በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እንደመሆኑ ጨርሶ ከሰዉነት ዉስጥ የሚያስወጣ መድሃኒት የለም ቢሆንም አንዳንድ ሁኔታውን ለማቅለል የሚታዘዙ የፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ ፡፡ በአፍም ሆነ በቅባት መልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ቁስሉ ወዲያው እንደጀመረ ቶሎ መወሰድ አለባቸው፤ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ፡፡
በተጨማሪም - ህመምና ሽፍታ በአይን ዙሪያ ከወጣ ይህ አይነት እንፌክሽን ካልታከመ የማይመለስ ጉዳት በአይን ላይ ሊያመጣ ይችላል፡፡

#መልካም #ጤና
አብዛኛዉ ጊዜዉን የሚያሳልፈዉ ፀጉር ማስተካከያ ቤት ዉስጥ ነዉ።
💇‍♂️ #ሀይፐርትሩኮሲስ (Hypertrichosis)
ይሄ የመጠርያ ስሙ ነው የአንድ ሰዉ ፀጉር ከተለመደዉ በላይ ማለትም ከእድሜም፣ ከፆታም
እንዲሁም ከግለሰቡ የዘር ማንነት ዉጪ የሆነ የፀጉር እድገት ነዉ።
#ሀይፐርትሩኮሲስ #በምን #ይከሰታል
👉ምክንያቱ በምን እንደሚከሰት አይታወቅም ከዉልደት ጀምሮ የሚከሰተዉ ችግር ከዘረመል መታወክ ጋር እንደሚያያዝ ይታመናል በዚህም ምክንያት የፀጉር እድገት ከተለመደዉ በላይ ይሆናል
#ህክምናዉ
👉ዋናው ህክምና የበዛዉን ፀጉር ማንሳት ነዉ
የተለያዩ የፀጉር ማንሻ ዘዴዎች አሉ ነገር ግን የፀጉር እድገቱ ስለማያቆም ቶሎ ቶሎና መደጋጋም አለበት
👉ደጋግሞ መላጨት
👉Chemical epilation፦ ኬሚካል በመጠቀም ፀጉርን ህመም ሳይሰማ ከሰዉነት ላይ ማንሳት
👉Electrolysis and thermolysis.እያንዳዷን የፀጉር መብቀያ ቀዳዳ በኤሌክትሪክ ንዝረት ፀጉሩን የማጥፋት ህክምና
👉Waxing፦ሰም በመጠቀም ፀጉርን ማስወገድ
👉በቅርቡ ደሞ ጨረር በመጠቀም ፀጉርን ማስወገድ ተችሏል
ከላይ የምናየው ሰዉ በዚሁ hypertrichosis የተጠቃ ሰው ነዉ።

እስቲ መረጃዉ ከተመቾት 100 👍 አድርሱልን

#መልካም #ጤና
#ኒውሮብፋይብሮማቶሲስ

(Neurofibromatosis) በዘረመል መዛባት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን የነርቭ ህዋሳቶች እድገት ላይ ተፅእኖ አለዉ ይሄም የሰዉነታችን ቆዳ እንዲሁም አይናችን አካባቢ እና የተለያዩ የሰዉነታችን አካላት ላይ ባሉ የነርቭ ጫፎች ላይ የሚወጣ እባጭ ነዉ።

#ሁለት_አይነት_ኒውሮብፋይብሮማቶሲስ_አለ

#እነዚህም
👉Neurofibromatosis 1 :- ሲሆን ምልክቱም በተለይ በቆዳ ላይ የሚወጡ አነስ ያሉ ቡናማ እባጮች እንዲሁም ብብት አካባቢና ንፊፊት አካባቢ የሚወጡ በመጠን ቀለል ያሉ ብዛት ያላቸው እባጮች ናቸው
👉Neurofibromatosis 2 :-ሲሆን በቆዳ ላይ ተለቅ ያሉ እንደ ጆሮ የተነጠለጠሉ እባጮች እና የጡንቻዎች መላላት ከዚህም በተጨማሪ የአይን ሞራን ጨምሮ የመስማት ችግርንም ያስከትላል

#ህክምናዉ

እስካሁን ምንም አይነት መከላከያም ሆነ ህክምና አለተገኘለትም ነገር ግን አንዳንድ ጊዚያዊ የሆኑ ህክምና ዘዴ አለ እነዚህም
በቀዶ ህክምና እባጮቹን ማስወገድ በመጀመርያ ግን እባጮቹ በሚወጡበት ግዜ ሌላ ችግር እንደማያመጡ መታወቅ አለበት
በህፃናት ላይ ይህ በሽታ ሲከሰት ቶሎ ማወቅና በየአመቱ ያለውን ለዉጥ መከታተል ህክምናዉን ቀለል ያረገዋል

ለመረጃዉ 👍 አይንፈጉን

#መልካም_ጤና