መኀደረ ጤና
2.6K subscribers
36 photos
13 videos
6 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝
ስለ ጤናዎ ወሳኝ መረጃዎች💊 ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ የጤና መረጃዎችን ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ ይማሩበታል ያስተምሩበታል መልካም ጤና ለሁላችን..


መልካም ጤና ለሁላችን..
Download Telegram
ከዚህ ቀደም ለHIV ቀን በቀን የሚወሰደውን መድኃኒት በአመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲወሰድ የሚያስችል ምርምር ይፋ ሆነ.....

በአሜሪካ በኔብራንካ የህክምና ትምህርት ቤት ኬኒያዊው ፕሮፌሰር ቤንሶን ኢዳንጋዋና ቡድናቸው ኤች አይ
ቪን አስመልክቶ አዲስ አገኘን ባሉት ግኝት ከዚህ ቀደም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ይወስዱት የነበረውን በቀን በቀን የሚወስዱትን መድኃኒት በአመት አንድ ጊዜ መውሰድ እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምርምሩ አሁን ላይ በላብራቶሪ ሙከራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በእንሰሳት ላይ ተሞክሮም ውጤታማ መሆኑን ነው የተነገረው፡፡ ይህ መድኃኒት ቫይረሱ ያለባቸውን ለማከም ብቻ ሳይሆን ስርጭቱንም ይገታዋል ይህም ትልቅ እምርታ ነው ተብሎለታል፡፡

በአለም በአማካኝ 39.9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሲሆኑ አፍሪካ ትልቁን ቁጥር ትሸፍናለች፡፡ ይህም በቁጥር ሲቀመጥ 25.7 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ከቫይረሱ ጋር ይኖራል፡፡ አዲሱ መድኃኒት ( Cabotegravir Drug ) የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ትልቅ ተስፋ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡
#ቢጫ_ወባ (Yellow Fever)

#ቢጫ_ወባ_በሽታ_ምንድነው?

የሎው ፊቨር ወይም ቢጫ ወባ የሚባለው በሽታ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣና የመድማት ችግር የሚያስከትል በወባ ትንኝ አማካኝነት የሚተላለፍ የትኩሳት በሽታ ነው፡፡

👉ትንኟ በበሽታው ከተያዘ ሰው ደም በምትመጥበት ጊዜ በተህዋሲያኑ ትያዛለች፤የተህዋሲያኑ ተሸካሚ የሆነች የወባ ትንኝ ከጤነኛ ሰው ደም ለመምጠጥ ቆዳውን በምትበሳበት ጊዜ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
👉በሞቃታማ ስፍራ በሚገኙ ጥቅጥቅ ባሉ ደኖች፣ በስራ ወይም መኖሪያ ቦታ ረግረጋማና የአቆረ ውሃ፤ በየቦታው የተጣሉ ውሃ የሚያቁሩ ቁሳቁሶች፣ በማይከደኑ የውሃ ማጠራቀሚያ እቃዎች ለትንኞች መራቢያነት ምቹ ስፍራዎች ናቸው፡፡

#የቢጫ_ወባ_በሽታ_ምልክቶች

የመጀመሪያ 3 እና 4 ቀናት የሚከሰቱ

👉በድንገት የሚከሰት ትኩሳት
👉ብርድ ብርድ የሚል ስሜት፣
👉 ራስ ምታትና አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣
👉 የጀርባና የጡንቻ ህመም፣
👉 ማቅለሽለሽና ትውከት ዋናዎቹ ናቸው

#በሁለተኛ_ደረጃ_የሚከሰቱት

👉የትኩሳት ማገርሸት፤
👉የሰውነት ወይም የዓይን ቢጫ መሆን (juandice)፤
👉የሰውነት (ከዓይን፣ አፍ፣ አፍንጫ፣ ወ.ዘ.ተ.) መድማትና
👉ደም የተቀላቀለበት ትውከት ናቸው፡፡

የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በአስቸኳይ ሕክምና እርዳታ በጤና ተቋማት ካላገኙ ራስን መሳትና ብሎም ሞት ያስከትላል፡፡

#የቢጫ_ወባ_በሽታ_መከላከያ #መንገዶች

👉በሽታው እጅግ አስተማማኝ የሆነ ምንም ጉዳት የማያስከትል፣ በአንድ ጊዜ የሚወሰድና ለበሽታው የዕድሜ ልክ የሰውነት መከላከያ የሚፈጥር ክትባት ስላለው ክትባቱ በሚሰጥበት ወቅት በመገኘት በነፃ መከተብ በሽታውን፡ መከላከልም ሆነ በሕክምና ሙሉ በሙሉ ማዳን ይቻላል፡፡

👉ትንኟ እንዳትራባ መቆጣጠር

፦ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቁሳቁሶችን ማስወገድ፣
፦ውሃ ያቆሩ ስፍራዎችን ማጠንፈፍ ማድረቅ
፦ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ስፍራዎችን ፀረ-ተባይ ማስርጨት፣
፦በቤት ውስጥ የወባ መግደያ ፊሊት መርጨት፡፡

እንዴት_የትንኟን_ንክሻ_እንከላከል

፦እጀ ሙሉና ረጂም ልብሶችን መልበስ
ትንኝ ማባራሪያ የሰውንተ ቅባት መጠቀም፤
፦በማንኛውም ስዓት የአልጋ አጎበር በመጠቀምና መተኛት፤
፦መኖሪያ ቤትን የትንኝ መግደያ ፍሊት በመርጨት ትንኞችን ማስወገድ፤

#የበሽታው_ምልክቶች_ሲታዩ

በአስቸኳይ በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ሪፖርት ማድረግና ሕክምና ማግኘት ከበሽታው ለመዳን ስኬታማ ለውጥና ፈውስ ለማግኘት ወሳኝ ተግባር ነው፡፡

#መልካም_ጤና

Like and share
#የጉበት_በሽታ ( #ሄፖታይተስ_ቢ )

#ሄፖታይተስ_ምንድን_ነው?

ሄፖታይተስ ማለት ከጉበት መቆጣት ጋር የተያያዘ የጉበት ጉዳት ማለት ሲሆን ይህ የጉበት መቆጣት በሁለት ይከፈላል፡፡

👉የመጀመሪያው ድንገተኛ ሄፖታይተስ (አኪዩት) ይባላል፡፡

👉ሁለተኛው ደግሞ ስር የሰደደ የቆየ የጉበት መቆጣት (ክሮኒክ) ሲባል

የህመሙ ምልክቶች ስድስት ወርና ከእዚያ በላይ ሲቆይ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ድንገተኛው ሄፖታይተስ በቀናት ውስጥ ይጀምርና በሁለት ወይም በሦስት ወራት በዛ ከተባለ በስድስት ወር ውስጥ ህመምተኛው ከበሽታው ያገግማል፡፡ የሄፖታይተስ መንስዔዎች በሁለት ይከፈላሉ።

ተላላፊ (ከኢንፊክሽን) ጋር የተያያዙ እና ከኢንፌክሽን ጋር ያልተያያዙ ናቸው፡፡

በአብዛኛው በሽታው የሚከሰተው ግን ከኢንፊክሽን ጋር በተያያዘው መንስዔ ነው፡፡ ከኢንፊክሽን ጋር በተያያዘ ለሚመጣው በሽታ መንስዔ ከሚሆኑት ውስጥ
👉ከፍተኛ መጠን ያለው የአልኮል መጠጥ
👉መድሐኒቶች፣ የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች፣ መርዛማ ነገሮች ይጠቀሳሉ፡፡
አልፎ አልፎ የሰውነታችን የውስጥ መከላከያ (ኢሚዩኒቲ) ሲዛባ የእራሳችን የበሽታ መከላከያ ጉበታችንን ይጎዳውና «አውቶ ኢሚዩን» ሄፖታይተስ የተባለውን የጉበት መቆጣት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ምንም መንስኤው የማይታወቅ የጉበት መቆጣት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም «ክሪብቶጄኒክ» ሄፖታይተስ ይባላል፡፡

#ሄፖታይተስ_ቢ_ምንድንነው

አብዛኛው ሄፖታይተስ የሚከሰተው በአምስት ዋና ዋና የጉበት ቫይረሶች ማለትም ሄፖታይተስ #ኤ #ቤ #ሲ #ዲ እና #ኢ ተብለው በሚጠሩ የቫይረስ ዓይነቶች ሲሆን፤ የእያንዳንዳቸው ባህሪና ምንነት የሚታወቀው በውስጣቸው ባለው ጄኔቲክ ማቴርያል ነው፡፡ ከአምስቱ አራቱ ሄፖታይተስ #ኤ #ሲ #ዲ እና #ኢ አር ኤን ኤ ቫይረስ ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህ ቫይረሶች በውስጣቸው ያለው ጄኔቲክ ማቴርያል ባለ ነጠላ እረድፍ ነው፡፡ ሄፖታይተስ ቢ ባለጥንድ ረድፍ ጄኔቲክ ማቴርያል የያዘ በመሆኑ ዲ ኤን ኤ ቫይረስ ይባላል፡፡ በእዚህም ከላይ ከተጠቀሱት የሄፖታይተስ ቫይረሶች ይለያል፡፡ እነዚህ ቫይረሶች በሽታን የሚያመጡበት መንገድ ይለያያል፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ እና #ኢ ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ በተበከለ ውሃና ምግብ አማካኝነት የሚተላለፉ ሲሆን፤ ሄፖታይተስ #ቢ #ሲ እና @ዲ ልክ እንደ ኤች አይ ቪ ቫይረስ ከደምና ከደም ጋር በተያያዙ መንገዶች የሚተላለፉ ናቸው፡፡
እነዚህ ቫይረሶች የሚራቡት ጉበት ውስጥ ሲሆን ፤ከተራቡ በኋላ ወደ ደም ዝውውራችን ይገባሉ። በእዚህ ጊዜ ሰውነታችን ቫይረሱን ለመዋጋት ፀረ ህዋስ (አንቲ ቦዲ) ያመርታል፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ #ሲ #ዲ እና #ኢ በተዘዋዋሪ መልኩ በምርመራ የሚገኙ ሲሆን ፤ እነዚህ ፀረ ህዋሶች በደማችን ውስጥ በምርመራ በመለየት የትኛው ቫይረስ እንደያዘን ለማወቅ ይቻላል፡፡ ሄፖታይተስ ቢ ከሌሎች ለየት የሚለው የቫይረሱን አካል (አንቲጅን) በምርመራ ከደም ውስጥ በመለየት ቫይረሱ እንዳለብን በቀጥታ ማወቅ ይቻላል፡፡ በቫይረሱ ሽፋን ላይ ያለው አንቲጅን (ሄፖታይተስ ቢ ሰርፊስ አንቲጅን) በደም ውስጥ ከተገኘ ቫይረሱ እንዳለብን ያሳያል፡፡ ከቫይረሱ ውስጠኛው ክፍል የሚመነጭ አንቲጅን (ሄፖታይተስ ቢ ኢ አንቲጅን) በምርመራ ከተገኘ በደም ውስጥ ያለውን የመራባት መጠንና የማስተላለፍ አቅሙን ከፍተኛነት ያሳያል፡፡
የቫይረሱ መጠን በላቦራቶሪ በደም ውስጥ በዝቶ በአንድ ሲሲ ከአሥር ሚሊዮን እስከ መቶ ሚሊዮን ከተገኘ የህመሙን ደረጃ ከፍተኛነት ያሳያል፡፡ በአጠቃላይ የተለያዩ አንቲጅኖችን በደም ውስጥ በመመርመር የበሽታው ደረጃ ምን ያህል እንደሆነና ዓይነቱን ለማወቅ ይረዳል፡፡
አምስቱም የጉበት ቫይረሶች ድንገተኛ የጉበት መቆጣት ሲያመጡ ተመሳሳይ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡ ሄፖታይተስ #ኤ እና #ኢ ድንገተኛ የጉበት መቆጣት ያስከትሉና ጉበታችን በራሱ ጊዜ አገግሞ ሰውነታችንም ቫይረሶቹን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። ስለዚህም በደም ውስጥ አይቆዩም፡፡ ሄፖታይተስ #ቢ #ሲ እና #ዲ ደግሞ ምንም ምልክት ሳያሳዩ በደም ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመቀመጥ እየተራቡ ሄደው ስር የሰደደ የጉበት መቆጣት መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጉበት በሽታና ካንሰርንም ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
ከአምስቱ ቫይረሶች ሄፖታይተስ #ዲ ስንኩል በመሆኑ ለብቻው ሰውን የማጥቃት አቅም የለውም፡፡ ሰውን የሚያጠቃው ከሄፖታይተስ ቢ ጋር በመዳበል ወይም ሄፖታይተስ ቢ የተያዘን ሰው ነው፡፡ ሁለቱ አብረው ሲከሰቱ የሚያስከትሉት ጉዳትም የከፋ ነው፡፡
ሄፖታይተስ ቢ በአገሪቱ በከፍተኛ የጉበት በሽታና የጉበት ካንሰር መነሻነት በዋነኛነት የሚጠቀስ ቫይረስ ሲሆን ፤ከኤ እስከ ኤች የሚደርሱ ዝርያዎች (ጅኖታይፕስ) አሉት፡፡ እነዚህ ዝርያዎች በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ ሲሆኑ፤ የሚያስከትሉት የህመም መጠን አንዱ ከሌለው ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ በህክምና ቶሎ ሲድኑ አንዳንዶቹ ግን አይድኑም። በእዚህም ምክንያት ሄፖታይተስ ቢን ለህክምና አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

#በሽታው_ከሰው_ወደ_ሰው_ ይተላለፋል

አዎ! በሽታው የሚተላለፈው በቫይረሱ በተበከለ ደም፣ ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የተበከሉ መርፌዎችና ስለታም ነገሮችን በጋራ በመጠቀም፣ በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ በመሳሰሉት መንገዶች ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
ቫይረሱ በበሽታው በከፍተኛ ደረጃ በተጠቁ ሰዎች ውስጥ መጠኑ ይለያይ እንጂ በማንኛውም ፈሳሽ የሚገኝ በመሆኑ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፍ ያስችለዋል፡፡
የሄፖታይተስ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ለመግባት ቀዳዳ ይፈልጋል፡፡ ምንም ጉዳት የሌለው ጤነኛ ቆዳ ውስጥ አልፎ አይገባም፡፡ ነገር ግን የዓይናችን የውስጠኛው ሽፋን ያለምንም ችግር ሊያስተላልፈው ስለሚችል ቫይረሱም ያለበት ፈሳሽ ዓይናችን ውስጥ ቢረጭ በበሽታው ለመያዝ መንገድ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በቫይረሱ የተጠቁ ሕሙማንን የሚያስታምሙ የቤተሰብ አባላት የተላጠ ወይንም የተሰነጠቀ ማንኛውም ቁስል እጃቸው ላይ ካለ በፕላስተር መሸፈን አለባቸው፡፡
ማንኛውም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ (ላብንና ዕንባንም ጨምሮ) በጥንቃቄ መያዝና መወገድ አለበት፡፡ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ሲገባ ከዘጠና እስከ ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆኑ ሰዎች ላይ የሰውነታችን መከላከያ ኃይል ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ አስወግዶ ቋሚ መከላከያ ይፈጥራል፡፡ ቫይረሱን ይዘው የሚቀሩት ከአንድ እስከ አምስት ከመቶ የሚሆኑ ሕመምተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ቫይረሱ ካለባቸው ጥቂቶቹ ስር የሰደደ የጉበት መቆጣት ሲይዛቸው አብዛኞቹ ምንም ምልክት አያሳዩም፡፡ በአጠቃላይ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ ሃያ ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ከፍተኛ የጉበት በሽታ (ክሮኒክ ሊቨር ዲዚዝ) ይይዛቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ከዓመታት በኋላ የጉበት ካንሰር ሊይዛቸው ይችላል፡፡
ኢንፌክሽኑ በብዛት የሚታየው ከሃያ እስከ አርባ ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ሲሆን ሕፃናት ላይ እንብዛም አይገኝም፡፡ ከአርባ ዓመት ዕድሜ በላይ ባሉ ሰዎች የበሽታው መጠን የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል፡፡
ቫይረሱ ወደ ሰውነት በሚገባበት ወቅት ድንገተኛ የጉበት መቆጣት የሚያሳየው ምልክት
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉ማቅለሽለሽ
👉የሰውነት መቀነስ
👉ዐይን ቢጫ መሆን
👉በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል የህመም ስሜት የሚሰማ ሲሆን፤
ህመምተኛው ህክምና ከወሰደ በሦስት ወር ውስጥ ያገግማል፡፡ ስድስት ወር ከሞላው ግን ስር ወደ ሰደደ የጉበት በሽታ ይቀየራል፡፡

#ህክምናው_ምንድነው
ለድንገተኛ የጉበት መቆጣት ምንም የሚሰጠው መድኃኒት የለም፡፡ ህመምተኛውም ከፍተኛ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን እንዲመገብና መልቲ ቫይታሚኖችን በመጠቀም ከበሽታው ለማገግም ይችላል፡፡ ሄፖታይተስ ቢ ኢንፌክሽን ህክምና አለው። የህክምናውም ዓላማ በደም ውስጥ ያለውን ቫይረስ እስከመጨረሻ ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት እና የጉበት በሽታ እንዳይከሰት ወይም እንዳይባባስ ለማድረግ ነው። ህክምናው ለሁሉም ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ላለባቸው ሰዎች አይሰጥም። ህክምናውን ለመውሰድ የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ። መስፈርቶቹን የሚያሟሉት ብቻ ናቸው መድኃኒቱን የሚጀምሩት። መድኃኒቱ ከመጀመሩ በፊት በደም ውስጥ ያለው የቫይረሱ መጠንና የቫይረሱ ዝርያ (ጂኖታይፕ) በምርመራ መታወቅ አለበት። ይህ የደም ናሙና ወደ ውጭ ተልኮ የሚሠራ ምርመራ ነው። ወደ ህክምናው ስንመጣ ዋናው ለቫይረሱ የሚሰጠው ህክምና «ኢንተርፌሮን አልፋ» በመባል ይታወቃል። ይህ መድሀኒት በሳምንት 3 ጊዜ ለአራት ወራት በመርፌ መልክ የሚሰጥና እጅግ በጣም ውድ የሆነ ሀገራችን ውስጥ የማይገኝ መድኃኒት ነው። ሙሉ የ4 ወር ህክምናው እስከ 300,000 ብር ይፈጃል። ህክምናው በአብዛኛው ጊዜ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከሰውነት ውስጥ ባያጠፋውም በማያገረሽ መልኩ እስከመጨረሻ አዳክሞት ምንም ዓይነት የጉበት በሽታ እንዳይከሰት ያደርጋል።
ሌላው መድኃኒት ለፀረ ኤች አይ ቪ ህክምና የም ንጠቀምባቸው መድኃኒቶች አንዱ የሆነው «ላሚቩዲን» የተባለ መድኃኒት ነው። ነገር ግን ከእዚህ መድኃኒት ጋር የተያያዙ አንዳንድ ችግሮች አሉ። ለምሳሌ ይህ መድኃኒት ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰጥ በተወሰኑ ሰዎች ላይ ቫይረሱ መድኃኒቱን ይለማመድና መራባቱን ሊቀጥል ይችላል። ይህ ሁኔታ ቢከሰትም አንዳንድ የህክምና ኤክስፐርቶች ህክምናው ሳይቋርጥ መስጠትን ይመከራሉ። ምክንያቱም መድሀኒቱን ተለማምዶ የሚፈጠረው ቫይረስ የመራባት አቅም የሌለው የከፋ ጉዳት የማያስከትል ደካማ ቫይረስ ስለሚሆን ነው።

#በሽታውን_ እንዴት_መከላከል_ይቻላል?

በሽታውን በሁለት ዓይነት መንገድ መከላከል ይቻላል። የመጀመሪያው የተፈጥሮ መከላከያ ሲሆን፤ በሽታው ሲከሰት ሰውነታችን የተፈጥሮ መከላከያ በማመንጨት ራሱን የሚያድንበት ነው፡፡ በእዚህ ዓይነት መንገድ የዳኑ ሰዎች ቫይረሱ ከሰውነታቸው ከጠፋ በድጋሚ ለበሽታው አይጋለጡም፡፡ አርቴፊሻሉ መከላከያ ደግሞ በክትባት መልክ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህም «ፓሲቭ» እና «አክቲቭ» ተብለው ይጠራሉ፡፡ የፓሲቭ ህክምና ፀረ ህዋሱ በአንቲ ቦዲ መልክ ተዘጋጅቶ ይሰጣል፡፡ አክቲቩ ደግሞ ክትባቱን ከተከተበ በኋላ በደም ውስጥ አንቲ ቦዲ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ሄፖታይተስ ቢ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ ከኤች አይቪ ጋር ሲወዳደር ሃምሳ ከመቶ በላይ እጥፍ ነው፡፡ በኤች አይቪ በተበከለ መርፌ አንድ ሰው ቢወጋ በቫይረሱ የመያዝ ዕድሉ ዜሮ ነጥብ ሦስት ከመቶ ሲሆን ፤ በሄፖታይተስ ቢ ከሆነ ግን ከስድስት እስከ ሠላሳ ከመቶ ይደርሳል፡፡

የበሽታው ተጋላጮች የትኞቹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ናቸው?
ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ያልተከተቡ ሕፃናት በሽታውን ለመከላከል የተዘጋጀውን ክትባት መከተብ ይኖርባቸዋል። ክትባቱ በሦስት ዙር ማለትም የመጀመሪያ፣ ከወር በኋላ እና ከስድስት ወር በኋላ የሚሰጥ ሲሆን፤ እስከ አሥር ዓመት ድረስ የመቆየት አቅም አለው፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑት የኅብረተሰብ ክፍሎች ከበርካታ ሰዎች ጋር ልቅ የፆታ ግንኙነት የሚያደርጉ፣በጣም የታመመ የቤተሰብ አባል ያላቸው ቤተሰቦች፣ ቫይረሱ ያለበት የትዳር አጋር ያለው ሰው፣የጤና ባለሞያዎች፣ በጤና ችግር ምክንያት በተደጋጋሚ ደም የሚለገሳቸው ህሙማን ናቸው።

#ምክር

ቫይረሱ በደሙ ውስጥ ያለበት አንድ ሰው ስለመድኃኒቱ ከመጨነቅ ይልቅ ጉብቱ ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ነገሮች ራሱን እየጠበቀ (እንደ አልኮል ያለ፣ ሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰድ መድኃኒት፣ ያበሻ መድሀኒት) በተወሰነ ጊዜ ርቀት ቋሚ የህክምና ክትትል ቢያደርግ በቂ ነው እንላለን።

#መልካም_ጤና

Like and share
መኀደረ ጤና pinned «#የጉበት_በሽታ ( #ሄፖታይተስ_ቢ ) #ሄፖታይተስ_ምንድን_ነው? ሄፖታይተስ ማለት ከጉበት መቆጣት ጋር የተያያዘ የጉበት ጉዳት ማለት ሲሆን ይህ የጉበት መቆጣት በሁለት ይከፈላል፡፡ 👉የመጀመሪያው ድንገተኛ ሄፖታይተስ (አኪዩት) ይባላል፡፡ 👉ሁለተኛው ደግሞ ስር የሰደደ የቆየ የጉበት መቆጣት (ክሮኒክ) ሲባል የህመሙ ምልክቶች ስድስት ወርና ከእዚያ በላይ ሲቆይ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ድንገተኛው…»
#ሪህ

ሪህ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲሆን ሰውነታችን ለማስወገድ አቅም ያጣል፡፡ በዚህን ጊዜ ካልሼም ፎስፊት ወደሚባል ጠጣር ንጥረ ነገርነት ተቀይረው ወደ መገጣጠሚያ ቦታዎች ይሰበሰባሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የተከማቸው ዩሪክ አሲድ በኩላሊት ውስጥ እና በሽንት ማመላለሻ መስመሮች ውስጥ በመዝቀጥ የኩላሊት ጠጠር ሊፈጥር ይችላል ፡፡

#መንስኤው_ምንድንነው

ለሪህ የጤና ችግር በመንስኤነት የሚገለፁ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

#የዕድሜ_መጨመር

በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ የንጥረ ነገሮች መፈጠርና መከማቸት
በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አማካኝ
ከቤተሰብ መካከል የጤና ችግሩ ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድል ይኖረዋል
ምክንያታቸው በውል የማይታወቅ ጉዳዮች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች ለሪህ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ቀይ ሥጋ፣ ጉበት ኩላሊትና የጭንቅላት ስጋን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ለሪህ በሽታ ተጋላጭ የመሆን ዕድልን ያሰፋሉ፡፡ ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ
👉የሰውነት ክብደት መጨመር፣
👉በቁጥጥር ስር ያልዋለ ደም ግፊት፣
👉ውሃ በብዛት ያለመጠጣት፣
👉የኩላሊት በሽታና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለሪህ በሽታ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡

#የህመሙ_ምልክቶች

👉ከትንሽ የጣት ጫፍ እስከ ትላልቆቹ የሰውነት ክፍሎች አካባቢያሉ መገጣጠሚያ ቦታዎች ያብጣሉ
👉የሰውነት ትኩሳት መከሰት
👉 ከቁርጥማት ጀምሮ መላ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በመንካት እስከሚቸግር ድረስ ህመም
👉 ከፍተኛ ስቃይ ያለው ህመም
👉መገጣጠሚያ አካባቢዎች በተለይ መልኩ መቅላት
👉በመገጣጠሚያ አካባቢዎች የማቃጠል ሁኔታ ይከሰታል
👉የጡንቻ መዛል በተለይ ጠዋት ጠዋት እጅና እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር ይኖራል
👉የጤና ችግሩ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ በመገጣጠሚያ ቦታዎች ጠጣርየሆኑ ነገሮች ይፈጠራሉ
👉በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ
👉ቁርጥማት
👉በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡

#ህክምናው_ምንድነው

አንድ ሰው ለመጀመሪያ ወይም በተደጋጋሚ ጊዜ የሪህ በሽታ ከተከሰተበት ከፍተኛ ስቃይ ይኖረዋል፡፡ የመጀመሪያው የህክምና ስቃዩን ለማስታገስ የሚያስችል መድሃኒቶች ይታዘዛሉ ፡፡ በዚህ ረገድ Non-Steroid Anti-Inflamaty drugs /Nsaids/ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለውጥ ካልመጣ Corticoid Steroids የሚባሉ መድሃኒቶችን በመርፌ ወይም በሚዋጥ መልክ ይሰጣል ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች የህመም ስቃይን ከማቃለል በተጨማሪ መገጣጠሚያ ከጥቅም ውጭ እንዳይሆን ለጊዜው ፋታ ይሰጣሉ፡፡
ሌላኛው የህክምና ዘዴ Uric acid ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ የሚችሉ መድሃኒቶች ነው፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡ እጅና እግር መንቀሳቀስ ካቆመ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡

#መልካም_ጤና
Spinal cord injury levels and effects on body
በተለያየ አጋጣሚ ፅንስ በራሱ ጊዜ ይወርዳል ከዚ ውስጥ አንዱ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Removing brain hematoma (ጭንቅላት ውስጥ የፈሰሰን ደም ሲወጣ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ)
Learning about compatible blood types
Donor and Recipient ABO Blood Type Compatibility Chart
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Here is a short video showing a rare caesarean delivery with the baby in fully intact amniotic sac!
-
The amniotic sac remaining unbroken during the birth makes the infant appear to be inside a bubble, which is rare to experience.
It's almost like the baby is protected. It cushions the fetus from physical trauma, permits fetal lung growth, and provides a barrier against infection.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቤት_ውስጥ_የተደረገ_ውልጃ

እናቶች በወሊድ ጊዜ ምን ያህል በህመም ሥቃይ እንደሚይዙ ይመልከቱ ፡፡ብዙ ዶክተሮች ብዙውን ጊዜ ቤት ውስጥ ከመውለድ ጋር ተያይዘው በሚመጡ የአደጋ ተጋላጭነቶች ምክንያት ሆስፒታል መውለድን ይደግፋሉ ፡፡ ሆኖም በአጋጣሚ ከተከሰተ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርቦታል።
#የጨጓራ_አልሰር (Peptic ulcer disease /PUD)

በተለምዶ የጨጓራ አልሰር የምንለው በህክምና አጠራሩ ፔፕቲክ አልሰር ዲዚዝ ይባላል።በተለምዶ ያልኩበት ምክንያት የጨጓራ አልሰር ጨጓራንም ትንሹንም አንጀት ስለሚያጠቃ የጨጓራ ብቻ እንዳይመስላችሁ ለማለት ነው። ይህ አልሰር(የጨጓራና የትንሹ አንጀት የውስጥ ግድግዳ መላጥ፣መቦርቦ ወይም መቁሰል )የሚከሰተው በጨጓራ በሚመነጭ አሲድ ምክንያት ነው።

#የጨጓራ_አልሰር_በምን_ይመጣል ?

👉ኤች-ፓይሎረ የተባለ ባክቴሪያ ከ50 በመቶው የአለም ህዝብ የዚህ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን አለው። ምንም እንኳ በዚህ ባክቴሪያ የተያዘ ሁላ በጨጓራ አልሰር ባይጠቃም የዚህ ባክቴሪያ መኖር ለአልሰር የመጋለጥን እድል ከፍ ያደርገዋል ።ይህ ባክቴሪያ የጨጓራን ግድግዳ ከአሲድ የሚከላከለውን ሙከስ በመቀነስና የአሲዱንም መጠን በመጨመር ጉዳት ያደርሳል። ይህ ባክቴሪያ ከሰው ወደ ሰው በተበከለ ምግብና ውሃ የሚተላለፍ ሲሆን እንደ መሳሳም ባሉ የቅርብ ንኪኪዎችም ሊተላለፍ ይችላል ።

👉አንዳንድ የህመም ማስታገሻዎች፦ እንደ አስፕሪን ፣አይቡፕሮፌንና ዳይክሎፌናክ ያሉ ነንስቴሮይዳል ፀረ-ብግነት መድሀኒቶች የጨጓራ ለረጅም ጊዜ ከተወሰዱ የጨጓራ አልሰር ያስከትላሉ ።

👉ማጨስ
👉አልኮል መጠጣት
👉የሰውነት ጫና/Stress ፦ከባድ የአካል ጉዳት፣ ከፍተኛ ቃጠሎ፣ የጭንቅላት አደጋ፣አደገኛ ኢንፌክሽን (sepsis ) እና ከባድና የተወሳሰበ ቀዶ ህክምና የጨጓራ አልሰር ሊያመጣ ይችላል ።

#የጨጓራ_አልሰር_ምልክቶችስ?

👉የሆድ መነፋት ስሜት
👉ማስገሳት
👉የምግብ ፍላጎት ማጣት
👉ማቅለሽለሽ
👉ማስመለስ
👉እንብርት እና ከፍ ብሎ ያለው አካባቢ አለመመቸት ስሜት
👉የሰገራ ሬንጅ መምሰል

#ምርመራዎች

👉የ ኤች-ፓይሎሪ ምርመራ
👉የኢንዶስኮፒ ምርመራ ፦ቱቦ መሰል መሳሪያ በአፍ ወደ ሆድ ገብቶ የጨጓራ የውስጥ ግድግዳ በቴሌቪዥን የሚታይበትና ካስፈለገም ናሙና የሚወሰድበት ዘዴ
👉ሌሎች ምርመራዎች ሌላ ነገር አለመሆኑን ለማረጋገጥ ሊታዘዙ ይችላሉ።

#ህክምናው

👉በጣም ለታመሙ ሰዎች ህክምናው በመርፌ ሊሰጣቸው ይችላል
👉የአሲድ መቀነሻ የተለያዩ የሚዋጢ መድሀኒቶች
▫️አሲድ ማምከኛ(neutralize ) የሚታኘኩ መድሀኒቶች
▫️አሲድ ማምከኛ ሽሮፖች
▫️ኤች-ፓይሎሪን ማጥፊያ መድሀኒቶች

#መልካም_ጤና
​​#ሁሉም_ከማህፀን_የሚወጣ_ፈሳሽ #በሽታ_ነው ?
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#ከሴት የመራቢያ አካል የሚወጣው ተፈጥሮአዊ ፈሳሽ ከሰውነት ሆርሞን ጋር በተገናኘ ከፍና ዝቅ በማለት በሚሮሩ ለውጦች የሚመጣ ሲሆን በእርግጥ ከሰው ሰው ቢለያይም በአብዛኛው ጊዜ ከ2-5 ml (ከ 2-5 ሚሊ ሊትር) ወይም ከግማሽ እስከ ሙሉ የሻይ ማንኪያ መጠን ሊፈስና ነጭ ወይም ቀለም የሌለው ውሃ መሳይ፤ ወፈር ያለ ንፍጥነት ያለው እና ሽታ የሌለው ነው፡፡
መጠኑ በተለያየ የወር አበባ ኡደት ወቅት ሊለያይ ቢችልም የሚበዛው፦ በእርግዝና ወቅት፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት በሚጠቀሙ ጊዜያት፤ ኦቩሌሽን (Ovulation) እንዲሁም የወር አበባ ለመምጣት ባለው 7 ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡ የተፈጥረ የማህጸን ፈሳሽ የሽንት ቱቦ እና የማህጸን ኢንፌክሽን ለመከላከል እንዲሁም የመራቢያ አካል መድረቅን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡

👉 #በበሽታው_በምንጠቃ_ጊዜ #የሚያሳዩት_ምልክቶች_ምንድ_ናቸው?

📌 በመራቢያ አካላት አካባቢ ማሳከክ፣ መቅላት፣ ማቃጠል፣ የህመም ስሜት እንዲሁም እብጠት መኖር።
📌 አረፋ ያለው በቀለሙም ቢጫ፣ አረንጓዴ የሚመስል ፈሳሽ መኖር።
📌 ሽታ ያለው ፈሳሽ።
📌 በወር አበባ እንዲሁም በግንኙነት ጊዜ ሽታ መኖር።
📌 ከማህጸን ፈሳሽ ጋር ደም መቀላቀል።
📌 በግንኙነት ጊዜ ህመም መኖር።
📌 የሆድ፤ የማህጸን አካባቢ እንዲሁም የታችኛው ወገብ። ህመም መኖር እንደ ዋና ዋና ምልክቶች ይካተታሉ።

👉 #ለዚህም_በሽታ_ከሚያጋልጡ #ምክንያቶች_መካከል

📌 እድሜ ፡ እድሜ እየጨመረ እና የወር- አበባ መምጣት ሲያቆም የማህጸን ፈሳሽ ሊዛባ፣ ድርቀት እና ማሳከክ ሊኖረ ይችላል፡፡
📌 በወር አባባ ወቅት ለንጽህና መጠበቂያ የሚጠቀሙበትን አቆይቶ መቀየር ማቃጠል፣ ማሳከክ እንዲሁም ማበጥ ከማስከተሉም በተጨማሪ ለኢንፌክሽን መራቢያ ጥሩ መንግድ ይከፍታል።
📌 ሽታ ያለው ሳሙና እና አለርጂ ወይም የማይስማማዎትን ሳሙና መጠቀም ተመሳሳይ ምልክት ያመጣሉ።
📌 ጠባብ እና ላይነን የሆኑ ፓንቶችን መጠቀም ።
📌 ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት እና ከአንድ በላይ የግብረስጋ ግንኙነት ጓደኛ መኖር ይጠቀሱበታል፡፡

👉 #ይህን_በሽታ_ለመከላከል_ምን
#ማድረግ_አለብን?

📌 ሞቅ ባለ ውሀ በየቀኑ መታጠብ።
📌 ሽታ ያላቸውን ሳሙናዎቸ፤ ዋይፐር ወይም ማድረቂያ ሶፍቶችን አለመጠቀም።
📌 የማያጣብቅ እና ጥጥነት ያላቸውን የውስጥ ልብሶች መጠቀም።
📌 ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በሆላ በውሀ መታጠብ እና በደረቅ ፎጣ ማድረቅ።

👉 👉 #ከዚህም በተጨማሪ እኚህን ምልክቶች የሚያመጡት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የሆነው በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ መገለጫ ሰለሆነ ይሄም በሽታ እየባሰ ሲሄድ የማህጸን ኢንፌክሽን ብሎም ማህንነትን ስለሚያመጣ ወደ ሀኪምዎ ሄደው ላለብዎት በሽታ ተገቢውን ምክር ያግኙ።


#መልካም_ ጤና
መኀደረ ጤና pinned «​​#ሁሉም_ከማህፀን_የሚወጣ_ፈሳሽ #በሽታ_ነው ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 #ከሴት የመራቢያ አካል የሚወጣው ተፈጥሮአዊ ፈሳሽ ከሰውነት ሆርሞን ጋር በተገናኘ ከፍና ዝቅ በማለት በሚሮሩ ለውጦች የሚመጣ ሲሆን በእርግጥ ከሰው ሰው ቢለያይም በአብዛኛው ጊዜ ከ2-5 ml (ከ 2-5 ሚሊ ሊትር) ወይም ከግማሽ እስከ ሙሉ የሻይ ማንኪያ መጠን ሊፈስና ነጭ ወይም ቀለም የሌለው ውሃ መሳይ፤ ወፈር ያለ ንፍጥነት…»