ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
🙋‍♂🗣🙋 የጥያቄው ጩኸት ያለው ታዲያ አላህ ቁርአኑን ቃሉን ጠብቆ ጠብቆታል ወይ? ለትውልድስ ያለምንም እንከን መተላለፍ ችሏል ወይ? የሚለው ይሆናል፡፡ መልሱ👇👇👇👇👇👇

#ፈጽሞ #አልጠበቀውም፤ እንደ እስልምና የመረጃ ምንጮች ማለትም ሐዲሳቱ፣ የሲራ መጽሐፍቱ፣ ተፍሲራት እና እራሱ ቁርአን እንደሚናገሩት ለትውልድ ያለምንም ችግር መተላለፍ አልቻለም ይላሉ🤦‍♂🤦‍♀🤦‍♂🤦‍♀🤦‍♂

ይህ ቁርአን በሁለት መንገድ ይጠበቅ እንደ ነበር ይነገርለታል፡-

☝️ ሰዎች እንዲሐፍዙት /በቃላቸው እንዲሸመድዱት/ በማድረግ

✌️ እንዲጻፍ በማድረግ

😭ሆኖም ሁለቱም አስተማማኝ የመጠበቂያ መንገዶች አልነበሩም፡፡😭 በቅደም ተከተል ምሳሌዎችን እንመልከት፦👣

በቃላቸው በመሸምደድ ይደረግ የነበረው ጥበቃ፡-

በቃላቸው በመሸምደድ/በመሐፈዝ/ የሚታወቁ ነቢዩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም #ዝንጉነት ያጠቃችው ስለነበር አስተማማኝ የመጠበቂያ መንገዶች አልነበሩም፡፡ ስለዚህ ቁርአን ለትውልድ ያለምንም እንከን መተላለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ እስኪ ነቢዩንና ከነቢዩ ጋር ሁለት ሱሃባዎችን እንውሰድ፤ እነርሱ ለሌሎቹ መነጽር ይሆኑናል፡-

🤕ነቢዩ ሙሐመድ🤕፡-
#ይረሱ_ነበር፣ ሰይጣንም እርሳቸውን የማስረሳት ብቃት ነበረው፡-

📖 (ሱረቱል አል-አንአም 6 ፡ 68)

"እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፡፡ ሰይጣንም (መከልከልህን) #ቢያስረሳህ ከትውስታ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ፡፡"

📚 (ሱና አቡ ዳውድ 11 ፡ 2166፣ 5 ፡ 2169)

…….. እንዲህ አሉ፡- በሰላ ሰይጣን አንዳች ነገር #እንድረሳ_ካደረገኝ ወንዶቹ የአላህን ስም ከፍ ከፍ አድርጉ ሴቶቹ ደግሞ በእጆቻችሁ አጨብጭቡ አሉ፡፡ ከዛ በኋ ላ የአላህ መልእክተኛ ጸሎት ጀመሩ በዛን ወቅት ምንም አልረሱም ነበር፡፡ 👏👏👏
📚 (ሱና አቡ ዳውድ ሐዲስ 3959)

📚 (ሳሂህ አል-ቡኻሪ 48 ፡ 823 ቅጽ 3)

የአላህ መልእክተኛ አንድ ሰው በመስጊድ ውስጥ ቁርአን ሲቀራ ስሙ አላህ ምህረቱን በእርሱ ላይ ያድርግ፡፡ #እኔ_የረሳሁትን በዚህ እና በዚህ ሱራ ውስጥ ቁጥር ይህንን እና ይህንን #አስታወሰኝ አሉ፡፡ አይሻ የዘገበችው ሐዲስ ነው፡፡

📚 (ሱና አቡ ዳውድ 3 ፡ 906)

ከአላህ መልእክተኛ ጋር አብረን ሰግደናል፣ ያኔ በሰላት ወቅት ቁርአን ሲቀሩ የተወሰኑ የቁርአኑን ክፍሎች አውጥተዋቸው #ሳይቀሯቸው_ቀሩ፡፡ አንድ ሰውም ቀርቦ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ይህንንና ይህንን የቁርአኑን ክፍሎች ሳይቀሯቸው ቀርተዋል አላቸው፡፡ እርሳቸውም #ለምን_አላስታወስከኝም? አሉት፤ እርሱም #በሌላ_ተተክቶ_ይሆናል ብዬ አስቤ ነው ብሎ ለማለቱ ምስክር ነኝ አለ፡፡ አል- ሚስዋር ኢብን ያዚድ አል-ማሊክ የተናገረው ሐዲስ ነው፡፡

📚 (ሱና አቡ ዳውድ 3 ፡ 1015)

📚 (ሳሂህ ሙስሊም 4 ፡ 1168 ምዕ 63)

…..እኔ ሰው ነኝ እናም እናንተ እንደምትረሱት #እኔም_እረሳለሁ፤ ስለዚህ በረሳሁ ጊዜ እናንተ #አስታውሱኝ አሉ፡፡ አብዱላ ኢብን መስኡድ የዘገበው ነው፡፡
👀ከሀፊዘሎች መካከል ሁለት ሰዎችን(👨‍👦) እንመልከት ዛይድ ቢን ሳቢትና አቡ ሙሳ አሻሪ፡-👀

እነዚህም አስተማማኝ መጠበቂያዎች አልነበሩም፡፡ እስኪ አቡ ሙሳ የተናገረውን እንመልከት፡-

📚 (ሳሂህ ሙስሊም 5 ፡ 2282-2286)

የነቢዩ ሙሐመድ ተከታይ የሆነው አቡ ሙሳ አሻሪ እንደ ዘገበው፣ በአንቀጾቹ ብዛትና በቅደም ተከተሉ ከአል-ተውባህ ጋር የሚመሳሰል ሱራ እንቀራ ነበር፡፡ ነገር ግን #እረስቸዋለሁ፤ አሁን ከእርሱ #የማስታውሰው #ይህንን #አንቀጽ #ብቻ #ነው፡፡🤷‍♀🤷‍♂🤷‍♀…….. ሌላው እንቀራው የነበረው ሱራ ደግሞ ከሙሳቢሃት ሱራዎች እንደ አንዱ የሚሆን አንቀጾች ያለውና የሚመሳሰል ነው፡፡ ነገር ግን #እረስቸዋለሁ፤ ከዛ አሁን #የማስታውሰው #ይህንን #አንቀጽ #ብቻ #ነው፡፡…………. 🤷‍♂🤷‍♀🤷‍♂

👵ዛይድ ቢን ሳቢት👵፡-
📚 (ሳሂህ አል-ቡኻሪ 60 ፡ 201 ቅጽ 6)

……. ከማንኛውም ሰው ማግኘት ያልቻልኳቸውን የሱራ አል-ተውባህ ሁለት ቁጥሮችን ከኹዜይማ አገኘሁ፤ እነርሱም ቁጥር 128-129 ነበሩ፡፡
🗝ስለዚህ🔑
አላህ ቃል በገባው መሰረት ቁርአንን በፍፁም ሊጠብቀው አለመቻሉ ገሐድ የወጣ እውነት ነው፡፡ በዚህም ቁርአን ፈጽሞ እደግመዋለሁ ፈጽሞ መለኮታዊ መጽሐፍ ሊሆንበት የሚችልበት እድል እንኳን የለውም፡፡
The corrupted book of Islam part 3

አሁን ቀጥለን የምናየው ከ ታሪክ አንጻር የ እስልምና መጽሐፎች reliable አለመሆናቸውን ነው። ከዛ መልሰን ብዙ የ ጠፉ አንቀጾችንም የምናይ ይሆናል። ( Historical background of the Muslim manuscripts)

እንግዲህ ሙስሊሞች የሚሉን ቁርአን መውረድ የጀመረው በረመዳን ወር ' lailat al Qadr' በሚባል ምሽት እንደ ሆነና ከዚያም በሃላ ምንም አይነት እንቅፋት ያልተገኘበት፤ምንም አይነት የሰው influence ያልገባበት እንደሆነ ነው።  ስለዚህ ነገር ግን ታሪክ ምን ይላል??? ስለ ቁርአን ብዙ ያጠኑ " secular Muslim scholars" የ መዘገቡትን የምናይ ይሆናል።

የእነኚ scholars የጥናት ውጤት የሚያሳየን ከ 750 AD ( ነብዩ ሙሐመድ ከሞተ 120 አመት  ) በፊት የ እስልምና መጽሐፍ የተባለ ምንም የተጻፈ ነገር እንደሌለ እና ሁሉም አሁን የምናነባቸው ሐዲዞች ነብዩ ከሞቱ ከ 200 እሥከ 300 መቶ አመታት በሓላ የተጻፉ እንደ ሆነ ነው። (Wansbrough 1978; 58-59) ከዚህ ከ 750AD  በፊት ምንም ስለ እስልምና ባህል or ህግጋት፣ ሱና ጋር የተያያዘ ታሪክ ውስጥ እንደሌለ ይታወቃል። አብዛኞቹ የተጻፉት 800 AD ናቸው፤ ይህ ደግሞ ልክ አንድ ሰው አርጅቶ ደስ የሚሉ የ ወጣትነት ዘመኑን ሲያስብ ሁሉም ቆንጆ አድርጎ እንደሚያስብና ሲያወራም ሁሉን አስውቦ colorful አድር ጎ እንደሚናገር ሰው ነው።  ይህ ደግሞ ታሪኩን ለመቀበል አስቸጋሪ ያደርገዋል።
ማንኛውም ታሪክ ሲጻፍ primary source እና secondary source አለው። የእስልምና primary source የሆኑ መጽሃፎች ሁሉም ግን ሙሃመድ ከሞተ 150-300 አመት በሃላ ናቸው ።እጅግ በጣም ሩቅ ( Nevo 1994: 108; Wansbrough 1978:119; Crone 1987:204)

Muslim Traditions የምንላቸው ( ሲራዎች, ሀዲዞች even ተፍሲሮች)  የተሰበሰቡትና የተጻፉት ሁሉ  8th to 10th century ውስጥ ናቸው። ( ነብዩ supposedly የሞተው በ 7th century ( 632 AD ) ነው። እስኪ በ ቅደም ተከተላቸው እንመልከት

1.sira(  ሱራ) ፦ ስለ ነብዩ ህይወት ታሪክ የሚተነትን ነው። የመጀመሪያ እና ሚታመን ሲራ የ እብን እሻቅ ( sirat rasul allah by Ibn Ishaq) ነው።  እብን እሻቅ የሞተው በ 765AD ነው። ይሁን እንጂ ይሄ ትንታዊ መጽሃፍ ኡሁን የለም። ስለዚ አሁን የሚነበበው Ibn Hisham የ ጻፈው ሲራ ነው። እብን ሒሻም ግን ሲራውን ኮፒ ያረገው አብዛኛው ከ inn Ishaq እንደ ሆነ ተናግሯል። inb Hisham የሞተው  በ 833 ነበር። (Crone 1980:6)

2. ሐዲዞች፦ ነብዩ ስለ ተናገራቸው እና ስለ ስራው፣ ሁሉም ሙስሊም ሊከተለው የሚገባው ነገሮች የሚተነትን ነው። ከነኚህም ውስጥ በጣም ተአማኝነት አለው የሚባለው Sahih Al Bukhari  እንኲን የተጻፈው እስከ 850-870 AD ( 200 years after death of muhammad) የተጻፉ ናቸው።

3፦ Ta'rikh-  የነብዩ ታሪክ ( and chronologies). ከነኚ ውስጥ Al Tabari በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው። Al Tabari  የሞትው በ 923 AD ነው

4. TAFSIR- እነኚ COMMENTARY ናቸው።

መጠየቅ ያለብን ነገር እነኚ ሁሉ የተጻፉት ከ 100 -300 አመት በሃላ ከሆነ፣ ታሪኩን ከየት አግኝተው ነው የጻፉት?? Humphrey ( secular Muslim scholar) (1991; 69)  እና ሌሎችም ያገኙት ውጤት እነኚ traditions ተአማኒነት የጎደላቸው እንደ ሆነ ነው።

 ወደ ቁርአን ተመልሰን ስንመጣ፣ ሁስማን ከእሱ በፊት የ ነበሩት የቁርአን አንቀጾችን ግጭት ስለተገኘባቸው ሁሉንም ሰብስቦ እንዳቃጠለ ከዛም በ 5 copy አጽፎ እንደ በተነ;  sahih al bukhari vol 6 bk 61 number 509 ላይ ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ እነኚ የ ኦሪጅናል ኮፒዎች የሉም። (schimmel 1984: 4)  ( Jam' al Quran 1989 pp 140- 154)  የ እስልምና መጽሐፎች የሚሉንም ሁሉም ከ 646-650 AD  እንደጠፉ ነው።

 ከዚህ ማምለጫ ብለው ሙስሊሞች ብዙ ማኑስክሪብቶችን ኦሪጅናል ነው ብሎ እውቀቱ የሌለውን ሊያታልሉ ይሞክራሉ። እነኚን MANUSCRIPTS ደግሞ ቀጣይ የምናይ ይሆናል።
  ታድያ ይሄ ጉዱ ተወርቶለት የማያልቅ መጽሃፍ ነው በ አላህ የተጠበቀው??  ይሄ በ ሰው እጅ እንኲን የተቃጠለው መጽሀፍ 'ምንም በ ሰው እጅ ያልተበረዘ , perfect...ማለት ያሳፍራል!!"

ይቀጥላል.....
በ ሚቀጥለው part 4 እስክንገናኝ ድረስ በመሃል እስኪ በዚህ ዘና እንበል

Sahih Al Bukhari volume 7 book 62 number 006
" The prophet use to go round have sexual intercourse with ALL HIS WIVES IN ONE NIGHT and he HAD NINE (9) WIVES!!!
( ነብዩ በ አንድ ለሊት እየዞረ ከ ሁሉም ሚስቶቹ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ያደርግ ነበር። እነሱም በ ቁጥር 9 ነበሩ።)") :-D
እኔ የምለው ፤መቼ ነው የሚተኙት ነብዩ???
ሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድ፡፡
ሠላም ለሁላችሁ፦
አብዛኞቹ መናፍቃዌ ቤተ እምነቶችና እስልምና በጌታችንና በመድሀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት እንዲሁም ቤዛዊ ሞት እና ትንሳኤ ዙርያ መርዛማ ትምህርቶችና አመለካከቶች እንደሚያራምዱ ገሀድ የወጣ ሀቅ ነው ከነዚህም መካከል የይኾዋ ምስክሮች ፣ አድቬንቲስቶች ፣ ሰርጎ ገቡ የእምነት እንቅስቃሴ ፣ እና እስልምናን ለዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንደሚታወቀው የጌታችን ቤዛዊ ሞትና ትንሳኤ ከአበይት የክርስትና አስተምህሮዎች መካከል የሚቀመጥ አውራ የእምነታችን መሠረት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሀዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሳኤ እውንነት ሲሞግት የክርስቶስን ከሞት መነሳት ከካድን እምነታችን ዋጋ ቢስ እንደሆነ ያስገነዘበን፡፡ " ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:14)
እውነትም ክርስቶስ ካልሞተና ካልተነሳ እምነታችን ከንቱ ነው፡፡ ክርስትና ብሎ እምነትም ባልናረና ተስፋ ቢስ ተላላ ሆነን በቀረን ነበር፡፡ ነገር ግን በምህረቱ ባለጠጋው አምላካችን የቸረን ታላቅ ስጦታን የተቀበልንበት ፣ የአለምን ጥበብ ከንቱ ያደረገበት ፣ ሀይሉንና የፀጋውን ባለጠግነት ያሳየበት የጌታችን ሞትና ትንሳኤ የአለምን ታሪክ የቀየረ እውነተኛ ክስተት ነው፡፡ ለዚህ ነው ጠላት ዲያብሎስ የጌታችን ሞትና ትንሳኤ ጉዳይ የእግር እሳት የሚኾንበት፡፡ እንደውም ባለንጀራዯ ቤኪ የሚጠቅሳት አባባል ትዝ አለችኝ "ጣሊያን ስለ አድዋ ሠይጣን ስለ ቀራንዮ መስማት አይፈልግም"፡፡ እውነቱን ነው ወዳጄ!! እንዴት ችሎ ይስማ!! ጌታችን በስጋ የተገለጠው ስራውን ሊያፈርስም አይደል? በርግጥም አንኮታኩቶ ሰብሮታል!! ታዲያ ስራው መፍረሱን ያየው አጅሬ ዲያብሎስ መቼ አርፎ ሊቀመጥ፤ ገና ከትንሳኤው እለት ጀምሮ ነበር የሀሰት ዲስኩሩን መንዛት የጀመረው፡፡ "ደቀመዛሙርቱ አካሉን ሠርቀውት ነው" አይነት ከንቱ ተረት የጀመረው ያኔ በእለተ ትንሳኤው ነበር፡፡ ነገር ግን ጌታችን በእውነትም ተነስቶአል፡፡ ከቅዱሳት መፅሀፍት እንደተማርነው የጌታችን ሞትና ትንሳኤ ለሰው ልጆች ሁሉ በተለይም ላመንን ለኛ ፋይዳው እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ፋይዳውን በሌላ ዝግጅት እመለስበታለሁ፡፡ ነገር ግን በዚህ ለሰው ልጆች የነፍስ እንቆቅልሽ ጥያቄ መልስ በሰጠው መሠረተ እምነታችን ላይ እስልምናና ሙሀመድ ይኼነው የማይባል ጥቃት አልሞተም አልተሠቀለም በሚል ጥቂት ቃላት ሰንዝሯል በዚህም የሀሰት ምስክርነት ቢልዮኖች ከነነፍሳቸው እንቆቅልሽ ያለመልስ ታስረው ተቀምጠዋል፡፡ በዚች አጭር ሙግቴ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት እሞክራለሁ አንድም የሙሀመድን ሀሰተኛ ምስክርነት አንድም የእስልምናን የጨለማ መንገድነት፡፡
ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ እርገቱ ለሀዋሪያት ደቀመዛሙርቱ ከነገራቸው ነገሮች መካከል እስከምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቹ እንደሚሆኑ ነበር ያም ማለት ከሞትና ከትንሳኤው በኋላ ማለት ነው፡፡ ይኽም ማለት የምስክርነታቸው ቃል የሚሆነው ያ አስቀድሞ በነብያት የተነገረለት የእግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ በስጋ እንደመጣ ፣ በሰዎች መካከል እንዳደረ ፣ የእግዚአብሔርን መንግስ እንዳስተማረ ፣ ጊዜው ሲደርስ በቅዱሳት መፅሀፍት እንደተፃፈው መከራን እንደተቀበለ የአለምን ሀጢያት ያስወግድ ዘንድ በመስቀል እንደሞተ እነደተቀበረና በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ ፣ እነዳረገና በአባቱ ቀኝ በክብር እንደተቀመጠ ፣ ዳግም እንደሚመጣና በህያዋንና በሙታን መካከል እንደሚፈርድ ፣ ለዘላለምም እንደሚገዛ ያስተማራቸውንና በአይን እማኝነት የተመለከቱትን እንዲመሠክሩ ነበር፡፡ ጠቅላላውን የአዲስ ኪዳን ትረካ ተከትለን ስንነጉድ ከላይ የዘረዘኳቸው የጌታችንን ገድላትና ማንነት እንዲሁም በሞቱና በትንሳኤው ተመርቆ የተከፈተውን በእምነት የሚገኘውን የእግዚአብሄር ፀጋ በሙላት እናገኛለን፡፡ በነበረኝ ዳሰሳ በሀዋሪያት ስራ መፅሀፍ የሀዋሪያቱ ምስክርነት የነገረ ሞቱና ትንሳኤው ጉዳይ ሀያ ሶስት ጊዜ ተጠቀሷል፡፡ የጠቅላላውን አዲስ ኪዳን ምስክርነት ብንዳስስ የመፅሀፍቱ ዋነኛ ትረካ ነገረ ሞትና ትንሳኤው መኾኑን ከሀዋሪያት ስራ ሳንዘል ማስተዋል እንችላለን፡፡ ታማኝ ምስክር ይሏል ይኼ ነው!! ታዲያ የታማኝ ምስክሮቹን ምስክርነት ከሰማንና ካመንን አምስት ክፍለ ዘመናት በኋላ ራሱን ነብይ ያደረገ የዲያቢሎስን የቀደመች ሰላላ ዲስኩር ተቀብሎ የተነሳው ሙሀመድ አልሰቀሉትም አልገደሉትም አሏህ ሸውዶ በርሱ ፈንታ ሌላ ሰው እንዲገድሉ አጭበርብሮ እርሱን አስመልጦታል ብሎ እርፍ አለ፡፡ ሀሰተኛ ምስክር ይሏል ይኼ ነው!! ይኼን የሙሀመድ ምስክርነት ሀሰት ከሚያደርጉ ነጥቦች መካከል 1. ማን ይነገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንደሚሉት አበው የአይን እማኞቹን ምስክርነት ሽምጥጥ አድርጎ የካደ ያውም ከአምስት መቶ አመታት በኋላ የተሰጠ ምስክርነት መኾኑ፡፡ 2. አስቀድሞ በቅዱሳት ነብያት ሲነገር የነበረን የፀና የተመነ ምስክርነትን የካደ መኾኑ፡፡ 3. የታሪክና የስነቁፋሮ ማስረጃዎችን የካደ ምስክርነት መኾን፡፡ 4. የእውነተኛውን አምላክ ባህሪ የላገናዘበ መኾኑ፡፡ ማለትም ኢየሱስን አስመስሎ ሸውዶ ሌላ ሰው መስገደል እና ኢየሱስን ማስመለጥ የእውነተኛ አምላክ ባህሪን አይወክልም የሁሉን ቻይነትና የፍተሀዊነት ጥያቄ ያጭራል፡፡ በነዚህና ሌሎች ልንዘረዝራቸው በምንችላቸው መክንያቶች ሙሀመድ በቁርአን ሱራ 4:157-158 ለይ የተጠቀሰው የአልገደሉትም አልሰቀሉት ምስክርነት የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ አይነት የሀሰት ምስክርነት ነው ስንል አንቀበለውም፡፡ በሌላ አማረኛ ሙሀመድ ሀሰተኛ ነብይ ነው ብለን ደረታችንን ነፍተን እንድንናገር የሚያደርገንን ምክንያት ራሱ ሙሄ እንዳቀበለን እንቆጥረዋለን፡፡ ቅድሱ የአምላካችን ቃል በሰጠን መርምሮ የመቀበል እና ያለመቀበል መብት ተጠቅመን ጉዳዩን ስንመረምር ፈጣሪ አምላክ ለሰው ልጆች የነፍስ ጥያቄ ምላሽ አድርጎ የሰጠውን በብዙ ታማኝ ምስክሮች የታጀበ ድንቅ ስጦታ በአንዲት ተራ ያውም አወዛጋቢ በኾነች አንቀፅ ሽምጥጥ አድርጎ የካደ አባይ እንጂ ነብይ ሊኾን አይችልም ይኼን አባይ ምስክር የሚከተል ሀሉ ደግሞ ምስኪንን ተላላ እስካሁንም ከነነፍሱ እንቆቅልሽ የጨለማ ጉዞውንን የተያያዘ የሲኦል መንገደኛ ነው ፡፡ እውነቱ አንድ ብቻ ነው እርሱም የወንጌል እውነት ነው ወንጌሉም:- " ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 1:3-4) ልጁ ያለው ህይወት አለው አሜን፡፡
1
ሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድ ክፍል ሁለት፡፡

ከላይ ለመዳስ እንደሞከርኩት በጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ ሙሀመድና እስልምና ያላቸውን ኢ-ተአማኒ የሀሰት ምስክርነት በማንሳት የሙሀመድ ሀሰተኛ ምስክርነት የእስልምናን የጨለማ መንገድነት በወፍ በረር ለመቃኘት ሞክሬ ነበር በዚህ በቀጣዩ ዳሰሳዬ ደግሞ ከላይ ለኮፍ አድርጌ ያለፍኳቸውን የሙግት ሚስማሮች አጥልቄ መቸንከር እጀምራለሁ፡፡ በቀደመው ዳሰሳዬ የምስክርነቱን ሀሰተኝነት የሚያሳብቁ አራት ነጥቦችን አንስቼ ነበር ከአራቱ ነጥቦች መካከል ለዛሬ ፍጆታ ያህል ከአራተኛው ነጥቤ መነሳት እፈልጋለሁ፡፡ አራተኛው ነጥቤ የተመሠረተው ኢስላም በጌታችን ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ የተነሸዋረረ እይታ እንዲኖረው ካደረገው የሙሀመድ መገለጥ ማለትም በቁርአኑ አንቀፅ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ አንቀፁ የሚገኘው በሱረቱል አል ኒሳ (የሴቶች ምዕራፍ) ቁጥር 157-159 ላይ የሚገኝ ሲኾን ፦
"157 እኛ የአላህን መልክተኛ የመሬምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸው (ረገምናቸው)፤ አልገደሉትም፤ አልሰቀሉትምም ግን ለነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ እነዚያም በርሱ ነገር የተለያዩት፣ ከርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፤ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፤ በእርግጥም አልገደሉትም። 158 ይልቁኑስ፣ አላህ ወደርሱ አነሳው፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው። 159 ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በርሱ (በዒሳ) በእርግጥ የሚያምን እንጂ (አንድም) የለም፤ በትንሣኤም ቀን በነሱ ላይ መስካሪ ይሆናል"።
በዚህ አንቀፅ ላይ ቆመን በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት👆 ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ በዚህ አንቀፅ የተገለፀው አላህ በርግጥ የአለማቱ ጌታና ፈጣሪ ሀሉን ቻዩ አምላክ ነውን?? ይሄን እንድንጠይቅ የተገደድነው በነዚህ ጥቂት ቁጥሮች ብቻ በርካታ አወዛጋቢ ተግባራትን ስለመፈፀሙ ስለተዘገበ ነው፡፡ 👆 ራሱ እንደገደሉት እንዲመስላቸው በሌላ ሰው መስሎ ካምታታቸው በኋላ መራገሙ ምን ይባላል🤔 ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል ካልሆነ፡፡ ✌️ ኢየሱስን ከገዳዮቹ ለማዳን ሌላ ሰው እንዲመስላቸው አድርጎ ንፁህ ሰው ያለጥፋቱ ያውም በሮማውያን እጅግ አሰቃቂ የወንጀለኛ ግርፋት ስርዐት አሰቃይቶ በመስቀል ማስገደል ምን አይነት ፍትሀዊነት ነው🤔 3⃣ እንደሚታወቀው የክርስትና እምነት ዋልታና ማገር ፣ ድሩም ማጉም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ሞትና ትንሳኤ ነው፡፡ እምነታችንም ተስፋችንም የተገነባበት ለዚህም ሀዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር " ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:14) ታዲያ በዚሁ የአላህ ኢየሱስን በሌላ አስመሰሎ ቀይሮ ማታለል የተታለሉ ፣ በሞቱና በትንሳኤው እምነታቸውንም ተስፋቸውንም ያደረጉ በቢልየን የሚቆጠሩ ሰዎች እጣፋንታ ምንድን ነው🤔 🤔🤔 ያታለላቸው ራሱ አላህ!!፡፡ 4⃣ እንደሚታወቀው በጌታችን ሞትና ትንሳኤ ተመርቆ የተከፈተው በፀጋ የሆነ በእምነት የሚገኘው የእግዚአብሔር ፅድቅ መሰበክ ከጀመረ 2000 ዘመናት ተቆጥረዋል በነዚህ ሁሉ አመታት በተለይም በመጀመሪያዎቹ 300 አመታት በርካቶች የዚህ የምስራች ወንጌል አማኞች በመሆናቸው ብቻ ንብረታቸውን ትተው ተሰደዋል ፣ ተገርፈዋል አካለ ጎደሎ ሆነዋል ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው ግን በአላህ ማታለል ምክንያት መሲሁ ኢየሱስ ቤዛዊ ሞት ሞቷል በሚል መታለል ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እነዚህን ሁሉ ንፁሀን ደም በማን እጅ ነው?? በገዳዮቻቸው ወይስ ኢየሱስን አስመስሎ በጭበረበራቸው አላህ እጅ 🤔🤔🤔
5⃣ በቁጥር 59 ላይ እንደተጠቀሰው በፍርድ ቀን ራሱ ኢየሱስ በሱ በማያምኑት ማለትም ሟቷል ተሰቅሏል በሚሉት ሰዎች ላይ እንደሚመሰክርባቸው ተዘግቧል፡፡ ይሄ ሁሉ በአላህ ማታለል ምክንያት ነው፡፡ አሁንም በራሱ ማጭበርበር ያመኑትን የመጨረሻ ዘመን ፍርድ ሰለባ ማድረግ ምን ይሉት ፍትሀዊነት ይሆን 🤔🤔🤔፡፡
ውድ አንባቢያን በዚህ አንቀፅ የተገለፀው አላህ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሁሉን አዋቂ የሆነው አምላክ እነዚህን አወዛጋቢ ተግባራት የሚፈፅም ይመስላችኋል??? በራሱ የተምታታና አወዛጋቢ የሆነ ይህ በሙሀመድ የተሰጠ ምስክርነት ሀሰተኛ ምስክርነት መሆኑን ለመገንዘብ የሚያዳግት አይመስለኝም፡፡ ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት አይጥምም ይባል የለ🤓፡፡ በዚህ አጋጣሚ ቁርአን እንዲህ ባለ የተምታታ የአምላክ ባህሪ አስተምህምሮ መያዙ መለኮታዊ መፅሀፍ ለመሆን በቁ አለመሆኑን ማስተዋል እንችላለን፡፡ በተጨማሪም እንደ አላህ ያለ አጭበርባሪ እንደሌለ ግልጥ አድርጎ የነገረን ራሱ ቁርአኑ ነው፡፡ እነዚህን የቁርአን አንቀፆች ተመልከቱ፦ 👇👇👇👇👇👇👇👇
But they (the Jews) were deceptive, and Allah was deceptive, for Allah is the best of deceivers (Wamakaroowamakara Allahu waAllahu khayru al-makireena)! S. 3:54; cf. 8:30

Are they then secure from Allah's deception (makra Allahi)? None deemeth himself secure from Allah's deception (makra Allahi) save folk that perish. S. 7:99

እነዚህን አንቀፆች በአማረኛ የላቀረብኩት የአማረኛው ትርጉም በትክክለኛው የበኩር ቋንቋ አረብኛ ትርጉሙ ስላልተተረጎመ ነው፡፡ ተርጓሚዎቹም እንደ አላህ አጭበርባሪ ናቸው፡፡
ይቀጥላል ---------
👳ሙስሊም ብሆን ኖሮ👳

ሙስሊም ብሆን ኖሮ በቁርዓን 5፡51 ላይ በተጻፈው ጥቅስ እደነቅ ነበር ‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ አይሁዶችንና ክርስትያኖችን ረዳቶች (ጓደኞች፣ ጠባቂዎች አጋዦች) አድርጋችሁ አትያዙ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው ከናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም›፡፡

ይህ አረፍተ ነገር ትክክል አለመሆኑን የሚያረጋግጡ ምሳሌዎች አሉ፡፡ 🇦🇫በአፍጋኒስታን🇦🇫 ውስጥ የነበረውን የዲክታተሮች አገዛዝ ለማክተም፣ 🇮🇶በኢራቅ🇮🇶 ውስጥ ከነበረው አምባገነን አገዛዝ ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት🗽፣ እና የኩርድ ሙስሊሞች ባገኙት ነፃነት እጅግ በጣም ደስ እንዲላቸው ለማድረግ #የረዱት_ሙስሊም_ያልሆኑ_አገሮች_ናቸው፡፡

ባለፈው ምዕተ ዓመት መጨረሻ አካባቢ 👉👉👉ሙስሊም ያልሆኑ አገሮች ሙስሊም ካልሆኑ አገሮች ጋር ተዋግተው #ሙስሊሞችን_ነፃ_አውጥተዋል፡፡🏳🏳🏳 በዚያን ጊዜ ከዚህ በላይ በሱራ ከተጠቀሰው ጥቅስ በተፃራሪ መንገድ የአይሁድ ዶክተሮች የኮሶቮ ሙስሊሞችን 💉አክመዋል፡፡🌡

#እኔ_ሙስሊም_ብሆን_ኖሮ ክርስትያኖችንና አይሁዶችን በመጥላት ስለሚሰብከው ኢማም ሁለት(🤔🤔)ጊዜ አስብ ነበር፡፡ አንድም ጊዜ ያላዩአቸውን እና ያላገኙአቸውን አይሁዶችንና ክርስትያኖችን በመጥላት ብዙ ኢማሞች ይሰብካሉና፡፡
👍1
ይህ ሙስሊሞች የሚያሳዩት እና የሚሰብኩት ሁኔታ አንድ ሰው እጅግ በጣም ከፍ ያለ ትምክህት ነው በማለት ሊገልጠው የሚችለው ነገር ነው፡፡ ወደ ምዕራብ የሚመጡ ብዙ ሙስሊሞች በሚያጋጥማቸው ወዳጃዊ አቀባበል ይደነቃሉ፡፡ የመሐመድን ጠላቶች የእናንተ ጠላቶች አድርጋችሁ ለምን ትቆጥራላችሁ? በሚገርም መልኩ ብዙ ሙስሊሞች ሂንዱዎችንም ወዳጃዊዎችና ሞቅ ያለ አቀባበል ያላቸው ሆነው ያገኙዋቸዋል፡፡ በሂንዱዎች ፍቅርና ደግነትም ይገረማሉ፡፡ #እኔ_ሙስሊም_ብሆን_ኖሮ በእንደዚህ ዓይነት ነገር እገረምና ይህ - ለምን ሆነ? ብዬ እጠይቅ ነበር፡፡🙋‍♂🙋
👳ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- ቁርዓንን አንብቤ ምን እንደሚል ለመረዳት እፈልግ ነበር፡፡ ብዙ ሙስሊሞች በአረብኛ ይሸመድዱታል ነገር ግን ትርጉሙ ምን እንደሚል አይረዱትም፡፡ አንድ ሰው ካልተረዳው የአረብኛ ጥቅሙ ምንድነው ብዙ ሙስሊሞች ቁርዓን ምን እንደሚል በፍፁም 😇አያውቁም😇፡፡ ስለዚህም እነሱ እራሳቸው ሊጠይቁት የሚችሉትን ብዙ ነገሮች እንደሚል ሲያዩ 😟ይደነግጣሉ😧፡፡ #እኔ_ሙስሊም_ብሆን_ኖሮ ቁርዓን ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንደሚል ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡

ለምንድነው አንድ ሰው በአረብኛ መፀለይ ያለበት አላህ ሁሉን አዋቂ ከሆነ ከአረብኛ ሌላ ሌሎች ቋንቋዎችን አያውቅም ማለት ነውን⁉️⁉️

👳ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- ሙስሊም ያልሆነው ዓለም መሐመድ ከህፃን 👯‍♂ 👯ሴት ልጅ ጋር ግብረስጋ ግንኙነት🤰🤰 አድራጊ ወይም (ፔዶፋይል) ነው በማለት ለምን እንደሚያስብ ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡

ሳሂህ ቡካሪ እንደተረከው ‹ነቢዩ አይሻን ያገባት የስድስት6⃣ ዓመት ልጅ ሆና ሲሆን ጋብቻው የተፈፀመው ግን የዘጠኝ9⃣ ዓመት ልጅ ስትሆን ነው ከዚያም ከእሱ ጋር ለዘጠኝ ዓመታት አብራው ኖራለች (ማለትም እሱ እስኪሞት ድረስ)፡፡ 📗Sahih Bukhari Volume 7, Book 62, Number 64፡፡
👳ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ እስከፈለገው ቁጥር ድረስ ሚስት👩‍👩‍👧‍👦👩‍👩‍👧👨‍👩‍👧‍👧👩‍👧‍👧👩‍👧‍👦 ሲኖረው እኔ በአራት✌️ ✌️ሚስቶች መወሰኔ ለምን እንደሆነ ለማወቅ እፈልግ ነበር፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተጻፉት የቁርአን ምዕራፎች የመጀመሪያው ሱራ የሚመለከተው መሐመድን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተራ ሙስሊሞችን ነው፡፡

‹አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ እነዚያን መህሮቻቸውን የሰጠሃቸውን #ሚስቶችህን አላህ ባንተ ላይ ከመለሰልህም እነዚያን እጅህ የጨበጠቻቸውን ምርኮኞች እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን 👆የአጎትህን ሴቶች ልጆች ✌️የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች 👉የየሹማህንም ሴቶች ልጆች 🖖የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች (ማግባትን) ለአንተ ፈቅደንልሃል የአመነችንም ሴት ነፍሷን (ራሷን) ለነቢዩ ብትሰጥ ነቢዩ ሊያገባት የፈለገ እንደ ኾነ ከምእምናን ሌላ ላንተ ብቻ የጠራች ስትኾን (ፈቀድንልህ) በነርሱ (በምእምናን ) ላይ በሚስቶቻቸውና እጆቻቸው በጨበጧቸው (ባሮች ነገር) ግዴታ ያደረግንባቸውን በእርግጥ ዐውቀናል ባንተ ላይ ችግር እንዳይኖር (ያለፉትን ፈቀድንልህ) አላህም መሐሪ አዛኝ ነው፡፡› 33:50፡፡

‹በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ) ከሴቶች ለናንተ የተዋበላችሁን ሁለት - ሁለት ✌️ሦስት - ሦስትም 3⃣ አራት - አራትም 4⃣ አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረትን ያዙ ይህ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው› 4:3፡፡
👳ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- ቁርዓን በእውነት ያልተፈፀሙ 🗣ልብ ወለድ🗣 ተረቶችን ለምሳሌም ያህል በዋሻ ውስጥ ለዘመናት (ለሦስት መቶ 3⃣0⃣0⃣ ዓመታት) እንደኖሩ፡፡ እና በሌላው ዓለም እንደ ተረት የሚቆጠሩት ሌሎችም ታሪኮች ለምን እንደተጨመሩበት አስብ እና በትክክል የእግዚአብሔርን ቃል ስለመያዙ እጠይቅ ነበር፡፡ ለምሳሌም ያህል፡-

‹ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና፡- ጌታችን ሆይ ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን ለኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን ባሉ ጊዜ (አስታውስ)› 18.10፡፡ ‹በዋሻቸውም ውስጥ ሦስት መቶ ዓመታትን ቆዩ ዘጠኝንም ጨመሩ› 18.25፡፡
ሙስሊም አልሆንም እንጂ "ሙስሊም ብሆን ኖሮ" ግን ይቀጥላል....

ምንጭ፦ http://www.answeringislam.org/amargna/quran/if_muslim.html
በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ሁሉ ሠላም ይብዛላቹህ፡፡

ሙስሊም ብሆን ኖሮ እንዲህ ይቀጥላል...

👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ #የተቹትን#የተቃወሙትንና ስለ እሱም አሽሙር ያለበትን ግጥም የጻፉትን ሰዎች #ለምን_ይቅር_እንዳላለ እጠይቅ ነበር፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እነሱ ለምን የሞት ቅጣት እንደተቀበሉ እጠይቅ ነበር፡፡ የአሽሙር ዓይነት አነጋገር የሞት ቅጣት ይገባው ነበርን⁉️

#መሐመድ_አጎቱን አቡ ላሃብን፣ መልእክቱን ስላልተቀበለው #ረግሞታል፡፡ እርግማኑም በቁርዓን ውስጥ 111:1-5 ላይ ተጽፎ ይገኛል "የአቡ ለሃብ ሁለት እጆች ከሰሩ (ጠፉ እርሱ) ከሰረም፡፡ ከርሱ ገንዘቡና ያም ያፈራው ሁሉ ምንም አልጠቀመውም፡፡ የመንቀልቀል ባለቤት የኾነችን እሳት በእርግጥ ይገባል፡፡ ሚስቱም (ትገባለች) እንጨት ተሸካሚ ስትኾን፣ በአንገትዋ ላይ ከጭረት የኾነ ገመድ ያለባት ስትኾን፡፡"

👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- ሰዎች መሐመድን #እንደ #ነቢይ #ባለመቀበላቸው ብቻ፣ ሙስሊሞች ለምን እንደሚገድሏቸው እጠይቅ ነበር 2፡191 "ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት በተከበረው መስጊድም ዘንድ በርሱ ውስጥ እስከሚገድሉዋቸው ድረስ አትጋደሉዋቸው ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው"፡፡
👍1
👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- ኢየሱስ እንደ አንድ ነቢይ በባህርዩ፣ በስነ ምግባሩ፣ በአስተምህሮው ከመሐመድ #በጣም #በላቀ #መልኩ ለምን ጥሩ እንደነበረ በማሰብ እጠይቅ ነበር፡፡ "መላእክት ያሉትን (አስታውስ)፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ (ልጅ) ያበስርሻል" 3.45፡፡

"እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ #ጠላቶቻችሁን_ውደዱ#የሚረግሙአችሁንም_መርቁ#ለሚጠሉአችሁም_መልካም_አድርጉ#ስለሚያሳድዱአችሁም_ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።› ማቴዎስ 5.44-45፡፡

👉👉መሐመድ አለ፡🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♂🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀

"ለነሱም ከማንኛውም ኀይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በርሱ የአላህን ጠላትና #ጠላታችሁን ሌሎችንም ከነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቁዋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን #(መናፍቃን) #የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡ ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል እናንተም አትበደሉም፡፡" 8:60፡፡
👍1
አሁንም ይቀጥላል...
ክርስቲያኖች መርዝ እንዲጠጡ ታዘዋልን? የማርቆስ 16፡18 ተግዳሮት።

http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/mark_1618_challenge/
👇👇👇
If you are serious apologetics student, read this የመጽሐፍ ቅዱስ የንባብ ልዩነቶች መነሻ ምክንያትና ተፅዕኖ (ቁርአንም ይፈተሻል) http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/textual_criticism/