ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ስለዚህ መረዳት ያለብን ቁም ነገር፣ በአብና በወልድ መሀል የአካል (not ‘body’ but ‘person’) ልዩነት ስላለ፣ ወልድ ከአብ ጋር በዘላለማዊ ደረጃ ያለው ተዛምዶ ልጅ ከአባቱ ጋር ያለው አይነት እንደሆነ መረዳት አለብን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም ለማለት ቁርአን ያቀረበው መረጃ፣ መልእክቱ መለኮታዊ አለመሆኑን ያሳያል፡፡ ለምሳሌ፡- ሱረቱል አል-ተውባህ 9 ፡ 30

አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው፡፡ (ከእውነት) እንዴት ይመለሳሉ!"

ሱረቱል አል-አንአም 6 ፡ 101
እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ #ለእርሱ_ሚስት_የሌለችው_ሲኾን_እንዴት_ለእርሱ_ልጅ_ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ሱረቱል ጅን 72 ፡ 3 ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ #ሚስትንም_ልጅንም_አልያዘም፡፡
ቁርአን እንዳስተማረው አላህ ልጅ እንዲኖረው የግድ ሚስት ያስፈልገዋል ብሏል፡፡ ይህ ምን ያህል የቋንቋ ስርአትን እንዲሁም ነገረ መለኮትን በቅጡ ያልተረዳ እንደሆነ በቀላሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ልጅ ማለት የግድ በስጋ የተወለደ ነው ማለት አይደለም፡፡ በአረብኛ ቋንቋ እንኳ ልጅን ለመግለጽ ሁለት ቃላት አሉ፤ "ዋላድ" (Metaphoric) ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን "ኢብን" (Biological) በሩካቤ ስጋ የተወለደ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም መንፈሳዊ ወይም የእምነት ልጅ አለ፡፡ ለምሳሌ፡- ሳሙኤል የኤሊ ልጅ (Biological) ሳይሆን የኤሊ ልጅ ተብሏል (1 ሳሙ 3፡6)፣ አይሁዶች የሰይጣን ልጆች ተብለዋል (ዮሐ 8፡44)፣ ጢሞቴዎስ የጳውሎስ የስጋ ልጁ ሳይሆን ‘ልጄ’ ብሎታል (1 ጢሞ 1፡2)፡፡
👍1
በአጠቃላይ የስጋ ልጅነት፣ የጉዲፈቻ ልጅነት (ገላ 3፡26፣ ሮሜ 8፡15-16)፣ ዘይቤአዊ ልጅነት (የጥፋት ልጅ[2 ተሰ 2፡3]፣ የሞት ልጅ[2 ሳሙ 12፡5]፣ የሰላም ልጅ[ሉቃ 10፡6]፣ የዚህ አለም ልጆች[ሉቃ 20፡34]፣ የብርሀን ልጆች [ሉቃ 16፡8])፣ የግንኙነት ልጅነት (እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር [ዘጸ 4፡23]፣ ነገስታት [መዝ 2፡7]፣ መላእክት [ኢዮ 1፡6]) ሩቅ ሳንሄድ በሀገራችን ኢትዮጵያ እንኳ ያልወለዱትን ልጅ በጉዲፈቻ ወስደው "ልጄ" ብለው ይጠሩታል፡፡ "ባልወልድህም ሌጄ ነህ" የሚለው የእናቶችም ንግግር በሀገራችን የተለመደ ነው፡፡

ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ቁርአን "ልጁ" ሲባል Biological ብቻ ነው ብሎ ማሰቡ ያሳፍራል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ "የእግዚአብሔር ልጅ" ብሎ ሲጠራ በሩካቤ ስጋ ወልዷል ብሎ ቁርአን መናገሩ ምን ያህል መለኮታዊ መጽሐፍ አለመሆኑን ስለሚያሳይ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምሮ ለመመዘን ቁርአን ምንም አይነት ብቃት የለውም፡፡
በቅርቡ July 17, 2017 G.C (ሐምሌ 12፣ 2009 ዓ.ም) በአንድ ሙስሊም ልጅ አማካኝነት የተላከ የድምጽ ቅጂ የደረሰን ሲሆን ውይይቱ የተካሄደው በአብርሃም መለሰ ሰለሞንና በዋሒድ (አቡ ኢኽላስ) መካከል ነበር፡፡ አብርሃም የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ቤተ እምነት አባል ሲሆን ከዚህ ቀደም ከዋሒድ ጋር በጽሑፍ ይነጋገሩ እንደነበር ከውይይታቸው ተረድተናል፡፡ በእርግጥ ይህ ወደ አስራ አምስት የሚደርስ የድምጽ ቅጂ የደረሰን በአንድ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንንና የወንጌላውያንን (Evangelical Protestants) መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት በውል ካልተረዳ ሙስሊም ጋር በምንነጋገርበት ጊዜ ነበር፡፡ ዋሒድ የአብርሃምን መሰረተ እምነት ለመቃወም ሲል እውነተኛ የሆኑትን የክርስትና አስተምህሮዎች በሀሳዊ የሙግት መንገዱ ያለአግባብ ስለነካካቸውና ምላሽ የሚያሻቸው በመሆናቸው ነው፡፡ ያልታደለ ዱቄት ከንፋስ ጋር ይጣላል ይሉታል ይህ ነው፡፡

ገና በመግቢያው ላይ "ኢየሱስ የፍጡር ስም ነው" በማለት ሲሆን የጀመረው፣ በዚህች የሙግት መደምደሚያው "የፍጡር ስም ስለያዘ፣ ፍጡር ነው" ብሏል፡፡ ይህ የእግዚአብሔርን መገለጥ ካለማወቅ፣ የቋንቋን ስርአት ካለመረዳት እንዲሁም እራሱን እስልምናን ካለመገንዘብ የመጣ ስህተት ሲሆን፥ ክፉኛ የአመክንዮ እጥረትም ይስተዋልበታል፡፡

ስለ ‘ስም’ በምናወራበት ጊዜ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በአጠቃላይ በሰማይምና በምድር ‘ስም’ን የምንጠቀምበት ዋነኛ ምክንያት፣ ስሙን፥ የስሙ ትርጉም የያዘው (የወከለው) አካል ባሕርይውን፣ ግብሩንና ስልጣኑን፣ ወ.ዘ.ተ ነገሮች ስለሚገጥልን ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ሰማይና ምድርን የፈጠረውን አካል ለመገለጽ ጥቅም ላይ የዋሉት ስሞች በሙሉ ባሕርይውን፣ ግብሩንና ስልጣኑን የሚያሳዩ የሆኑት፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ፍጥረት ባይኖርና አምላክ/እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች ባይገልጥ ኖሮ ስምም ባላስፈለገው ነበር፡፡ ‘ስም’ የሚለው ጉዳይ ‘መጠሪያን’ ያማካለ ስለሆነ፣ ለእኛ ለፍጡራን አምላካችንን የምንገናኝበት መስመር ለመዘርጋት ታስቦ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡
ስለዚህ በአጠቃላይ ‘ስም’ን መጠቀም ፍጥረት ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ የመጣ ነገር ነው እንጂ፣ የተለየ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ ምንም ስም የለም፡፡ እግዚአብሔር ግን ራሱን ለፍጥረቱ ሲገልጥ፣ ማንነቱን ደግሞ ሊገልጥ የሚችል የፍጡሩን የሰው ቋንቋ ተጠቅሞ ለራሱ ስም ሰጠ፡፡ ለምሳሌ፡- "ያሕዌ" የሚለው ስም ሉአላዊና ገዢ የሆነውን አምላክ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ስም ነው፡፡ (ዘጸ 3:15) ነገር ግን "ያሕዌ" የዕብራይስጥ ቃል ነው፡፡ በዚህ ቋንቋ መነጋገር የተጀመረው ከእግዚብሔር ዘላለማዊነት አንፃር ስንመለከተው ‘ትላንትና’ የተጀመረ የሰዎች ቋንቋ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉን ቻዩ ዘላለማዊው አምላክ በሰዎች ቋንቋ ስም ተጠቅሟልና ፍጡር ነው አላልነውም፡፡ ዋሒድ ያልገባውና የሳተው ጉዳይ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ "ኢየሱስም" ከፍጥረት መፈጠር ጋር ተያይዞ የመጣ ስም ነው፣ "ያሕዌ"ም እንዲሁ ከፍጥረት ጋር ተያይዞ የመጣ ስም ነው፡፡ ሌላው የሚደንቀው ነገር፥ ወሒድ የፍጡር ስም አይደለም ብሎ ባሰበበት በ"ያሕዌ" ስም ኢየሱስ መጠራቱ ነው፡፡ (ኢሳ 40:3 እና ማቴ 3:3ን ይመልከቱ፡፡) [ሌሎች ጥቅሶችም አሉ]፡፡

ስለዚህ ጉዳዩ ያለው ስሙ የተሰጠው አካል ስሙ የያዘውን ትርጉም የሚወክል ማንነት አለው ወይ የሚለው ጥያቄ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ ስም ስንመጣ ገና ለገና ዕብራውያን በቀደሙት ዘመናት ስሙን ለፍጡር ሰው ተጠቅመውታልና ኢየሱስ ፍጡር ነው ወደሚል ድምዳሜ አይወስደንም፡፡ ይህ እጅግ የደከመ አመክንዮ ነው፡፡

ቅድመ እስልምና አረቢያን ስናጠና እስልምና በመሐመድ ከመጀመሩ በፊት "አላህ ተዓላን/አል-ኢላህ" የተሰኘ ጣኦት ነበር፡፡ (Encyclopedia of World Mythology and Legend, "The Facts on File", ed. Anthony Mercatante, New York, 1983, I:61) ይህም ከ360 ጣኦታት መካከል አንዱ ነበር፡፡ ኃላ ግን መሐመድ አንድ አምላክ አለ ስሙም "አላህ" ነው ብሎ አረብኛ ቋንቋ ተጠቅሞ ‘አንድ አምላክ’ ብሎ ለጠራው አካል ስም ሲያውለው፣ አላህ ፍጡር ነው አላላችሁም፡፡ አረብኛ ቋንቋ የሰማይ ቋንቋ ነው የምንል ከሆነ፣ አላህ ፍጥረታት ባልነበሩበት ጊዜ በአረብኛ ቋንቋ ከማን ጋር ነበር የሚነጋገረው? አረብኛ ቋንቋ ከዘላለም ጀምሮ ነበር ከተባለ ለቋንቋውም መስገድ ይገባችኃል፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን ሌላም መታወቅ ያለበት ጉዳይ "አስማ ወሲፈትን" (የአላህን ስም ለአላህ ብቻ) በጣሰ መልኩ ከአላህ 99 ስሞች መካከል ፍጡሩ መሐመድ ወደ 20 የሚሆኑ ስሞቹን ተጋርቷል፡፡ (አስማ አን-ነቢ ከቅጽ 1-3) በመጀመሪያ ፍጡሩ መሐመድ እንዴት የፈጣሪን ስም ሊጋራ ቻለ? እንደገናም አላህ መሐመድ የተጋራውን ስም በመጠቀሙ፥ የፍጡር ስም ለእሱ ጥቅም ላይ ውሏልና አላህ ፍጡር ነው ለምን አላላችሁም? ‘አይ’ ኃላ የመጣው ፍጡሩ መሐመድ ስሞቹን ስለተጠቀመ አላህ ቀድሞውኑም ስሙ የሚገባው ስለነበረ በዚህ መልኩ አላህ ላይ ጥያቄ አያስነሳም ከተባለ፤ ሲጀመር መሐመድ ምን ሲል ስሞቹን ተጋራ? ራሱ መሐመድ የፍጥረት መገኛ አላህ ባይሆን ኖሮ ይህ ባልሆነ ነበር፡፡ (ሃያት ቁሉብ ቅጽ 2፣ ገጽ 5)

'ኢየሱስ' የሚለው ስም ቀጥተኛ ትርጉም ብንሰጠው ‘አዳነ’ ከሚለው አማርኛ ስም ጋር አቻ ፍቺ ይኖረዋል፡፡ ስም ከተሰጠበት ዋና አላማዎች መሀል ግብር እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡ ኢየሱስም ሰዎችን ለማዳን ወደ አለም ስለመጣ ከግበሩ የተነሳ ‘ኢየሱስ/አዳነ’ ተባለ፡፡ ለዚህ ነው ለመሐመድ ተገለጠለት እንደተባለው አይነት ሳይሆን ጨዋውና እውነተኛው መልዐክ ለዮሴፍ በህልም ሲገለጥ "እሱ ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋልህ" (ማቴ 1፡21) ብሎ ስሙ የተሰጠበት ምክንያት ግብሩ/ስራው እንደሆነ ማስተዋል የቻልነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በአለም ላይ ያለ ስም ከፍጥረት ጋር ተያይዞ የመጣ ስም ነው፡፡ ስም ያለው ሁሉ ግን ፍጡር አይደለም፡፡

በወሒድ የሚደረገውን የእስልምናን ቅጥፈት አጋልጦ ምላሹን ማቅረብ ይቀጥላል....
👉 ሥነ-ፅንስ በቁርአን ሳይንሳዊ ተአምር ወይስ ቁርአናዊ ውዥንብር👂
ክፍል-1
በዚህ የቁርአንን የስነ-ፅንስ አስተምሮ በራሳቸው እስላማዊ በሆኑ መፅሀፎችና በሳይንስ መነፅር በምንገመግምበት ተከታታይ ፅሁፍ እውን ቁርአን የተባለለትን ይዟል ወይ ደግሞስ ይህንን እንዳረጋገጡ የተነገረላቸው ምሁራን ለምን ያንን የመሰለ አንድምታ ያለው ንግግርንና ፅሁፍን እንዳዘጋጁ(የት ጋር በተለመደው የማታለያ ስልት እንደተታለሉ) እናያለን። ይህንንም የምናደርገው የፈጣሪ ቃል ሁሌም ከሳይንስ ጋር መስማማት አለበትንና እስቲ ቁርአኑንም በዚህ እያታ እንቃኘው ብለን ሳይሆን እራሳቸው ወገኖቻችን "የኛ ቁርአን ሳይንሳዊ ተአምር ነው። ይህን ካላረጋገጠማ ምኑን የፈጣሪ ቃል ሆና።" ስላሉን የቁርአን የሥነ-ፅንስ አስተምሮው ሳይንሳዊ እንዳልሆነና እግረ መንገዱንም እንዴት ቁርአን የፈጣሪ ቃል እንዳልሆነ ራሳቸው በሰሩት የሙግት ነጥብ እናያለን። እስቱ የተጠቀሱትን የእድገት ደረጃዎች አንድ በአንድ እንመልከት(ይህን ይምናነፃፅረው ወሂድ ኡመር ስለ ጉዳዩ ከፃፈው ፅሁፍ ጋር ይሆናል)።
👉 ደረጃ-1 ኑጥፉህ፦ ይህን ወቅት ወሂድ "የፍትወት ጠብታ ሲሆን ይህም የተባእት ህዋስ እና የሴት እንቁላል ህዋስ ነው" በሚል ገልፆታል። እውነት ኑጥፍህ የሁለቱ ውህድ ነውን? እውን ቁርአን "የእንስት እንቁላል ህዋስ" የሚለውን ያቀዋልን?
ይህን ስንመልስ እርሱ እንድናመሳክራቸው ከሰጠን ጥቅሶች መሀከል ሱራ 35፥11፣ 36፥77፣ 40፥67 ሌሎቹንም ሄደን እውን ምን ማለት እንደሆነ የኢብን አባስን ማብራርያ ብናይ "weak and stinking sperm drop" የሚልን ማብራርያ እናገኛለን(መቼም እዚህ ውስጥ ስለሴቷ ድርሻ የተነገረ ምንም እንደሌለ ማስተዋል አያዳግትም)። ሌሎችንም ማብራርያዎች መመልከት ይችላል(Al-Jalalain, Ibn kathir...)። በመቀጠልም mashaj and mashij ማለት የተቀላቀለ የተዋሀደ ነው ይለናል መልካም ግን እርሱ እንዳለው የወንዴው የዘር ፈሳሽና የሴቷ እንቁላል ነውን የተዋሀደው? በፍፁም አይደለም ይልቁኑ በ Tafsir Ibn Kathir 76፥2 እናም በሌሎች ምንጮች መሰረት የወንዴው እና የሴቷ ፈሳሽ ነገር ውህድ እንደሆነ ይነግረናል። በዚህም አያበቃም ይህን ፈሳሽ ሲገልፅልን(በsahih muslim book 3 no. 608፣ sunan an Nasai vol. 1፥200፣ sunan Ibn Majah Vol.1፥601 ወ.ዘ.ተ.) ላይ የወንዱ ወፍራምና ነጭ የሴቷ ቀጭንና ቢጫ ፈሳሽ ነው ይሉናል። እና እንቁላል የሚለው ከየት መጣ? ይህ ፈፅሞ ሳይንስ የማያቀው ለነDr. Moor ያልተነገራቸው በታወቁ የእስልምና ፃሁፎች ላይ የሰፈሩ እራሳቸውን የሚያጋልጡ እውነታዎች አላዩአቸውምን?
ይቀጥላል.........🙏ተባረኩ!!!🙏
👍1
@Jesuscrucified
ይሄን የዚህን ቻነል ሊንክ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር በማድረግ ለሌሎች ማካፈል አንርሳ.... share
ወሒድ ከአብርሃም ጋር በነበረው ውይይት ያነሳው፣ "ቃል ስጋ ሆነ ማለት፣ ቃል ወደስጋነት ተለወጠ ሳይሆን በዕብ 10፡5 መሰረት "ስጋን አዘጋጀህልኝ" እንደሚለው በማሪያም ማህፀን ውስጥ ፈጠረው ማለት ነው" ብሏል፡፡ በእርግጥ ወሒድ ‘ቃል ወደ ስጋነት ተለወጠ’ ሳይሆን ያለው፣ ለተሳሳተው የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አስተሳሰቦች ምላሽ ለመስጠት ቢሆንም እውነቱ ግን ከዚህ የራቀ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‘ቃል ስጋ ሆነ’ ሲል እንደተባለው ‘ቃል ወደስጋነት ተለወጠ’ ሳይሆን ቃል የተባለውና አምላክ የሆነው ኢየሱስ፣ ሠው ሆነ ማለት ነው (ዮሐ 1:1;14)፡፡

ሥጋን አዘጋጀህልኝ" ማለት ማርያም ማህፀን ውስጥ ፈጠረው ማለት ሳይሆን፣ ቁጥር አምስት "ስለዚህ ክርስቶስ #ወደ_ዓለም_በመጣ_ጊዜ እንዲህ ብሎአል፤" ብሎ "ሥጋን አዘጋጀህልኝ" ከማለቱ በፊት ሕሉው የሆነ (exist ያደረገ) እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አንድ አካል "መጣ" ከተባለ፣ ወደመጣበት ቦታ ከመምጣቱ በፊት የሆነ ቦታ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በወሒድ ትርጉም ከሄድን "ከመፈጠሩ በፊት ተናገረ ወይም የሆነ ቦታ ኢየሱስን ፈጠረው እንደገናም መልሶ ማርያም ማህጸን ውስጥ ደግሞ ፈጠረው" እያለን ነው፡፡ ይህ ደግሞ በእጅጉ የነሆለለ ሀሳብ ነው፡፡ ክፍሉ ግን ከመዝ 40፡6-8 ጋር በተያያዘ መልኩ፣ ክርስቶስ ኢየሱስ በፍጹም ታዛዥነት፥ በግ ወይም ጥጃ ሳይሆን፣ እራሱን መባና መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ መፍቀዱን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም የአብ ፈቃድ ነበር፡፡ ዘማሪው በክፍሉ ውስጥ "ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ" እንዳለ፣ ኢየሱስም የአባቱን ፈቃድ አደረገ፡፡
ይህም መስዋዕት በብሉይ ኪዳን ከሚቀርቡት መስዋዕቶች እጅግ የከበረና የላቀ መስዋዕት ነበር፡፡ የዕብራውያን ምዕራፍ አስር ዐውድ ስለኢየሱስ መፈጠር የሚናገር ሳይሆን፣ ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያቀረበው መሥዋዕት ምንያህል የከበረ ኪዳን እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ቁርአን የቅዱሳት መጽሐፍት ግርንቢጥ (ተገላቢጦሽ) ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደቁርአን የቃላት ውርጅብኝ ያጠቃው መጽሐፍ ሳይሆን ዐውድ ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ ቁርአን ግን ለዚህ እጅግ ባይተዋር ነው፡፡ ይህንን አለመረዳታቸው ነው ወሒድና ተከታዮቹ የሳቱት፡፡

በተጨማሪ ሃሳቡም፣ "ኢሳ 9፡6 ለኢየሱስ ነው ተብሎ እንደመረጃ የቀረበበት ነገር የለም" ብሏል፡፡ ወሒድ/አቡ ኢኽላስ እየቀለደ መሆን አለበት እንጂ፣ እንዲህ የወየበ ሃሳብ ባልተናገረ ነበር፡፡ ይህን መረዳቱን በዚህ ጥያቄ ብቻ ነው የማልፈው፣ "ታዲያ ኢሳ 9፡6 ስለማን ነው የሚያወራው?" መቼስ ለመሐመድ ነው እንደማትለኝ ጎንዳላ ቢሆንም፣ ተስፋ አለኝ፡፡
👉ሥነ-ፅንስ በቁርአን ሳይንሳዊ ተአምር ወይስ ቁርአናዊ ውዥንብር👂
ክፍል-2
👉 ደረጃ-2፦ #ዐለቅ ይህ የቁርአን የፅንስ የእድገት ደረጃ በቁርአን ወደ ስድስት ጊዜ አምስት በሚሆኑ ቦታዎች ተጠቅሶ እናገኘዋለን። የዚህን ቃል ትርጉም ኡስታዞቹ ሲያብራሩ የረጋ ደም፣ አልቅት የመሰለ ነገርና የተጣበቀ ነገር ማለት ሊሆን ይችላል ይሉናል። ወሒድም በፅሁፉ " 'የረጋ ደም' ማለት ሲሆን ፤ ይህን የሁለተኛው ደረጃ ከሚታይ አልቅት ከሚባል የባህር ትል #'insect' እና ከረጋ ደም ጋር ስለሚመሳሰል ነው..." በማለት ያትታል። ሲቀጥልም እንዴት ወደዚህ ደረጃ እንደሚደርስ በመተንተን (ይህን ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ) ሂደቱ #በ21 ቀን ውስጥ የረጋ ደም የሚባለው ደረጃ እንደሚመጣና ይህንንም የጊዜ ርዝመት "ከዚያም" በሚል አያያዥ እንደሚገለፅ ያስቀምጣል።
🤔እ ስቲ እንጠይቅ፦
1,እውነት ዐለቅ ይህን ሁሉ(ከላይ የጠቀስኳቸውን ትርጉሞች) ማለት ነውን?
2,እውነት የአምላክ ቃል ያውም ለአምላክ ግልፅ የሆነን ሚስጥር "እንዲም ሊሆን ይችላል... ይሄም ያስኬዳም... እንዲያም ቢባል አይከፋም" እያልን እንደፈለግን በብዙ ትርጉሞች እንፈታለንን?
3, ያኔ ይህ ቃል ሲነገር ምን ለማለት እንደተፈለገ ገብቷችኃልን? ነው ያኔም ይህን ሁሉ ትርጉም ለመግለጥ ታስቦ ነበር የተነገረው?
4, እሺ #የረጋ ደም ማለት ነው ከተባለ አንድም Dr. Moorም እንደተናገሩት የረጋ ደምን ይመስላል የምንለው ፅንሱ በተለያዩ ምክንያቶች ከወረደ ነው(ደግሞም መቼም የረጋ ደም የሚመስለው ከማህፀን ግርግዳ ተለይቶ ከወረደ ብቻ መሆኑ ግልፅ ነው)። እና ይህን የወረደን ወይም የጨነገፈን ነገር አይቶ መናገር ተአምር ነውን? አምላክ ሳይወርድ ያለውን ምስል ለምን አልተናገረው? ነው ወይስ የሰው መላምት ነው የምትነግሩን?
5, #አልቅት ማለት ነው ከተባለ እስቲ ቃሉን እጥቅሶቹ ውስጥ አስገብታችሁ እን ብቡት። መቼም "..ሰውን ዐለቅ መሳይ ነገር በፈጠረው..." አይልም ይልቁኑ "ከዐለቅ በፈጠረው ..." ይላል እንጂ። ደግሞ ይህን ማለት ነው የሚልን መዝገበ ቃላትንም እንድትጠቅሱልኝ ፈልጋለሁ!!
6, #የተጣበቀ ነገር( thing which clings)... ማለት ነው ከተባለም እስቲ ማን ይሙት ፅንሱ በዚህ የእድገት ደረጃ ላይ ብቻ ነውን በእንግዴ ልጅ በኩል እማህፀን ግርግዳ ላይ የሚጣበቀው? በሌላውስ ግዜ(ከዛ በፊትና በኃላስ)?
7, ወደ ሚፈጀው ግዜ ስንመጣ እውን ቁርአንና ታላላቅ ሙፈሲሮች #21 ቀን ነው የሚወስድበት ይሉናል? ለመጀመሪያው ደረጃ ብቻ 40 ንፁህ ቀናት እንደሚያስፈልገው የተነገረባቸው ሐዲዞችና ተፍሲሮች የትገቡ? ለምንስ ለነDr. Moor አልተነገራቸውም🤔😏(መልሱ ግልፅ ቢሆንም )?
💁‍♂ መረጃ አላችሁ ይኽው፦ ተፍሲር ኢብን አባስ 23:14፤ ሷሂህ ቡሓሪ ቅፅ 4 ቁጥር 430 እና 549፣ ቅፅ 8 ቁጥር 593፣ ቅፅ 9 ቁጥር 546፤ ሷሂህ ሙስሊም መፅሀፍ 33 ቁጥር 6390-6392፤ ሱና ኢብን ማጃህ ቅፅ 1 ቁጥር 76፤ አት ትርሚዝ ቅፅ 4 ቁጥር 2137 ወ.ዘ.ተ.
መልካም በነ ዚ ዘገባዎች ላይ የተገለፁትን ሁነቶችና እውነተኛውን ምላሽ ከዘመናዊው ሳይንስ አንፃር በሚቀጥለው እንመለበታለን።
ይቀጥላል......🙏ጌታ ይወዳችኃል!!!❤️
ወሒድ የይሖዋ ምስክሮችን የሙግት ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ቀድቶ ያቀረበው ክፍል ዮሐ 5፡26 "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።" ሲሆን፣ ኢየሱስ ሕይወት ስለተሰጠው ፍጡር ነው፤ የሚል መደምደሚያ ሰጥቶታል፡፡ ክፍሉ እንዲህ የሚል ሃሳብ ፈጽሞ የለውም፡፡ ለዚህ አይነት ጥያቄ ደጋግመን እንደተናገርነው፣ የኢየሱስን አምላክነት አውጆ ጀምሮ (ዮሐ 1፡1) አውጆ ከሚጨርሰው (ዮሐ 20፡28) መጽሐፍ፣ "ኢየሱስ ፍጡር ነው" የሚል እንግውላይ (ገለባ) ትምህርት ማደራጃነት ከዮሐንስ ወንጌል መጠቀም እጅግ አላዋቂነት ነው፡፡ ዮሐ 1፡4 "በእርሱ ሕይወት ነበረች" ይላል፡፡ ይህም በቅድመ ትስብዕቱ ጊዜ እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ በዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ በማርያም ማህፀን ውስጥ ተፈጠረ የሚለውን የዋሒድን ሙግት ዳር ላይ ያወጣዋል ማለት ነው፡፡

"መጀመሪያ ቃል ነበር::" ዮሐ 1:1 "በመጀመሪያ" ግሪኩ፦ ኢን አርኬ "᾿Εν ἀρχῇ" የሚለው ቃል በሰብዓ ሊቃናት በዘፍ 1:1 ላይ እናገኘዋለን፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት "ኢን አርኬ" የሚለው ቃል ከዘፍጥረት 1:1 ጋር አንድ አይነት ጅማሬ ስለሚያመለክት ነው፡፡ የዘፍጥረት 1:1 እና የዮሐንስ 1:1 ዐውድ "መጀመሪያ" የሚለው ቃል የጊዜ ጅማሬን የሚያመለክት ነው፡፡ የሁለቱንም ዐውድ በመመልከት ተመሳሳይ ሀሳብ እንዳላቸው መረዳት እንችላለን፡፡ ሁለቱም ስለፍጥረት ጅማሬ ይናገራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ጊዜን እንደፈጠረ በግልፅ ይናገራል (ዕብ 1:2፤ 11:3) " )En" የሚለው የግሪክ መስተዋድድ ኢየሱስ አለማት በተፈጠሩ ጊዜ ነው ህልውናውነ ያገኘው የሚል ሀሳብ አይሰጠንም፡፡ ምክንያቱም ዮሐንስ ይህንን ለማለት ቢፈልግ ኖሮ " )En" ከሚሊው የግሪክ ቃል መስተዋድድ ይልቅ "ኤግኒቶ" (ἐγένετο ዮሐ 1:3:6:10...) የሚለውን ይጠቀም ነበር፡፡ በመጀመሪያ ቃል ህልውና አገኘ ተብሎ ይተረጎም ነበር፡፡ "ነበር" የሚለው የግሪክ ቃል "ኢን" የሚለውን በግሪክ ሰዋሰው መሰረት ህልውናው ቀጣይነት እንደነበረው (imperfect) የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም ኢየሱስ ጊዜአት ወይም አለማት ከመፈጠራቸው በፊት እንኳ ህልውናው ቀጣይነት የነበረው እንደነበር ሳያሻማ የሚያሳይ ነው፡፡
👍1
ስለዚህ "በእርሱ ሕይወት ነበረች" ማለት፥ እርሱ እራሱ የሕይወት መገኛ ምንጭ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ዮሐንስ መልዕክቱን ሲጽፍ ይህንን አሳስቦናል (1 ዮሐ 5፡11-12) "እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።" ስለዚህ እራሱ ኢየሱስ ሕይወት ነው ማለት ነው፡፡ ዮሐ 5፡26 "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።" ማለት "አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ ለወልድም ሕይወትን ሰጥቶት ፈጥሮታል" ማለት አይደለም፡፡ ክፍሉ በንጽጽር ነው የቀረበው፡፡ "ሕይወትን ሰጥቶት" ሲል "ፈጥሮታል" ማለት ነው ብለን ከተረጎምን አብንም "ሕይወት እንዳለው" ይለዋልና እራሱን ፈጥሯል ወደሚል ድምዳሜ ይወስዳል፡፡ ይህ ደግሞ ሌላ ስህተት ነው፡፡

ማስተዋል ያለብን፣ በሁለቱም ሐረግ ውስጥ "በራሱ" የሚሉ ቃላት እንዳሉ ነው፡፡ ይህንን ለመረዳት ዐውዱን መመልከት የግድ ይለናል፡፡ ቁጥር ሃያ አንድ "አብ ሙታንን እንደሚያስነሳ ሕይወትን እንደሚሰጥ፣ ወልድም ደግ ለሚፈቅደው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል፡፡" ይላል፡፡ የዚህ ቁጥር አረፍተ ነገር አቀራረቡ ከቁጥር ሃያ ስድስት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አብ በራሱ ሙታንን በማስነሳት ሕይወት እንደሚሰጥ ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ለሚፈቅድላቸው ሙታን ሁሉ ከሞት በማስነሳት ሕይወትን ይሰጣቸዋል ማለት ነው፡፡ ከዚህም የምንረዳው አብ ለሙታን ሕይወትን መስጠት እንደሚቻለው ሁሉ፣ ኢየሱስም ለሙታን ሕይወትን መስጠት ይችላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዮሐ 5፡26 መሰረት ለኢየሱስ የተሰጠው ሕይወት ‘ለመፈጠር’ ሳይሆን በራሱ ሙታንን በማስነሳት ለእነሱ ሕይወትን ለመስጠት ነው፡፡ ከቁጥር 22-31 ቀጥለንም ብንመለከት ስለ ሙታን ትንሳኤና ፍርድ ነው የሚያወራው፡፡ "አብ ኢየሱስን ፈጥሯል" የሚለው ትምህርት ሽታው እንኳ የለም የሚባለው እንደውም እዚህ ላይ ነው፡፡ "ሰጥቶታል" የሚለው ቃል ኢየሱስ ከያዘው ግብር አኳያ የሚታይ ነገር ይሆናል፡፡
ወሒድ/አቡ ኢኽላስ እረሳው እንጂ በዛው በዮሐንስ ወንጌል 6፡57 የሚገኝ የይሖዋ ምስክሮች የሙግት ነጥብ ነበር፡፡ ይህም ኅይለ ቃል ኢየሱስ ቀድመው ተፈጥረው ለነበሩ ሰዎች ሕይወትን እንዴት እንደሚሰጣቸው የሚያወራ ነው፡፡ ኢየሱስ በአብ አማካኝነት ከሙታን ሕይወትን አግኝቶ እንደሚነሳ ሁሉ፣ በኢየሱስ ለሚያምኑት ሁሉ በኢየሱስ አማካኝነት ከሙታን መካከል በመነሳት ሕይወትን (የዘላለም) ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ለሰዎቹ "ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል" ሲል ፈጠራቸው ማለት ካልሆነ፣ ለኢየሱስ "ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን"ሲል እንዴት ፈጠረው ሊሆን ይችላል? በፍጹም አይሆንም፡፡ አረፍተ ነገሩ future tense ነው፡፡ እንጂ past tense አይደለም፡፡ ይህም ስለመጻኢው የሙታን ትንሳኤ የሚናገር ነው፡፡ የኢየሱስ የተፈጸመ ሲሆን፣ የእኛ ወደፊት ይፈጸማል፡፡ አሜን!!
👉 ሥነ-ፅንስ በቁርአን ሳይንሳዊ ተአምር ወይስ ቁርአናዊ ውዥንብር👂
ክፍል-3
🤔👨‍⚕👨‍⚕🕵🔦🔦➡️👳‍♀👳
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
👇👇👇👇...ይቀጥላል
ጌታ ይወዳችኋል!!!
ለመስዋዕት የተመረጠው ይስሐቅ ወይስ እስማኤል?

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አብርሃም እንዲሰዋው የታዘዘው ልጅ ይስሐቅ ሲሆን በቁርአን ግን የልጁ ማንነት አልተጠቀሰም፡፡ አቶ ሐሰን እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-

ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ኢስማኢልን እንዲያርዱ በአላህ መታዘዛቸው በቁርአን ተተርኳል (ገፅ 173)

ይህንን ብለው ሱራ 37፡100-107 ላይ የሚገኘውን ተከታዩን የቁርአን ክፍል ጠቅሰዋል፡፡

“ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡”

አቶ ሐሰን ከተናገሩት በተጻራሪ ይህ የቁርአን ክፍል ለመስዋዕት የቀረበውን ልጅ ማንነት በግልፅ አይናገርም፡፡ ነገር ግን በውስጠ አዋቂነት ለመስዋዕት የቀረበው ልጅ ይስሐቅ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ቁርአን በተከታዮቹ ጥቅሶች ላይ ይስሐቅን በተመለከተ አብርሃም መበሰሩን ይናገራል፡-

“መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን (በልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡ ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡” (11፡69-73)

“በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡” (37፡112)

በመጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ ተመሳሳይ ታሪክ እናገኛለን፡-

“እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ፡፡ እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርስዋ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካትማለሁ፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፤ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርስዋ ይወጣሉ፡፡” (ዘፍ. 17፡15-16)

ጥንታዊያን ሙስሊም ሊቃውንት ለመስዋዕት በቀረበው ልጅ ማንነት ዙርያ ስምምነት የላቸውም፡፡ ከኋለኞቹ ሊቃውንት መካከል አብዛኞቹ እስማኤል መሆኑን ቢናገሩም ከጥንት ሊቃውንት መካከል ብዙዎቹ ይስሐቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡[30] የኢስላም ኢንሳይክሎፒድያ ውስጥ ተከታዩ ተጽፏል፡-

“የተጠቀሰው የቁርአን አንቀፅ ለመስዋዕት የቀረበው ልጅ ማን እንደሆነ አይናገርም፡፡ ብዙ ሙስሊም ሊቃውንት ለመስዋዕት የታሰበው እስማኤል መሆኑን ይናገራሉ … ነገር ግን አል-ታላቢ የተሰኘው ቀደምት ትውፊት በአፅንዖት እንደሚገልጸው አስሃባ እና ታቢዑን፣ ማለትም የነቢዩ ወዳጆችና ከዑመር ኢብን ኸጧብ ጀምሮ እስከ ከዕብ አል-አሕባር ድረስ የሚገኙት ወገኖች ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተለየ አቋም አልነበራቸውም፡፡”[31]

ኢብን አባስ የተሰኘ የመሐመድ ወዳጅ የነበረ ሙስሊም ጸሐፊ ለመስዋዕት የቀረበው ልጅ እስማኤል ይሁን ይስሐቅ እርግጠኛ ባልሆነ አነጋገር ሁለቱንም በመጥቀስ ጽፏል፡፡[32] ሁለቱ ጃለሎችም ሙስሊም ሊቃውንት ለመስዋዕት በቀረበው ልጅ ማንነት ዙርያ አንድ ዓይነት አቋም እንደሌላቸው ጽፈዋል፡፡[33]

አል ጠበሪ የተሰኘ ጥንታዊ ሙስሊም ሊቅ ሱራ 37፡100-107 ላይ የተገለጸው የመስዋዕቱ ልጅ ይስሐቅ መሆኑን ጽፏል፡፡[34] ዘገባውም የተላለፈው ከነቢዩ መሐመድ መሆኑን በመግለጽ የዘገባ አስተላላፊዎቹን ስም ዘርዝሯል፡፡[35] ሙስናድ አሕመድ ኢብን ሐንበል ሐዲስ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡-

“አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ለመሰዋት ሲዘጋጅ ልጁ እንዲህ አለው፣ ‹አባቴ ሆይ እንዳልፈራና የኔ ደም በአንተ ላይ እንዳይረጭ እሰረኝ…›”[36]

ሚሽካት አል-መሳቢህ በተሰኘ የሐዲስ ስብስብ ውስጥ እንዲህ ተጽፏል፡-

“ሙሐመድ ኢብን አል-ሙንተሸር እንዳስተላለፈው አላህ ከጠላቶቹ ቢታደገው ራሱን ለመሰዋት ስዕለት የተሳለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ኢብን አባስን ለምክር በጠየቀው ጊዜ መስሩቅን እንዲያማክረው ነገረው፡፡ እርሱን ባማከረ ጊዜ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጠው፡- ‹‹ራስህን አትሰዋ ምክንያቱም አማኝ ከሆንክ አማኝ ነፍስ ትገድላለህና ከሃዲ ከሆንክ ደግሞ ወደ ገሃነም ትፈጥናለህና፤ ነገር ግን በግ በመግዛት ለድኾች ስትል መስዋዕት አድርግ ምክንያቱም ይስሐቅ ካንተ የተሻለ ሆኖ ሳለ በበግ ተዋጅቷልና፡፡›› ጉዳዩን ለኢብን አባስ ባወጋው ጊዜ ‹‹እኔም ልነግርህ የፈለኩት ውሳኔ ይኸው ነበር›› በማለት መለሰለት፡፡”[37]

መጽሐፍ ቅዱሳችን የመስዋዕቱ ልጅ ይስሐቅ መሆኑን በግልፅ ስለሚናገር በድንግዝግዝ የተሞላውን የሰባተኛ ክፍለ ዘመን መጽሐፍ የምንቀበልበት ምንም ዓይነት ምክያት የለም፡፡ ሙስሊም ወገኖች የመስዋዕቱ ልጅ እስማኤል መሆኑን እንድናምንላቸው ጥረት ከማድረጋቸው በፊት በጉዳዩ ዙርያ በገዛ ሊቃውንታቸው መካከል የሚገኙትን ልዩነቶች ማስታረቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡

አቶ ሐሰን ዘፍጥረት 22፡9 ላይ ይስሐቅ የአብርሃም አንድያ ልጅ መሆኑ እንደተነገረ በመግለጽ ተከታዩን ሙግት ያቀርባሉ፡-

እስማኤል የኢስሐቅ ታላቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንዲያርድ የታዘዘው ኢስሐቅን ቢሆን ኖሮ አንድዬ ልጅ የሚለው ትርጉም ያጣል፡፡ ምክያቱም ሁለት ልጆች ነበሩትና፡፡ ኢብራሂም አንድዬ ልጅ ሊኖረው የሚችለው ኢስሐቅ ከመወለዱ በፊት ነው፡፡ እርሱም እስማኤል ነው፡፡ (ገፅ 174)

ይስሐቅ የአብርሃም አንድ ልጅ መሆኑ የተገለጸው በተከታዮቹ ምክንያቶች ነው፡-

ይስሐቅ ብቸኛው የቃልኪዳን ልጅ ነው (ዘፍ. 17:15-21)፡፡ ይህንን ሐቅ ቁርአን እንኳ በግልፅ ይመሰክራል (ሱራ 11:69-73፣ 37:112-113፣ 51:24-30)፡፡
ይስሐቅ በዕድሜና በመካንነት ምክንያት መውለድ ከማትችለው ከሣራ ተዓምራዊ በሆነ መንገድ የተወለደ ልጅ ነው፡፡ እስማኤል ግን በተፈጥሯዊ መንገድ የተወለደ ነው (17፡15-17፣ 18፡9-15፣ 21፡1-7፣ ገላትያ 4፡28-29)፡፡ ቁርአንም ከዚህ ሐቅ ጋር ይስማማል (ሱራ 11፡69-73 51፡24-30)፡፡
ከነዓንን እንደሚወርስ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የሰጠው በይስሐቅ በኩል ላለው የአብርሃም ዘር እንጂ በእስማኤል በኩል ለሚመጣው አይደለም (ዘፍ. 13፡14-18፡ 15፡18-21፣ 28፡13-14)፡፡
እስማኤል ከእናቱ ጋር ስለተሰደደ በወቅቱ በቤት ውስጥ የነበረው ብቸኛው ልጅ ይስሐቅ ነበር (ዘፍ. 21፡9-21)፡፡
ሙስሊም ሰባኪያን እንኳንስ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅመው የመስዋዕቱ ልጅ እስማኤል መሆኑን ሊያረጋግጡልን ይቅርና በገዛ ቁርአናቸው እንኳ ያንን ማድረግ አይችሉም፡፡ ስለዚህ የማያዋጣቸውን ክርክር በመተው እውነቱን ቢቀበሉ መልካም ይመስለናል፡፡

ማጣቀሻዎቹን ለማየት http://www.ewnetlehulu.org/am/our-answers/hasentaju/ch5_2/ ይጎብኙ
እውነት ቁርአን ያለ ምንም ነቀፋ ተጠብቊልን??
(The Corrupted book of ISLAM)

ሙስሊም ወገኖቻችን ውይይት ባደረግን ቁጥር የሚያነሱት አንዱና ዋነኛው ነገር ቁርአን የ አላህ ቃል መሆኑንና ያለምንም ነቀፋ መጠበቁን ነው። እውነቱ ግን ምንድንነው?? ይሄንን አብረን የምናይ ይሆናል።
 ይህንን ክፍል አንብበን እንጀምር

" አንድ ሠሞን ላይ ዑመር ከቁርአን ጥቅሶች( verses) ውስጥ በድንግዝግዝ( vaguely) ብቻ ሚያስታውሰውን ክፍል ሲያስፈልግ ነበር። ይሁን እንጂ አያውን የሚያስታውስ (the verse) ብቸኛው ሰው በ የመማ ጦርነት ውስጥ መሞቱን ሲሰማ በጣም አዘነ። አያውም በዛው ጠፍቶ ቀረ።" (Ibn Abi Dawud,Kitab al-Masahif, p. 10 ; and as-Suyuti’s al-Itqan fi ‘ulum al-Quran, volume 1, p. 204)

እንግድህ አሱዩቲ ማለት ከቁርአንና ከ ሱና አዋቂዎች መካከል እጅግ የከበሩና ተቀባይነት ያላቸው ብዙም ተፍሲሮች የመዘገቡ ታላቅ አዋቂ ናቸው። አሁን ካሉትም አዋቂ ነን ባዬች scholars ጋር እንኲን ሊወዳደሩ የማይችሉ ናቸው።  እስኪ ጨምረን እንመልከት

Jalaluddin as-suyuti የመዘገቡት ከ Sufyan al-Thawri (d. 161 A. H) ይዘገበው ሃዲዝ እንዲህ ይላል
 "..ቁርአንን ሲቀሩ የነበሩ የነብዩ ሳሃባውች ሙሰይለማ ቀን ላይ በመገደላቸው የያዙትም ( the verses that only they knew) የቁርአን ክፍሎች ጠፍቶ ቀርቷል። Tafsir Dur al-Manthur,Muqaddamah of Surah Ahzab, Volume 6, p. 558 by as-suyuti

አብድ አልረዛቅ ከ እብን አባስ የተናገረው ሃድዝ እንድህ ይላል: ዑመር ብን አልከታለ ጀመአት ሰላት ሰውች እንዲሰበሰቡ ካደረገ በሓላ ወደ መድረክ (pulpit) ወጥቶ እንዲህ አለ።' ሰዎች ሆይ! ስለ ረጅም አያ (verse of stoning) ምንም ስጋት አይግባቹ፤ ምክኒያቱም ይህ አያ በቁርአን ውስጥ ወርዶ ሲነበብ ነበር። ግን አሁን ብዙ ከሙሃመድ ሞት ጋር ከጠፉ የቁርአን አካላት ውስጥ አንዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ማረጋገጫው፣ ሙሐመድ በድንጋይ ሲወግር ነበር፣አቡበከርም ወግሯል፤ እኔም እንደዚያው። ግን ምፈራው ከናንተው ወገን፤የማይወግሩ ሰውች ይነሳሉ።"
(Tafsir Dur al-Manthur, Muqadmah of Surah Ahzab) by as suyuti and al bukhari  volume 8 pg 208
  ልክ ዑመር እንደ ፈራ ዛሬ ዝሙተኞችን የመውገር አያ በቁርአን ውስጥ አናገኝም። የት ገብቶ ነው???

እነ አቡ-እክላስ  ከዚህ ማምለጫ ሲያጡ አንድ ውሸት መፍጠራቸው ይታወሳል። እሱም "  "ውስጥ " የሚለው ቃል ከ "ፊማ" የሚል የ Arabic ቃል የተተረጎመ ሲሆን ትርጉሙም "ጋር" የሚል እንጂ "ውስጥ" አይደለም። ስለዚህም እነኚ አያውች ከ ቁርአን 'ጋር' እንጂ በ ቁርአን ውስጥ አለወረዱም" ብለዋል። ይህ ንን መቼስ የ እስልምና ምሁራን እራሳቸው ቢሰሙ አመት የሚስቁ ይመስለኛል።
"ፊማ" የሚለው ቃል፤ በየትኛውም የ Arabic ድክሽነሪ ብትፈልጉት "ውስጥ፣ there in, within, in that"  የሚል ትርጉም እብጂ " ጋር፣ together, beside, with" የሚል ትርጉም ኖሮትም አያውቅም። ለዛም ነው ሁሉም የሙስሊም ምሁራን " ውስጥ" ብለው ተስማምቶበት የተረጎሙት።

ይቀጥላል.....
The corrupted book of Islam part 2

ጎዶሎ ሱራዎች

ብዙ የእስልምና መጽሐፎች እንደሚያረጋግጡት የ ሱራ 9 ( ተውባ)  ርዝመት ሱራ አል በቀራን ያክል እንደነበር ዘግቧል።አሁን ግን 9ኛው ሱራ 128 verse ሲኖሩት አል በቀራ ግን 286  አሉት። እስኪ እናንብብ

"መሊክ እንደተናገረው፤እብን አል ቀሲም፣ እብን አብዱል ሐከም፣እብን ወሃብ እንደዘገቡት፤ የ ሱራ በረዕ (9) መጀመሪያ ክፍል ሲጠፋ:' ብሥሚላህ አል ረህማን አል ረሂም' የሚለውም አብሮት ጠፍቶ ነበር። እብን አጅላንም እንደ ዘገበው ሱራ በረዓ በ ርዝመት ከ ሱራ አል ብቅራ ጋር እኩል ወይም በጣም ተቀሬቢ ነበረ። ሳለዚ የ ሱራ በረዓ መጀመሪያ ክፍሎች ሲጠፉ ከሱም ጋር ' ብሥሚላህ አል ረህማን አል ረሂም'  ጠፍቷል።" ( ተፍሲር አል ቁርቱቢ ቅጽ 8 ገጽ 62 , ሱራ በረዓት (9)))

ጀለሉዲን አል ሱዩቲም እንዲህ ብሏል
"...አል ተውባህ (የ 9ኛው ሱራ ሌላ ስም ነው) ብላቹ የምትጠሩት ሱራ በትክክል ብትጠሩት 'ሱራ አዛብ' ነው፤ እናንተ የምትቀሩት ግን አንድ አራተኛውን ብቻ ነው ( only one forth of the original)
” (Tafsir Dur al-Manthur, Volume 3 p. 208 by as suyuti)

እስኪ ስለ ሱራ አህዛብ ደግሞ እንይ

" አይሻ እንደዘገበችው ' ነብዩ በሕይወት እያሉ ሱራ አህዛብ 200 የሚያክል አያ ነበረው። ነብዩ ሞተው ቁርአን ከተሰበሰበ በሃላ ግን አሁን ያሉት (73 Verse) ብቻ  ቀርቷል። Tafsir Qurtubi, Volume 7, p.113)

ይቀጥላል.....
📌 በተጨማሪም📌
ሙስሊም ወገኖቻችን ቁርአን በአላህ ጥበቃ ውስጥ የኖረ እና ለትውልድ ያለምንም እንከን መተላለፍ የቻለ ነው ለሚለው ሃሳባቸው ሱረቱል አል-ሒጅር 15 ፡ 9 "እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ #ጠባቂዎቹ ነን፡፡" ይጠቅሳሉ፡፡

👉👉👉👉 በዚህም አላህ እራሱ ሃላፊነቱን ስለወሰደ አያሰጋንም ይላሉ፡፡

🙅‍♂🙅እንደው አላህ ይህንን ቁርአን ምን እንዳይሆን ከማን ነው የሚጠብቀው?🙅‍♂🙅‍♂ የሚለውን እንይ፦

👳‍♀👳 ሙፈሲር ኢብን አባስ👳‍♀👳 ፡-

[15:9]

(Lo! We, even We, reveal the Reminder) We sent Gabriel with the Qur'an, /ገብርኤልን ቁርአኑን አስይዘን ላክነው/ (and lo! We verily are its) the Qur'an's (Guardian) from satans /ከሰይጣን ቁርአንን እንጠብቀዋለን/ such that they do not add /እንዳይጨምሩበት/or diminish from it anything /ከውስጡ ምንም #እንዳይቀንሱበት/nor change its judgements;/ሕግጋቶቹንም #እንዳይለውጡ/ it is also said that this means: We are Guardian of Muhammad (pbuh) from the disbelievers and satans./በተጨማሪ ይህ ማለት እኛ #ከሰይጣንና #ከማያምኑት የሙሐመድ ጠባቂዎች ነን ማለት ነው፡፡/

👳‍♀👳ሙፈሲር ጃላላይን👳‍♀👳 ፡-

[15:9]

Verily it is We (nahnu emphasises the subject of inna, or [functions as] a separating pronoun) Who have revealed the Remembrance, the Qur’ān, and assuredly We will preserve it, against substitution, /በሌላ #ከመለወጥ/  distortion, /ከመበረዝ/ additions /#ከመጨመር/ and omissions. /ተገድፎ እንዳይጣል(እንዳይተው)/