ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
🔵 ቁርኣን = ዝብርቅርቅ መጽሐፍ

በስነጽሑፍ ረገድ ቁርአን ከሞላ ጎደል የተረከው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ሙሉ ታሪኩን ከምናገኘው ዮሴፍ በስተቀር የአንድን ርዕሰ ጉዳይ #መነሻና_ፍጻሜ_የሚያብራ_የአጻጻፍ_ስርዓት_የለውም፡፡ ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላው፣ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላው፣ ከአንዱ ቤተሰብ ወደ ሌላው፣ በማጣቀስ የተደራጀ መጽሐፍ ነው፡፡ ከመጥምቁ ዮሐንሰ ጀምሮ ወደ ሙሴ ይመለሳል፡፡ ስለ አብርሃም ጀምሮ ስለማይታወቅ ጉዳይ ይተርካል፡፡

📌ቁርአን ራሱን እንኳ አያብራራም፡፡ የመልዕክት ቅደም ተከተል የለውም፡፡ ከአንድ ሀሳብ ወደ ሌላው ሲዘልቅ የቋንቋን ስርዓት በጠበቀ መንገድ የማያያዣ ቃላትን (መስተዋድድና መስተፃምር) አይጠቀምም ግስና ስምን እያመሳቀለ ግራ የሚያጋባ ድግግሞሽ የበዛበት ስለሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው አይችልም፡፡ 👉የቁርአን ሊቃውንት እንኳን ሃያ ከመቶውን ወይም አንድ አምስተኛውን ያህል አልተረዱትም፡፡

🔴 በርካታ ሙስሊሞች ቁርአን አይነኬ፣ አይጠየቄ፣ አይደፈሬ፣ ተደርጎ ስለተነገራቸው ብቻ በጭፍን ድንቅነቱን ይናገራሉ እንጂ በአግባቡ ያልተረዱት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከአረብኛው ቋንቋ ውጪ የተተረጐሙትን ቁርአኖች ሙሉ ተቀባይነት ስለሌላቸው የአረብኛን ቋንቋ በከፍተኛ ዕውቀት ደረጃ ያልተረዱት ተከታዮቹ አያውቁትም፡፡ እናውቀዋለን የሚሉትም ለራሱ ለቁርአን ማብራሪያ የተዘጋጁትን መጽሐፍቶች ከመቀበል ውጪ መተርጎምም መጠየቅም መተቸት አይፈቀድላቸውም፡፡
👍1
⚫️ ሊቃውንት ስለሙስሊሞች መጽሐፍ ስለ ቁርአን የሚሉትንም ስንመለከት ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑን እናረጋግጣለን "ስልማንራይደል" የተባለው ጀርመናዊ ተመራማሪ የቁርአንን ስነ ጽሑፋዊ ይዘት ስናየው #ትኩረትን_የማይስብ_ድግግሞሽ_የበዛበትና_ማን?_መቼ?_እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ለማጥናት #አመቺ_ያልሆነ፣ 🔹የተጠየቅ እጦት የበዛበት፣🔹 ተከታታይነት በሌለው አንቀፆች የታጨቀ #የቃላት_ውርጅብኝ_ነው፡፡ ቁርአን በማንኛውም ገፅ አንባቢውን ግራ የሚያጋባ በመሆኑ ብዙ ሰዎች እሱን አንብበው ለመረዳት ጊዜያቸውን ሲያውሉ ማየት በጣም ይገርማል ብሏል፡፡ "ቴዎዶር ኖልዶኬ" የተባሉት ሌላ ተመራማሪም 🔶ቁርአን የተሯሯጠና ግራ አጋቢ አንቀፆችን፣ የደረቁ መልዕክቶች ያሉባቸው ጥቅሶችን የያዘ መጽሐፍ ነው🔶 ብለዋል፡፡

⚪️
እንግዲህ ስለቁርአን የሚያጠኑ ሰዎች ይህንን መሰል ድምዳሜ ላይ እየደረሱ ቁርአን የእነሱ እንደሆነ የተቀበሉ ሰዎች ግን አመለካከታቸው ሲመዘን ልንል የምንችለው ወይ አልተረዱትም ወይም በጭፍን መረዳት ይገዙለታል ብቻ ነው፡፡ በየቋንቋቸው ያልቀረበላቸውን እንዲቀርብም ያልፈቀደላቸውን መጽሐፍ የአረብኛውንም ቅጂ አንብበው መረዳት ሳይችሉ ቁርአን ድንቅ ነው ለምን ይላሉ?
🔴
ቁርአን በአረፍተ ነገር አወቃቀሩ ስህተተ አልባ ነው ወይ? ይህንን ጉዳይ ለአረብኛ ቋንቋ ሊቃውንት መተው ተገቢ ይመስለናል፡፡ ቁርአን በርካታ ስህተቶች እንዳሉበት ተረጋግጧል፡፡ ሙስሊሞች የቁርአን አረብኛ ያልተዳቀለ አረብኛ እንደሆነ ያምናሉ፣ 🔛 ነገር ግን አስራ አምስት 1⃣5⃣ ከሚደርሱ ቋንቋዎች እንደተዋሰ የቋንቋ ሊቃውንት ገልጠዋል፡፡ 👉ከግብፃውያን፣ 👉ከዕብራውያን፣ 👉ከሲሪያን ክርስቲያን፣ 👉ከአርማይክ፣ 👉ከሀበሻ /ግዕዝ/ ቋንቋዎች ተውሷል፡፡

ይህ የሚያሳየው መጽሐፉ ከሌሎች ቋንቋዎችም #ተቀነጫጭቦ_የተደራጀ እንደሆነ ነው፡፡ የተውሶ ቃላትን እየተጠቀመ ንፁህ ነው፣ በቀጥታ በጅብሪል አማካይነት እየተነበበ ለመሐመድ ተደምጦ፣ እሱ ደግሞ ለተከታዮቹ ተናግሮት በመጽሐፍነት ለመደራጀት ችሏል ብለን ለመድፈር እንችላለን?
የሰማይ ቋንቋ አረብኛ ነው ብለን ከወሰንን ማነው ከተጠቀሱት ቋንቋዎች ቃላትን የተዋሰው ሙስሊሞች ግን ከአላህ እንደሆነ፣ ሌላ ቋንቋ እንደሆነ ይናገራሉ መተርጎሙንም ይከለክላሉ፡፡
Answering-Islam/amharic/ለእስልምና መልስ አማርኛ
Forwarded from Ναολ Τζιγι
የሃያ እብኑ ኑህ የሚባል የሙስሊሞች "ኡዝታዝ ነኝ" ባይ፣ ከዚህ በታች ያለውን "women in bible" የሚል እውቀት ያጎደለው post ለትፎ ነበር። እኔል መልስ ሰጥቸው ነበር። እስኪ እናንተ judge አድርጉት
945858426.yeset-lj-mebt-be-baybl-mn-ymeslal-bewendm-yehya
<unknown>
💎 ሴቶችን በባይብል 💎

💨 አቅራቢ 💨

🎙🎙 የሕያ ኢብኑ ኑህ

http://Telegram.me/yahya5
Forwarded from Ναολ Τζιγι
Audio
Forwarded from Ναολ Τζιγι
👍1
Audio
Part 3... How Muslims project their own problem on the Holy Bible
Naol
አንዳንድ ሰዎች ኢሳይያስ 7፡14 ላይ የሚገኘው “…ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” በሚለው ጥቅስ ውስጥ “ድንግል” ተብሎ የተተረጎመው “አልማህ” የሚለው የእብራይስጥ ቃል “ወጣት ሴት” ተብሎ መተርጎም እንዳለበት ሲናገሩ እያየሁ ነው፡፡ በነዚህ ሰዎች መሠረት “ድንግል” ለሚለው ትክክለኛው የእብራይስጥ አቻ “ቤቱላህ” የሚል በመሆኑ ኢሳይያስ 7፡14ን “ድንግል” ብሎ መተርጎም ስህተት ነው፡፡
ይህ ሙግት በሚከተሉት ምክንያቶች በእጅጉ የተሳሳተ ነው፡፡
1. በእብራይስጥ ዲክሺነሪ መሠረት “አልማህ” የሚለው የእብራይስጥ ቃል ወጣት ሴትን የሚያመለክት ሲሆን “ድንግል” የሚለው ከቀጥተኛ ትርጉሞቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ https://www.bibletools.org/index.cfm/fuseaction/Lexicon.show/ID/H5959/%60almah.htm
2. በእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “አልማህ” የሚለው ቃል ድንግል የሆኑ ሴቶችን ለማመልከት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ድንግል ያልሆነችን ሴት ለማመልከት አንድም ጊዜ ጥቅም ላይ አልዋለም፡፡ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር እንዲህ ይላሉ፡- "There is no instance where it can be proved that 'almâ designates a young woman who is not a virgin. The fact of virginity is obvious in Gen 24:43 where 'almâ is used of one who was being sought as a bride for Isaac." (R. Laird Harris, et al. Theological Wordbook of the Old Testament, p. 672.)
የአንድ ቃል ትርጉም የሚወሰነው በዲክሺነሪ ትርጉሙ ብቻ ሳይሆን በአንድ መጽሐፍ ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋለበት መንገድ በመነሳትም ነው፡፡
3. በእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ “ቤቱላህ” የሚለው ቃል ድንግል ያልሆነችን ሴት ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ለምሳሌ ያህል ኢዩኤል 1፡8 ላይ ባል ያላት ሴት “ቤቱላህ” ተብላለች)፡፡
4. የዚህ ሙግት አቅራቢዎች “አልማህ” የሚለውን ቃል “ድንግል” ብለው የተረጎሙት ክርስቲያኖች እንደሆኑ በማስመሰል ቢናገሩም ቅሉ ይህንን ቃል “ድንግል” ብለው ወደ ግሪክ የተረጎሙት የመጀመርያዎቹ ተርጓሚዎች ከክርስቶስ ልደት በፊት የኖሩት አይሁድ ነበሩ፡፡ እነርሱ ምን የተለየ motive ኖሯቸው ይሆን ይህንን ቃል “ድንግል” ብለው የተረጎሙት?
ከዚህ ሁሉ የምንረዳው የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ኢሳይያስ 7፡14 ላይ የሚገኘውን “አልማ” የሚለውን ቃል “ድንግል” ብለው መተርጎማቸው ትክክል መሆኑን ነው፡፡
ከአዋቂ መሳይ አላዋቂዎች ተጠበቁ!
1👍1
📌ሐዋርያው ጳውሎስ በቁርአን📌
ሙስሊሞች፣ መፅሐፍ ቅዱስ እና ቁርአን መስማማት እንደማይችሉ ከተረዱ በኋላ ማድረግ ያለባቸዉ ነገር፥ ቁርአን ትክክል እንዲሆን መፅሐፍ ቅዱስን ሐሰት ማድረግ ነው። 🔑ምክያቱም ሁለት ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ ነገሮች ሁለቱም ሐሰት ወይም ከሁለት አንዱ እዉነት እንጂ ሁለቱም እዉነት ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ የለም።

ስለዚህ መፅሐፍ ቅዱስን ሐሰት ለማድረግ ደግሞ ምክንያት ያስፈልጋል። ያልተበረዘውን ቅዱስ መጽሐፍ፣ "ማን በረዘዉ?" የሚለዉ መሬት ያልረገጠው ጥያቄ እስካሁን መልስ አላገኙለትም፡፡ ግን ዝም ከማለት ይሻላል፥ በማለት "አንድ ሰዉ በረዘው" የሚል ወቀሳ ይሰነዝራሉ። ለዚህም፣ "መፅሐፍ ቅዱስን ኢየሱስ በረዘው፤" እንዳይሉ በቁርአን የኢየሱስን ያህል የተከበረ ሰዉ የለም። (2:87፣ 4:171፣ 5:110፣ 19:19፣ 43:61) "የእሱ ሐዋርያት በረዙት፤" እንዳይሉም አላህ እነሱን እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የበላይ እንደሚያደርጋቸዉ ቃል ገብቶላቸዋል። ስለዚህ በማን ይመካኝ? ብለዉ ሲያወጡና ሲያወርዱ ከኢየሱስና ከሐዋርያቱ ዉጭ በክርስትና ላይ ትልቅ አሻራ ያለዉ ሰው አስፈለጋቸዉ። ይህ ሰው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ነዉ።
👍1
ከመፅሐፍ ቅዱስ ስለ ቅዱስ ጳዉሎስ ለማወቅ የሐዋርያት ስራን ማንበብ ብቻ በቂ ነው። እንግዳ ሊሆን የሚችለዉ ጥያቄ ግን፣ "ቅዱስ ጳዉሎስን ቁርአን ያውቀዋል ወይስ አያውቀውም?" የሚለው ነው። ብዙዎቻችን፣ ሙስሊሞችን ጨምሮ ኧረ በፍፁም አያውቀውም እንደምንል አልጠራጠርም። ከዛሬ ጀምሮ ግን እንወቅ፣ ቁርአን ቅዱስ ጳዉሎስን ያውቀዋል። የሚያውቀውም የዘመናችን ሙስሊሞች በሚሉት መልኩ ሳይሆን እጅግ ጠንካራና አበርቺ ሆኖ የተላከ መልዕክተኛ እንደሆነ ነዉ የሚያውቀዉ። ባያውቀውም ግን ምንም የሚቀርበት ነገር የለም፡፡

ቅዱስ ጳዉሎስ እዉነተኛ ነቢይ ነዉ የሚለዉ የቁርአን ክፍል ይህ ነዉ::
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
“ወደነርሱ ሁለት ሰዎችን በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ፣ በሦስተኛው አበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ፣ (የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)።” (ሱረቱ ያሲን (የያሲን ምዕራፍ) 36:14)
😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔😔
አሁን እዚህ ጋር ጳዉሎስ የሚለዉ የታለ? ትሉ ይሆናል:: ደግሞም ብላችኋል ግን አልተሳሳታችሁም ልክ ናችሁ "ጳዉሎስ" የሚል ስም የለም። ነገር ግን፣ ቁርአንን ለመረዳት የቁርአን መተርጉማን (ሙፈሲሮች) የተናገሩትን ማየት ያስፈልጋ፤ እንጂ ቁርአንን (ቁርአን የቃላት ውርጂብኝ ብቻ ስለሆነ) በቁሙ በማንበብ ብቻ መረዳት በፍጹም አይቻልም፡፡ ይሄንን ሙስሊሞችም ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ።
የቁርአን ትርጉም ተፍሲር ይባላል። በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮች ደግሞ ኢብን ካቲር እና አል ጃለሊን ናቸው። ከነዚህ ውስጥም እንደ #ኢብን_ካቲር ያለ ተቀባይነት ያለው ተፍሲር የለም። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይም የምናየው የኢብን ካቲርን ተፍሲር ይሆናል። እንዲህ ይላል:-

📚“(በሶስተኛዉ አበረታናቸዉ) ማለት፣ “እኛ በሶስተኛዉ መልዕክተኛ ደገፍናቸዉ ፣ አበረታናቸዉ” ማለት ነው። ኢብኑ ዩራይጅ ከ ዋህብ ኢብኑ ሱለይማን እና ከሹአይብ ያባይ እንዳስተላለፉት:-“ የመጀመሪያዎቹ የሁለቱ መልዕክተኞች ስም #ስምኦን(#ጴጥሮስ) እና #ዩሐንስ የሶስተኛዉ ስም ደግሞ #ጳዉሎስ ነበር። ከተማዋም አንፆኪያ ነበረች።”📚😳😳😳😳

እንግዲህ ምን ትሉ ይሆን? የዘመናችን ሙስሊሞች በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚያዘንቡት መሠረት የለሽ ውርጅብኝ ከየት የመጣ ነው? እናንተ ከመተርጉማኖቹ (ሙፈሲሮች) ትበልጣላችሁን? ማነዉ ሶስቱን የላካቸው? አላህ አይደለምን? ደግሞም የቅዱስ ጳውሎስ መምጣት ምን ያህል #_አበረታችና_አፅናኝ እንደነበር ተመልከቱ:: ማን ነው የሳተው? አላህ ወይስ በአላህ የተላከው ጳውሎስ ወይስ የዘመናችን ካለ ማስረጃ የሚለፈልፉት ሙስሊሞች

ይሄን አላምንም የሚል ሰው ካለ ከራሳቸው ከሙስሊሞች ድረ-ገፅ በመግባት ማየት ይችላል። ለማረጋገጥ የፈለገ ሰው “www.qtafsir.com” በመግባት የቁርአኑን ምዕራፍና ቁጥሩን በመፃፍ በአረበኛም በእንግሊዝኛም ማየት ይችላል።
👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳
ሙስሊሞች ደግሞ በተራችሁ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ሐሰተኛነት ከቻላችሁ እንደኛ ከቁርአን ተፍሲር ካልቻላችሁ ከሐዲስ ማሳየት ትችላላችሁ። እኛ እውነተኝነቱንና የተላከውም በአላህ እንደሆነ አሳይተናል።

http://www.qtafsir.com/index.php?option=com_content&task=view&id=1491&Itemid=
በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሠላም ይብዛላቹህ፡፡ ከዚህ በላይ በተለቀቀው ጽሑፍ ምክንያት በተለያዩ ግሩፖች ያሉ ሙስሊም ወገኖቻችን፥ ጥያቄዎችን እያነሱ ይገኛሉ፡፡ ጥያቄውን ባሉበት ቦታ ምላሽ ለመስጠት ብንሞክርም በተለመደው ረብሻቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ጥያቄአቸውም ሙፈሲር ኢብን ከቲር በሱረቱ ያሲን 36:14 ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ፤ ማለትም፦

"(So We reinforced them with a third,) means, We supported and strengthened them with a third Messenger. ' Ibn Jurayj narrated from Wahb bin Sulayman, from Shuayb Al-Jaba'i, "The names of the first two Messengers were #Sham`un and #Yuhanna, and the name of the third was #Bulus, and the city was Antioch (Antakiyah)."

ሲሆን በማብራሪያው ውስጥ "ስምኦን(ጴጥሮስ)፣ ዮሐንስና ጳውሎስ" የሚል የለም፤ ከኪሳቹህ ነው የጨመራችሁት፣ የሚል ነው፡፡ በተፍሲሩ የተጠቀሱት ስሞች Sham'un, Yuhanna እና #Bulus ሲሆኑ፥ ከዚህ የተነሳ ስሞቹ ስምኦን (ጴጥሮስ)፣ ዮሐንስና ጳውሎስ ከሚለው ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፥ የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ሊነሳ የቻለው፥ በቅጡ የስም አጠቃቀምንና የቋንቋ ስርዓትን ካለመረዳት ነው፡፡

ዋናው ርዕሳችን በሆነው በጳውሎስ ላይ ያለውን ምላሽ እናቅርብና፣ የተቀሩትንም ስሞች በተመሳሳይ አካሄድ ምላሻቸውን ማግኘት ይቻላል፡፡ "ጳውሎስ" ብለን ያስቀመጥነው #የአረብኛው_ቃል 👉Bulus የሚል ሲሆን፣ የቃሉ ፆታ (የአንዳንድ ቋንቋዎች ቃላት ፆታ አላቸው፦ ለምሳሌ ግሪክኛ) Masculine (ወንድ) ሲሆን፣ Usage፦ አረብኛ ነው፡፡ ሲነበብም "BOO-loos" የሚል ነው፡፡ ይህ አረብኛ ቃል በተለያዩ ቋንቋዎች የተለያየ የመጠሪያ ንበት አለው፡፡

🔵 ስለዚህ #Bulus ለሚለው የአረብኛ ቃል፣ ወደ እንግሊዘኛ ሲመለስ #Paul ሲሆን፣ ወደ አማርኛችን ሲመጣ ደግሞ #ጳውሎስ የሚል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ኢብን ከቲር "Bulus" ሲል "ጳውሎስን" እየጠቀሰ ነው ማለት ነው፡፡

ሙስሊሞች "Bulus" የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰውን ሐዋርያው ጳውሎስን አያመለክትም ካሉ፣ በአንጾኪያ ያለ የትኛውን ጳውሎስ እንደሚያመለክት ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
የ ዋሒድን የተሳሳተ መረጃ ከዚህ በታች እንመልከት
See the response 👆
ቀጥለን የቁርአንን ጥንታዊ የሚባሉ ቂጂዎች ጉድ የምናይ ይሆናል።