ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ለተወሰኑ ጊዜያት ጽሑፍ ከመጻፍ ጠፍተን ነበር፤ አሁን ግን በተቻለን መጠን ፅሁፎችን እናስቀምጣለን፡፡
[የተቀመጡ ሊንኮችንም በመንካት ሄደን ብናነብ በብዙ እንጠቀማለን፡፡ ካልሆነ ለዚህ ግሩፕ በሚመች መልኩ እናቀርበዋለን።] ተባረኩ፣ አሜን!

👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- መሐመድ ሽፍታነትን ሲያካሂድ ንፁሃን ሰዎችን #ሲገድልና_ሲያስገድል በአንዳንድ መገለጦቹ ላይ ደግሞ #አላህ_ሐሳቡን_ቀይሯል ሲል በአረቢያ በነበሩ አረቦች ያለምንም ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ጥያቄ ውስጥ አስገባው ነበር፡፡

"ከተከበረው ወር (ከረጀብ) በርሱ ውስጥ ከመጋደል ይጠይቁሃል በላቸው በርሱ ውስጥ መጋደል ታላቅ (ኃጢአት) ነው ግን ከአላህ መንገድ (ሰዎችን) መከልከል በርሱም መካድ ከተከበረውም መስጊድ (ማገድ) ባለቤቶቹንም ከርሱ ማውጣት አላህ ዘንድ ይበልጥ ታላቅ (ወንጀል) ነው ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመኾን አይቦዝኑም ከናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ኾኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱ በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች እነዚያ የእሳት ጓደኞች ናቸው እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው" (2:217)፡፡

♻️ መሐመድ በመጀመሪያ በቅዱስ ወር ውስጥ ጦርነትን አላደረገም ነበር ደግሞም ጦርነት ካደረጉት ሰዎች ምርኮን አይካፈልም ነበር፡፡ በኋላ ግን ቆይቶ ሐሳቡን በመቀየር በቁርዓን ውስጥ እንዲቀመጥ አደረገ፡፡ ከዚህም በላይ በተጠቀሰው ቁርዓን ጥቅስ ውስጥ እንዲረጋገጥ አደረገ፡፡

👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- 👭ሴቶች🤦‍♀ ከወንዶች እኩል የሆነ መብት ለምን እንደማይኖራቸው እጠይቅ ነበር፡፡ መሐመድ ሴቶች አዋቂዎች አይደሉም ብሎ በመናገሩ የተነሳ ግማሽ ቢሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ሉሙሉ የሰብኣዊ መብታቸውን ተነጥቀዋል፡፡

እኔ ሙስሊም ብሆን ኖሮ በዚህ የእኩልነት ጉድለት የተነሳ በጣም እቸገር ነበር፡፡ በምዕራቡ ዓለም ውስጥ እጅግ በጣም አስደናቂ የሆኑ ብዙ ግኝቶች፣ አዳዲስ ነገሮች በሴቶች ተፈልስፈዋል እንዲሁም ተገኝተዋል፡፡ በእስላማዊ አገሮች ውስጥ ለሴቶች አዕምሮ የዝቅተኛነት ቦታ ስለተሰጠው የጎደለውን ሳስብ አሁንም ጥያቄ ያድርብኛል፡፡

"ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው በመኝታዎችም ተለዩዋቸው (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዡዋችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና" (4:34)፡፡

ይህንን አንድ ሰው ⛪️ከክርስትያን⛪️ አመለካከት ጋር ሊያነፃፅረው ይችላል "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።"

(ገላትያ 3.28)፡፡
👳‍♀ሙስሊም👳 ብሆን ኖሮ፡- አንድ ሙስሊም ሰው የሲዊድናዊትን ሴት በመድፈሩ ትክክል እንደሆነ የሚቆጥርበትንና፣ አንድ ሲዊድናዊ ሰው ግን አንዲትን ሴት በሃይማኖት ምክንያት መድፈሩን ትክክል አይደለም ሲለው ሙስሊሙ ግን ትክክል ነው በማለት የሚናገረውን ሳስብ ጥያቄ ያድርብኛል፡፡

የትኛውምየአይሁዳዊም ሆነ የክርስትያን ቅዱስ መጽሐፍና ጽሑፍ ሴትን ስለመድፈር ምንም ድጋፍን አይሰጥም፡፡ (ፍትሃዊ ነው አይልም)፡፡ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ይህ ከስነ ምግባርና ከትክክለኛ አስተሳሰብ የመነጨ እንዳልሆነ ነው የማስበው፡፡

በሲዊድን ውስጥ የተዘጋጀ ጥናት እንደሚያሳየው፡ "ወንጀልን በመከላከል ካውንስል ‹ብራ› መሠረት ሴቶችን አስገድደው ደፋሪዎች በመሆን ከታወቁት መካከል አራት እጥፍ የሚሆኑት ከሲዊድን ውጭ የተወለዱ ናቸው፡፡ ይህም በሲዊድን ውስጥ ከተወለደው ጋር ሲነፃፀር ነው፡፡ ከአልጀሪያ፣ ከሊቢያ፣ ከሞሮኮ፣ እና ከቱኒዝያ የሆኑት መጤዎች ናቸው የአስገድዶ መድፈር ቡድን ውስጥ በብዛት ያሉበት፡፡ በዚህ የጥናት ዝርዝር መሠረት ብዙዎቹ ወንጀለኞች መጤዎቹ ናቸው፡፡"
ይቀጥላል...
ዛሬ ተከታዮቹ ጽሑፎች ለንባብ በቅተዋል፦

መጽሐፍ ቅዱስ - ወደር የማይገኝለት ግሩም መጽሐፍ!

እስላማዊ አጣብቂኝ :- መጽሐፍ ቅዱስ ከተበረዘ ቁርኣን ዋሽቷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ካልተበረዘ ቁርኣንየፈጣሪ መጽሐፍ አይደለም!

ስለመሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተተንብዮአልን?

የቁርአን ታሪካዊ ስህተቶች

http://www.ewnetlehulu.org/am/new-articles/
መጽሐፍ ቅዱስና ሥነ-ቁፋሮ
👇👇👇👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/archeology
👉የመድኋኒታችና የአምላካችን
የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል
🙌 ሰላም የጌታ ቤተ-ሰዎች ረዘም ላለ ጊዜ ሳንገናኝ ብንሰነብትም እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ዛሬ አንድን ነገር ወደ እናንተ ልናደርስ በቅተናል። ይህም የሆነው ከታላቁ ከእግዚአብሄር ቸርነትና ምህረት የተነሳ ነውና እናተም ለቀጣይ ስራዎች እግዚአብሄር እንዲረዳን ማሳሰብን አትተዉ!!!🙏🙏🙏
በቅርቡ "ወንጌል" በሚል ርእስ 👳‍♀በወሒድ ዑመር በአራት ተከታታይ ክፍሎች ተዘጋጅቶ በማህበራዊ ድህረ-ገፃች የተለቀቀውን የተለመደ ማደናገርያ በመመልከት ላቀረባችሁት ጥያቄ🤔 በተከታታይ የማያዳግምን ምላሽ🔍🔑🗝 የምንሰጥበት ይሆናል💡። ይህንንም በቅርቡ በድምፅ 🗣 ከክፍል አንድ በመጀመር የምንለቅ ቢሆንም ለመግቢያ ይክል ግን ከክፍል አንድ መልስ ላይ የተቀነጨበን ሐሳብ በፅሁፍ እነሆ፦
....መልስ፡-
የመጀመሪያው መነጽሩ ልክ አይደለም፡-

ወንጌልን ሊያይበት የሞከረበት መነጽር ቁርአን ነው፤ ታዲያ መነጽሩ ጤናማ መነጽር ነውን? ቁርአን በሚባል መነጽርስ መጽሐፍ ቅዱስን መገምገም ይቻላል? መለኮታዊ መጽሐፍ ቢሆን በእርግጥ መልስ ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ቁርአን መለኮታዊ መጽሐፍ ባለመሆኑ በእርሱ መጽሐፍ ቅዱስን ለመገምገም መሞከር ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ቁርአንን በምን ተመዝኖ ነው መለኮታዊ አለመሆኑ የተረጋገጠው ትሉኝ ይሆናል፤ በራሱ መለኪያዎች ተመዝኖ፡፡ ቁርአን የራሱን መለኮታዊነት ያሳዩልኛል ያላቸውን አምስት መለኪያዎች አስቀምጧል፡-

1:-እንደ ሱረቱል አል-ሐቅ 69 ፡ 50-51 እውነተኝነት የሚለው የመጀመሪያው ነው፤ ነገር ግን ቁርአን በብዙ ሳይንሳዊ፣ መቸታዊ፣ ታሪካዊ፣ ሒሳባዊ ስህተቶችና ሐሰቶች የተጨናነቀ መጽሐፍ በመሆኑ መለኪያውን አያልፍም፤

2:-በበርካታ አንቀጾች እንደተገለጸው ከአላህ ዘንድ የወረደ መሆን ይኖርበታል የሚል ነው፤ ነቢዩ ራእይ እንዴት እንደሚወርድላቸው ሲጠየቁ መልአኩ አንዳንዴ በደወል ድምጽ እየተናገረ እንደሚመጣ ተናግረው ነበር፤ የሚገርመው ይህ ድምጽ ሰይጣንን አላህ በረገመው ጊዜ መልኩ ከመላእክት መልክ ወደ ሌላ ሲቀየር ድምጹም ወደ ደወል ድምጽ ተቀይሮ ነበር፡፡ ስለዚህ እርሳቸው ጋር ይመጣ የነበረው ጅብሪል ሳይሆን ሰይጣን ነበር ማለት ነው፡፡ እናም አሁንም ቁርአን ከአላህ ዘንድ የወረደ መጽሐፍ ባለመሆኑ ይህንን መለኪያ አላለፈም፡፡

3:-እንደ ሱረቱል አል-ኒሳእ 4 ፡ 82 እርስ በእርሱ የማይቃረን ሊሆን ይገባል የሚል ነው፤ ነገር ግን እንደ ቁርአን በምድር ላይ እርስ በእርሱ የሚቃረን መጽሐፍ ታይቶ ተሰምቶም አይታወቅም፤ ስለዚህ በዚህም መለኪያ ቁርአን ከመለኮታዊ ቃልነት ውድቅ ይሆናል::

4:-የሰውና የሰይጣን ጣልቃ ገብነት የሌለበት የሚለው ሌላው መለኪያ ነው፡፡ ቁርአን ሰውና ሰይጣን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም ጣልቃ ገብተው ያዋጡለት መጽሐፍ ነው፡፡

5:-እንደ ሱረቱል አል-ሒጅር 15 ፡ 9 በአላህ ጥበቃ ውስጥ የኖረ የሚለው የመጨረሻው ነው፤ ሆኖም ቁርአን አንዴም በአላህ ተጠብቆ እንደማያውቅ ታሪኩን የሚያውቁ የሚመሰክሩት ነው፡፡
ቁርአን የራሱን መለኪያዎች ባለማሟላቱ መለኮታዊ ቃል አለመሆኑን አስመስክሯል፡፡ እናም የጠራ መነጽር ሊሆን አይችልም ማለት ነው፡፡ አንዴ ኡስታዝ ሳዲቅ ኢስላም ብቸኛው መለኮታዊ ሃይማኖት በሚል ርእስ ባዘጋጀው ሲዲ፡- "ሰው በተሰነጠቀ መስታውት ፊቱን አይቶ ማማር እንደማይችለው ሁላ የቁርአንን መልእክት ለመረዳት በራሱ በቁርአን መነጽር ማየት ያስፈልጋል፡፡" ብሎ የተናገረው ትዝ አለኝ፡፡ ይኸው አየነው እንግዲህ ዋሂድ አጥርቶ ለማየት ቅድሚያ መነጽሩን ማስተካከል ያስፈልገዋል፡፡
ሌላው ቁርአን የጠራ መነጽር የማይሆንበት ምክንያትም በየዘመናቱ የሚኖሩ ሕዝቦችን ሊመራ የሚችል ማንነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ሰው በቁርአን መመራትና መዳኘት ካለበት ሁሌ ቁርአን በወረደበት ሰበብ ሁኔታ ውስጥ መገኘት ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የቁርአን ለ 20 ወይም 23 ዓመታት ሲወርድ የወረደው በጊዜው ይከሰቱ ለነበሩ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ለዚህ ዘመን የሚሆን ምንም ነገር የለውም፤ ለክስተቶቹ ያኔውኑ ምላሽ ሰጥቶ ሒሳብ ዘግቷል፡፡ አሁን እስልምና እየተመራ ያለው በተወሰኑ ኡለማዎች ፈትዋ ነው፡፡ ያም በመሆኑ ወደ የትኛውም የምድር ጥግ ድረስ ቢኬድ አንድ ወጥ መሪና አስተዳዳሪ የሆነ የሸሪአ መጽሐፍ ማግኘት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ቁርአን መነጽር ሆኖ ሊያገለግ አይችልም፡፡
የዋሒድ የጠቃቀሳቸው የቁርአን አንቀጾች በግድ እንዲጮሁ መደረጋቸው ሌላው ስህተት ነው፡-

አውራ መስሎ ለመታየት የሚደረግ መንፈራገጥ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ዋሂድም በዚህ ችግር ተጠምዷል፡፡ አንቀጾቹን ከእርሱ በፊት እርሱ ሊጠቀምበት ላሰበው ዓላማ በብዙዎች ሲጠቃቅሷቸው ከርመዋል፤ አዲስ አይደሉም፡፡ ዋሂድ በጀሮ ጠገብ የሚኖር ባይሆን ኖሮ ቁርአን መለኮታዊ ቃል አለመሆኑን ስለሚያሳብቁበት አይጠቅሳቸውም ነበር፤ እስኪ የተወሰኑትን አንቀጾችን እንውሰድና እንገምግመው፡-
ወንጌሉ ከሌላ መቀላቀሉን ለማሳየት የተጠቀሱት የቁርአን አንቀጾች 2 ፡ 79 እና 3 ፡ 71 ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ አንቀጾች የተባለውን ለማለት የወረዱ ናቸውን? አይደሉም፡፡ እነዚህ አንቀጾች የወረዱት የመጽሐፉ ሰዎች የተባሉት የነቢዩ ሙሐመድን ባሕሪ እያወቁ "ከሐሰተኛው ክርስቶስ" ጋር በማመሳሰላቸው፤ ሌላኛው ነቢዩ ሙሐመድ በመጽሐፎቻቸው ቡናማና መካከለኛ ተብሎ የተገለጹበትን መልክና ቁመና ነጭና ረዥም በሚል በመተካታቸው እርሱን ለማስተባበል የወረዱ ነበሩ፡፡ ታዲያ ከየት አምጥቶ ነው ዋሂድ እንዲያ የሚያናግራቸው? ይህንን ጠቅሶ ወንጌሉ ተበርዟል ማለት በየትኛውም የተፍሲር ሕግ ተቀባይነት የለውም፡፡ መዲና የነበሩ የመጽሐፉ ሰዎች አድርገዋል እንኳን ቢባል የሆነው መዲና ውስጥ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ አንድ መጽሐፍ ሆኖ አገራትን ከናኘ በርካታ መቶ ዓመታትን አሳልፏል፡፡ ድርጊቱም ነገሩ ከነበሩበት ጊዜና ክልል የዘለለ አይሆንም፡፡ ስለዚህ አባባሉ ሌሎችን ሊወክልና መርህ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ደግሞ መለኮታዊ ቃል ላለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡
ሌላው የተጠቀሰው 5 ፡ 1 5 ነው፡፡ ይህ አንቀጽ የወረደው ከላይ የተገለጹትን አሳብና አመንዝራን በድንጋይ ወግሮ ስለመግደል የሚያዘውን የመጽሐፍ ክፍል መደበቁን ለመንቀፍ ነው፡፡ ተቀባይነት ያላቸው ሙፈሲሮች ሁሉም በዚህ ይስማማሉ፡፡ አመንዝራን በድንጋይ በመውገር የመቅጣቱን ጉዳይ የሚያይዘው በዛው ምእራፍ አንቀጽ 42-48 ካለው ጋር ነው፡፡ ይህ የቁርአን ክፍል የወረደው በሁለት አመንዝረው በተያዙ የመዲና አይሁዶች ምክንያት ነው፡፡ ነቢዩ እንዲፈርዱ ተጠየቁ ለዚህ አይነት ኃጢአት ቶራው ምን እንደሚል መልሰው ጠየቁ፤ ቶራው ተነበበ ይገደሉ ስለሚል ፍርዱን በቶራው መሰረት አስፈጸሙባቸው፡፡ በዚህ ላይ ተሸሸገ የተባለው ይገደል በሚለው ቃል ላይ አንባቢ የነበረ ሰው እጁን በመጫኑ ነበር፡፡ ያ ማለት ያኔ በነበረው የቶራው መጽሐፍ ውስጥ እንደ ነበር እንዳልተበረዘ ያሳያል፡፡ የአንቀጹ መውረድ ክርስቲያኖች የደበቁትን አመንዝራን በድንጋይ ወግሮ የመግደል ሕግ ለመግለጥ ከሆነ የገለጠበት አንቀጽ የት ገባ? አመንዝራን በድንጋይ ስለመውገር የሚናገር የቁርአን አንቀጽ የት አለና፡፡ አንቀጹ በሌለበት ገላጭ ሊባል አይችልም፡፡ እንዲያውም አይሻ ባስተላለፈችው ሐሰን ደረጃ ባለው ሐዲስ አንቀጹ ተጻፈበትን የኮባ ቅጠል ያሳደጓት ፍየል እንደበላች ተናግራለች፡፡ ሕጉ ያኔም አሁንም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ አላህ ደበቃችሁት ብሎ ለምን ይዋሻል? አላህ የማይዋሽ ከሆነ ደግሞ ቁርአን የሌላ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ ዋሂድ ቁርአን ያልተናገረውን እንደተናገረ ማስመሰሉ ቅጥፈት አይደለም ትላላችሁ? ስለዚህ ይህንን አንቀጽ ጠቅሶ ወንጌል ተበርዟል ማለት ፈጽሞ ስህተት ነው፡፡
ዋሂድ ይህንን የቁርአን አንቀጽ ከካርቴጅ ጉባኤ ጋር በማያያዝ ያኔ ካነን ሲካሔድ መሰወሩ እንደተከናወነ ለማሳየት ይሞክራል፡፡ ይህ ደግሞ የዋሒድን እውቀት ጉድለት የሚያሳይ ነው፡፡ መቸም የቁርአንን ታሪክ የሚያውቅ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዟል ለማለት እንዲህ አይነት ጉባኤን እንደማስረጃ ሊጠቅስ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ላይ የተሰራውን ወንጀል ስለሚያውቅ ተመልሶ እንዳይተኮስበት ይጠነቀቃል፡፡ ዋሂድ ግን ከዚህ የራቀ የሰማውን እንደገደል ማሚቶ የሚያስተጋባ ጀሮ ጠገብ ሰው መሆኑን ያሳያል፡፡ ካነን መለኮታዊ መጽሐፍትን መለኮታዊ ካልሆኑት መለያ እንጂ እንደ ከሊፋ ኡስማን አዲስ ጽሁፍ ማዘጋጃ አልነበረም፡፡
ይቀጥላል....ተባረኩ!!!
በሳሂህ ኢማን
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታውያ የእጅ ጽሑፎች (Manuscripts)
👇👇👇👇👇
http://www.ewnetlehulu.org/am/the-holy-bible/manuscripts/
ሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድ ክፍል ሦስት፦

በቀደሙት ሁለት ዳሰሳዎቼ እስልምናና ሙሀመድ በክርስትና ዐብይ አስተምህሮ ማለትም በጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ ያላቸውን አባይ ምስክርነት ለመቃኘት ሞክሬ ነበር፡፡ ለዚህም እስልምናና ሙሀመድ በጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ የሰጡት ምስክርነት ዋሾ የሚሆንበትን ምክንያቶች ስነቅስ የእስልምናና የሙሀመድ የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ቅጥፈት አስቀድሞ ከብዙ ዘመናት በፊት በቅዱሳን ነብያት የተነገረ የታመነ ምስክርነትን ሽምጥጥ አድርጎ የካደ እንደሆነ በወፍ በረር ጠቅሼ ነበር፡፡ በክፍል ሦስት ዳሰሳዬ በጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ አስቀድሞ በቅዱሳት መፅሀፍት የተነገረውን፣ የሀዲስ ኪዳን ፀሀፍትና ቅዱሳን ሀዋሪያት የጠቀሱትን ፣ በብሉዩ በታመኑ ነብያት የተሰጠውን የታመነ ምስክርነት 🔎አስቃኛለሁ🔍፡፡
1⃣ የክስተቱ የቅርብ የአይን እማኝ የነበረው ሀዋሪያው ቅዱስ ዮሀንስ የአሟሟቱን ክስተት ከተረከ በኋላ የሰጠው አማኝነትና የተፈፀመውን የትንቢት ቃል እንዲህ አስፍሮታል ፦
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19)
32፤ ጭፍሮችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤ 33፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ 34፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ። 35፤ ያየውም መስክሮአል፤ ምስክሩም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል።
36፤ ይህ የሆነ። ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። 37፤ ደግሞም ሌላው መጽሐፍ። የወጉትን ያዩታል ይላል።
በዚህ ክፍል ሀዋርያው ዮሀንስ ኢየሱስ ቀድሞ በመሞቱ አጥንቱ አለመሰበሩና በጦር መወጋቱ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት ፍፃሜ እንደሆነ በወነጌሉ አስቀምጦልን አልፏል፡፡ አጥንቱ እንደማይሰበር፦ ዘፀ 12:46 , ዘሁ 9:12, መዝ 34:20, የወጉት ያዩታል፦ ዘካ 12:10.
2⃣ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 53፡፡ ይህን የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ መከራ ፣ ሞት ብሎም መቀበር የተተረከበትን ትንቢታዊ ምዕራፍ በበርካታ የሀዲስ ኪዳን ወንጌላትና መልዕክቶች ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡፡ 53:5-6 ያለውን ሐዋሪያው ጴጥሮስ በ1ኛ ጴጥ 2:24 ላይ ጠቅሶት እናገኛለን፡፡ 53:4 ያለውን ሐዋሪያው ማቴዎስ በ ማቴ 8:17 ላይ ጠቅሶት ይገኛል፡፡ በ53:9 መቃብሩ ከባለጠጎች ጋር እንደሚሆን የተነገረው ቃል መፈፀሙ በ ማቴ 27:57-60 ተዘግቦ እናገኛለን፡፡ በ53:12 ከወንበዴዎች ጋር መሠቀሉን ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ የሚለው ፍፃሜ መሆኑን ቅዱስ ማርቆስ በ ማር 15:28 አስፍሮታል፡፡
3⃣ በሌላው የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ መከራ የተተረከበት ትንቢታዊ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 22 በበርካታ የወንጌል ክፍሎች ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ከእነዚህም መሀል፦ በማር 15:34 እና በማቴ 27:46 ተዘግቦ የምናገኘውን የጌታችንን የመስቀል ላይ የጣር ጩኸት መዝሙረኛው በምእራፍ 22:1 ላይ የመሲሁን የጣር ጩኸት በትንቢታዊ እይታ አስፍሮታል፡፡ " አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ?"
(መዝሙረ ዳዊት 22:1)፡፡ ሌላው በአራቱም ወንጌላት ሰፍሮ የምናገኘው ወታደሮቹ የጌታችንን ልብስ ዕጣ የተጣጣሉበትን ትረካ በቁጥር 18 ላይ የተተነበየው ፍፃሜ መሆኑን ወንጌላውያኑ ዘግበውልናል፡፡ መዝ 22:18 👉 ዮሀ 19:23-24, ማቴ 27:35, ማር 15:24, ሉቃ 23:34.
4⃣ በመዝሙር 16:8-10 የተነገረው ቃል ሐዋርያው ጴጥሮስ 3000 ሰዎች ባመኑበት የበዐለ ሀምሳ ስብከቱ ስለ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት እንደሆነ አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሐዋ 2:24፡፡ እንዲሁም ሐዋሪያው ጳውሎስ መዝ 16:8-10 ጨምሮ መዝ 2:7 ስለ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት እንሚናገር የታመነ ምስክርነቱን ሰጥቶ አልፏል፡፡
ታዲያ ስለ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ እንዲሁም ሞትና ትንሳኤ ከዘመናት አስቀድሞ በታመኑ ነብያት በሙሴ፣ በዳዊት፣ በዘካሪያስ እና ሌሎች ይህን የሚያህል ከተነገረለት ቀጥሎም በቅዱሳን ሐዋርያትና ወንጌላውያን ያ አስቀድሞ የተነገረው ትንቢት ፍፃሜ ማግኘት ከተረጋገጠ በኋላ ያውም በአይን እማኝነት፤ አባይ ምስክሩ ሙሀመድ ክስተቱ ከላፈ 500 አመታት በኋላ ብቅ ብሎ አልገደሉትም አልሰቀሉትም ብሎ እርፍ፡፡የሀሰት ምስክር ይሏል ይሄ ነው፡፡ ውድ አንባቢ ስለ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ሙሀመድ በቁራን ሱረቱል አል ኒሳዕ 4:157-158 የሰጠው ምስክርነት የለየለት ውሸት መሆኑን ተገንዘብ ያም ማለት ቁርዐን የፈጣሪ ቃል አይደለም ሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድም የፈጣሪ መልዕክተኛ ሊሆን አይችልም፡፡
" የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34)
ዮሴፍ:
ሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድ ክፍል አራት፦

የዚህ ቻነል ተከታታይ የሆናችሁ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዲሁም ሙስሊም ወገኖች ሰላም ይብዛላችሁ፡፡ በቀደሙት "የሀሰተኛው ምስክር ሙሀመድ" ሙግቶቼ ሙሀመድና ኢስላም በጌታችን መድሀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በዛዊ ሞትና ትንሳኤ ዙሪያ የሰጡትን አባይ ምስክርነት ለማሳየት ሞክሬአለው በዚህ በቀጣዩ ሙግቴም ስለሞቱና ትንሳኤው በራሱ በጌታችን በመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንደበት የተሰጠውን እማኝነት እዳስሳለሁ።
ከባለቤቱ ያወቀ______ እንደሚሉት አበው ከራሱ ከድርጊቱ ባለቤት የተሻለና የታመነ ምስክርነት ሊሰጥ የሚችል አካል ያለ አይመስለኝም፡፡ ለዚህም ጌታችን በመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሞቱና ትንሳኤው በአፀደ ስጋ በነበረ ጊዜ ሲወጣ ሲገባ እንዲሁም ከትንሳኤው በኋላ ለደቀመዛሙርቱ እንዲሁም በራዕይ ለተገለጠት ለቅዱስ ዮሀንስ ሙቱንና ትንሳኤውን ሳያሳስብ ያለፈበት ቅፅበት አልነበረም ለዚህም አራቱን የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌላት በመቃኘት ማስተዋል እንችላለን፡፡ በወንጌላቱ ጌታችን ስለሞቱና ትንሳኤው አስቀድሞ የተናገረባቸውን ክፍሎች ለአንባቢው ዘርዝሬ በመተው እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት አስቀድሞ የተናገረባቸውን ሁለት ክፍሎች በጥልቀት ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 16:21, 17:9, 17:22-23, 20:18-19, 21:38, 26:2, 26:31-32
የማርቆስ ወንጌል 8:31, 9:9, 9:31, 10:33-34, 12:7-8, 14:8, 14:27-28, 14:41.
የሉቃስ ወንጌል 9:22, 9:44, 18:31-33, 20:14-15, 24:6-7
የዮሀንስ ወንጌል 3:14, 8:28, 10:17-18, 12:7, 12:23-24, 12:32-34.
በዚህኛ ሙግቴ ኢላማ አድርጌ የተነሳሁት ሙሀመድ በሱረቱል አል-ኒሳዕ 4:157-158 አልሰቀሉትም አልገደሉትም በማለት የተናገረበትን ሀሳዊ ምስክርነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት የተናገረበትን ክፍሎች በማንሳት እንደሞተ እንደተሰቀለ መመስከር ነው፡፡ የመጀመሪያው ጌታችን እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት የተናገረበት ክፍል በዮሀንስ ወንጌል ምዕራፍ 3:14 ላይ ከአይሁድ ህግ መምህሩ ኒቆዲሞስ ጋር ባደረገው ንግግር ሲሆን እንዲህ ይነበባል፦
"ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15)
ይህ የሙሴ በምድረበዳ እባብን የመስቀልና የተሰቀለውን እባብ የተመለከተ ከእባቡ መርዝ የመፈወሱን ታሪክ ለሙሴ ደቀመዝሙሩ ህግአዋቂውና መምህሩ ኒቆዲሞስ መንገር ለቀባሪው የማርዳት ያህል ነው፡፡ በዚህ ንግግሩ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ እየነገረው ያለው ሙሴ በምድረበዳ እባብን አንደሰቀለና የተሰቀለው ተመልክቶ ህዝቡ ከመርዙ እንደዳነ ሁሉ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊሰቀል እንደሚገባ ነው፡፡
ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስቅላት እንደሚሞት በዚህ ክፍል አረጋግጦ መስክሯል፡፡
ሌላው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት በግልፅ የተናገረበት ክፍል ይህ ነው ፦ (የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 12)
32፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። 33፤ በምን ዓይነትም ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ። 34፤ እንግዲህ ሕዝቡ። እኛስ ክርስቶስ ለዘላለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው? ብለው መለሱለት። በቁጥር 32 ጌታችን ከምድር ከፍ ከፍ ስለማለት ይናገራ ይህንን ማለቱ ደግሞ በምን አይነት አሟሟት እንደሚሞት የተናገረበት አንደሆነ በቁጥር 33 ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ ታዲያ ከፍከፍ የሚለው ቃል ከስቅለት ጋር ምን አገናኘው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ለዚህም ምላሽ የሚሆነን በስፍራው የነበሩ ሰዎች ከፍከፍ እላለው ለሚለው የጌታችን ንግግር የነበራቸው መረዳትና ምላሽ ነው፡፡ በቁጥር 34 ስለአሟሟቱ መናገሩ እንደገባቸውና ክርስቶስ ለዘላለም ለዘላለም ይኖራል እንጂ እንዴት ይሞታል የሚል ጥያቄ ውስጥ ሲገቡ እናያለን፡፡
በዘመኑና ከዛም በፊት በነበሩ ሰዎች "ከፍ" የሚለው አነጋገር ከስቅለትና ከሹመት ጋር በተገናኘ መልኩ ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ ለዚህም ዮሴፍ በግዞት ቤት በነበረ ጊዜ ለሁለቱ ሰዎች በፈታላቸው ህልም ላይ ለአንዱ ለሹመት ለአንዱ ለስቅለት ተመሳሳይ "ከፍ" የሚለውን ቃል ተጠቅሞ እናገኛለን፡፡
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 40)
12፤ ዮሴፍም አለው። የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ አረግ ሦስት ቀን ነው፤
13፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል፤ ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታደርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።
(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 40)
18፤ ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው። የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19፤ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ በእንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።
እንዲሁም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሄንኑ "ከፍከፍ" የሚለውን ቃል በሌላ
ስፍራ ተጠቅሞታል፡፡ "ስለዚህም ኢየሱስ። የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:28)
ውድ አንባቢ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለአሟሟቱ ማለትም ተሰቅሎ እንደሚሞት በግልፅ መስክሮ እያለ ከበርካታ መቶ አመታት በኋላ ነብይ ነኝ ብሎ የተነሳው ሀሳዊው ነብይ ሙሀመድ አልተሰቀለም አልሞተም የሚል የእብለት ምስክርነት መስጠቱና የተከታዩቹም በሙሀመድ አባይ መነፅር የጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ ለመዳኘትና ለመተቸት መኳተን አያስተዛዝበንምን??በርግጥም ያስተዛዝባል!! ጌታችን አስቀድሞ እንዳለ፦ " ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።" የዘላለም ህይወት ማግኛ ብቸኛ መንገዱ የጌታችን የመስቀል ላይ ቤዛነት ነው፡፡ ይህን የሚክድ ነብይም ሆነ ተከታዩ ጠፊ ነው፡፡
(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 1)
17፤ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
18፤ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

ይቀጥላል....
ሰላም

ወንጌልን በተመለከተ ተንጋዶ በቀረበ አጭር ተጓዥ በሆነ ባለቀ ቀለም ለተጻፈ ደብዛዛ ቅጂ ምላሽ እነሆኝ እላለው። የተነሳው ሃሳብ ጥቅሶችን ጠቅሶ ብቻ ጥቅሶቹ ያላሉትን በማለት የቀረበ ገሃድ የወጣ እብለት ስለሆነ ጥልቅ ማብራሪያ ባያስፈልገውም እንዲያው ለወጉ አጭር ሃሳብ ላካፍላችሁ።

እየሱስ ሰው ነው! ክርስትና ይህንን ክዳ አታውቅም ። የጌታችንን የመድሃኒታችንን የ እየሱስ ክርስቶስን በስጋው ወራት ያሳለፋቸውን እውነቶች ክርስትና አብዝታ ጠብቃ ይዛለች።( ዕብ 5:7 ሉቃ 22:43 ማቴ 4:11 1ጢሞ 2:5 ሐዋ 2:22 ሉቃ 18:31)
ክርስትና ማለቴ “መጽሃፍ ቅዱሳዊ ክርስትና” በ ቀደምት ሃዋሪያት እና ነቢያት የታነጸች ብሎም በማይናወጥ በ ክርስቶስ እየሱሳዊ መሰረት ላይ የጸናች አንዲት ቤተክርስቲያን ሰማያዊ እየሩሳሌም ሆና በሙሽሪት ምሳሌ ሙሽራዋን እምትጠብቅ አለ ጉድፍ እና አለ ነቀፋ ሆና በደሙ የዋጃት እምንጠብቃት አንዲት እምነታችን በ ህብረት ናት ክርስትና። ሐዋ 20:28
ችግሩ እሚመጣው “እየሱስ ሰው ብቻ ነው” ስለሚሉት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ነው። እነዚህ ሰዎች እየሱስ ክርስቶስ በገዛ አፉ የተናገረውን (ዮሐ 10:30) ከሰው ልቦና ሊጠፋ እማይችለውን እማያልፈውን የጌታችንን ቃል፤ እማይሰሙ ሆነው አምላካዊ መግነጢስን ሊያለያዩ እሚጥሩ ትንሽዬ ቁራጭ ጨለማዎች ናቸው። ክርስቶስ እየሱስ ግን ብርሃናችን ነው። እርሱ ‘አፋራም’ አይደለም። ጨለማም አላሸነፈውም።ጌታችን አለ ፡ “እኔ እና አብ አንድ ነን” አትገንጥሉን። እንሞክር እንዴ ልንገነጥላቸው? አይሆንማ!! እየሱስ ክርስቶስ ከ ብርሃን ብርሃን ከባህርይ ባህርይ ሆኖ በረቂቅ አካላዊ ቃል እግዚአብሄር ሆኖ የ አህዛብ ጌታ የሆነ ሃያል የ እስራኤል አምላክ ሆኖ ምንም አምላካዊ ማንነት ሳይቆራረስ ሳይሸራረፍ በሙላት የሆነ ብሩክ የ እግዚአብሄር አንድያ ልጅ ነው ። አሜን!!
(ዮሐ 1:1 ፣እብ 13:8 ፣ዮሐ 14:7-10፣ዮሐ 16:15፣ዮሐ 16:16፣ዮሐ 1:2፣ሮሜ 1:4፣ሮሜ 9:5፣ቆላ 1:15 ፣ቆላ 2:9፣1 ጢሞ 3:16፣1 ጢሞ 6:15፣እብ 1:3፣ራዕ 19:16፣ማቴ 3:17፣ማቴ 17:5፣ዮሐ 5:32፣ዮሐ 10፡38፤ዮሐ 10:37፣ሉቃ 22:70፣ሉቃ 22:69፣ዮሐ 5:37፣ዮሐ 8:18፣1 ዮሐ 5:9፣ዮሐ 10:30)

ከ ሶስት ውስጥ ሰባት አለኝ እሚሉት የሀሰት ልጆች ባለ ጎዶሎ ዝንፈታዊ እማኞችን ነቅሰው የቅዱሱን መጽሃፉ ሚጢጢ አዛንፈው ወደ እራሳቸው ቁራን ቀድተው ሲያበቁ፤ ቅዱሱን መጽሃፉን ሊተቹ መነሳታቸው “ የልጅ ነገር “ ያረግባቸዋል። አርጅቶም ሰርክ አዲስ የሆነውን ታላቁን አለም አቀፋዊ ቅዱስ መጽሃፍ ለራስ ገዝ ስራአት እንኳ በማይበቃውን መጽሃፋቸው ማስተንተኛነት ትንኮሳ መክፈት አሳዛኝ ልፋት አይደልምን? ነው!! ድብን ያለ ሞኝነት። ከ “ ሶስት ሰባት አለኝ “ ባዶ ስብስብ ሲሆን ምክንያተ-ቢስ ባዶነት እሚፈጥረው ስነ ልቦናዊ ኩፈሳ ነው።

የሰለሉ ሃሳቦች ፤በ እውነት እጦት መንምነው ጠኔ የጎዳቸው አመክንዮዓዊ አቀራረቦች የተሰነዘሩበት ፤ጉባኤት ያላቀረቧቸው ግላዊ ግንዛቤዎች የቃኙቸው፤ በ ጉማጅ ጥቅስ የቆሙ፤ አንካሳ መሰረተ-ቢስ ግላዊ አመለካከቶች ናቸው! በዋሂድ የተሰነዘሩ ቀሊል እይታዎች።
እከሌ ሃሳብ ሲያነሳ ቢውል ቢያድር የቆምንበትን መሰረት አይነቀንቀውም መሰረታችን እነሆ እማይነቃነቅ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋ መሰላል ነው ።(ዘፍ 28:12፤1ዮሐ 1፡52)። አለታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው ! (ማቴ 7:25፤ 1ቆሮ 10:4 ) እየሱስ ለማያምኑም የማሰናከያ አለት ነው (1ጴጥ 2:7 ) ። በ እየሱስ እማይሰናከል ቢኖር ብጹዕ ነው!! (ሉቃ 7:23 )
ቅዱስ መጽሃፍ እንዲህ ይላል “ ከተመሰረተው በቀር ማንም መሰረት ሊመሰርት አይችልም እርሱም እየሱስ ክርስቶስ ነው።” (1ቆሮ 3:11 ) እነሆ እግዚአብሄር እንደተናገረው የከበረው መሰረት(ኢሳ 28:16) ፣ የጸናው የማእዘን ድንጋይ የመተማመኛ አለት ሆነ! በሰው ያልታሰበው ይህ ታላቅ መድህን ለአለም ተረፈ! ይህ በ ‘አንዲት አገር ያልተቀመጠ’ ፤ቅርጽ ፤መጠን፤ቀለም የሌለው የመተማመኛ አለት ምሳሌ ሆኖ ሳይዳሰስ፤ ሳይነካ እና ሳይታይ ፤ ከመዳሰስ ፣ክመነካት እና ከመታየት አልፎ ዛሬም ያድነናል! አስቀድመው ከ እኛ ወገን ያልነበሩት ከ ልባቸው ሳያምኑ በ አሸዋ ላይ ቆመው ፤ ምናልባትም ልፈፋ ከለመዱ፣ ፍቅረ-ንዋይ ብሎም አጉል አመል አገር ካስከዳቸው እስላማዊ ወጣቶች ፤የተሰነዘረው ኢምንት ሃሳብ በክርስትናችን መነጽር “ከንቱ የሆነ የሰው ትምህርት “ ብለን እንጠራዋለን።

የተሰነዘረው ሃሳዊ ትንኮሳ ዋጋ ቢስ ነው! ሺ አመት ቀድሞ አስቀድሞ ቅዱስ ጴጥሮስ አንዲህ አለ፦ “ የ እርሱን ግርማ አይተን እንጂ በ ብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የ ኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ” (2ጴጥ 2:16) ተረትላይ አልቆምንም! ስር መሰረት ያለው እውነት ላይ ነው የቆምነው!

ለሰው ልጆች ስህተታቸውን በማስታቀፍ የስህተታቸውን ዋጋ በፍርደ-ገምድል ስራዓት ማስፈራሪያ እሚያድለው ሀሰተኛው ነቢይ ሙሃመድ፤ የፍርድን ምንጭ ለሰው ልጆች በማሳየት አስቀድቶ ለሞት እሚያበቃ መርዘኛ ቃላትን ጽፏል። ለዚያም ቁራንን የ ፍርድ ድምጽ በማድረግ ፤አምላካዊ ጭካኔንን ያጎሉ አንቀጻትን ከራሱ አመንጭቶ ድቅድቅ ጨለማ የሆነ መጽሃፍን አፈለቀ፤ አባሪዎቹም ጭለማውን አከፋፈሉ። ቁራን ለሚያነበው ተስፋን ሊያስነግብ ቀርቶ፤ ፍርድ እና ወዮን በመዝራት የፈሪ ተገዢ ያደርጋል እንጂ ፍቅርን አንስቶም ሰብኮም አያቅም። ፈጣሪ አለምን በልጁ ሞት በማረበት በዚህ የምህረት ዘመን ፍዳን ማብላት ዘግናኝ ነገር ነው። ሙሓመድን ሃሰተኛ የሚያደርገው ይህ ነው። ሙሃመድ ፈጣሪን ከፈጣሪ አጋጭቶ ያቀረበ ጽሁፍ ጽፏል። የ እኛ ኤሎሂም በፍጹም ቁራን ላይ ያለው አላህ አይደለም። (16:93፤7:179፣ 27:91 ፣53:19-20 ፣16:57፣37:149፣ 14:14፣16:93፣32:13፣2:106፣16:101,6:34፣10:64፣96:2፣51:56፣90:4 ሌሎችም ) በ እነዚህ ጥቅሶች ብቻ እራሱ እግዚአብሄር እና የቁራኑ አላህ አይገናኙም እኮ!
እርግጥ ነው በመሰረታዊነት እማይጨበጥ አንቀጻት(ህግጋትን ) ያቀፈው የሙሃመድ ድርሰት አንቀጽን እንደፈለገ በመቀያየር ርቱእነት ፤ተዓማኒነት እና መርጋት የጎደለው ሰዋዊ አስትረዕዮ መሆኑን አስመስክሯል! መጽሃፉ እራሱ በራሱ አትመኑኝ እኔ እቀያየራለው በማለት ተናግሯል። (2:106)፣ (16:101) እግዚአብሄር ግን ቃሌ ከሚያልፍ ሰማይ እና ምድር… ብሏል! (ማቴ 24:35፣ማር 13:31፣ሉቃ 21:33 )። ስለዚህ ከቁራን እውነትን መጠበቅ እራሱ ሞኝነት ነው። እራሱ ለ ራሱ ወዝዋዛነት ምስክር ሰጥቷል።



የ ጌታችንን ስጋ መርገጥ እሚወዱት ቆራጣ ጨረቃውያኑ ፤ እንደ ተምሳሌቱ ጉማጅ አስተሳሰብን በተላበሰው ባልበራ ድብዝዝ ጨለማ ሃሳባቸው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስን ሰው ብቻ በማለት እራሳቸውን በ እራሳቸው ወግተዋል! ለዚህም ማስተባበያ “ታላቁ ነቢይ” የሚል ከንቱ መካሻ መሳይ ቢያቀርቡም ፤ መለኮትነቱን መካጃ ጥንስስ አበጅተዋል ። ስልጣኑን ያልተቀማውን የቀሙ ቀማኞች፤ ጌታችን ለፍርድ ይጠብቃቸዋል! እርሱ በ እግዚአብሄር አምሳል ከብርሃን ብርሃን ከ እውነተኛ አምላክ እውነትኛ አምላክ ሆኖ ሁሉን በስልጣኑ

ቃል እየደ

ገፈ
የ ክብሩ መንጸባረክ ሆኖ ከ ስም ሁሉ በላይ ስም ይዞ የማይታየውን አምላክ ተምሳሌት የሆነ በቀኝ የተቀመጠ አጽናፈ አለሙን ሰማይ ተምድሩ ያበጀ ፈጣሪ መሃንዲስ ነው።

ለምሳሌ ያህል ዋሂድ ካነሳቸው
*ዮሀ 17:8
የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ
“ፈጣሪ ቃልን ሰጥቶታል፤ ቃሉን ለ ሃዋሪያቶቹ ሰጣቸው” የሚለውን ለማስረዳት ወልድን ቃል አልባ አድርጎ አቅርቧል።
ቃል የሆነውን ቃል የለውም ብሎ የቃል ድሃ አድርጎ ያቀረበው ሃሳዊው አሳች ከ አንዲት ጥቅስ እንኳ መጉመዱ አሳፋሪ ነው።
ይህንን ክፍል ሲጠቅሰው የጌታችን የመድሃኒታችን የ እየሱስ ክርስቶስን ‹ከ አብ መውጣት › እሚያሳየውን ክፈለ-ጥቅስ ዘሎ ሄዷል ድሮም ያልተገራ ተዝላይ ውጪ ምን ያውቃል? የ እየሱስ ከ አብ መውጣት ከክርስትናችን መሰረታዊ አስተምሮ አንዱ ነው።
የተነዳው ጸሃፊው ቅዱስ ዮሐንስ በጽሁፍ መጀመሪያ “በመጀምሪያው” ብሎ ያሰፈረውን ዋነኛ ጠቋሚ ሃሳብ ለቀው የትንታኔ እጦት ወጀብ ላጎሳቆላቸው ፤ ይህ ቃል ረቂቅ ሆኖ አካላዊ እንጂ ዝርው ‹ፊደል› አለመሆኑ መረዳት ግድ ይላል። ዮሀ 1:3 ፤እብ 11:3፣መዝ 33:6
ይቀጥላል........
ከJohnof
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Yoha:
የክርስትና አቋማችን (ከ ኒቂያ ጉባኤ የተቀዳ)

""ሁሉን በያዘ ፡ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በ አንድ አምላክ በ እግዚአብሄር አብ እናምናለን ዓለም ሳይፈጠር ከ እርሱ በተወለደ የ አብ አንድያ ልጁ በሚሆን በ አንድ ጌታ በ ኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ከ ብርሃን የተገኘ ብርሃን ከ እውነትኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በመለኮቱ ከ አብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በ እርሱ የሆነ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ከ ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆነ ሰው ሆኖም በ ጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ፤ሞተ ፤ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ በ ቅዱሳት መጻህፍት እንደ ተጻፈ በ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በ አባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በ ህያዋን እና በሙታን ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ፡የለውም""

መሰረታዊ ጉባዔ ከሆኑት የመጀመሪያው የ ኢየሩሳሌም ጉባኤ ነው። ይህም በመጽሃፍ ቅዱሳችን የሰፈረ ጉባኤ ነው። እየሱስ ካረገ ሃያ አመት ገደማ የተደረገው ይህ ጉባኤ አህዛብ እና ህገ- ሙሴ እንዴት መሄድ እንዳለባቸው አስፍሯል።(ሐዋ 15 )ይመልከቱ። ከዚህ እንደምንረዳው አለመግባባት ብሎም ቋሚ አስተምሮ መቅረጽ ሲያስፈልግ ጉባኤን ማድረግ በክርስትና የተለመደ ድርጊት መሆኑን ነው። አንዳዶች ሃሳዊ ማወክ ስለጀምሩ (ሐዋ 15:24) ሓዋርያት የጌታችንን አስተምሮ አውስተው፤ህጉን አገናዝበው፣መጽሃፍትን አጣቅሰው፣ቃሉን መክረው፣ ትንታኔ አቅርበው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ድንጋጌን አበጁ(ሓዋ 15፡ 28-32)። በየዘመኑም ቃሉ እማይለውን ግላዊ አመኔታ በማንሳት ለተነሱ አለመግባባቶች በክርስትና ታሪክ ውስጥ ድንጋጌን በማውጣት አባቶች መጽሃፍ ቅዱሱን እና የጌታችንን ትምህርት አንጸባርቀዋል። ፈጥረው ሳይሆን መጽሃፉን ጠቅሰው ጽሁፎችን አስቀምጠውልናል።ሌሎች ዐብይ ጉባኤያትን አቆይተን በቅጂው የተወሳችውን ካርቴጅን እንያት። ታዲያ ካርቴጅ ማን ትሆን? በመሰረቱ የካርቴጅ ጉባኤያት ብንል ሳይሻል አይቀርም በሰሜን አፍሪቃ የዛሬ ቱኒዚያ አካባቢ የምትገኝ ሆና በርካታ ጉባኤ የተጠራባት ስለሆነች። ታዲያ ካርቴጅን ማውሳት ስለምን አስፈለገ? በካርቴጅ ጉባኤ መጽሃፍት ጅማሮን እንዳገኙ አርጎ ማቅረብ ምስኪንነት ነው። ሃዲስ ኪዳን ከ ክርስቶስ ማረግ ወዲያ ስድሳ ባልበለጠ ዓመታት ተጽፈው አልቀዋል። ወሂድ የጠቀሰው ካርቴጅ ጉባኤ (369 ዓ.ም) ደግሞ መጽሃፍቱ ከተጻፉበት ወቅት ሶስት መቶ አመታት ገደማ በኋላ ነው። ቀደም ብዬ ከላይ እንዳነሳውት የጉባኤያት ዓላማ የነበረውን ማጽናት እንጂ መፍጠር አይደለም (2ጴጥ 1:21፣ኢሳ 34:16፣ሮሜ 10:17)። ታሪክን ሳያውቁ ማፋለስ ስትራቴጂ ነው የተሰነዘረው። ቅዱሳት መጽሃፍትን በአንድ ወጥ ጥራዝ ማዘጋጀት በነበረ ነገር ላይ የተሰራ የስብስብ ስራ እንጂ ያልነበረን ጽሁፍ ማስፈር አይደለም።ቅዱሳት መጽሃፍቶቻችን በወቅቱ የተጻፉ ናቸው። በዋቢነት (ራዕ1:11፣ሉቃ 1:1-4፣1ቆሮ 4:14፣ 2ቆ9፡ ፊል 3:12፤ዮሐ 1:12 ፤ይሁ 1:3 ፤3ኛ ዮሐ 1:13) ። ስለዚህም የ አንድ ሰው ድርስት አምነን አንቀሳቀስም ሊያውም የቅድሳት መጽሃፍት ሽራፊ እውነት በታተመበት ሰብአዊ አቋም ላይ አልቆምንም። መሰረታችን ክርስቶስ ነው! በሃዋርያት እና በነቢያትም መሰረት ላይ ታንጸናል። ይህም የተደላደለ እማይነቃነቅ መሰረት ነው!




አባቶቻችን ደምተዋል በስጋቸው መዘልዘል ላይ ተሰጥተናል። ደማቸው አሳምሮናል! ላመኑት የ እግዚአብሄር ልጅ ክርስቶስ ሞትን ሳይፈሩ ያደርጉት መስዋእትነታቸው ዛሬም ድረስ አናፍርበትም። ለዚህም በአባቶች ምስክርነትም ቆመናል! አባቶቻን ያሰመሩትን ቀጭን ቀደምት መስመር አናፋልስም ብለን ለራቻችን ቃል አለን ።

****እየሱስ ማለት ከ አምላክ ሰምቶ እሚናገር ሰው ነው” እና ወንጌል በምንለው ጉዳይ በተባለው ላይ.....

እየሱስ ከአምላክ ሰምቶ እሚናገር ሰው ብቻ አይደለም ጌታችን እኔ እና አብ አንድ ነን ያለ አንድያ ልጅ ነው። ይህ ማለት ከ እየሱስ ከርስቶስ ሌላ እግዚአብሄር ልጅ የለውም(ዮሐ 10:30 ፤ዮሐ 3:16) ። አንድያ ማለት ብቸኛ ማለት ነው። አንድ ነን ማለት ደግሞ ሊፈረካከስ ፤ሊፋለስ እማይችል ፍጹም አንድነትን አመላካች ነው። እየሱስ ጌታ ነው ስንል እየሱስ ኤሎሂም ሁሉን እሚገዛ የምድር የሰማይ ስልጣናትና ጌቶች ሁሉ አብን ሳይጨምር በስሩ ያደሩ ነው ማለታችን ነው። አብ እና ወልድ ጊዜ በሌለበት መቅደም መቀዳደም ሳይኖር ወልድ ከአብ ውጥቶ ስለ ሰው ልጅ በደል ምድርን ሊፈውስ ሰው ሆኖ በመታዘዝ ምሳሌ ስልጥኑን ሳይቀማ ራሱን በማዋረድ ወደ ምድር መጥቷል። ስለመታዘዙ ግን እግዚአብሄር አለ ልክ በነበረው ክብር ከፍ ከፍ አረገው። ይህ ልክ ስሌት አልባ ስለሆነ ወልድ ከየትም ወደ የትም አያድግም ይልቅስ የያዘውን እቅድ ፈጽሞ እግዚአብሄርን በስጋው በመታዘዝ ህግን ፈጸመ። ሰውነቱ ለ እኛ መታረቂያችን ነው። ሰውነቱ ለ እኛ ከ እግዚአብሄር መንፈስ ጋር የተግባባንበት ድልድያችን ነው። ሰው ሲሆንልን ሰው አረገን። ከ ሓጢያት ፍዳ ዳንን እንደ እንስሳ ሆነን በመንፈስ ሞተን ነበር ጭለማ ሆነን መንፈስ እውራን ነበርን ልጁ ግን ለእኛ በራልን እግዚአብሄር ብርሃናችን ነው። እንግዲህ በጨለማ ላሉት ሁሉ ይህ ብርሃን ይበራል አለምም እግዚአብሄርን በማወቅ ትባረካለች። ከ ውጭ ያረክሰኛል ከሚባለው ውሻ እና ከወጭቱ እድፍ ይልቅ የከፋ ነፍስ መንፈስን እሚያስር ዘላለማዊ ኃጢያት እየሱስ ክርስቶስ ያድናል (ማቴ 1:21) ውስጣዊ ገዳይ መርዝ እግዚአብሄር ባጸደቀው መንገድ ደህንነትን አለመፈለግ ነው። እግዚአብሄር ያጸደቀው መንገድ በልጁ በክርስቶስ እየሱስ በማመን በጸጋው ሃይል ድነትን ማግኘት ሲሆን ፤ ከዚህ ውጪ የሚደረግ ጉዞ ሁሉ መጨረሻው ሞት እንጂ ህይወት አይደለም።

ወንጌላችን ለ እኛ ስለ ጌታችን መድሃኒታችን ክርስቶስ እየሱስ ነው።
ይህም ወንጌል በስጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሳት የተነሳ በኃይል የ እግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ስለተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው። (ሮሜ 1:3-4፣ ሮሜ 1:16 ፣ ሮሜ 10:9-13 ፣ 1ቆሮ 15:1-28 ፣ሮሜ 10:14 ፣ ሐዋ 2:38፣ ዮሐ 3:16 ፣ሉቃ 5:21 ፣ ማር 16:15፣ ኤፌ 2:8-9 ፣1ጴጥ 3:18-22 ) ። ወንጌሉ የፊደላት ስብጥር ብቻ ሳይሆን እሚጠጣ ውሃ እሚበላ እንጀራችን ክርስቶስ እየሱስ ነው።( ዮሐ 6:50 ፣ዮሐ 4:10)። ስለበላነው ስለ ጠጣነው አንሞትም። አሜን!
እንዲረዱን እምንፈልገው ወንጌሉ ስለ እየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ነው። እንደመሰላቸው ወንጌሉን መሸቃቀጫ ማረግ ዋጋ ያሰክፍላቸዋል።
መጽሃፍ ቅዱሳችን ደራሲው እግዚአብሄር ነው! ይህ እስትንፋሰ መለኮት ለዓለም የተሰጠ መተዳደሪያ የተስፋ ቃል ያለው እግዚአብሄር አያልፍም ብሎ የተናገረለት ጽኑ ዘላለማዊ ሃሳቡ ነው። ቃሉ የነጠረ ነው። (መዝ 18:30 ፤ 1ሳሙ 22:31) ። መጽሃፋችን እንከን የሌለበት በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚገለጥ ስራዓታዊ ትጋት እና ንባበ ቆይታን እና ተመስጦን ማሰላሰልን እሚፈልግ እንቁ የታጨቀበት የጥበብ መናሃሪያ ነው። እንቁላል ሶስት ክፍላት እንዳሉት እንቁላሉን መብላት እሚፈልግ ሁሉ በጥልቀት እንደሚገባ እና እንደሚመረምር የሰው ልጅም መኖሪያ መሬት ሶስት ዓበይት ክፍላት እንዳሏት ፤አብዛኛ
ው ሰው ግን ስለ ቅርፊቷ እንጂ ስለሌላው እንደማያውቅ፤ ከምድር አልፈው ግን በህዋ ጥልቅ ምርምር እና ቁፋሮ ያደረጉት ግን ምድር መካከለኛ እና ውስጣዊ ክፍላት እንዱላት አስረድተዋል።የከበሩ ማእድናት አቧራ አይደሉምና አቧራ እያቦነኑ ትልቅ ጀብዱ የሰሩ እሚመስላቸው አላዋቂዎችም አቧሯው አስቀድሞ እሚበቀለው አጠገቡ ያሉትን ሀሰት ጎርጓሪዎች መሆኑን ቢረዱት መልካም በሆነ። በየ ገጸ ምድሩ ሳይገኙ ይልቅስ በምስጢራት የተከሸኑ ፈልጎ ላገኛቸው ክብር ናቸው። እንዲሁ ሁሉ ቅዱሳት መጽሃፍት ማሰላሰል እሚሹ ሆነው ለጨለፋቸው ግን እሚጨለፉ አጥልቆ ቆፍሮ ለቀዳቸው ደግሞ ጥምን እሚያረኩ የከበሩ እንቁዎች ናቸው ። እምናስተውለው ነገር ከሙስሊም ማህበረሰቡ አንዳዱ ወደ ቅዱሳት መጽሃፍት አስተምሮ ፊቱን በማዞር መጨለፍ መጀመሩን ነው። እምንመክረው ደግሞ አጥልቀው በቅን ልቦና መድሃኒቱን እንዲጠቀሙ ነው። መድኃኒዓለም እየሱስ ክርስቶስ ነው።
ቁራን ለቅዱስ መጽሃፋችን እውቅናም ሆነ ትችት ማቅረብ አይችልም። ቁራን በራሱ ያልቆመ በመጽሃፋችን ግርጌ ተንተርሶ አንቀጻትን ከ ታሪክ አዛብቶ የቀዳ ግለሰባዊ ድርሰት ነው። ይህ መሰርት የለሽ መጽሃፍ እንደ ማስፈራሪያ ከሰማይ ወረደ እንደ ሞርሞን ፤ዞራስተር የመሳሰሉ ጥንቆላዊ መጽሃፍት አምላካዊ ጭካኔን እንጂ ርህራሄ ያልታየበት የመጽሃፉም ተወላጆች አጥፊነትን የቀሰሙበት በ ዓመተ-ምህረት ፍቅር አልወረደም የለምም እነሆኝ ሰይፍ እንኩ ግደሉ ያለ ድርሰት ነው ። ሰዎች ዛሬም ከዚህ ጨለማ እንዲወጡ እነሆ የፍቅር መጽሃፍ ቀርቧል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው ። ይህ ሃዲስ ኪዳን አልሆነም ያለ መጽሃፍ ፤ምንም የመዳኛ አምላካዊ ጸጋ የሌለው ሰዎችን ጣሩ ብቻ ብሎ መጣሪያውን አቅም ያላስታቀፈ፤ መሰረት የለሽ መጽሃፍ ታላቁ መጽሃፋችንን ሊተችም መተማመኛም ሊሰጥ አይችልም።
ዛሬ ሙስሊም የሆኑት ሁሉ ወደ ክርስቶስ ሊመጡ የተገባ ነው! እየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ነው። ስል ፍቅርም ስልጣኑን ለመጣል ስልጣኑን ትቷል። ሞት ውርደት አይደለም ! ሞት የሞት መግደያ ብቸኛ አማራጭ ነው። ሞት ሞትን ከገደለ ድል ነሺነት እንጂ ውርደት አይደለም። አምላክ እነሆ የአለምን ጥበብ እንዲያሳፍር የዚህን አለም ሞኝ ነገር መረጠ ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ጌጣችን ነው እንጂ በ እኛ ላይ የተደረገ አምላካዊ የማሳት ሴራ አይደለም። አውቆ ሞቷል አውቆ አድኖናል። እርሱ ሁሉን አዋቂ ነው! ስለዚህም ከ እግዚአብሄር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናችሗለን ። ቃሉ ሁሉን ማድቀቅ እሚችል መዶሻ ነውና ከ እግዚአብሄር ጋር እሚጣሉ ደግሞ ይደቅቃሉ ። ዛሬም ይህን ቅዱስ ቃል ከታዛዥነቱ የተነሳ ቢለዝብ እና ቢለምጥ ለማዳን እንዲሆን ያለን የ እግዚአብሄርን ትዕግስት የሚያሳይ ትህትና እንጂ የቃሉን ጠንካራነት አይነካውም። የ ክርስትናችን ድሩም ማጉም ፍቅር ነው። አምላክ ለሰው ልጆች የገለጸው ፍቅር ላይ ቆመን እናውራለን ።
ምናልባትም አምላካዊ እቅድ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አልገባውም። የ አምላካዊ እቅድ ተርጓሚ ማስተንተኛ፡ፍቅር ነዋ ።
ፍቅር ደግሞ እንዲህ ነዋ ፦ እግዚአብሄር እንደወደድን ስለሓጢያታችንም ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ልጁን አንደላክ እንጂ እኛ እንደወደድነው አይድለም! (1ዮሐ 4:10 ) ስለዚህ ያለ ደም ስርየት የለም! ( እብ 9:19-22)::
ከJohnof