ለምን አልሰለምኩም?
3.01K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
⚫️ ሊቃውንት ስለሙስሊሞች መጽሐፍ ስለ ቁርአን የሚሉትንም ስንመለከት ለመረዳት አስቸጋሪ መሆኑን እናረጋግጣለን "ስልማንራይደል" የተባለው ጀርመናዊ ተመራማሪ የቁርአንን ስነ ጽሑፋዊ ይዘት ስናየው #ትኩረትን_የማይስብ_ድግግሞሽ_የበዛበትና_ማን?_መቼ?_እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ለማጥናት #አመቺ_ያልሆነ፣ 🔹የተጠየቅ እጦት የበዛበት፣🔹 ተከታታይነት በሌለው አንቀፆች የታጨቀ #የቃላት_ውርጅብኝ_ነው፡፡ ቁርአን በማንኛውም ገፅ አንባቢውን ግራ የሚያጋባ በመሆኑ ብዙ ሰዎች እሱን አንብበው ለመረዳት ጊዜያቸውን ሲያውሉ ማየት በጣም ይገርማል ብሏል፡፡ "ቴዎዶር ኖልዶኬ" የተባሉት ሌላ ተመራማሪም 🔶ቁርአን የተሯሯጠና ግራ አጋቢ አንቀፆችን፣ የደረቁ መልዕክቶች ያሉባቸው ጥቅሶችን የያዘ መጽሐፍ ነው🔶 ብለዋል፡፡

⚪️
እንግዲህ ስለቁርአን የሚያጠኑ ሰዎች ይህንን መሰል ድምዳሜ ላይ እየደረሱ ቁርአን የእነሱ እንደሆነ የተቀበሉ ሰዎች ግን አመለካከታቸው ሲመዘን ልንል የምንችለው ወይ አልተረዱትም ወይም በጭፍን መረዳት ይገዙለታል ብቻ ነው፡፡ በየቋንቋቸው ያልቀረበላቸውን እንዲቀርብም ያልፈቀደላቸውን መጽሐፍ የአረብኛውንም ቅጂ አንብበው መረዳት ሳይችሉ ቁርአን ድንቅ ነው ለምን ይላሉ?