ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የቁርአን ትርጉም ተፍሲር ይባላል። በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮች ደግሞ ኢብን ካቲር እና አል ጃለሊን ናቸው። ከነዚህ ውስጥም እንደ #ኢብን_ካቲር ያለ ተቀባይነት ያለው ተፍሲር የለም። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይም የምናየው የኢብን ካቲርን ተፍሲር ይሆናል። እንዲህ ይላል:-

📚“(በሶስተኛዉ አበረታናቸዉ) ማለት፣ “እኛ በሶስተኛዉ መልዕክተኛ ደገፍናቸዉ ፣ አበረታናቸዉ” ማለት ነው። ኢብኑ ዩራይጅ ከ ዋህብ ኢብኑ ሱለይማን እና ከሹአይብ ያባይ እንዳስተላለፉት:-“ የመጀመሪያዎቹ የሁለቱ መልዕክተኞች ስም #ስምኦን(#ጴጥሮስ) እና #ዩሐንስ የሶስተኛዉ ስም ደግሞ #ጳዉሎስ ነበር። ከተማዋም አንፆኪያ ነበረች።”📚😳😳😳😳

እንግዲህ ምን ትሉ ይሆን? የዘመናችን ሙስሊሞች በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚያዘንቡት መሠረት የለሽ ውርጅብኝ ከየት የመጣ ነው? እናንተ ከመተርጉማኖቹ (ሙፈሲሮች) ትበልጣላችሁን? ማነዉ ሶስቱን የላካቸው? አላህ አይደለምን? ደግሞም የቅዱስ ጳውሎስ መምጣት ምን ያህል #_አበረታችና_አፅናኝ እንደነበር ተመልከቱ:: ማን ነው የሳተው? አላህ ወይስ በአላህ የተላከው ጳውሎስ ወይስ የዘመናችን ካለ ማስረጃ የሚለፈልፉት ሙስሊሞች

ይሄን አላምንም የሚል ሰው ካለ ከራሳቸው ከሙስሊሞች ድረ-ገፅ በመግባት ማየት ይችላል። ለማረጋገጥ የፈለገ ሰው “www.qtafsir.com” በመግባት የቁርአኑን ምዕራፍና ቁጥሩን በመፃፍ በአረበኛም በእንግሊዝኛም ማየት ይችላል።
👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳
ሙስሊሞች ደግሞ በተራችሁ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ሐሰተኛነት ከቻላችሁ እንደኛ ከቁርአን ተፍሲር ካልቻላችሁ ከሐዲስ ማሳየት ትችላላችሁ። እኛ እውነተኝነቱንና የተላከውም በአላህ እንደሆነ አሳይተናል።

http://www.qtafsir.com/index.php?option=com_content&task=view&id=1491&Itemid=