#ምርጥ ( #ምርትነሽ_የማነ)
እቴትዬና..... እሜ
አደዬና ......ሀርሜ
በየ ፈርጀ ........ፈርጁ
በእያንዳንዱ ቋንቋ ፥ ቃላት ቢወዳጁ
አንቺን .....እኮ እናቴ
የጠዋት አስኳላ ፥ የልጅነት ሀብቴ
ኑር አንተ ለኔ .......ባይ
ቅንጣት ሳይታወስ ፥ ላንቺ ያንቺው ጉዳይ
በጉያሽ አቅፈሺኝ ፥ በጪንጫ ተኝተሽ
ውሀ ባፍሽ ርቆ ፥ ወተቱን ያጠጣሽ
ማጀት ያጠቆረሽ
ረሀብ ያከሳሽ
ጎኔን ....... ጨርቄን...... ማቄን
የሚሉት ጥበቃ ፥ ከራስ በላይ ንፋስ ፥ ሰይሞ መዳከር
ላንዲት ነብስ ስስት
ላንድ አካል መንቧቸር
ከራስ በላይ ልጄ'ን
በሚል ልግስና ፥ እድሜን በመቸርቸር
ብ 'ርክ በማለት ፥ ብርክሽን የረሳሽ
በመከነ ቀለም ፥ ብዕርሽ የጠፋች።
ያ..............#ፀሀይ ውበትሽ
ኩሽና ተሳስሮ ፥ ከምጅጃ ግርጌ፥ ዕድያው የቀረ
ወዘናሽ ተሟጦ ፥ ገፅሽ የጠቆረ
በመጨናበስ #ነው
አካልሽ ለጋሱ ፥ አይነ ግቡ መልኬን ፥ ዛሬ የወቀረ ።
የአፍላነት ግዜሽ
ጥንቡሳሱን ጥሎ ፥ ያለ እድሜሽ ያረጀሽ
ደ 'ስታን ልክ እንደ መርዝ
ለልጅ በመኖር ውስጥ ፥ ዘመንሽ የቀማሽ
በአለሙ መሀል ፥ ለአለም እንግዳ
ትክሻሽ የሳሳ ፥ ቅስምሽ የተጎዳ
የህይወት ቀንበር ተጫኝ
ለፍሠሀ ባዳ !!
ሀኪም እናታለም
#ኮስማናዋ #እናቴ!!!
የህይወት መቅድሜ
የጉም ቀን መብራቴ
ተስፋ አለምሽ ይጥና
#በርቺልኝ በሞቴ
እናትነትሽ ነው ፥ በዚህ ልፋጭ አለም ፥ የቀን ክራሞቴ።
የሰማዩ ንጉስ የምድሩም ጌታ
ከምንም አብልጦ ፥ እናቱን ይወዳል
ትንሽም ሲራሩ
እናቴ ያሉ እንደው ፥ ምዕንተ ማርያም ፀሎት ይማለዳል
ውህብቶ ብዙ ነው ፥ ዳና በመከተል ፥ በገፍ ይሰደዳል
እናቴ ለሚሉት እናት መሆን ያውቃል
ስለዚህ ....
ልጄን ብለሽ አንቺ ፥ ፊቱን እንደ ሰማሽ
ያብቃኝ ....
አንቺም ያብቃሽ....
ለልጅ የተሰዋ
አድሮ የበረታ ፥ የህላዌ ጥዋ
ብሩህ ጀምበር ገጥሞ
በልጅ የፈዘዘ ፥ ዳግም በልጅ ቀልሞ
እንጥፍጥፍ አለም ....በእድሜ ስልቻ ፥ ጠብቆ ተቀምቅሞ
እያጠነጠነ...... የግዜ ሰሌዳ ፥ በመቁጠሪያ ሲታሽ
አድማስ ተሻጋሪ ... #ቦግ!!! ብሎ ማታሽ
ውድ ሸማሽ ሆኜ ፥ መቀነት ያውለኝ
ለውበት ...ለድጋፍ ፥ መጠቅለል የቀናኝ
ገንዘብ ....መቋጠሪያ
ውጋት ......ማባረሪያ
ላዱኛ ቀን ብርታት
ለጭንቅ ቀን ፅናት
አድርጎ .....እኔን ላንቺ ፥ ፈቅዶልኝ ፈጥሪ
የእናቱን ቀን አውጪ ፥ በወዘናው ጣሪ
ግብ ቀንቶት ፅናቴ
ሹልክ ብለሽ ወጥተሽ ፥ ከኑሮ ግርግር
ከእንጉርጉሮ አለም ፥ ጠማማ ውንግርግር
ምርቃትሽ ደርሶኝ ....መነን ሁኚ እናቴ
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ ፥ በኔ ትኖሪ ዘንድ ፥ ይባረክ ጉልበቴ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
እቴትዬና..... እሜ
አደዬና ......ሀርሜ
በየ ፈርጀ ........ፈርጁ
በእያንዳንዱ ቋንቋ ፥ ቃላት ቢወዳጁ
አንቺን .....እኮ እናቴ
የጠዋት አስኳላ ፥ የልጅነት ሀብቴ
ኑር አንተ ለኔ .......ባይ
ቅንጣት ሳይታወስ ፥ ላንቺ ያንቺው ጉዳይ
በጉያሽ አቅፈሺኝ ፥ በጪንጫ ተኝተሽ
ውሀ ባፍሽ ርቆ ፥ ወተቱን ያጠጣሽ
ማጀት ያጠቆረሽ
ረሀብ ያከሳሽ
ጎኔን ....... ጨርቄን...... ማቄን
የሚሉት ጥበቃ ፥ ከራስ በላይ ንፋስ ፥ ሰይሞ መዳከር
ላንዲት ነብስ ስስት
ላንድ አካል መንቧቸር
ከራስ በላይ ልጄ'ን
በሚል ልግስና ፥ እድሜን በመቸርቸር
ብ 'ርክ በማለት ፥ ብርክሽን የረሳሽ
በመከነ ቀለም ፥ ብዕርሽ የጠፋች።
ያ..............#ፀሀይ ውበትሽ
ኩሽና ተሳስሮ ፥ ከምጅጃ ግርጌ፥ ዕድያው የቀረ
ወዘናሽ ተሟጦ ፥ ገፅሽ የጠቆረ
በመጨናበስ #ነው
አካልሽ ለጋሱ ፥ አይነ ግቡ መልኬን ፥ ዛሬ የወቀረ ።
የአፍላነት ግዜሽ
ጥንቡሳሱን ጥሎ ፥ ያለ እድሜሽ ያረጀሽ
ደ 'ስታን ልክ እንደ መርዝ
ለልጅ በመኖር ውስጥ ፥ ዘመንሽ የቀማሽ
በአለሙ መሀል ፥ ለአለም እንግዳ
ትክሻሽ የሳሳ ፥ ቅስምሽ የተጎዳ
የህይወት ቀንበር ተጫኝ
ለፍሠሀ ባዳ !!
ሀኪም እናታለም
#ኮስማናዋ #እናቴ!!!
የህይወት መቅድሜ
የጉም ቀን መብራቴ
ተስፋ አለምሽ ይጥና
#በርቺልኝ በሞቴ
እናትነትሽ ነው ፥ በዚህ ልፋጭ አለም ፥ የቀን ክራሞቴ።
የሰማዩ ንጉስ የምድሩም ጌታ
ከምንም አብልጦ ፥ እናቱን ይወዳል
ትንሽም ሲራሩ
እናቴ ያሉ እንደው ፥ ምዕንተ ማርያም ፀሎት ይማለዳል
ውህብቶ ብዙ ነው ፥ ዳና በመከተል ፥ በገፍ ይሰደዳል
እናቴ ለሚሉት እናት መሆን ያውቃል
ስለዚህ ....
ልጄን ብለሽ አንቺ ፥ ፊቱን እንደ ሰማሽ
ያብቃኝ ....
አንቺም ያብቃሽ....
ለልጅ የተሰዋ
አድሮ የበረታ ፥ የህላዌ ጥዋ
ብሩህ ጀምበር ገጥሞ
በልጅ የፈዘዘ ፥ ዳግም በልጅ ቀልሞ
እንጥፍጥፍ አለም ....በእድሜ ስልቻ ፥ ጠብቆ ተቀምቅሞ
እያጠነጠነ...... የግዜ ሰሌዳ ፥ በመቁጠሪያ ሲታሽ
አድማስ ተሻጋሪ ... #ቦግ!!! ብሎ ማታሽ
ውድ ሸማሽ ሆኜ ፥ መቀነት ያውለኝ
ለውበት ...ለድጋፍ ፥ መጠቅለል የቀናኝ
ገንዘብ ....መቋጠሪያ
ውጋት ......ማባረሪያ
ላዱኛ ቀን ብርታት
ለጭንቅ ቀን ፅናት
አድርጎ .....እኔን ላንቺ ፥ ፈቅዶልኝ ፈጥሪ
የእናቱን ቀን አውጪ ፥ በወዘናው ጣሪ
ግብ ቀንቶት ፅናቴ
ሹልክ ብለሽ ወጥተሽ ፥ ከኑሮ ግርግር
ከእንጉርጉሮ አለም ፥ ጠማማ ውንግርግር
ምርቃትሽ ደርሶኝ ....መነን ሁኚ እናቴ
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ ፥ በኔ ትኖሪ ዘንድ ፥ ይባረክ ጉልበቴ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
#ቅዳሜ!
።።።።።
#ፀሀይ አድልታለች
ከሰርክ ብርሀኗ.. .ሀይሏን አለዝባ
በስሱ ወታለች ።
እኔ.. .
ስለምን ነው? እያልሁ እያየኋት ቆሜ
ትዝ ቢለኝ ድንገት ቀኑ ነው ቅዳሜ ።
#ቅዳሜ!
የሚፈካ ሰማይ ... ያረበበ አየር
ላብራ ሳልሞቅ ብላ የምትወጣ ጀንበር።
የአዳም ዘር እረፍት.. .
የደስታ ሰገነት ...
የጀበና ቡና.. . ጥቂት ማኪያቶ
ዱለት ምላስ ሰንበር በአዋዜ ታሽቶ
ካፌ በረንዳ ላይ ጨዋታ ተጋርቶ
መፅሄት ጋዜጣ መፅሀፍ ሸምቶ
ከጥበብ ጋር መዋል ... !
ወርቅን ማመሳጠር በቅኔ መሰላል።
#ቅዳሜ!
በጠጉሮቿ መሀል አበባ ሰክታ
ሲኒማ ኢምፓየር ስሩን ተጠግታ
አስር ጊዜ የጇን ፥ ሰዓት የምትቆጥር
ከመንገዱ ቁልቁል ፍቅሯን የምትማትር
አይመጣም ወይ ብላ ከንፈሯን የጣለች
ይመጣልም ብላ
ፈገግ ወደማለት ...ዳርዳርታ ላይ ያለች
እርሷን የምትመስል የቀናት ምስጢር ነች።
#ቅዳሜ!
ነጠላ ባጣፉ ፣ ቄጠማ በያዙ
ሽቶ ተነስንሰው
ከባንኮኒው ግድም ፣ አልኮልን በሚያዙ
በመዝሙር ውዳሴ ከመላዕክት ጋራ
በማለዳው ጮራ.. .
ደግሞ ወዲህ ምሽት
በሳልሳ በቡጊ.. .. በሬጌ ጭፈራ
በኒህ ሁለት ፅንፎች መሀል ተወስና
"አፍቃሪሽ አይቋረጥ" ብለው የመረቋት
ዘማሪም ደናሹም እኩል የሚወዷት
የቀኖች ንግስት ናት !
....
(ሚካኤል አስጨናቂ)
@getem
@getem
@paappii
።።።።።
#ፀሀይ አድልታለች
ከሰርክ ብርሀኗ.. .ሀይሏን አለዝባ
በስሱ ወታለች ።
እኔ.. .
ስለምን ነው? እያልሁ እያየኋት ቆሜ
ትዝ ቢለኝ ድንገት ቀኑ ነው ቅዳሜ ።
#ቅዳሜ!
የሚፈካ ሰማይ ... ያረበበ አየር
ላብራ ሳልሞቅ ብላ የምትወጣ ጀንበር።
የአዳም ዘር እረፍት.. .
የደስታ ሰገነት ...
የጀበና ቡና.. . ጥቂት ማኪያቶ
ዱለት ምላስ ሰንበር በአዋዜ ታሽቶ
ካፌ በረንዳ ላይ ጨዋታ ተጋርቶ
መፅሄት ጋዜጣ መፅሀፍ ሸምቶ
ከጥበብ ጋር መዋል ... !
ወርቅን ማመሳጠር በቅኔ መሰላል።
#ቅዳሜ!
በጠጉሮቿ መሀል አበባ ሰክታ
ሲኒማ ኢምፓየር ስሩን ተጠግታ
አስር ጊዜ የጇን ፥ ሰዓት የምትቆጥር
ከመንገዱ ቁልቁል ፍቅሯን የምትማትር
አይመጣም ወይ ብላ ከንፈሯን የጣለች
ይመጣልም ብላ
ፈገግ ወደማለት ...ዳርዳርታ ላይ ያለች
እርሷን የምትመስል የቀናት ምስጢር ነች።
#ቅዳሜ!
ነጠላ ባጣፉ ፣ ቄጠማ በያዙ
ሽቶ ተነስንሰው
ከባንኮኒው ግድም ፣ አልኮልን በሚያዙ
በመዝሙር ውዳሴ ከመላዕክት ጋራ
በማለዳው ጮራ.. .
ደግሞ ወዲህ ምሽት
በሳልሳ በቡጊ.. .. በሬጌ ጭፈራ
በኒህ ሁለት ፅንፎች መሀል ተወስና
"አፍቃሪሽ አይቋረጥ" ብለው የመረቋት
ዘማሪም ደናሹም እኩል የሚወዷት
የቀኖች ንግስት ናት !
....
(ሚካኤል አስጨናቂ)
@getem
@getem
@paappii
👍2❤1
#ፀሀይ
፡
፡
፡
ወዲያ ማዶ ያየሽ ጊዜ፣ቁንፅል ብርሃን ድንግዝ ላምባ፤
የኔ ምለው አንድ ልብሽ፣ድንገት ከድቶኝ ገሌ ገባ።
ነቁጥ ጨረር ለሚያክለው፣ለማይባል እሩብ ሲሶ፤
ስንቁን ጭኖ ገሰገሰ፣ልብሽ ልቤን ጥሎ ምሶ።
፡
፡
የቤታችን ክዳን ጣሪያው፣ያስገባትን ተሸንቁሮ፤
ንዑስ ፀዳል ያየ ጊዜ፣ገፍቶኝ ቢሄድ ልብሽ ዞሮ፤
እንዳልከረምሽ በወገግታ፣ፋኖስ ሆኜሽ ስታበሪ፤
ብልጭ ድርግም የሚል ኮከብ፣አሸፍቶሽ ተወርዋሪ፤
መስዬበት ጠፍጨረቃ፣የወረሰው ድቅድቅ ጭልም፤
ብርቅርቅታን ከሩቅ አይቶ አለ ልብሽ ጥሎኝ እልም።
፡
፡
አቤት ልቤን ሰነበጠው፣
ሀቅ እያደር እስኪገልጠው።
፡
፡
ያኔማ፣
ሀቅ ጮሀ ስትሰማ፣
ፅልመት ሌሊት እየተባልኩ፣ባንቺ ዘንዳ እንዳልነበር፤
ፍቅር ፈርዶ ልቤን ሲክስ፣ስትመሰክር ለ'ውነት ጀንበር፤
ፍክት ስል ባደባባይ፣እኔው በኔው ተማምኜ፤
የዛን ለታ ምን ሊውጥሽ፣ስታገኚኝ ፀሀይ ሆኜ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
ወዲያ ማዶ ያየሽ ጊዜ፣ቁንፅል ብርሃን ድንግዝ ላምባ፤
የኔ ምለው አንድ ልብሽ፣ድንገት ከድቶኝ ገሌ ገባ።
ነቁጥ ጨረር ለሚያክለው፣ለማይባል እሩብ ሲሶ፤
ስንቁን ጭኖ ገሰገሰ፣ልብሽ ልቤን ጥሎ ምሶ።
፡
፡
የቤታችን ክዳን ጣሪያው፣ያስገባትን ተሸንቁሮ፤
ንዑስ ፀዳል ያየ ጊዜ፣ገፍቶኝ ቢሄድ ልብሽ ዞሮ፤
እንዳልከረምሽ በወገግታ፣ፋኖስ ሆኜሽ ስታበሪ፤
ብልጭ ድርግም የሚል ኮከብ፣አሸፍቶሽ ተወርዋሪ፤
መስዬበት ጠፍጨረቃ፣የወረሰው ድቅድቅ ጭልም፤
ብርቅርቅታን ከሩቅ አይቶ አለ ልብሽ ጥሎኝ እልም።
፡
፡
አቤት ልቤን ሰነበጠው፣
ሀቅ እያደር እስኪገልጠው።
፡
፡
ያኔማ፣
ሀቅ ጮሀ ስትሰማ፣
ፅልመት ሌሊት እየተባልኩ፣ባንቺ ዘንዳ እንዳልነበር፤
ፍቅር ፈርዶ ልቤን ሲክስ፣ስትመሰክር ለ'ውነት ጀንበር፤
ፍክት ስል ባደባባይ፣እኔው በኔው ተማምኜ፤
የዛን ለታ ምን ሊውጥሽ፣ስታገኚኝ ፀሀይ ሆኜ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
👍38❤13😱2🔥1