ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ምርጥ ( #ምርትነሽ_የማነ)

እቴትዬና..... እሜ
አደዬና ......ሀርሜ
በየ ፈርጀ ........ፈርጁ
በእያንዳንዱ ቋንቋ ፥ ቃላት ቢወዳጁ
አንቺን .....እኮ እናቴ
የጠዋት አስኳላ ፥ የልጅነት ሀብቴ
ኑር አንተ ለኔ .......ባይ
ቅንጣት ሳይታወስ ፥ ላንቺ ያንቺው ጉዳይ
በጉያሽ አቅፈሺኝ ፥ በጪንጫ ተኝተሽ
ውሀ ባፍሽ ርቆ ፥ ወተቱን ያጠጣሽ
ማጀት ያጠቆረሽ
ረሀብ ያከሳሽ
ጎኔን ....... ጨርቄን...... ማቄን
የሚሉት ጥበቃ ፥ ከራስ በላይ ንፋስ ፥ ሰይሞ መዳከር
ላንዲት ነብስ ስስት
ላንድ አካል መንቧቸር
ከራስ በላይ ልጄ'ን
በሚል ልግስና ፥ እድሜን በመቸርቸር
ብ 'ርክ በማለት ፥ ብርክሽን የረሳሽ
በመከነ ቀለም ፥ ብዕርሽ የጠፋች።
ያ..............#ፀሀይ ውበትሽ
ኩሽና ተሳስሮ ፥ ከምጅጃ ግርጌ፥ ዕድያው የቀረ
ወዘናሽ ተሟጦ ፥ ገፅሽ የጠቆረ
በመጨናበስ #ነው
አካልሽ ለጋሱ ፥ አይነ ግቡ መልኬን ፥ ዛሬ የወቀረ ።

የአፍላነት ግዜሽ
ጥንቡሳሱን ጥሎ ፥ ያለ እድሜሽ ያረጀሽ
ደ 'ስታን ልክ እንደ መርዝ
ለልጅ በመኖር ውስጥ ፥ ዘመንሽ የቀማሽ
በአለሙ መሀል ፥ ለአለም እንግዳ
ትክሻሽ የሳሳ ፥ ቅስምሽ የተጎዳ
የህይወት ቀንበር ተጫኝ
ለፍሠሀ ባዳ !!
ሀኪም እናታለም
#ኮስማናዋ #እናቴ!!!
የህይወት መቅድሜ
የጉም ቀን መብራቴ
ተስፋ አለምሽ ይጥና
#በርቺልኝ በሞቴ
እናትነትሽ ነው ፥ በዚህ ልፋጭ አለም ፥ የቀን ክራሞቴ።

የሰማዩ ንጉስ የምድሩም ጌታ
ከምንም አብልጦ ፥ እናቱን ይወዳል
ትንሽም ሲራሩ
እናቴ ያሉ እንደው ፥ ምዕንተ ማርያም ፀሎት ይማለዳል
ውህብቶ ብዙ ነው ፥ ዳና በመከተል ፥ በገፍ ይሰደዳል
እናቴ ለሚሉት እናት መሆን ያውቃል
ስለዚህ ....
ልጄን ብለሽ አንቺ ፥ ፊቱን እንደ ሰማሽ
ያብቃኝ ....
አንቺም ያብቃሽ....
ለልጅ የተሰዋ
አድሮ የበረታ ፥ የህላዌ ጥዋ
ብሩህ ጀምበር ገጥሞ
በልጅ የፈዘዘ ፥ ዳግም በልጅ ቀልሞ
እንጥፍጥፍ አለም ....በእድሜ ስልቻ ፥ ጠብቆ ተቀምቅሞ
እያጠነጠነ...... የግዜ ሰሌዳ ፥ በመቁጠሪያ ሲታሽ
አድማስ ተሻጋሪ ... #ቦግ!!! ብሎ ማታሽ

ውድ ሸማሽ ሆኜ ፥ መቀነት ያውለኝ
ለውበት ...ለድጋፍ ፥ መጠቅለል የቀናኝ
ገንዘብ ....መቋጠሪያ
ውጋት ......ማባረሪያ
ላዱኛ ቀን ብርታት
ለጭንቅ ቀን ፅናት
አድርጎ .....እኔን ላንቺ ፥ ፈቅዶልኝ ፈጥሪ
የእናቱን ቀን አውጪ ፥ በወዘናው ጣሪ
ግብ ቀንቶት ፅናቴ
ሹልክ ብለሽ ወጥተሽ ፥ ከኑሮ ግርግር
ከእንጉርጉሮ አለም ፥ ጠማማ ውንግርግር
ምርቃትሽ ደርሶኝ ....መነን ሁኚ እናቴ
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ ፥ በኔ ትኖሪ ዘንድ ፥ ይባረክ ጉልበቴ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@Abr_sh

@getem
@getem
እምወዳትዋ ...ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!
❤️

ነገ የ2012 የመጨረሻዋ ቅዳሚት ነች.....😍 ዛሬ ደሞ ንጉሱም ቅዱሱም የሆነው የምሉእ ጌታ በስጋ ከተለየን 16 ዓመቱ ነበር እጅግ በጣም ደስ የሚል ቀን ነበር ብዙ ወዳጆች እንዲሁም የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ዚዘክሩት ውለዋል ...ከዚህ በፊት ባልነበረ መልኩ ስለሆነ ነው ይበልጥ ደስ ያለኝ😍 የሚቀጥለው ዓመት በጣም በተሻለ መልኩ እንደሚከበር ሙሉ እምነት አለኝ ማንም ግጥም እወዳለሁኝ የሚል የሱን ስራ ካነበበ ሀይለኛ ፍቅር ይይዘዋል ከሰውዬው....ታሪኩን ለመረመረ ደሞ እውነት እንደዚህ ዓይነት ሰው አለ ብሎ መተኣጀቡ አይቀርም። ....ከላይ ያለው ፎቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በጓደኛው የተለቀቀ ነው ተደብቆ ነው ያነሳው ያው ፎቶ መነሳት ስለማይወድ.......ወደ ግጥማችን ብንሄድስ....



ደግሞ ለመዘነጥ???
ኩርማንጋፎ ላሎ፣
ከተማ ባንወጣ ቀይ ሴት ባናይ፣
እኛስ ከተመኞች አይደለንም ወይ????
ኩርማንጋፎ ላሎ፣
እንደከተሜ ልጅ ፣
ኮበሌው ሲወጣ፣
በቦላሌ ሱሪ አምሮ ተወልውሎ፣
የምን ተንቧ ተንቧ፣
ማን እጁን ይሰጣል፣ብርዱ መጣ ብሎ፣
እንደው ጎዳናው ላይ፣
ነጠር ነጠር እንጅ፣
እሳት እንደገባው እንደ ጠመጅ ቆሎ።
ኩርሚንጋፎ ላሎ፣


ሙሉጌታ ተስፋየ በምፅዋ ጎዳናዎች ላይ ሲሸልል የተነሳው ፎቶ፣
((የፎቶ ምንጭ፣ አውገረድ ስንዱ አበበ መሃመድ))

((ጃ ኖ ))💚💛❤️

#ምርጥ ቅዳሜዎች ነበሩን!

@getem
@getem
@balmbaras
👍1