ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ቸል እያሉ መጉደል! 

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።
ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

ዶሮዎች!

ለቅመው አዳሪዎች...

ከእጀባው ወጥታ.. .. ከመንጋው ተጠቅታ

በታደነች ጫጩት.. .

ሀዘን ተሸብረው ፥ ለስጋት ተድረው ፥ ጮኸው ይንጫጫሉ

ከአፍታ በኋላ.. .

ዳግም ፍርሀት ሽረው ፥ በኗሪነት ተስፋ ፥ ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እነዛ ዶሮዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ጥሬ ሲናጠቁ ፥ መሬት እየጫሩ

ከቁጥር ተናንሰው ...

ከመንጋነት ጎድለው ፥ ምንም ሆነው ቀሩ።

#አሁን በዛ መሬት!

ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ 

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

አዳዲስ ዶሮዎች.. .

ጭሮ አዳሪዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ 

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ኗሪ ነን እያሉ ... ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እኔ

#ድመት ይታየኛል!

እንደ ሙት መልዓክ ፥ ጥፍሮቹን ያሾለ

ነፍስን ጌጥ አድርጎ ፥ አይኖቹን የኳለ

ጨለማውን ህልፈት ፥ ጀርባው ላይ ያዘለ

ቀስ እያለ ይቀርባል.. .

...........................፥ ቸልታቸው አለ ።


@getem
@getem
@getem