ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተረኛ ነህ ተነስ !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።

#እግዜርን ቀስቅሱት!

ከተኛበት አንቁት.. .

ዝም ብለህ ነበር ፥ አሸልበህ ነበር

ሲተራመስ ሀገር ፥ ቅጡን ሲስት መንደር

ብላችሁ ንገሩት! 

#አርምሞህ አይሎ ፥ እሳት ሆኖ ፈጀን

እንዳበደ ውሻ ...

አቅሉን እንደሳተ ፥ እኛን አናከሰን 

እንባችን ፈሰሰ 

ባለም ተዳረሰ 

ክብራችን ተጣለ 

ኩራትም ጎደለ 

አቀርቅረን ቀረን 

ጀርባ ሰጠን ዘመን

#በእረፍታችን ማግስት ፥ በሞታችን ሳልስት

"ኩራትን አክብሩ" ፥ ብሎ የሚቧልት

ተነሳብን መንግስት !

አሁን ምን ይሉት ነው ?

እንዲህ ያለ ፈሊጥ ፥ የነገር ጨዋታ

የኩራት ቀን ማክበር ...

ከራት በሞተበት ፥ የመቃብር ቦታ?

ብላችሁ ጠይቁት !

ጎደልን !

ጎደልን!

ከክብር ተጣልን ...

መውደድ ፅፈት ሆኖ ፥ ቀረ በወረቀት 

ፍቅር በቃል ወርዶ ፥ ሰማን እንደተረት

ህዝብህ ሽንቁር ሆነ ፥ ጠፋ አንዳች ውታፍ

ገላውን ገረፈ...

እርሱ ባበጃጀው ፥ በገመደው ጅራፍ ።

ብላችሁ ንገሩት!

#አሁን ምን ይሉት ነው ?

ፍቅር በሞተበት ፥ በሰነፎች ሀገር 

"የፍቅር ቀን" ብሎ ፥ የቃል ፍቅር ማክበር?

ብላችሁ ጠይቁት ! 

ዝም ያለም እንደሆን.. .

እንዳምናው ካቻምናው ፥ እንደዛኛው ዘመን 

ዛሬ ቀን ከፋብህ 

የስላቅ ጨዋታው ባንተም ደረሰብህ ።

የእኛ ቤት ፈርሶ ...

ቅጥራችን ተድሶ ...

ዝም ብለህ ስታፌዝ ፥ ስትስቅ በሰው ለቅሶ

ያንተም ቤት ነደደ ፥ መቅደስህ ፈራርሶ ።

አሁንስ ምን ቀረህ?

እናትህ ስትነድ ፥ እሳት ሲለቁባት 

በል ሰይፍህን ምዘዝ ፥ ዝምታህን ሻራት ።

ብላችሁ ንገሩት.. .

እግዜሩን ቀስቅሱት !!

@getem
@getem
@getem