ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሰው_በመሆን_ጥጋት

በግብረ ክርስቶስ
እስከሞት ማፍቀርን ነፍሳቸው ታድላ
ብፁአን መዳፎች
ማቀፍ ሳይታክቱ የበዳይን ገላ
ላ'ረመኔው ልብህ
የይቅርታን ፀጋ መስጠት ካልነፈጉ
ሞኞች እንዳይመስሉህ
አቅፈው ሲማፀኑህ በ'ጅህ እየተወጉ፡፡

ይልቅ ያንተን ቋንቋ
በጦረኛ ጆሮ ከውስጥህ አድምጠው
ለክፋትህ ምላሽ
ልብህን ሲሰብሩት ፍቅርህን አብልጠው
የይቅርታን ብርታት
እንድታይ ነውና ከደማው ጀርባቸው
ሰው መሆን ከገባህ
ቀስትህን ጣልና በ'ጅህ እቀፋቸው፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
#እንደ #ሰው

አንድ ሙት ቅርንጫፍ
በክብሪት ህላዌ
ትውልዱን ሊያስቀጥል~ሺህ ስንጥር ይወልዳል!
አንድ የክብሪት እንጨት
ከእልፍኙ ተጋጭቶ
ታሪኩን ሊያጠፋ ~ እልፍ ዛፍ ያነዳል!
===||===

ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤
#ትርፍ_ልብ_የለኝም!!?
<><><><><><><><>
(#የፍቅር_ቃል)
><><><><><><><><

በእለተ ቅዳሜ ከበተስኪያን #መልስ
እኛ ቀድመን ወተን #ሰው ሳይመለስ
ከማናዉቀው ጎጆ ዉስጥ ከሰው #ተጠልለን
በፍንደቃ ዉስጥ በናፍቆት #ተቃቅፈን

ነግረሽኝ #ነበረ <ማሪያምን ብለሽ>
እኔን #እምትረሽበት ትርፍ ልብ እንደለለሽ!

እኔም ብየሽ #ነበር <በጊዎርጊስ ምየ>
እኔ አንችን ከረሰሁ #ሰው አያርገኝ ብየ!

ታዲያ ምን ያደርጋል #ቃል አልከበደሽም
በሌላ ስትተኪኝ #ፍቅሬን አላሰብሽም
ስለዚህ #ከሀዲ ነሽ ወይ ትርፍ ልብ ነበረሽ
ከመርሳትሽ ሌላ ማፍቀርሽን #የካድሽ!!

እኔ ግን #የዋህ ነኝ አንችን መርሳት 'ማልችል
የት ደረሰች እያልኩ በቀን መብራት ይዤ #ስፈልግሽ ምዉል..!

ባይገባሽ ነው! እኔን #ስታፈቅሪ
ቃላችን #ቃል ሳይሆን ፍቅር ነው አሳሪ
#ማሪያምን ብለሽ ያኔ ቃል ስትገቢ
ትርፍ ልብ እንዳለሽ ምነው #ሳታስቢ..??

እኔ #አንችን ከረሳሁ ሰው አያርገኝ ብያሉሁ
ግን ይሄው #ሳረሳሽ ከሰውነት ወጥቻለሁ..!!

አየሽ? አለሜ ያንዱ ወደኋላ ማለት ሌላዉን #ያስቀራል
ያንዱ መስዕዋት #አለመክፈል ለሌላው ይተርፋል
ያለ እኔ ያንች ኑሮ መቅናት #አላሳዘነኝም
ደስተኛ ከሆሽ እኔን #አይከፋኝም!!
እኔና'ችን ወደኋላ አድርገሽ ወደፊት #ሄደሻል
ማሪያም #ይቅር እንድትልሽ ንሰሃ ያስፈልግሻል!?

#ለእኔ…!?

እኔ ቃሌን #በጠበኩ ከሰው ተራ
ወጥቸ ጥላሻ ሆኛለሁ
አንች ቃልሽን ብትረሽ በቁሜ #ሙቻለሁ

#እና የኔ አለም…
በመጨረሻም #አታስቢ ይቅር ብየሻለሁ ባጠይቂኝም
ባንች ማቄምበት ትርፍ ልብ #የለኝም
!!!!
??????#የፍቅር_ቃል???????

ሚያዝያ 23/2012 ዓ.ም

Aman😑 YTZ
@aman116🖤

@getem
@getem
@getem
[#ሰው_ብቻ . . . 🙂 ]
.
#አሌክስ_ይህ
.
.
ነፋሱ : ሲቆጣ : የሚያነሳት : ቅጠል
ዛፉ : ሲወዛወዝ : የምትረግፍ : እንደ : ጠል
ክሱት : እንደ : ኣልባትሮስ : ‘ምንም’ : እንደ : ተረት
እንደ : ሶሪት : ላባ : የምታምር : ፍጥረት
. . .
እንደ : እስስት : የሆነች
ወይ : እንደ : ጨረቃ : ግብሯ : የተውሶ
ኣትገል : እንደ : ፍቅር : ኣትሽር : እንደ : ኮሶ
የማትሄድ : የማትኖር : የመሃል : ላይ : ንግስት
ሞትን : ድል : ኣድራጊ : ‘በቀበሯት’ : ማግስት🙂
.
የልቧ ቅኝቱ
ቅልስልስ : ወደ : ቀኝ
ምልስ : ወደ : ግራ
በቀን : ትመሻለች : ሌሊት : ልታበራ
.
.
ደ ግ ሞ . . . እ ወ ዳ ታ ለ ሁ !
.
.
መሰልቼት : ሲበዛ
ሲናውዝ : ኣለሜ
በስንት : ይመዘናል
የምፈካው : ነገር
ሳቋን : ኣጣጥሜ . . .
የነፍስ : ምግብ : ናት : የቀኔ : ማሰሻ
የማር : እንጄራ : ሰው : የጣዕም : መጨረሻ !
.
.
እርሷን ኔኦደድ`ኳት🙂
.
.
ግን . . . !
.
ባልበላሽው : ጠግበሽ
ባልጠጣሽው : ሰክረሽ
ስትንገዳገጂ : ‘ዳንስ’ : እየመሰለ
ኣለብሽ : ‘ክፉ’ : ኣመል
የቆምሽ : ኣስመስሎ : ‘ኣፅናኝ’ : የከለለ

@getem
@getem
@getem
👍1
...... እየሳቁ ማልቀስ.....
ዳግም ደጀኔ (ሄራን)
በቅርቡ በአዲስ መፅሀፍ ይመጣል!!
#ሰው_ፍቅር_ናፍቆት
በቅርብ ቀን !!
@getem
@getem
@getem
ናዝራዊያን /አዳማዊያን አላችሁ??
:
:
:
"ሰው ፍቅር ናፍቆት " ወደ ስምጥ ሸለቆዋ እንቁ አዳማ/ናዝሬት ጉዞ ጀምራለች! ናዝራዊናን ልጃችሁ እየመጣች ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ!!

#ሰው_ፍቅር_ናፍቆት……
#በምንተስኖት_መፅሀፍ_መደብር…መብራት አካባቢ
#በዳሪክ_ቡና_አዳማ……ኮሌጅ ይገኛል!

#ነገ ከ10 ሰዓት ጀምሮ ናዝሬት ኮሌጅ አካባቢ ዳሪክ ቡና ለሚገኝ ደግሞ የተፈረመበት መፅሀፍ ያገኛል!
……………………………………………**
#ድረ_ደዋ
#ሀዋሳ
#ጎንደር
#ባህር_ዳር …የምትገኙ አንባቢያን
በዚህ በኩል አውጉኝማ
0942459046 @dagiamen12
Join and share……………👇👇
@heranawi
@getem
@getem
@getem
#ሰው_ኹሉ_ቢርቀኝ

( አይቆጨኝ፤ አይደንቀኝ፤ • ሰው ኹሉ ቢርቀኝ፤ )

ሀቄን የሚሸከም፣ ማንም እስከማይቀር፣

• ከርግቦች፣

• ከጨቅሎች፣

•ከአበቦች፣

• ከእናቶች፣

• ከዜማ፣

• ከፍቅር፣

#ከእመ_ብርሐን_እና_ከግጥም_በስተቀር

( አይቆጨኝ፤ አይደንቀኝ፤ • ሰው ኹሉ ቢርቀኝ። )

....................................................

#ሠይፈ__ወርቅ

@getem
@getem
👍2
#ንብ+#ሰው+#ሴት

ደከመኝ
ኪሳራ ነው ትርፉ
አልፎ አንቺን መመኘት
ከእሾሽ ተመልጦ ወለላሽን ማግኘት...

ንብ ናት ያንቺ ፍጥረት
በሩቅ እያየሁሽ
ፈራሁኝ ለመቅረብ
አልቻልኩም ለመቅረት
አቤት...የኔ....እፍረት
ማሩም ያንቺ አካል
እሾሽ ያንቺ ፍጥረት።

ከወለላሽ አልቀመስኩኝ
ነድፈሽኝ አላረፍኩኝ
ልቤን ብቻ አስደንግጠሽ
ምነው መሰወርሽ
ምነው ማስፈራትሽ...

ማሩ ያንቺ አካል
እሾሽ መች ያስነካል።



ዮኒ
ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍45😢126🔥3🤩3