ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሰው_በመሆን_ጥጋት

በግብረ ክርስቶስ
እስከሞት ማፍቀርን ነፍሳቸው ታድላ
ብፁአን መዳፎች
ማቀፍ ሳይታክቱ የበዳይን ገላ
ላ'ረመኔው ልብህ
የይቅርታን ፀጋ መስጠት ካልነፈጉ
ሞኞች እንዳይመስሉህ
አቅፈው ሲማፀኑህ በ'ጅህ እየተወጉ፡፡

ይልቅ ያንተን ቋንቋ
በጦረኛ ጆሮ ከውስጥህ አድምጠው
ለክፋትህ ምላሽ
ልብህን ሲሰብሩት ፍቅርህን አብልጠው
የይቅርታን ብርታት
እንድታይ ነውና ከደማው ጀርባቸው
ሰው መሆን ከገባህ
ቀስትህን ጣልና በ'ጅህ እቀፋቸው፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem