ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሰው_ኹሉ_ቢርቀኝ

( አይቆጨኝ፤ አይደንቀኝ፤ • ሰው ኹሉ ቢርቀኝ፤ )

ሀቄን የሚሸከም፣ ማንም እስከማይቀር፣

• ከርግቦች፣

• ከጨቅሎች፣

•ከአበቦች፣

• ከእናቶች፣

• ከዜማ፣

• ከፍቅር፣

#ከእመ_ብርሐን_እና_ከግጥም_በስተቀር

( አይቆጨኝ፤ አይደንቀኝ፤ • ሰው ኹሉ ቢርቀኝ። )

....................................................

#ሠይፈ__ወርቅ

@getem
@getem
👍2
#ተፈፀመ

እየ"ተ"ሸከመ
የስጋዬ ሸክም - ድካሜ ከሰመ

እየ"ተ"ወገረ
የሕይወቴ ቀንበር - ወጥመድ ተሰበረ

እየ"ተ"ገረፈ
የኃጢአቴ ቁስል - ከላዬ እረገፈ

እየ"ተ"ንገላታ
የዛለ ስጋዬ - ከስጋት ተፈታ

እየ"ተ"ሰቃየ
ክፋቴ፣ መርገምቴ፣ ከእኔ ተለያየ

ውኃ እየ"ተ"ጠማ
በጽድቅ እረጠበች - የነፍሴ ባድ´ማ
እየጠጣ ሐሞት
አስደነገጠልኝ - የዕድሜዬን ሙሉ ሞት

እየ"ተ"ሰቀለ
'ኤሎሄ' እያለ
ገላው እየዛለ
ከገዛ እስትንፋሱ - እየ"ተ"ነጠለ
የዘለአለም ሞቴን - በሞቱ ገደለ

°°
ልጇን ሲሰቅሉባት - 'ተዉ' ባይ ሰው አጥታ
ማርያም እያነባች - ሰይፍ አልፎ በአንጀቷ
'እነኋት እናትህ'
ቢለው ለዮሐንስ - "ተ"መስቀል ላይ ጌታ
ሐዘኔ "ተ"ሻረ - በእናትነቷ

••
በቁስሉ ካልዳነች - በደሙ ታክማ
ዓለም ቁስለኛ ነች - የስቃይ አውድማ
..
እየ"ተ"ሸከመ
እየ"ተ"ወገረ
እየ"ተ"ገረፈ
እየ"ተ"ንገላታ
እየ"ተ"ሰቃየ
ውኃ እየ"ተ"ጠማ
እየጠጣ ሐሞት
እየ"ተ"ሰቀለ
'ኤሎሄ' እያለ
ገላው እየዛለ

መድኃኒት ለመኾን - መድኃኒት ታመመ´
ቃሉም " #ተፈፀመ "

°°°| #ሠይፈ_ወርቅ |°°°

@getem
@getem
50👍40😢5😱2🔥1🤩1