#ሰውኛ እውነቶች!
።።።።።።።
በላይ በሰማይ ቤት ፣ በሰፊው አዳራሽ
ከንጉስ ፊት ቆመው ፣ ለፍርዳቸው ምላሽ
ሲኦል አንጣልም ፣ ሰይጣን ባሳሳተን
እሱ በሚያጠፋው ፣ እኛ የምን ቤት ነን?
ቢለው ሚሟገቱ ፣ ምክንያት የሚሰጡ
ለክፉ ስራቸው ፣ ከዋኝ ሲያማርጡ
ለፍርድ ቢፋለሙም ...
ገነት ግቡ ተብለው ፍርዳቸው ቢረጋ
መልዓክት በሰሩት በመልካሙ ዋጋ
እኛ የምን ቤት ነን.. ገና የምንገባ ?
ብለው አይጠይቁም !
@getem@getem@getem#ሚካኤል አስጨናቂ