#የድሀ ትሩፋት!
.
ሀብታም ሆኜ ሳለው ...
ጨብራራ ጎረምሳ ፥ ኑሮ ያሸመደው
ሸራውን ወድሮ ፥ ቀለሙን ሲያፈሰው
እብድ እየመሰለ ፥ ገርሞ እየታየኝ
አብስትራክት ብሎ ፥ ስዕሉን ቢያሳየኝ
ይበልጡን ደበረኝ!
አሁን ይሄ ራስታ ...
የሀሳብ ከርታታ...
በቀላም ጭቃዎች ፥ ተለውሶ ቆሞ
ብሩሽ እያነሳ.. . የሚለቀልቀው
አብስትራክት ያለው ስዕሉ ምንድነው?
እኔን የሚገባኝ አብስትራክት ማለት
ነው ስራ ፈትነት !
ዓላማ ቢስነት !
በውስኪዎች ፈንታ ቀለማትን መርጨት
ከሴት ጋር ተቀምጦ እንደመጉረስ ከንፈር
በወጣኒ እድሜ ... በግዑዝ መደበር
ካልጠፋ መዋቢያ ... መፈሸንን ንቆ
በዝተት አልባሳት.. . ገላውን አላሽቆ
ሳየው ይገርመኛል..
ስዕል እየሳለ ስዕል ይመስለኛል ።
...
ሀብታም ሆኜ ሳለው ...
በጫት ቅጠል ነፍዞ ...በሲጃራ ጥንባት
እድፋሟን ስከርቭ.. . አንገቱ ላይ ጥሏት
ውዴ ፍቅሬ ግና.. . ጨረቃና ፀሀይ
የደመናው ንጣት.. .ደግሞም ይሄ ሰማይ
ምናምን እያለ የሚፈላሰፈው
ያ ምስኪን ገጣሚ እውነት ጤነኛ ነው ?
እያልኩ አስባለሁ ።
አሁን ለዚህ ወጣት ...
ድህነቱ ገዝፎ ... ፊቱን ላገረጣት
ሰማይ ፀሀይ ብሎ ስንኝ ከሚቋጥር
ምናል ስራ ሰርቶ እህል በልቶ ቢያድር?
እያልሁኝ ኖሬያለሁ ብዙ ዓመታትን
እኔም ድሀ ሆኜ እስካያት ጥበብን።
..
አሁን የሚገርመኝ.. .
በመፅሀፍት ፈንታ ዳሌ የሚያነበው
ቀለም እንደመርጨት ውስኪ የሚያፈሰው
መኪና ሲቀይር ... ሀሳብ ያልቀየረው
ከግጥም ተጋብቶ እንደመኖር አብሯት
ይህችን ብርቅ ዓለም ከሴት ጋር ጨርሷት
የሚኮፈሰው ነው ያ ከርታታ ሀብታም
የጥበብ ስስታም.. .
አብስትራክት ስሎ.. . ስዕል ሳይደረድር
ዓለምን መስጥሮ ... መፅሀፍትን ሳይጭር
ለሙዚቃው ቅኝት.. . ክራሩን ሳይወድር
ነፍስያን መበደል ... ገንዘብ ብቻ መርጦ
አያስጠላውም ወይ ... መኖር ከሀሳብ ዘቅጦ?
እያልሁ አስባለሁ.. .
የድህነት ትርፉ.. .ጥበብ ነው አውቃለሁ።
....
@getem
@getem
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ....
.
ሀብታም ሆኜ ሳለው ...
ጨብራራ ጎረምሳ ፥ ኑሮ ያሸመደው
ሸራውን ወድሮ ፥ ቀለሙን ሲያፈሰው
እብድ እየመሰለ ፥ ገርሞ እየታየኝ
አብስትራክት ብሎ ፥ ስዕሉን ቢያሳየኝ
ይበልጡን ደበረኝ!
አሁን ይሄ ራስታ ...
የሀሳብ ከርታታ...
በቀላም ጭቃዎች ፥ ተለውሶ ቆሞ
ብሩሽ እያነሳ.. . የሚለቀልቀው
አብስትራክት ያለው ስዕሉ ምንድነው?
እኔን የሚገባኝ አብስትራክት ማለት
ነው ስራ ፈትነት !
ዓላማ ቢስነት !
በውስኪዎች ፈንታ ቀለማትን መርጨት
ከሴት ጋር ተቀምጦ እንደመጉረስ ከንፈር
በወጣኒ እድሜ ... በግዑዝ መደበር
ካልጠፋ መዋቢያ ... መፈሸንን ንቆ
በዝተት አልባሳት.. . ገላውን አላሽቆ
ሳየው ይገርመኛል..
ስዕል እየሳለ ስዕል ይመስለኛል ።
...
ሀብታም ሆኜ ሳለው ...
በጫት ቅጠል ነፍዞ ...በሲጃራ ጥንባት
እድፋሟን ስከርቭ.. . አንገቱ ላይ ጥሏት
ውዴ ፍቅሬ ግና.. . ጨረቃና ፀሀይ
የደመናው ንጣት.. .ደግሞም ይሄ ሰማይ
ምናምን እያለ የሚፈላሰፈው
ያ ምስኪን ገጣሚ እውነት ጤነኛ ነው ?
እያልኩ አስባለሁ ።
አሁን ለዚህ ወጣት ...
ድህነቱ ገዝፎ ... ፊቱን ላገረጣት
ሰማይ ፀሀይ ብሎ ስንኝ ከሚቋጥር
ምናል ስራ ሰርቶ እህል በልቶ ቢያድር?
እያልሁኝ ኖሬያለሁ ብዙ ዓመታትን
እኔም ድሀ ሆኜ እስካያት ጥበብን።
..
አሁን የሚገርመኝ.. .
በመፅሀፍት ፈንታ ዳሌ የሚያነበው
ቀለም እንደመርጨት ውስኪ የሚያፈሰው
መኪና ሲቀይር ... ሀሳብ ያልቀየረው
ከግጥም ተጋብቶ እንደመኖር አብሯት
ይህችን ብርቅ ዓለም ከሴት ጋር ጨርሷት
የሚኮፈሰው ነው ያ ከርታታ ሀብታም
የጥበብ ስስታም.. .
አብስትራክት ስሎ.. . ስዕል ሳይደረድር
ዓለምን መስጥሮ ... መፅሀፍትን ሳይጭር
ለሙዚቃው ቅኝት.. . ክራሩን ሳይወድር
ነፍስያን መበደል ... ገንዘብ ብቻ መርጦ
አያስጠላውም ወይ ... መኖር ከሀሳብ ዘቅጦ?
እያልሁ አስባለሁ.. .
የድህነት ትርፉ.. .ጥበብ ነው አውቃለሁ።
....
@getem
@getem
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ....
👍3