ለሰርግሽ አልቀርም!
.
#ያኔ !
በጠባብ ቤታችን ... ስንኖር ተጣምረን
ወርቁ ሰውነትሽ ... በመዳብ ሲተመን
ምንድን ነበር ያልሽኝ?
በእጅህ የያዝከው ወርቅ ... ስስ መዳብ ሆኖብህ
ካጣኸኝ በኋላ.. . ማጌጥ እንዳይሳንህ
የጣልከው ሲነሳ ...
የፀፀት ንፋሱ ... ወጀብ እንዳይወስድህ
በያዝከው ተጠንቀቅ
ባለህ አትሳለቅ።
ስትይኝ.. .
ምክር ስትለግሽኝ።
ምንድን ነበር ያልኩሽ?
አስካለ ብትሄድ ትመጣለች ዘውዴ
ይሄ ነው ስሌቴ ይሄ ነው መንገዴ ።
እያልኩኝ ስመካ ...እያልኩሽ ስኮፈስ
አይመስለኝም ነበር ይሄ ቀን የማይደርስ።
ዛሬ !
ዘውዴን እያቀፍኩኝ ጉያዋ ሰምጬ
አንቺን ነው የምራብ ከሷ አስበልጬ
ለካ ወርቄ ነበርሽ !
አምሮብኝ የነበር ለካስ ባንቺ ጌጥ ነው
ይሄንን ያወቅሁት ከጎኔ ሳጣሽ ነው ።
አሁን ላጊጥ ብዬ
ነጭ ጥጥ ፈትዬ
የሚያምር ፀዓዳ ከላይ ብደርብም
ማንም ተውበሀል ብሎ አይነግረኝም።
ለካ ጌጤ ነበርሽ ...
የአንገት ሀብሌ.. . አይን ማሳረፊያ
የራስ ዘውድ አክሊሌ ... የሹሜ መታያ
ሳጣሽ ነው ያወኩት ... ምሉዕ እንደነበርኩ
ይሄ ባይሆን ኖሮ
አንድ ገላ አቅፌ ለምን አንቺን ና'ፈኩ ?
ዛሬ እንዲህ እላለሁ...
የላክሽልኝን ካርድ አተኩሬ እያየሁ
.
አሁን ይሄ ባልሽ ... አንቺን የነጠቀኝ
ክፉ ጠላት ሳይሆን ወዳጅ ነው የሆነኝ
እሷን ባትገፋ
ደርሰህ ባትደነፋ
በመዳብ ለማጌጥ ወርቅህን አትሸጥም
የሚል ትምህርትን ነው ያሻረኝ በልቅም
.
ሰርግሽ ጉባኤ ነው ያደባባይ ውግዘት
እሷን በመተውህ ሰርተሀል ስህተት
ብሎ የሚለፍፍ
እኔን የሚነቅፍ
ስለዚህ መጥቼ ... ባልሽኝ ተገኝቼ
ግጥም እያቀበልሁ ...ዜማ አሰናድቼ
ሀይሎጋ እያልሁኝ ቆሜ እደርሻለሁ
ደስታው ሽፋን ሆኖ በሚታይ ሀዘኔ ልቤን አነፃለሁ።
.
ሽንፈቴ አይደለም ሰርግሽ ላይ መገኘት
ለኔ ንሰሀ ነው
በደሌን የሚያሽር ያፅድቆቴ ጥምቀት ።
.....................
@getem
@getem
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ....
.
#ያኔ !
በጠባብ ቤታችን ... ስንኖር ተጣምረን
ወርቁ ሰውነትሽ ... በመዳብ ሲተመን
ምንድን ነበር ያልሽኝ?
በእጅህ የያዝከው ወርቅ ... ስስ መዳብ ሆኖብህ
ካጣኸኝ በኋላ.. . ማጌጥ እንዳይሳንህ
የጣልከው ሲነሳ ...
የፀፀት ንፋሱ ... ወጀብ እንዳይወስድህ
በያዝከው ተጠንቀቅ
ባለህ አትሳለቅ።
ስትይኝ.. .
ምክር ስትለግሽኝ።
ምንድን ነበር ያልኩሽ?
አስካለ ብትሄድ ትመጣለች ዘውዴ
ይሄ ነው ስሌቴ ይሄ ነው መንገዴ ።
እያልኩኝ ስመካ ...እያልኩሽ ስኮፈስ
አይመስለኝም ነበር ይሄ ቀን የማይደርስ።
ዛሬ !
ዘውዴን እያቀፍኩኝ ጉያዋ ሰምጬ
አንቺን ነው የምራብ ከሷ አስበልጬ
ለካ ወርቄ ነበርሽ !
አምሮብኝ የነበር ለካስ ባንቺ ጌጥ ነው
ይሄንን ያወቅሁት ከጎኔ ሳጣሽ ነው ።
አሁን ላጊጥ ብዬ
ነጭ ጥጥ ፈትዬ
የሚያምር ፀዓዳ ከላይ ብደርብም
ማንም ተውበሀል ብሎ አይነግረኝም።
ለካ ጌጤ ነበርሽ ...
የአንገት ሀብሌ.. . አይን ማሳረፊያ
የራስ ዘውድ አክሊሌ ... የሹሜ መታያ
ሳጣሽ ነው ያወኩት ... ምሉዕ እንደነበርኩ
ይሄ ባይሆን ኖሮ
አንድ ገላ አቅፌ ለምን አንቺን ና'ፈኩ ?
ዛሬ እንዲህ እላለሁ...
የላክሽልኝን ካርድ አተኩሬ እያየሁ
.
አሁን ይሄ ባልሽ ... አንቺን የነጠቀኝ
ክፉ ጠላት ሳይሆን ወዳጅ ነው የሆነኝ
እሷን ባትገፋ
ደርሰህ ባትደነፋ
በመዳብ ለማጌጥ ወርቅህን አትሸጥም
የሚል ትምህርትን ነው ያሻረኝ በልቅም
.
ሰርግሽ ጉባኤ ነው ያደባባይ ውግዘት
እሷን በመተውህ ሰርተሀል ስህተት
ብሎ የሚለፍፍ
እኔን የሚነቅፍ
ስለዚህ መጥቼ ... ባልሽኝ ተገኝቼ
ግጥም እያቀበልሁ ...ዜማ አሰናድቼ
ሀይሎጋ እያልሁኝ ቆሜ እደርሻለሁ
ደስታው ሽፋን ሆኖ በሚታይ ሀዘኔ ልቤን አነፃለሁ።
.
ሽንፈቴ አይደለም ሰርግሽ ላይ መገኘት
ለኔ ንሰሀ ነው
በደሌን የሚያሽር ያፅድቆቴ ጥምቀት ።
.....................
@getem
@getem
@paappii
#ሚካኤል አስጨናቂ....
👍3❤2